ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር ሊወያዩ ነው

118
አዲስ አበባ ሐምሌ 12/2010 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሐምሌ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ከመምህራን ጋር ሊወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐምሌ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ከ 45 የመንግስትና 4 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተወጣጡ 3 ሺህ መምህራን ጋር “በተጀመረው አገራዊ ለውጥ እንዲሁም ምሁራን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ እንደሚወያዩ ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ፕሮግራሙን ያዘጋጁት የትምህርት ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር እንደሆነና ለእያንዳንዱ የትምህርት ተቋም መምህራን በጾታ፣ በትምህርት አይነትና በደረጃ አመጣጥነው መርጠው እንዲልኩ ተቋማቱ የተመሰረቱበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ ኮታ ተሰጥቷቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭም ከሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየት ለአገሪቷ ፈጣን የለውጥ እርምጃዎቹ ገንቢ ውጤት በማስመዝገብ ላይ መሆናቸው ይታወሳል። ህብረተሰቡም የዚህ ለውጥ መሪ ለሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ለመንግስታቸው ያለውን ድጋፍ በሰፋፊ የድጋፍ ሰልፎች በማሳየት ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም