ኢትዮጵያና ኤርትራ ለህዝቦቻቸው እድገት በጋራ እንደሚሰሩ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ

131
አዲስ አበባ ሀምሌ 8/2010 "የኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት ለህዝቦች እድገት በጋራ አቅደው ይሰራሉ" ሲሉ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ገለፁ። በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይህንን የገለፁት ትናንት ማታ በሀዋሳ ከተማ በተደረገላቸው የእራት ግብዣ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው። በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ በሁለት አገሮች የሚኖሩ አንድ ህዝብ በመሆናቸው ሰላማቸውን ለማረጋገጥና በጋራ ለማደግ ተባብረው መሥራት አለባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቆየው ጥላቻ መወገዱን አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚስተዋሉት የሰላም ማደፍረስ ተግባራት እንዲቆሙ የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ "አሁን የተጀመረውን ሰላም ለማደናቀፍ ግጭቶችን የሚፈጥሩ አካላት አሉ፤ እነዚህ አካላት ወደ ሰላም እንዲገቡ ለመጨረሻ ጊዜ የሰላም ጥሪዬን አቀርባለሁ፤" ብለዋል። "ይህ ካልሆነ ግን ሰውነንና ወዳልተፈለገ ተግባር ውስጥ እንዳታስገቡን" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አስጠንቅቀዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም