ኮቪድ-19ን ለመከላከል የተሰሩ ሥራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በጅማ ዩኒቨርስቲ ተከፈተ

70

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10/2013(ኢዜአ) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮቪድ-19ን ለመከላከል የተሰሩ ሥራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ተከፈተ።

አውደር ዕዩን የከፈቱት የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሣሙዔል ኡርቃቶና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቴክኖሎጂና የሰው ሀብት ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እምዬ ቢተው ናቸው።

አውደ ርዕይው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2012 ዓ.ም ኮቪድ-19ን ለመከላከል እንዲውሉ ያከናወኗቸው ዐበይት ተግባራትና ውጤቶቸን ለመገምገምና ልምድ ለመለዋወጥ ያለመ ነው።

በአውደ ርዕዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር፣ በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ያከናወኗቸውን ዐበይት ተግባራት ይዘው ቀርበዋል።

በአውደ ርዕዩ 40 የሚጠጉ ዩኒቨርስቲዎች ተሳታፊዎች ሲሆኑ ለአንድ ሣምንት ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም