የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ

197

አዲስ አበባ ጥቅምት 10/2013 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የቀረበለትን ልዩ ልዩ ሹመቶች ዛሬ አጸደቀ።
በዚህ መሠረት፦

1ኛ. አቶ ጥራቱ በየነ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ

2ኛ. ዶክተር መስከረም ፈለቀ - ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

3ኛ . ኢንጂነር አያልነሽ ኃብተማርያም - ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ

4ኛ. ዶክተር መስከረም ምትኩ - የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

5ኛ. ዶክተር ሚልኬሳ  ጃጋማ - መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

6ኛ. ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ - ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

7ኛ. አቶ ተፈራ ሞላ - ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

8ኛ. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም