700ሺህ ብር ግምት ያለው የመማሪያ ቁሳቁስ ለተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ--ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን

88

ነቀምቴ፣ ህዳር 18/2013 (ኢዜአ) በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በጅማ ገነቲ ወረዳ 700 ሺህ ብር ግምት ያለው የመማሪያ ቁሳቁስ ለተማሪዎች ድጋፍ መደረጉን የዞኑ ትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሥራ ሂደት አስተባባሪ  አቶ  ከተማ ጀቤሳ ለኢዜአ እንደገለጹት ድጋፉ የተደረገው በወረዳው ለገባ  ሮቢ  የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ነው።

ለተማሪዎቹ 30 ሺህ 884 ደብተሮችና 3 ሺህ 400 እስክሪብቶዎች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

ለአስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች የሚያገለግሉ 99 ዋቢ መጻህፍትም ለትምህርት ቤቱ በድጋፍ ተበርክታል።

ኑሯቸውን በአሜሪካን ሀገር ካደረጉት የአካባቢው ተወላጅ ኢንጂነር አምሣሉ ዱሬሣ አማካኝነት ድጋፉ መደረጉን ተናግረዋል ።

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ዓለሙ ወጋሪ በበኩላቸው ኢንጀነሩ በቀረበላቸው ጥያቄ መሰረት ድጋፍ ማደረጋቸውን ገልጸዋል።

ኢንጀነሩ ትምሀርት ቤቱን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማደራጀትና በ12ኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተና በከፍተኛ ውጤት የሚያልፉ ሶስት ተማሪዎችን የከፍተኛ ትምህርት ወጭ በመሸፈን ለማሰተማር ቃል መግባታቸውን አሰታውቀዋል።

የአካባቢው ነዋሪ የተማሪዎች ወላጆችም ለተማሪዎች ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም