ዓዲግራይት ዩኒቨርሲቲ አንድ ሺህ 732 ተማሪዎችን አስመረቀ

82

መቀሌ መስከረም 162013(ኢዜአ) ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በበተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ732 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።

 ከተመራቂዎች መካከል  75 የህክምና ዶክትሬት ሰልጣኞች ይገኙበታል።

የህክምና፣ ኬሚካል ምህንድስና ፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስ አድምኒስትሬሽን፣ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎች የትምህር ዘርፎች ተመራቂዎቹ የሰለጠኑባቸው የትምህርት መስኮች  ናቸው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎች ውስጥ 518 ሴቶች እንደሆኑ ተገልጿል።

በስነ-ሰርዓቱ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዛይድ ነጋሽ " ተመራቂዎች በቀሰሙትን ትምህርት ራሳቸው፣ ቤተሰቦቻቸውና ሃገራቸው ለመጥቀም ሊጠቀሙበት ይገባል "ብለዋል።

ተመራቂዎች በሄዱበት ቦታ ሁሉ የሰላም አምባሳደር ሆኖው እንዲሰሩም አሳስበዋል።

ተቋሞ መደበኛ የመማር ማስተማሩ በተጓዳኝ  ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የትምህርት ስራ እና የምርመራ ማዕከል አቋቁሞ እየሰራ መሆኑ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሐጎስ ጎደፋይ በበኩላቸው፣ በተለይ  የጤና ባለሙያዎች ህዝብ ከማገልገል የበለጠ ነገር እንደሌለ ተግንዝበው በስራቸው አርአያ እንዲሆኑ አደራ ብለዋል።

ከተመራቂዎች መካከል  በኮምፒተር ሳይንስ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቀችው  ፊልማዊት መኮንን ቁርጠኝነት ካለ የማይሰራ እና የማይሳካ ነገር እንደሌለ ተናግራለች።

የየእለት ስራዋን በማከናወን በተከታታይ የማታ ትምህርት  በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀው ወጣት አፍላይ ገብረ በበኩሉ፣ትምህርቱን ለመጨረስ ያገጠመውን ፈተና አልፎ  ለመመረቅ በመብቃቱ  መደሰቱን ገልጿል።

በ2004 ዓ.ም  960 ተማሪዎችን በመቀበል የማስተማር ስራውን የጀመረው የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የዛሬዎቹን ጨምሮ እስካሁን  ከ18 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁንና አሁንም ከ20 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች እንዳሉት ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም