ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ትምህርት ለማስጀመር በሀዋሳ እየተመከረ ነው

47

ጥቅምት 6/2013(ኢዜአ) የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርት በሚጀምሩበት ሁኔታ ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ በሀዋሳ ተጀመረ።

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ዛሬ በሀዋሳ በተጀመረው የውይይት መድረክ ላይ ሚኒስትሮችና የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ተሳትፈዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በወቅቱ እንደገለጹት  ዮኒቨርሲቲዎች ኮሮናን በመካላከል ትምህርት ለማስጀመር ለሚያደርጉት ጥረት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተዋቀረው ኮሚቴ በተለያዮ ዮኒቨርሲቲዎች በመገኘት ያደረገው ግምገማ ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል።

በዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ከመቼ እንደሚጀመር ይፋ እንደሚደረግም ከመርሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም