ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ትኩረት በመስጠት ለኢትዮጵያ ብልጽግና ስኬት መስራት ያስፈልጋል - ወጣቶች

160

 አዲስ አበባ  መስከረም 15/2013 (ኢዜአ) ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ትኩረት በመስጠት ለኢትዮጵያ የብልፅግና ስኬት መስራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወጣቶች የሰላምና ብልጽግና ተልእኮ ሊግ ገለጸ።

ሊጉ ለ30  ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራን የተመለከተ ስልጠና እንዲሁም ለ20 ሺህ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ወጣቶቹ ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ ለስራ የሚሆን ገንዘብ ከብድርና ቁጠባ  እንዲሁም ከተለያዩ ባንኮች ብድር በማመቻቸት ወደ ስራ እንደሚገቡ ለማድረግም ይሰራል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች የሰላምና ብልጽግና ተልእኮ ሊግ ፕሬዝዳንት ወጣት ብርሃኑ በቀለ እንደገለፀው፣ የአገሪቷን ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ ወጣቶችን ወደ ስራ ማስገባት የመጀመሪያ ተግባር ሊሆን ይገባል ብሏል።

በርካታ ወጣቶች ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የስራ እድል ይፈልጋሉ ብሏል።

ሊጉ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ፣በአማራ ፣በደቡብ እና በሱማሌ ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ሲሆን  ወጣቶች ወደ ስራ ፈጠራ እንዲገቡ በስፋት እየሰራ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች የሰላምና ብልጽግና ተልዕኮ የደቡብ ክልል ተወካይ ወጣት ዳዊት ታመነ እንዳለው ወጣቶች ላይ መስራት የአገርን እድገት በእጥፍ ማፋጠን በመሆኑ የተጀመሩት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብሏል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች የሰላምና ብልፅግና ተልእኮ ሊግ የአማራ ክልል ምክትል ሰብሳሲ ወጣት ደረጀ ታመነ ፣ ሊጉ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከስልጠነው ባሻገር ወደ ልማት እንዲገባ ተግተን እየሰራን ነው ብሏል።

የአገር ሰላምና ብልጽግና የሚረጋገጠው በወጣቱ ንቁ ተሳትፎ ነው በማለት፣ ይህን እውን ለማድረግ እንሰራለን ነው ያለው።

የኢትዮጵያ ወጣቶች የሰላምና ብልጽግና ተልእኮ ሊግ አሁን ላይ ከ20 ሺህ በላይ አባላት እንዳሉት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም