በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት ሊቋረጥ ነው

72

ህዳር 18/2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት ሊቋረጥ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማሻሻያ ሥራው ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎችን መርሃ-ግብር ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት ዕሁድ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡30 ድረስ፡-• በሲቪል ሰርቪስ ፊት ለፊት፣ በተባበሩት ልዩ ቤቶች፣ በሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል፣ በጃክሮስ፣ በሳሊተ ምህረት፣ በፊጋ ሆቴል እና አካባቢዎቻቸው ናቸው።

እንዲሁም በመጪው ሰኞ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ ቀኑ 5 ድረስ፡-• በየረር፣ በጎሮ ሰፈራ፣ በጎሮ ገብርኤል፣በየረር ድልድይ እና አካባቢዎቻቸው፤በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ፡-• በምስራቀ ፀሐይ ገብርኤል፣ በተባበሩት ነዳጅ ማደያ፣ በሚካኤል ፊት ለፊት፣ በጆሞ 1 በከፊል፣ በጆሞ 3 እና አካባቢዎቻቸው የሀይል አቅርቦት አይኖርም።

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ፡-• በሰሚት ለስላሳ፣ በሰሚት ኪዳነ-ምህረት፣ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ፣ በፍርድ ቤት፣ በአደዋ ድልድይ፣ በአቧሬ፣ በእንደራሴ ሆቴል፣ በመለስ ፋውንዴሽን፣ በልቤ ፋና ኮንደሚኒየም፣ በካዛንቺስ በከፊል እና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል።

በተጨማሪም ማክሰኞ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ፡-• በገላን ኮንደሚኒየም በከፊል፣ በቴሌ ስቶር እና አካባቢዎቻቸው እንደሚቋረጥ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ፡-• በወሰን ግሮሰሪ፣ በሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል፣ በየካ አባዶ ኮንደሚኒየም፣ በሮፓክ፣ በመንን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒዓለም፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ እና አካባቢዎቻቸውም እንዲሁ።

እንዲሁም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-• በወሎ ሰፈር፣ በጃፓን ኤምባሲ፣ በሩዋንዳ ኤምባሲ፣ በካራ ማራ ድልድይ እና አካባቢዎቻቸው ሀይል ይቋረጣል ተብሏል።

በመሆኑም የድርጅቱ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም