እስራኤል አንበጣን ለመከላከል የባለሙያዎች ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኢትዮዽያ ልትልክ መሆኗን ገለጸች

64

ጥቅምት 27/2013 (ኢዜአ) እስራኤል መንግስት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የአንበጣን መንጋ ለመከላከል የባለሙያዎች ቡድን በሚቀጥለው ሳምንት ልትልክ መሆኗን አስታውቃለች።

በዚህም የእስራኤል ምክትል ደህንነት ሚኒስትር ጋዲ ይቫርካን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሰሜናዊ  የአገሪቱ ክፍል የተከሰተው የአንበጣ መንጋ የሀገሪቱን የግብርና ሰብል እንደሚጎዳ  ጠቁመው፤ አገራቸው ይህን አንበጣ ለመከላከል በሚቀጥለው ሳምንት  የባለሙያ ልዑካ ወደ ኢትዮጵያ እንደምትልክ ተናግረዋል።

ሚስተር የቫርካን በኢትዮጵያ በነበራቸው ልዩ ተልእኮ  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደምቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው የሁለቱን አገራት ጠንካራ ትስስርና ቀጣይነትን ስለማስጠበቅ መወያየታቸውን  በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።

ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተጨማሪ ስብሰባዎችን እና ውይይትችን ማድረጋቸውንም ተናገርዋል።

“የኢትዮጵያ ህዝብ የእስራኤልን ሀገር ይወዳል እስራኤል ደግሞ  በብዙ መስኮች በቴክኖሎጂ ፣ በትምህርት፣ በግብርና እና በሌሎችም ኢትዮጵያን ትረዳለችም” ብለዋል።

ኢትዮጵያ በ110 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያሉባት በአፍሪካ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት አገራት አንዷ ናት ያሉት የቫርካን፤ የክርስትና ዕምነት ከመምጣቱ በፊት የአይሁድን ዘውዳዊነት በኢትዮጵያ ውስጥ ያካተተው የቤተ እስራኤል ማኅበረሰብ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ያስቆጠረ በመሆኑ የኢትዮዽያ ታሪክ ከሌሎች የጎላ ያደርገዋል ብለዋል።

ከ29 ዓመታት በፊት ከ15 ሺህ ቤተ እስራላዊ ጋር መሄዳቸውን አስታውሰው አሁን አገሪቷን ወክለው በመገኘታቸው ደስታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም