በተለያዩ ከተሞች ተቋርጦ የቆየው የቴሌኮም አገልግሎት መመለስ ጀምሯል - ኢትዮ ቴሌኮም

72

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23/2013(ኢዜአ) ባለፉት ሶስት ሣምንታት የሕግ ማስከበር ተልዕኮ ወቅት ተቋርጦ የቆየው የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉና በከፊል መጀመሩን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ። 

ተቋሙ ለኢዜአ በላከው መግለጫ የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ በነበረባቸው ከተሞች በነበረው ችግር የቴሌኮም አገልግሎት መስተጓጎል ማጋጠሙን አስታውሷል።

በቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይ ያጋጠሙ ጉዳቶችን በመጠገንና መልሶ በማቋቋም እንዲሁም አማራጭ የሃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም አገልግሎቱ እንዲቀጥል ማድረጉንም ገልጿል።

በዚሁ መሰረት በዳንሻ፣ ተርካን፣ ሁመራ፣ ሽራሮ፣ ማይፀብሪና ማይካድራ የቴሌኮም አገልግሎት በከፊል ተጀምሯል ብሏል።

በአላማጣም ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱ መጀመሩን ነው የገለፀው።

በተቀሩት አካባቢዎች አገልግሎቱን ለማስጀመር መሰረተ ልማቶችን በመጠገን፣ መልሶ በማቋቋም እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር በመስራት አማራጭ የሃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም አገልግሎቱ በተቋረጠባቸው ሁሉም አካባቢዎች አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ለማስጀመር ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም