በህወሓት ጁንታ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ ተግባር ነው- አምባሳደር ሙሉ

51

ህዳር 25/2013 (ኢዜአ) የፌዴራል መንግሥት በህወሓት ጁንታ ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ ተግባር መሆኑን በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ገለጹ፡፡

የፌዴራል መንግስት በህወሃት ጁንታ ቡድን ላይ የወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃን በተመለከተ በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ከዶቸ ቨለ ቱ ዘ ፖይንት ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ከዚህ በፊት በመንግስት የቀረቡ የሰላም አማራጮችን መለስ ብሎ ማየት እንደሚያስፈልግ አንስተው በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ ተግባር መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ስም ሲነግድና ለወንጀል መፈጸሚያ መሳሪያ አድርጎ ሲጠቀምበት ለበርካታ ዓመታት መቆየቱን አስታውሰው፤ እየተካሄደ ያለው ህግን የማስከበር ተግባርም ጦርነት ሳይሆን መንግስት ያቀረበውን የይቅርታና የእርቀ ሰላም አማራጭ ባለመቀበል በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት የፈጸሙ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ተግባር ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ሙሉ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን በቀጠናውና በአፍሪካ አህጉር ሰላም እንዲሰፍን ሰፊ ተግባራት እያከናወኑ ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት አቶ አስፋወሰን አስራቴ በበኩላቸው መንግስት ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በርካታ ጥረቶችን ማድረጉን እንደሚያውቁ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀገሪቱ ሁሉን አቀፍ ለውጥ እንዲመጣ ሲሰሩ እንደነበርና በአንጻሩ ህወሃት ለውጡ እውን እንዳይሆን በርካታ የጥፋት ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር አብራርተዋል፡፡

ለዚህም ባለፉት 2 እና ከዛ በላይ አመታት በሀገሪቱ የተፈጠሩ ችግሮችን በማቀድ߹ በማስተባበር߹ በቁሳቁስና በገንዘብ ሲደግፍ እንደቆየ አመላክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም