የሠላም ሚኒስቴር የችግኝ እንክብካቤ አካሄደ

162

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11/2013 ( ኢዜአ) የሠላም ሚኒስቴር ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የችግኝ እንክብካቤ መርሃ ግብር አከናወነ። 

የችግኝ እንክብካቤ መርሃ ግብሩ "ሠላምን እንተክላለን፤ ሠላምን እንከባከባለን" በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳትፈዋል።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን በመርሃ ግብሩ ላይ እንዳሉት፤ ሠላም ከተፈጥሮ ጋር ስለሚቆራኝ ዕፅዋትን በተንከባከብን ቁጥር ሠላምን እንተክላለን።

ሚኒስቴሩ ከችግኝ እንክብካቤ መርሃ-ግብሩ በተጨማሪ የዓለም ሠላም ቀንን ምክንያት በማድረግ ለኢትዮጵያ ሰላም ግንባታና ትኩረት ሲባል በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ መሆኑን ገልፀዋል።

የዓለም የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ ትናንት የእግር ጉዞና ደም ልገሳ ተከናውኗል።

ዛሬ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ማህበራዊ እሴቶች ለሠላም ያላቸውን ፋይዳን ለማጉላትና ግንባታ ላይ በማተኮር በችግኝ እንክብካቤና ፓናል ውይይት እየተከበረ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም