በሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት ድጋፍ የተገነቡ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማት ለአገልግሎት በቁ

145

ሰቆጣ ጥቅምት 16/2013 (ኢዜአ) በሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት በተመደበ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የበጀት ድጋፍ የንጹህ መጠጥ ውሀ ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን በአማራ ክልል የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አስታወቀ።

በብሄረሰብ አስተዳደሩ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተገኘ መብራቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው በጀት አመት የ17 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓዶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል።

በተቋማቱ ከሰባት ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተገነቡት የውሃ ተቋማት 45 ነጥብ 8 በመቶ የነበረው የብሄረሰብ አስተዳደሩ የንፁህ መጠጥ ውሀ ሽፋን ወደ 52 በመቶ ከፍ ማለቱን አመልክተዋል ።

በተያዘው በጀት አመትም በሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነትና በሌሎች አጋሮች ድጋፍ በተከዜ ሐይቅ ዙሪያ በሚገኙ 16 ቀበሌዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም