የኮይሻ ሃይድሮፖወር ፕሮጀክት የግንባታ ክንውኑ 37 በመቶ ደርሷል

80

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9/2013 ዓ.ም ( ኢዜአ) በኦሞ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የኮይሻ ሃይድሮፖወር ፕሮጀክት ግንባታ 37 በመቶ መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ እንዳስታወቁት የፕሮጀክቱ ግንባታ በከፍተኛ ሁኔታ ተጓቶ የቆየ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

የኃይል ማመንጫ ግንባታው  ሲጠናቀቅ በዓመት የ6 ሺህ 400 ጊጋ ዋት አወርስ መጠን ያለው ኃይል የሚያመነጭ መሆኑንም ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ እስካሁን ለ4000 ያህል ሰዎች የሥራ ዕድል ያስገኘ ሲሆን፤ በቀጣይ ለተጨማሪ ሰዎች ሥራን ይፈጥራል ብለዋል።

"ግድቡ ከአዲሱ የኮይሻ ፕሮጀክታችን ጋር ተዳምሮ አካባቢውን ወደ ልህቀት ያደርሰዋል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም