የሚኒስቴሩ አመራሮች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል

79

አዲስ አበባ፣ መስከረማ 12/2013(ኢዜአ) በዛሬው እለት የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።


በአሁኑ ሰዓት አመራሮቹ በጉዳዩ ላይ እየተወያዩ ነው።

ውይይት እየተካሄደባቸው እና ውሳኔ ከሚያገኙ ጉዳዮች መካከል መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፣ የ8ኛና 12ኛ ክፍል ክልላዊ እና ሀገራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች ላይ እየቀረቡ ባሉ ቅሬታ ላይ ውሳኔ ይሰጣል።

ከዚህ በተጨማሪም አዲሱ የትምህርት ስርዓት ዝግጅት አካሄድና ሁኔታ በውይይቱ ላይ የሚገመገም እና ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎን ይጠበቃል።

የጎልማሶች ትምህርት አሰጣጥና አፈፃፀምም በውይይቱ ውሳኔ ከሚያገኙ ጉዳዮች መካከል ነው።

በውይይቱ ላይ የተደረሰውን ውሳኔም በነገው እለት ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል ማለቱን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም