የከተማ አስተዳደሩን ንብረት ለማስተዳደር የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

98

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/2013 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንብረቶችን በአንድ ማእከል ለማስተዳደር የሚያስችል መተግበሪያ (ሶፍትዌር) ይፋ አደረገ። 

መተግበሪያው የከተማ አስተዳደሩን ንብረት በተመለከተ እስከ ወረዳ ድረስ በአንድ ማእከል ለማስተዳደር የሚያስችል ነው።

በአስተዳደሩ የመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የንብረት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ውብሸት ሙላቱ መተግበሪያው የመንግስት ንብረቶችን ብክነት ለማስቀረት የሚያስችል ነው።

መተግበሪያው የንብረት ቁጥጥርና አስተዳደርን የሚያዘምን ስለመሆኑም አስረድተዋል።

የመንግስትን ንብረት ለሚያስተዳድሩ የተቋማት ተወካዮች በየደረጃቸው ስለ ሶፍትዌሩ በቂ ገለጻ ከተደረገላቸው በኋላ በቀጣይ ወደ ሙከራ ትግበራ ይገባልም ብለዋል።

የተቋማት ንብረት ግዥና አወጋገድ ስርዓትም በተገቢው መንገድ እንዲከናወን መተግበሪያው የሚያግዝ መሆኑን አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ነጂባ አክመል "ሶፍትዌሩ የንብረት አስተዳደርን በማዘመን ኋላቀር በሆነ መንገድ በወረቀት በመመዝገብ ይከሰት የነበረውን የንብረት ብክነት ይታደጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም