በጂግጂጋ ከተማ ለሚገነባው የባህል ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

72

አዲስ አበባ መስከረም 17/2013 (ኢዜአ) በሶማሌ ክልል ጂግጅጋ ከተማ ለሚገነባው የባህል ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ ።

ባህል ማዕከሉ ሙዚየም ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ለቤተ መጻህፍትና ሌሎች አገልግሎት መስጫ የሚሆኑ ተጨማሪ ክፍሎች እንደሚኖሩት ተገልጿል።

ዛሬ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን በዓል በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ እየተከበረ ባለበት ወቅት የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ናቸው።

ለባህል ማዕከሉ የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ በተዘጋጀ ስነስርአት ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦድሪን በድሪ ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሒሩት ካሳው እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።

የባህል ማዕከሉ የግንባታ ሥራ በተያዘው ዓመት መጨረሻ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም