ሰላምን ለማስፈንና የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቋቋም የቆዩ ማህበራዊ እሴቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቆመ

81

አዲስ አበባ  መስከረም 15/2013 (ኢዜአ)ሰላምን ለማስፈንና ተፈጥሯዊ እና ማህበራዊ አደጋዎችን ለመቋቋም የቆዩ ማህበራዊ እሴቶችን በአግባቡ 

የሰላም ሚኒስቴር የዓለም ሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ በቆየው ኢትዮጵያዊ የሠላም እና ማህበራዊ እሴቶች ላይ ያተኮረ ውይይት ከሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አካሂዷል።

የሰላምና ማህበራዊ እሴት ሃብቶች ለአገር ሰላም እንዲሁም ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ለመቋቋም ያላቸውን ሚና በማስመልክትም ኢዜአ የውይይቱን ተሳታፊዎች አነጋግሯል።

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ በጎ ፈቃደኞች እና የክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በሠላምና አንድነት ላይ በበጎ ፍቃድ ሥራ የተሰማራው በጎ ፈቃደኛ ወጣት አካሉ አብርሃም ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ አገር በቀል የሚባሉ ማህበራዊ እሴቶች እየተበላሹ መምጣታቸውን ጠቁሟል።

ስነምግባርን በማስረጽ በኩል በትምህርት ቤቶች ላይ በአግባቡ ትኩረት ተደርጎ አለመሰራቱ ችግሩን ይበልጥ እንዳባባሰው ነው ወጣቱ የገለጸው።

ከዩዝ ኤንድ ካልቸራል ፋውንዴሽን የመጡት አቶ ዜናየነህ ግርማ በበኩላቸው በተለይ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች አገር በቀል ማህበራዊ እሴቶችን በማስረጽ በኩል የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠቁሟል።

"የሃይማኖት ተቋማትና አባቶች በአገር ሰላምና ተጠያቂነት ላይ አተኩረው በመስራት ለአገራዊ እሴቶች መጎልበት፣ ለሰላምና አንድነት የድርሻቸውን መጫወት አለባቸው" ያለው ደግሞ ወጣት አካሉ አብርሃም ነው።

በኦሮሚያ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ መኮንን ሌንጂሶ በበኩላቸው በጎርፍና ግጭት ለተፈናቀሉ ከ1 ሚሊዮን በላይ ዜጐች ሰብዓዊ እርዳታ መደረጉ አስረድተዋል።

እንደእዚህ አይነት ማህበራዊ አደጋዎችን ለመቋቋም ከመንግስት ድጋፍ በተጨማሪ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ የቆዩ ማህበራዊ እሴቶች አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ ማህበራዊ እሴቶች በመደማመጥና በመደጋገፍ መኖር እንደሚቻል አመላካቾች በመሆናቸው ለሰላም ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነሩ አንስተዋል።

"በአሁኑ ወቅት ማህበራዊ መተሳሰብን የሚጠይቁ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ቢኖሩም መቅደም ያለበት ሰብዓዊነት ነው" ያሉት ደግሞ በሠላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን ናቸው።

ስለሆነም ፖለቲከኞችና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ማህበረሰቡን ማዕከል ያደረገ ሥራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ኢትዮጵያዊያን ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን በጋራ ለመወጣት የሚረዱ የቆዩ ማህበራዊ እሴቶች ባለቤት ቢሆኑም ከጊዜ ወደጊዜ እየተሸረሸሩ መምጣታቸው በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም