በጅግጅጋ የተከበረው የዓለም የቱሪዝም ቀን በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ

53

  አዲስ አበባ  መስከረም 18/2012 ( ኢዜአ) በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የተከበረው የዓለም ቱሪዝም ቀን በስኬት መጠናቀቁን የሶማሌ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

''ቱሪዝም ለገጠር ልማት'' በሚል መሪ ሀሳብ በአለም ለ41ኛ ጊዜ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለ33ኛ ጊዜ የተከበረው የቱሪዝም ቀን ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።


የሶማሌ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤልያስ አቢብ ለኢዜአ እንደገለፁት ቀኑን ለማክበር ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

ቀኑን ለማክበር የክልሉ ህዝብና መንግሥት ተቀናጅተው በመስራታቸው በታቀደው መመልኩ በሰላምና በስኬት ተከናውኖ መጠናቀቁን ገልጸዋል።


እንግዶቹ ቆይታቸው ያማረ እንዲሆን በተለይም የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪ ያሳየው ትብብር ከፍተኛ እንደነበረ ገልፀው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


እለቱ ከትናንት ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች የተከበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት የባህል ሙዚየም ጉብኝት ተካሂዶ እንዲሁም የፈረስ ግልቢያ ውድድሮች ተካሂደው ጠተናቅቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም