በህወሃት የሚተዳደሩ 34 ተቋማት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረታቸው ታገደ

107

አዲስ አበባ ህዳር 8/2013 (ኢዜአ) ህውሓት የሚያስተዳድራቸውና የግል ድርጅት ሆነው በቡድኑ የወንጀል ድርጊት ተሳትፈዋል የተባሉ 34 ተቋማት የባንክ ሒሳብ ጨምሮ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረታቸው መታገዱን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ።

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የባንክ ሂሳባቸውን ጨምሮ የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረታቸው የታገደባቸውን 34 ተቋማት ዝርዝር ገልጿል።

ከተጠቀሱት ተቋማት መካከል ከህወሓት ቡድን ጋር በመሆን በወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ የግል ድርጅቶች እንደሚገኙበትም አስታውቋል።

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቋማቱን ብሔር ተኮር ጥቃትና የሽብር ድርጊት እንዲፈጸም የገንዘብ ድጋፍ በማቅረብ፣ ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሰው የትህነግ /ህወሓት/ ቡድን ጋር ግንኙነት በመፍጠርና በመመሳጠር ጠርጥሬያቸዋለሁ ብሏል።

በተጨማሪም ለእነዚህ አካላት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የተሳተፉ ስለመሆናቸው፣ በግብር ስወራና በሙስና ወንጀል ድርጊቶች ስለመሳተፋቸው ምርመራ ለመጀመር የሚያበቃ በቂ ማስረጃ በድርጅቶቹ ላይ እንደተገኘባቸው ጠቁሟል።

ስለሆነም የድርጅቶቹ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ጨምሮ በባንክ ያላቸው ገንዘብ ከትናንት ሕዳር 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲታገድ ማድረጉን አስታውቋል።

ድርጅቶቹ ሀብታቸውን ለማሸሽ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ በቂ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ ንብረቶቹ ሳይሸሹ ተገቢውን ቁጥጥር ለማድረግ ዕግዱ ማስፈለጉንም ገልጿል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የመመርመርና ሀብት የማስመለስ ስራውን እስከሚያጠናቅቅ ድረስ የታገዱት ንብረቶች እንዳይጎዱና እንዳይባክኑ ጠብቆ የሚያቆይ የንብረት አስተዳዳሪ እንደሚሾም አስታውቋል።

እግዱ የተላለፈባቸው ተቋማት የሚከተሉት ናቸው።

1. ሱር ኮንስትራክሽን 

2. ጉና የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

3. ትራንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

4. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

5. ሰላም የሕዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማህበር

6. ሜጋ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

7. ኤፈርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

8. ኤፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

9. ኤፈርት ዲዛይን እና ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

10. ኢዛና ማዕድን ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

11. ቬሎሲቲ አፖራልዝ ካምፓኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

12. መሰቦ ቢውልዲንግ ማቴሪያል ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

13. ሳባ ዳይሜንሺናል ስቶን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

14. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ

15. ሼባ ታነሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

16. ኤ.ፒ ኤፍ 

17. ሜጋ ኔት ኮርፖሬሽን

18. ኤክስፕረስ ትራንዚት ሰርቪስ

19. ደሳለኝ ካትሪናሪ

20. ሼባ ታነሪ ፋክተሪ አክሲዮን ማህበር

21. ሕይወት አግሪካልቸር መካናይዜሽን

22. ሕይወት እርሻ ሜካናይዜሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

23. አልመዳ ጋርመንት ፋክተሪ

24. መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ 

25. ደደቢት ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር

26. አዲስ ፋርማሲቲካልስ ፕሮዳክሽን 

27. ትግራይ ዴቨሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

28. ስታር ፋርማሲቲካልስ ኢምፖርተርስ

29. ሳባ እምነበረድ አክሲዮን ማህበር

30. አድዋ ፍሎር ፋክተሪ 

31. ትካል እግሪ ምትካል/ ትግራይ/ ት.እ.ም.ት/

32. ብሩህ ተስፋ ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

33. ደሳለኝ የእንስሳ መድኃኒት አስመጪና አከፋፋይ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

34. ማይጨው ፓርቲክል ቦርድ ፋክተሪ ናቸው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም