ፋሲል ከነማ በቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስቲር ተሸንፏል

64

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19/2013 (ኢዜአ) በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ እግር ኳስ ጨዋታ ፋሲል ከነማ / አፄዎቹ/ በቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስቲር በሁለት ለዜሮ ውጤት ሽንፈትን አስተናግደዋል።

ፋሲል ከነማ እ.አ.አ በ2020/2021 በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የእግር ኳስ ጨዋታ ኢትዮጵያን ወክሎ እየተሳተፈ ነው።

ትናንት ምሽት የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጭ ከቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስቲር ጋር ያደረገው ፋሲል ከነማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

አፄዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን ከዩኤስ ሞናስቲር ጋር በሚቀጥለው ሣምንት የሚያካሂዱ  ይሆናል።

በሁለቱ ክለቦች የደርሶ መልስ ጨዋታ አሸናፊው ክለብ ከሊቢያው አል-አህሊ ትሪፖሊን ጋር ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም