ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የአስተሳሰብ ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ... ሰላም ሚኒስቴር

129

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2013(ኢዜአ)በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተከታታይነት ያለው የአስተሳሰብ ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ።

የሰላም ሚኒስቴር በሰላም ግንባታና በተለያዩ አገራዊ የለውጥ እሳቤዎች ላይ በመላ አገሪቱ ከወረዳና ክልል ለተውጣጡ ከ600 በላይ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የአሁኑ ስልጠና ለ3 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከክልል፣ ዞንና ወረዳ ለተወጣጡ አመራሮች በ2ኛ ዙር እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

የሰላም የሚነስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ሰኢድ እንዳሉት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተከታታይነት ያለው የአስተሳሰብ ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል።

የተጀመረው አገራዊ የለውጥ ሂደት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገርና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በብልሃት ለመፍታት በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሚና ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።

የለውጡ እሳቤ መዋቅራዊ ገጽታና የአፈፃፀም ሂደት ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለሁለተኛ ዙር በመሰጠት ላይ ያለው ስልጠና በሰላም ግንባታና በተለያዩ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተከታታይነት ያለው የአስተሳሰብ ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም