የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የሶስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ ተጀመረ

61

ጥቅምት 17/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ በቬርቿል ተጀምሯል።

የዛሬው ስብሰባ ሊጀመር የቻለው በደቡብ አፍሪካ የዓለምአቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሃገራቱ በጻፉት ደብዳቤ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት መሆኑም ተገልጿል።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የቬርቿል ስብሰባ ከቀኑ 10 ስዓት ላይ ተጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር እየተካሄደ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት ጉዳይ ዙሪያ የሚመክር መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም