የመቀሌ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከራያ ቢራ አክሲዮን ማህበር ጋር የማሊያ ማስታወቂያ ስምምነት ለሶስት አመታት ተፈራረመ

61
አዲስ አበባ ሀምሌ 8/2010 መቀሌ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከራያ ቢራ ፋብሪካ ጋር የማሊያ ማስታወቂያ ስምምነት ተፈራረመ። ዛሬ በመቀሌ ከተማ ይፋ የሆነውን ስምምነት የሁለቱ አካላት አመራሮች ይፋ አድርገውታል። ለሶስት ዓመት የሚቆየው ስምምነት መቀሌ ከተማ በጥሬ ገንዘብ፣ በአይነትና ከቢራ ሽያጭ ላይ ከሚገኝ ገቢ መቀሌ ከተማ 30 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚያገኝ የክለቡ የወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ለአከ ገብረህይወት ለኢዜአ  ገልጸዋል። የቢራ ፋብሪካው ማስታወቂያ ከ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ጀምሮ በማልያው ላይ እንደሚያደርግም ተናግረዋል። ስምምነቱ በየዓመቱ ማሻሻያ የሚደረግበትና ክለቡ ተጨማሪ ገቢ ሊያገኝበት የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል። በሌላ በኩል የመቀሌ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ዉል መጠናቀቁ ከክለቡ ጋር ተለያይተዋል። የመቀሌ ከተማ አሰልጣኝ ማን ይሆናል? የሚለው ባጭር ግዜ ውስጥ እንደሚገለጽ ክለቡ አስታውቋል። አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በዘንድሮው ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የመጣውን መቀሌ ከተማን በ49ኝ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ አስችለውታል።                          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም