በኢትዮጵያ የሳይንስ ፈጠራ ቀን እየተከበረ ነው

66

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1/2013 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ አምስተኛው አገር አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ ቀን እየተከበረ ነው፡፡

ቀኑ እየተከበረ ያለው "የሳይንስ ፈጠራ ለሰላምና ለብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ በፓናል ውይይት፣ በኤግዚቢሽንና በተለያዩ መርሃ ግብሮች ነው፡፡

ቀኑ የሳይንስ፣ የሂሳብና የምህንድስና(ኢንጂነሪንግ) ተማሪዎችን ለማበረታታትና በዘርፉ ችግሮች ላይ ተወያይቶ መፍትሄ ለማስቀመጥ ያግዛልም ተብሏል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከስቲም ፓወር /STEM Power/ ከተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር እያከበሩት ባለው ቀን የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሳይንስ ፈጠራዎች እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ለፈጠራ ሥራ አሸናፊዎች ሽልማት ይበረከትላቸዋል፡፡

በዓለም የሳይንስ ፈጠራ ቀን ሲከበር ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም