ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

94
ሀዋሳ ሐምሌ 7/2010 ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሃዋሳ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ ከደቂቃዎች በፊት በሃዋሳ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የገቡት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በአቀባባል ስነስርዓቱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃገር ሽማግሌዎች የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ በማርሽ ባንድና በኪነት ቡድን የታጀበ አቀባበል የተደረገላቸው ፕሬዝዳንቱ በፈረስ ጉግስና በእልልታ በታጀበ አቀባበል ሃዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ደርሰዋል፡፡ ረፋድ አደባባይ የወጣው የሃዋሳና አካባቢዋ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተላበሰ አክብሮት እንግዳውን ተቀብሏል፡፡ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተመራው ልዑክ ሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎብኝቷል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም