ብሄራዊ ፓርኮችን ከእሳት አደጋ የሚከላከል የእሳት አጥፊ ብርጌድ ተቋቋመ

52

አዲስ አበባ ጥቅምት 14/2013 (ኢዜአ) በብሄራዊ ፓርኮች ላይ  የሚከሰት የእሳት አደጋን  የሚቆጣጠር  የእሳት አጥፊ  ብርጌድ ማቋቋሙን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በብሄራዊ ፓርኮች ላይ  የሚከሰትን የእሳት አደጋዎች በአፋጣኝ ለመቆጣጠር ፓርኮቹን ከያሚጎራብቱ የህብረተሰብ ክፍሎች የመለመላቸውን  የእሳት አጥፊ ብርጌዶች  አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባቱን የባለስልጣኑ  ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ ተናግረዋል፡፡

የእሳት አጥፊ ብርጌዶቹ በፓርኮች ላይ የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ክትትል ከማደረጋቸውም በተጨማሪ   ህብረተሰቡ  በንቃት አካባቢውን አንዲቆጣጠር  ማንቃት  እንደሚሰሩም  አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል በፓርኮቹ ላይ የሚታዩትን  ህገ-ወጥ አደን ለመቆጣጠር  ግንዛቤ    እየተሰጠ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ  አስታውቀዋል፡፡

ህገወጥ አደንና የእንስሳት ዝውውርን ለመቅረፍ ከሚሰጠው ግንዛቤ ባለፈ በተግባሩ የተሰማሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን አቶ ኩመራ አስረድተዋል፡፡

ባለስልጣኑ በዱር እንስሳት ላይ የሚደርሱ ጉዳትን ለመቀነስ ከሚሰራው  ስራ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ መሰረተ ልማት አቅርቦትን ለማሻሻል መሰራቱን ገልተጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም