በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲው ለሦስተኛ ዙር ለዜጎች ድጋፍ አደረገ

69


አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 29/2012(ኢዜአ) በኬኒያ ናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለ1500 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ኤምባሲው በኬኒያ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ጋር በመተባበር ኬኒያ ውስጥ በነፍስ ወከፍ ለ1500 ወገኖችን ይዘው ለሚኖሩ 491 አባወራዎች ለአንድ ወር የሚሆን የምግብና የጽዳት ቁሳቁሶችን መለገሱን አመልክቷል።

ኢትዮጵያውያኑ በኬኒያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተክትሎ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን ኤምባሲው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም