የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በደቡብ ከልል ጉራጌና ስልጤ ዞን የሚገጙ የጤና ተቀማትን ጎበጙ

84

ጥቅምት 16/2013 (ኢዜአ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በደቡብ ክልል ጉራጌና ስልጤ ዞን የሚገጙ የጤና ተቀማትን ጎበጙ። 

ሚኒስትሯ በጉብኝታቸው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሆሰፒታል ማስፋፊያን፤ የከተማውን የሆሰፒታል ግንባታ እንዲሁም የአገና የኮቪድ ማገገሚያ ሆሰፒታልና የህክምና መስጫ ማእከልን ጎብኝተዋል።

በስልጤ ዞን የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የጤና አገልገሎት አሰጣጥም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው የጤና ተቀማቱ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል አያደረጉት የለውን ጥረትም ሚኒስትሯ አድንቀዋል ።

በቀጣይም የአገልገሎት ጥራትን ለማሻሻል የበለጠ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የተጀመሩ የማስፋፊያና የሆስፒታሎች ግንባታ ሚኒስቴሩ ድጋፉን አጠናከሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በጉብኝቱ የጤና ተቋማት ሃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም