በጤና ሚኒስትር ዲኤታ የተመራ ልዑክ ቡድን በሲዳማ ክልል ጤና ተቋማትን እየጎበኘ ነው

62

ሐዋሳ፣ መስከረም 12/2013 (ኢዜአ) በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የተመራ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የልዑካን ቡድን በሲዳማ ክልል የጤና ተቋማት የሥራ እንቅሰቃሴን እየጎበኘ ነው።

የልዑካን ቡድኑ ዛሬ ጠዋት በበንሳ ወረዳ ዳዬ ጤና ጣቢያና ዳዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመገኘት ጉብኝቱን ጀምሯል።

ቡድኑ ከቀትር በኋላም በዳሌ ወረዳና ሐዋሳ ከተማ የመደበኛ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን  በመጎብኘት ላይ ነው።

ጉብኝቱ በክልሉ የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥና የግብአት አቅርቦት ሁኔታ እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ክስተት በመደበኛው የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በመገምገምና በመለየት ድጋፍ ማድረግን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተመልክቷል።

ሚኒስትር ዴኤታውን ጨምሮ የልዑካን ቡድኑ አባላት ከጉብኝቱ በኋላ ከነዋሪዎች፣ ከዘርፉ የሥራ ኃላፊዎችና አመራሮች ጋር እንደሚወያዩ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም