የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት በአፋር በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች አንድ ሚሊዮን 500ሺህ ብር ለመለገስ ወሰነ

66

ጋምቤላ መስከረም 15/2013 (ኢዜአ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአፋር ክልል በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ እንዲውል አንድ ሚሊዮን 500ሺህ ብር ለመለገስ መወሰኑን አስታወቀ።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጀሉ እንደገለጹት ዘንደሮው የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው ጎርፍ  በጋምቤላም ሆነ ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ጉዳት ቢያደርስም የአፋር ክልልን ያህል የከፋ አይደለም።

የአፋር ክልል ህዝብ ችግር የጋምቤላም በመሆኑ ለተፈናቃዮች ድጋፍ እንዲውል የክልሉ መንግስት  አንድ ሚሊዮን 500ሺህ ብር   በጥሬ ለመለገስ መወሰኑን አስታውቀዋል።

ተጎጂዎችንም ያሉበት ሁኔታ ለማየትም በቅርቡ የክልሉ መንግስት ሉኡካን ወደ ቦታው እንደሚልክ ተናግረዋል።

በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ችግር የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመሻገር እርስ በእርስ የመደጋገፍ እሴት ወሳኝ በመሆኑ የክልሉ መንግስት  ድጋፍ እንዲደርስ መወሰኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም