ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የዴልሂ ግማሽ ማራቶንን በሁለቱም ፆታዎች ድል አደረጉ

67

ህዳር 20/2013 (ኢዜአ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በህንዷ ዋና ከተማ ዴልሂ በተካሄደው ኤርቴል ግማሽ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።

በወንዶች ዘርፍ አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ 58:53 ጊዜ ሮጦ በአንደኝነት በማጠናቀቅ የቦታውን ሰአት በማሻሻል አሸንፏል።

አትሌት አምደወርቅ በቅርቡ ፖላንድ ተካሂዶ በነበረው የአለም ግማሽ ማራቶን 3 ኛ በመውጣት የነሀሃስ ሜዳሊያ ተሸልሟል።

በውድድሩ ሌላኛው አትሌት አንዱ አምላክ በልሁ 2ኛ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በግማሽ ማራቶን የተሳተፈው አትሌት ሙክታር ኢድሪስ 4ኛ ደረጃ አግኝቷል።

እንዲሁም በሴቶች የአለም የግማሽ ማራቶን የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ አትሌት ያለምዘርፍ የኃለው ግማሽ ማራቶኑን በ64:46 ጊዜ በመግባት የቦታውን ሰአት ጭምር በማሻሻል አሸንፋለች።

በውድድሩ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አባብል የሻነው 3ኛ ስትወጣ ፤ጸሃይ ገመቹ 5ኛ ደረጃን አግኝታለች።ምስል፤ከEthiorunners

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም