ፌስቡክ በናይጀሪያ ዋና ከተማ ቢሮውን ሊከፍት ነው

94

መስከረም 10/2013(ኢዜአ) ግዙፉ የፌስቡክ ካምፓኒ በሚቀጥለው የፈረንጆች አመት በናይጀሪያ ዋና ከተማ ሎጎስ ቢሮውን ሊከፍት መሆኑን አስታውቋል።

ይህውም ካምፓኒው በአፍሪካ አህጉር ጽ/ቤቱን ሲከፍት ለሁለተኛ ጊዜ ያደርገዋል ተብሏል።

እንደ ኩባንያው መረጃ ከሆነ ይህ ጽ/ቤት የመሐንዲሶችን ቡድን የሚያስተናግድ የመጀመሪያው የአፍሪካ ቢሮ ይሆናል።

በናይጄሪያ የሚከፈተው ቢሮ በሽያጭ ፣ በሽርክና ፣ በፖሊሲ እና በኮሙኒኬሽን ውስጥ የሚሰሩ ቡድኖችን ያካትታል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፌስቡክ በሰጠው መግለጫ አዲሱ ማዕከል በአፍሪካውያን የተፈጠሩ ምርቶችን ለአፍሪካና ለመላው ዓለም ያዳርሳል የሚል እምነት አለኝ ብሏል።

እ.አ.አ በ 2016 የኩባንያው መስራች የሆኑት ማርክ ዙከርበርግ ወደ አፍሪካ አህጉር ባደረጉት የመጀመሪያ ጉዞው ሌጎስን መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም