ፓርቲዎች በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው

58

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5/2013(ኢዜአ) በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው።

በውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተሳታፊነት ተገኝተዋል።

ፓርቲዎቹ በመወያየት ላይ ያሉት ህገ-መንግስትና ህገ-መንግስታዊነት በኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አደረጃጀት ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫና የማያግባቡን ታላላቅ አጀንዳዎች በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነው።

እስካሁን ባለው ህገ-መንግስትና ህገ-መንግስታዊነት በኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ፖለቲካ አደረጃጀት ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው በሚሉት አጀንዳዎች ላይ የመወያያ ጽሁፎች ቀርበዋል።

በቀሪ አጀንዳዎች ላይም ለውይይቱ መነሻ የሚሆኑ ጽሁፎች ቀርበው ፓርቲዎቹ ይመክሩባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም