የቂሊንጦ ታራሚዎች መፈታት ይገባናል ሲሉ ጥያቄያቸውን አቀረቡ

82
አዲስ አበባ ሰኔ 6 /2010 በአዲስ አበባ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች መፈታት ይገባናል በማለት ጥያቄያቸውን እያቀረቡ  ነው። በማረሚያ ቤቱ ውስጥ የተከሰተውን ችግር ለማርገብም እየተሰራ መሆኑን ኢዜአ በቦታው ተገኝቶ ለማየት ችሏል። በእስር ቤቱ የሚገኙት ወንድ ታራሚዎች የረሐብ አድማ በማድረግ  "መንግስት ያስተላለፈው የይቅርታ ተግባር እኛንም ይመልከተን፤ የተለያዩ ክልሎች ይህንን በመጠቀም እስረኞችን እየለቀቁ ቢሆንም የፌዴራሉ ማረሚያ ቤት ግን ከዚህ ውጭ አድርጎናል ነው" የሚሉት። ችግሩ የተከሰተው በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎች በጅምላ በይቅርታ መፈታት አለብን የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው ነው። ታራሚዎች በጩኸትና ድምፅ በማሰማት ነው የእንፈታ የጅምላ ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ያሉት። በመሆኑም ልንፈታ ይገባናል ሲሉ የሚያቀርቡትን ጥያቄ ተከትሎ እየተነሳ ያለውን ችግር የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች እልባት ለመስጠት እየሰሩ ናቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም