ኦህዴድ በዞን በከተማ አስተዳደሮችና በወረዳዎች አዳዲስ የአመራር ምደባ እያደረገ ነው

58
አዲስ አበባ ግንቦት 4/ 2010 የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) በዞን፣ በከተማ አስተዳደሮችና በወረዳ  ደረጃ አዳዲስ የአመራር ምደባ በማድረግ ላይ መሆኑን የኦህዴድ  የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገለፁ። ኦህዴድ በህዝቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል። ኦህዴድ ከመልካም አስተዳደር፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ እና ከልማት ስራዎች መጓተት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታትና የህግ የበላይነትን ለማስከበር እንዲሁም የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ወደ አዲስ ምእራፍ እንደሚያሸጋግርም ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ በሁሉም ደረጃ የክልሉን መንግስት የማስፈፀም አቅም በየጊዜው እየፈተሸ ማስተካከያ ማድረግ እና ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል። በዚሁ መሰረት ኦህዴድ ሰሞኑን ባካሄዴው ግምገማ ላይ በመመስረት የአዳዲስ አመራር ምደባ ማድርጉን የገለጹት  ኃላፊው በዞን፣ በከተማ አስተዳደርና  በወረዳ ደረጃ እየተደረገ ያለው የአመራር ምደባ ማስተካከያም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል። በየደረጃው እየተወሰደ  ያለውን የአመራር ማስተካከያ እርምጃ ህብረተሰቡ እንዲያውቀው የማድርግ ስራ እነደሚሳራም አስታውቀዋል፡፡ ማስተካከያውን ተከትሎ በተካሄደው የአዳዲስ የአመራር ምደባ መሰረትም፦ በክልሉ መንግስት የተሰጡ ሹመቶች አቶ ሲራጅ አብዱልጀባር- የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሮባ ቶልጬ ሳፋይ- የጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዴንጎ ቦሩ ቆሲ- የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገመቺስ ጉታ ጆቴ- የሆሮ ጉዱሩ ወላጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገመቺስ ተመስገን- የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ወ/ሮ አለምፀሃይ ሽፈራው- የቢሾፍቶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ካባ መብራቱ- የወሊሶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ቢቂልቱ ከተማ በቀለ - የአምቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ሚኤሳ ኤሌማ- የሻሸመኔ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ ጂፋር- የሞጆ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ በዳዳ መርጋ- የጅማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ነቢ ጉታ- የባቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ደሳለኝ ኦልቀባ- የሆሮ ጉዱሩ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ በኦህዴድ የተሰጡ ሹመቶች አቶ ተፈሪ ንጋቱ- የአሰላ ከተማ የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀሚድ ቱርሲ- የሻሸመኔ ከተማ የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰንበታ አደባ- የነቀምቴ ከተማ የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ጣይቱ ያሚ- የሞጆ ከተማ የኦህዴድ አደረጃጀት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ተክለሀና- የሞጆ ከተማ የኦህዴድ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ አቶ ደባ አመንቴ- የቡራዮ ከተማ የኦህዴድ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ አቶ ድሪባ መኮንን- የሱሉልታ ከተማ የኦህዴድ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ አቶ ገነሞ ያቺሲ- የቢሻን ጉራቻ ከተማ የኦህዴድ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ አቶ እንዳሻው ብርሃኑ- የባሌ ዞን የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ ከበደ- የምእራብ ሸዋ ዞን የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታደሰ ወገኔ- የሰሜን ሸዋ ዞን የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መዲና ከድር- የአርሲ ዞን የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ኤባ የምስራቅ ወለጋ ዞን የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የአዳዲስ አመራር ምደባው የምሁራን፣ የወጣቶች እና የሴቶችን ተሳትፎ ግምት ውስጥ በማስገባት የተካሄደ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል። የአመራር ምደባው ላይ ክትትል የሚደረግ መሆኑን የገለፁት አቶ አዲሱ ጉድለት በሚታይባቸው ስፍራዎች ላይ የሚደረገው የአመራር ማስተካከያ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል። ምንጭ፡-የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም