ምክትል ከንቲባ አዳነች የ'ሆራ ፊንፊኔ' ኢሬቻ የሚከበርበትን ስፍራ ጎበኙ

54

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2013 (ኢዜአ) ምክትል ከንቲባዋና የስራ ኃላፊዎቹ በመስቀል አደባባይና የ'ሆራ ፊንፊኔ' ኢሬቻ ስፍራን ምቹ ለማድረግ የተሰራውን ስራ ነው የጎበኙት።

ምክልት ከንቲባ አዳነች ከጉብኘቱ በኋላ እንደተናገሩት፤ እስካሁን ጥሩ የዝግጅት ስራ እየተሰራ ነው።መንገድን ጨምሮ ከዚህ በፊት ምቹ ያልሆኑ ቦታዎች የተስተካከሉ ሲሆን የውኃና ሌሎች ለጥንቃቄ አስፈላጊ የሆኑ ስራዎች መከናወናቸውንና ''በአጠቃላይ እስካሁንም በዓሉን በራሱ እሴትና ሞገስ ለማክበር የሚያስችል አስፈለጊ ዝግጅት ተደርጓል'' ብለዋል።

የዘንድሮ ኢሬቻ ከወትሮው በተለየ መልኩ የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ስጋት በሆነት ሁኔታ የሚከበር በመሆኑ አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።ውስን ሰዎች በበዓሉ ላይ የሚታደሙ ቢሆንም ቦታው ምን ያህል ሰዎች ማስተናገድ እንደሚችል ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የኢሬቻ በዓል ሰላም፣ እርቅና መግባባት የሚሰበክበት በመሆኑ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ሊከበር እንደሚገባ ገልጸዋል።የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው ኢሬቻ በሰላም ሊከበር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የመስቀል በዓል በሰላማዊ እንዲከበር አስትዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነው፤ ኢሬቻ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር የአዲስ አበባ ሕዝብ የተለመደ ድጋፉን እንዲያረጋግጥ ጥሪ አቅርበዋል።የ'ሆራ ፊንፊኔ' ኢሬቻ በዓል በመጪው ቅዳሜ የሚከበር ሲሆን የ'ሆራ አርሰዲ' ደግሞ በማግስቱ እሁድ ይከበራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም