ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀንን ለማክበር እንግዶች ጂግጂጋ ከተማ ገቡ

181

አዲስ አበባ መስከረም 17/2013(ኢዜአ) ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን በዓልን ለማክበር እንግዶች በሶማሌ ክልል  ጂግጂጋ ከተማ ገቡ።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሒሩት ካሳውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ከደቂቃዎች በፊት ወደከተማዋ ገብተዋል።

በዓሉ በኢትዮያ ''ቱሪዝም ለገጠር ልማት'' በሚል መሪ ሀሳብ በጂግጂጋ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።

በዋናነት በሲፖዚየምና የቱሪስት መዳራሻ ስፍራዎችን በመጎብኘት እንደሚከበር ታውቋል።

ከእዚህ በተጨማሪ በጂግጂጋ ከተማ ለሚገነባው የባህል ማዕከል የመሰረት ድንጋይ እንደሚቀመጥ ከወጣው መርሃግብር ለማወቅ ተችሏል። 

የዓለም ቱሪዝም ቀን በጂግጂጋ ከተማ ሲከበር የዛሬው ለ2ኛ ጊዜ ነው።

ከተማዋ በ2008 ዓ.ም 28 ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀን በዓልን ማስተናገዷን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ቀኑ ዛሬ እየተከበረ ያለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ41ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ መሆኑ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም