የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረ ሀሳብ ቀረበ

112

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8/2013(ኢዜአ) የጤና ሚኒስቴር ዓለምአቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር እንደ የአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረ ሀሳብ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።

ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ግን እነዚህን መስፈርቶች በአግባቡ መከናወናቸው የሚያረጋግጥ ግብረ ኃይል በየትምህርት ቤቶቹ ሊቋቋም ይገባል ብለዋል ሚኒስትሯ።

የሰዎችን ቁጥር በመመጠን እና የኮቪድ -19 መከላከያ መስፈርቶችን በመተግበር ስብሰባ፣ ሲኒማ፣ ቲያትር፣ የስፖርት ዝግጅቶች፣ ማህበራዊና ሐይማኖታዊ በዓላት፣ የአደባባይ በዓላት፣ ሊፈቀዱ እንደሚገባም የጤና ሚኒስቴር ምክረ ሀሳቡን አስቀምጧል።

የጤና ሚኒስቴር በማንኛውም ሁኔታ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ በመላ ሀገሪቱ አስገዳጅ ሊሆን ይገባል ብሏል በማለት የኢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም