ጁንታው ባደረገው ልክ ሰው አውሬ ይሆናል ብለን አልገመትንም ነበር- ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

66

አዲስ አበባ ታህሳስ 1/2013 ጁንታው ባደረገው ልክ ሰው አውሬ ይሆናል ብለን አልገመትንም ነበር ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴ በተገኙበት በአዲስ አበባ ለመከላከያ ሰራዊት ለተደረገ ድጋፍ የእወቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ባደረጉት ንግግር ጁንታው ባደረገው ልክ ሰው አውሬ ይሆናል ብለን አልገመትንም ነበር ብለዋል።

ጁንታው አሁን ባደረገው ልክ የገመተም ካለ "ጠንቋይ" ሊሆን ይችላል ብለዋል።

ጦርነት ፍትሃዊ ሲሆን ማሸነፍ ትችላለህ ካልሆነ ግን ትሸነፋለህ፤ በመሆኑም ፍትሃዊ ስለሆነ አሸንፈናል ብለዋል።

በመሆኑም ጁንታው ሁለት አመት የተዘጋጀበትን ውጊያ እኛ በሁለት ሳምንት ማሸነፍ ችለናል ብለዋል።

አሁን ሁሉም ነገር አልቆለታል የጁንታው ቡድን ከመኪና ወርዶ እግረኛ ሆኗል፤ አሁን እግረኛ በማሳደድ ላይ ነን ብለዋል ጀነራል ብርሃኑ።

ህዝብ ያለ ሰራዊት ሰራዊትም ያለ ህዝብ መኖር አይችሉም ያሉት ጀነራሉ በህዝብ ድጋፍና እገዛ ሰራዊቱ አሸናፊ ሆኗል ብለዋል።በመሆኑም ህዝቡ ለሰራዊቱ ላደረገው ድጋፍ ሁሉ አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም