የመስቀልን በዓል ስናከብር ከጥላቻና መጥፎ ድርጊቶች በመቆጠብና በጎውን በመመኘት ነው

88

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2013 (ኢዜአ) የመስቀልን በዓል ስናከብር ሠላምን በመስበክ፣ ለሌሎች በጎ ነገርን በመመኘትና በማድረግ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አሳሰበች።  

ቤተክርስቲያኗ የመስቀል ደመራን በዓል በአዲስ አበባ ላዛሪስት ሚሽን ትምህርት ቤት አክብራለች።

በቤተክርስቲያኗ የአዲስ አበባሀገረ ስብከት የካርዲናል ብርሃነየሱስ እንደራሴ አባ ተስፋዬ ወልደማሪያም መስቀል ለክርስቲያኖች ታላቅ ምስጢር ያለውና እየሱስ ክርስቶስ ደሙን አፍስሶ የሰው ልጆችን የታደገበት መሆኑን መረዳት ይገባል ብለዋል።

ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ለራሱ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ መሆኑን በመረዳት ከሊቅ አስከ ደቂቅ ይህን  ለሌሎች በመኖር ዓርአያነቱን ሊከተሉ ይገባል ነው ያሉት።

የመስቀል በዓል ሀይማኖታዊ ቢሆንም ባሕላዊ እሴቶቹም የበዙ ናቸውና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ማግኘቱን አውስተዋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑምይህንበመረዳት በአንድነትና በፍቅር ሊያከብረው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

መስቀል ለሌሎች ደግነገርን በማድረግ ብርሃን እንድንሆን ነው የሚስተምረን ያሉት አባ ተስፋዬ ክርስቶስ የሰው ልጆችን አንድ ለማድረግ እንጂ ሀጢያት ኖሮበት አይደለም የተሰዋው ብለዋል።

በመሆኑም 'እኛም ለሕዝባችንና ለአገራችን አንድነትን ማሰብ አለብን' ሲሉም አክለዋል።

ኢትዮጵያየበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ መሆኗን በመረዳት በመዋደድ፣ በመፋቀርና በመተባበር የምንኖርባት መሆን አለባትም ብለዋል አባ ተስፋዬ።

በጎ ነገር በማድረግና ክፋትን በበጎ በመመለስ ማሸነፍ ይቻላል ነው ያሉት።

የደመራችቦተለኩሶየቤተክርስቲያኗ ምዕመናንም የተለያዩ ዝማሬዎችን በማቅረብ በዓሉን በድምቀት አክብረውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም