ለአገር መከላከያ ሠራዊት ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ተበረከተ

81

አዲስ አበባ ታህሳስ 2/2013 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የኦሮሚያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ለመከላከያ ሠራዊት ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አበረከቱ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአገር መከላከያ ሠራዊት 5 ሚሊዮን 28 ሺህ ብር፤ የኦሮሚያ ዲያስፖራ ኤጀንስ ደግሞ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ተቋማቱ የመከላከያ ሠራዊቱ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያመጣና የሚያኮራ ስራ ሰርቷል ብለዋል።

ይህም በተለይ በዘርና በሌሎችም አጀንዳዎች የተከፋፈለውን ማኅበረሰብ በአንድነት ያቀመ ብሎም በኢትዮጵያዊነቱ የሚደራደር ሕዝብ እንደሌለም አስመስክሯል ነው ያሉት። 

በመሆኑም አገሩንና ሕዝቡን ሳይታክት ከሚጠብቀው የመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ድጋፋቸውን እንድሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። 

አቶ አሚን ጂንዲ የኦሮሚያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዳይሬክተር፡-

ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፡-

ሊያጋጥሙ የሚችሉ ማኅበራዊ ቀውስች ከመኖራቸው አንጻር መቋቋምን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዩኒቨርሲቲው ዘጠኝ አባላት ያሉት የባለሙያዎች ኮሚቴ አቋቁሞ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ይህም ሕዝቡን ማረጋጋትና ሠብዓዊ ስራዎችን መስራት እንዲቻል የተቋቋመው ኮሚቴም በሠላም ማስፈን ላይ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ታደሰ መኩሪያ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ትልቅ አቅምና ጉልበት መሆኑን አስመስክሯል ብለዋል።

ሠራዊቱ ኢትዮጵያዊ ጀግንነትን እንዲላበስ ሕዝቡ ከኋላ በመቆም ከፍተኛ ድጋፍ በማድረጉ ሠራዊቱ በአሸናፊነት እንዲወጣ ትልቅ አቅም ሆኖታል ሲሉም ተናግረዋል።

የጽንፈኛውን ቡድን አባላት እየለቀመ እንደሚገኝ ገልጸው ሁሉም አካል ለሠራዊቱ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።    

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም