አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ ለስታርት አፖች ከፋይናንስ አቅርቦት ጀምሮ ምቹ ምህዳርን የሚፈጥሩ የፖሊሲ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምራለች-ዶክተር ብሩክ ታዬ
Apr 15, 2024 213
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለስታርት አፖች ከፋይናንስ አቅርቦት ጀምሮ ምቹ ምህዳርን የሚፈጥሩና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር የሚተገበሩ ጠንካራ የፖሊሲ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመሯን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ገለጹ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ስታርት አፖች ፈንድ ሊያገኙ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል። ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት መንግስት ስታርት አፖች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በተቀናጀ መልኩ ለመቅረፍ እየሰራ ነው።   ኢትዮጵያ ለስታርት አፕ ምቹ ምህዳርን ለመፍጠር ከፋይናንስ አቅርቦት፣ ከህግ፣ ከመሰረተ ልማትና ሌሎች ጉዳዮች አኳያ ጠንካራ የፖሊሲ እርምጃዎች መውሰድ መጀመሯን ለልማት አጋሮች አብራርተዋል። ይህንን ለማጠናከርም መንግስት ከልማት አጋሮች፣ ከግሉ ዘርፍና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ለስታርት አፖች ውጤታማነት ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን አንስተው፥ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ውይይቶችም እየተካሄዱ ስለመሆኑ አስረድተዋል።   በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የአካታች እድገት እና ዘላቂ ልማት የኢትዮጵያ ቡድን መሪ የሆኑት ግዛቸው ሲሳይ በበኩላቸው፥ ስታርት አፖች በፋይናንስ እጥረት ምክንያት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ከመንግስት ጋር በትብብር እየሰራን ነው ብለዋል። የመንግስታቱ የልማት ፕሮግራም ከብሔራዊ ባንክ እና ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ጋር በመሆን የፈጠራ ፋይናንስ አሰራርን መዘርጋቱን ተናግረዋል። በዚህም የቴክኒክ ድጋፍ እና ብድር ለስታርት አፖች እንዲቀርብ ይደረጋል ነው ያሉት።   የዓለም ባንክ ተወካይ ማርሎን ረውሊንስ እንዳሉት ባንኩ በኢትዮጵያ ለተለያዩ የልማት እና የድህነት ቅነሳ ፕሮግራሞች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሀገሪቱ የጀመረችው የዕድገት ጉዞ እንዲሳካ በቀጣይ ድጋፉን እንደሚቀጥል ጠቅሰው በተለይ በኢትዮጵያ በጅምር ላይ ያለው የስታርት አፕ ምቹ ምህዳርን ለማስፋት የቴክኒክ ድጋፎችን ያደርጋል ብለዋል። ባንኩ የስራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታትም ስታርት አፖችን የማማከር፣ ፕሮጀክታቸው ላይ ግብረ መልስ በመስጠት የማገዝ ስራን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ የድጋፍ ዕይታን እንደሚከተል ጠቁመዋል።              
በክልሉ በሚገኙ የባለበጀት መስሪያ ቤቶች የዘጠኝ ወራት የፋይናንስ አስተዳደር የሚፈትሽ ድጋፋዊ ግምገማ ዛሬ ተጀምሯል
Apr 15, 2024 107
ሀዋሳ ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል በሚገኙ የባለበጀት መስሪያ ቤቶች የዘጠኝ ወራት የፋይናንስ አስተዳደር የሚፈትሽ ድጋፋዊ ግምገማ ዛሬ መጀመሩን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ የፋይናንስ ቢሮው ሃላፊ ዶክተር አራርሶ ገረመው በዚሁ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። የድጋፋዊ ግምገማ ዓላማውም በክልሉ ከመንግስትና ከተለያዩ አማራጮች የሚመጣ ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ በጅት ያለምንም ብክነት የህዝብ የልማት ጥያቄ ሊመልስ በሚችል መልኩ እንዲውል ቢሮው ጠንካራ የሆነ የቁጥጥርና የምዘና ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። በክልሉ 106 ባለበጀት መስሪያ ቤቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ሃላፊው፤ እያንዳንዱ መስሪያ ቤት የሚመደብለትን ገንዘብ ለህዝብ ፍላጎት የማዋል ግብ ስለማሳካቱ ቁጥጥርና ክትትል ይደረጋል ብለዋል። የንብረትና ገንዘብ አያያዝና አስተዳደር፣ ሪፖርት ማድረግና አያያዝ፣ የግዥ ስርዓትን ጨምሮ ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ባላቸውና የአገር ዓቀፉንና ዓለም አቀፉን የፋይናንስ አሰራር በተከተሉ 26 የመገምገሚያ መስፈርቶች እንደሚፈተሹም አንስተዋል። በበጀት ዓመቱ ከተበጀተው ከ22 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር 34 በመቶ ለካፒታል ፕሮጀክቶች የተመደበ መሆኑን አስታውሰዋል። በአጠቃላይ በክልሉ የህዝብ ፍላጎት መሰረት በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ የሚገኙ የውሃ፣ የመንገድ፣ የጤናና ሌሎች መሰረተ ልማቶች በጀቱ እየዋለ ስለመሆኑ በአግባቡ እንደሚፈተሽ ተናግረዋል። የክልሉን የፋይናንስ ስርዓት ግልጽ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት ለመዘርጋት የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል። በክልሉ ባለፉት የዘጠኝ ወራት የፋይናንስ ስርዓት ለመፈተሽ የተጀመረው ድጋፋዊ ግምገማ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን፤ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩትን ማበረታታትና ጉድለት የሚታይባቸውን ማረም ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።    
በዓለም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የመንግስታትና የሃይማኖት ተቋማት የትብብር ስራ ወሳኝ ነው - ዶክተር ከይረዲን ተዘራ
Apr 15, 2024 164
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የመንግስታትና የሃይማኖት ተቋማት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ከይረዲን ተዘራ ገለጹ። የ37 የዓለም ሀገራት የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የተሳተፉበት ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በጉባዔው የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ከይረዲን ተዘራ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት በሃይማኖት መቻቻልና መከባበር የምትታወቅ ሀገር ናት፡፡   ሁሉም ሃይማኖቶች በጎነትንና ሰላምን በመስበክ ለሀገርና ለትውልድ በአብሮነት መቀጠል ጉልህ አሻራ ማሳረፋቸውንም ገልጸዋል። መንግስት የሃይማኖት ተቋማት በሰላም ግንባታና በሀገራዊ አንድነት ላይ ቁልፍ ሚና እንዳላቸው በፅኑ በማመን በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቅርቡ ከተለያዩ የእምነት አባቶች ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያደረጉትን ውይይት በማሳያነት ጠቅሰዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የመንግስታትና የሃይማኖት ተቋማት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው ያመላከቱት፡፡ ኢትዮጵያ የጋራ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ከራሷ ባለፈ በአፍሪካና በተቀረው የዓለም ክፍል ለሰው ልጆች ሰላምና ደህንነት በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሓን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት ዋና ፍላጎትና ስራቸው በምድሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ነው ብለዋል፡፡ ይህ እውን እንዲሆንም የዓለም መንግስታትና ህዝቦች መነጋገር፣ መደማመጥ፣ ልዩነቶች እንኳ ቢኖሩ በንግግር መፍታት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ክብርንና አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ ለመከላከል አበክሮ መስራት እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ የቡድን 20 የሃይማኖት ትስስር ማህበር ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ኮል ዱርሐም ናቸው፡፡ ላምን ማህበረሰባዊ እሴትነት ለማጎልበትም የሃይማኖት ተቋማት ሃላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል። የምክክር መድረኩ የሃይማኖት ተቋማቱ በጋራ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም በመያዝ ወደ ተግባር እንዲገቡ ለማድረግ ሚናው ከፍተኛ ነውም ብለዋል፡፡ "የሃይማኖት ተቋማት ትብብር ሰላምን፣ ሰብዓዊ ክብርን፣ ልማትን፣ አካባቢ ጥበቃን፣ ማጠናከርና የጥላቻ ንግግርን ግጭትንና ጠባብ ብሔርተኝነትን መቃወም" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሔደ ያለው የምክክር መድረክ ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ከአስር ቢሊዮን ብር በላይ የመንገድ ፈንድ ገቢ ተሰበሰበ
Apr 15, 2024 107
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለመንገዶች ጥገና እና የመንገድ ደህንነት ማስፈጸሚያ የሚሆን ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የመንገድ ፈንድ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ። በተሰበሰበው ገቢ የወቅታዊና መደበኛ የመንገድ ጥገና ሥራዎች መከናወናቸውም ነው አስተዳደሩ የገለጸው። ገቢው የተገኘው በነዳጅ ላይ ከተጣለ ታሪፍ፣ ከተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት፣ ከመንገድ ጠቀሜታ ክፍያ እና በክብደት ላይ የተመሰረተ ዓመታዊ የተሽከርካሪ ፈቃድ ማደሻ መሆኑም ተመልክቷል። የተሰበሰበውን ገቢ ለመንገድ ጥገና ከማዋል አንፃር በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ ባቀረቡት የክፍያ ሰርቲፊኬት መሰረት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር(ኢመአ) 4 ቢሊዮን 163 ሚሊዮን 410 ሺህ 907 ብር ከ23 ሳንቲም፣ የክልል ገጠር መንገድ ኤጀንሲዎች 1 ቢሊዮን 726 ሚሊዮን 478 ሺህ 976 ብር ከ99 ሳንቲም መከፈሉን ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። በተጨማሪም የከተማ መንገድ ኤጀንሲዎች 916 ሚሊዮን 865 ሺህ 104 ብር ከ27 ሳንቲም እንዲሁም ለድጋፍ ሰጪ(የአማካሪ ክፍያ) 17 ሚሊዮን 471 ሺህ 811 ብር ከ59 ሳንቲም፣ ለመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት 26 ሚሊዮን 519ሺህ 109 ብር ከ14 ሳንቲም እና የባንክ፤ ለፖስታ ቤት ኮሚሽን ክፍያ 12ሚሊዮን 770 ሺህ 80 ብር ከ33 ሳንቲም በአጠቃላይ በመንገድ ጥገና ጥቅም ላይ እንዲያውሉ 6 ቢሊዮን 863 ሚሊዮን 515 ሺህ 989 ብር ከ55 ሳንቲም መከፈሉን ገልጿል፡፡ የተመደበው በጀት ለተገቢው አገልግሎት መዋሉን ከማረጋገጥ አኳያ በአስተዳደሩ፣ በክልል እና በከተማ የመንገድ ኤጀንሲዎች በሚያስተዳድሯቸው ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ቅኝት የማድረግና የምህንድስና(ቴክኒካል) ኦዲት ሥራ መከናወኑም በመረጃው ተገልጿል። አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ከመንገድ ፈንድ የሰበሰበው ገቢ 10 ቢሊዮን 356ሚሊዮን 19ሺህ 307 ብር ከ40 ሳንቲም መሆኑንም አስታውቋል።
በኮንሶ ዞን አንድ ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሶላር ሃይል ፕሮጀክት 70 በመቶ ተጠናቋል -- ሚኒስቴሩ
Apr 15, 2024 112
ካራት ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በኮንሶ ዞን አንድ ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው የሶላር ሃይል ፕሮጀክት 70 በመቶ መጠናቀቁን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ የሚመራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና የኮንሶ ዞን ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ፕሮጀክቱን ዛሬ ጎብኝተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው በዚህ ወቅት እንዳሉት እንደ አውሮፓውን አቆጣጠር በ2030 የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ 35 በመቶውን በሶላር ሃይል ለመሸፈን እየተሠራ ነው። መስሪያ ቤቱ የኤሌክትሪክ ሀይል የማያገኙ የገጠር ነዋሪዎችን የሶላር ሃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች 650 ኪሎ ዋት ሃይል ማመንጨት የሚችሉ አምስት የሶላር ሃይል ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተከናወኑ ካሉ የሶላር ሃይል ፕሮጀክቶች በኮንሶ ዞን ኬና ወረዳ ጌራ ቀበሌ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው ፕሮጀክት አንዱ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት የግንባታ ስራው የተጀመረው ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት 70 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ በመጪው ሰኔ ወር ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ አንድ ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን ገልጸዋል። በሀገር ደረጃ ባለፉት 10 ዓመታት ዋናው ሃይል የማይደርስባቸው አካባቢዎች ላይ ሀይል ለማዳረስ በተከናወኑ ስራዎች 320 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የሶላር ሃይል በሁሉም ክልሎች በመገንባት ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ፕሮጀክቶቹ ኅብረተሰቡን የሃይል ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለመስኖ ልማት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልጌሎ ገልሾ በዞኑ ከፍተኛ የሃይል ተደራሽነት ችግር መኖሩን ጠቅሰው፣ ፕሮጀክቱ ከመሠረተ ልማት ርቆ ለሚኖር ሕዝብ መገንባቱ ፋይዳውን የላቀ ያደርገዋል ብለዋል።   ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ኅብረተሰቡን የሃይል ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ የእህል ወፍጮ፣ የእንጨትና ብረታ ብረት ሥራዎችን መስራት ስለሚያስችል ለወጣቱ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። የሕዝቡን የዘመናት የመልካም አስተዳደር ችግር ለሚፈታው ለዚህ ፕሮጀክት ተገቢው ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባም አስተዳዳሪው ተናግረዋል። ማህበረሰቡ ማገዶ እንጨት የሚጠቀም በመሆኑ በደን ሀብት ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በኮንሶ ዞን ኬና ወረዳ ጌራ ቀበሌ ነዋሪ አቶ በላቸው ቦራንቶ ናቸው።   ለብዙ ዓመታት በአካባቢያችን የኤሌክትሪክ ሃይል ባለመኖሩ ጨለማ ውስጥ ኖረናል ያሉት ነዋሪው፣ ፕሮጀክቱ ሥራ ሲጀምር በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከማስቀረት ባለፈ የዘመናት የሀይል ችግራችንን ይፈታል ብለዋል። በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 300 የሶላር ሃይል ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለሕዝብ የሃይል ስርጭቱን በፍትሀዊነት ለማዳረስ እየተሠራ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።  
የሚታይ

ኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌ ብር-ኢንጌጅ" የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ
Apr 15, 2024 152
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌ ብር-ኢንጌጅ" የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ኩባንያው ዲጂታል ኢትዮጵያን በሁሉም ዘርፍ እውን ለማድረግ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። በተለይ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓቱን ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰዋል። ዛሬ ይፋ የሆነው "ቴሌ ብር- ኢንጌጅ" መተግበሪያ በዲጂታል ፋይናንስ ሽግግር ውስጥ የንግድ፣ የመንግስትና የግል ተቋማትን ትኩረት በማድረግ የዲጂታል ኢኮኖሚ ምህዳሩን ለማስፋት የሚረዳ ነው ብለዋል። የግለሰብም ሆነ የቢዝነስ ደንበኞች የተናጠል ወይም የቡድን ቀጥታ ውይይቶችን ለማድረግ፣ የግብይት መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣ በውይይቶች ወቅት ገንዘብ ለመላክና ለመቀበል እንደሚያስችል ገልጸዋል። እንዲሁም በዚህ አገልግሎት ደንበኞች የቢዝነስ ወይም ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮቻቸውን በፅሁፍ፣ በፎቶ፣ በድምጽ፣ በቪዲዮና በሰነድ መልክ መለዋወጥ ይችላሉ ነው ያሉት። ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደግ በጀመረው ቴሌ ብር አገልግሎት በየቀኑ 5 ቢሊዮን ብር የሚዘዋወር ሲሆን በ3 ዓመታት ውስጥ 2 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ዝውውር ተደርጎበታል።
የሕዝብ በዓላትና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ አብሮነት እና መተሳሰብ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተጠቆመ
Apr 15, 2024 145
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡-የሕዝብ በዓላትና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ አብሮነት እና መተሳሰብ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማሕበራዊ ልማት፣ ባሕልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል። ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያን መብት እና ጥቅም ያስከበረ፣ ትውልድ ተሻጋሪ፣ ግጭትና ንትርክን እንዲያስቀር ታስቦ እንደሚወጣ የጤና፣ ማሕበራዊ ልማት፣ ባሕልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ፣ ዘመኑን የዋጄ፣ ህጋዊ ዕውቅና ኖሮት ለሕዘብ አብሮነት እና መተሳሰብ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ሰብሳቢዋ አብራርተዋል፡፡ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ በበኩላቸው በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮቸ ካሉ እንደሚስተካከሉ ጠቅሰው፣ በውይይቱ ጠቃሚ ግብዓት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡   የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ የካቲት 12 በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተጨፈጨፉበት ዕለት ሆኖ ሳለ በረቂቅ አዋጁ ታስቦ ይውላል ከሚባል ተከብሮ እንዲውል ቢደረግ የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ እንዲሁም፣ ሃይማኖታዊ እና ብሔራዊ በዓላት በሚከበሩበት እለት በአልባሳት እና በቦታ ምክንያት ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ከፍተኛ አለመግባባት ሲፈጠር ይስተዋላልና ችግሩን ለመፍታት ምን ታስቧል? የሚል ጥያቄም ተነስቷል፡፡   የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው ምንም እንኳ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ቢደርስም፣ የየካቲት 12 በአል ቀደም ሲልም ታስቦ እንጂ ተከብሮ ስለማያውቅ እለቱ ታስቦ እንደሚውል መግለጻቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘመው መረጃ ያመላክታል።
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 16966
ኢዜአ
ፖለቲካ
ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ስኬታማነት የጃፓን መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል-በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ
Apr 15, 2024 189
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ስኬታማነት የጃፓን መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ተናገሩ፡፡ የጃፓን መንግስት ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 12 ተሸከርካሪዎችን በዛሬው ዕለት ድጋፍ አድርጓል።   በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የተሽከርካሪ ድጋፉን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አስረክበዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው የጃፓን መንግስት ከዚህ ቀደም ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው፤ በዛሬው እለት የተከናወነው ድጋፍም የዚሁ ማሳያ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ዶው በበኩላቸው ችግሮችን ለመፍታት ብሎም ዘላቂ እድገትን ለማፋጠን ውይይት ቁልፍ ሚና እንዳለው የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳይ አውስተዋል፡፡   ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማስፈን ሀገራዊ ምክክሩ ሚናው የጎላ እንደሆነ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፤ ኮሚሽኑ በሀገሪቱ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን አሳታፊ የሆነ ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ በርካታ ስራዎች እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።   ኮሚሽኑ አሁን ላይ በ10 ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተሳታፊዎች ልየታ በማጠናቀቅ ወደ ቀጣይ ምእራፍ ለመሸጋገር በሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህ አኳያ ድጋፉ ኮሚሽኑ በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ለሚያከናውናቸው ስራዎች መቀላጠፍ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የጃፓን መንግስት ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 3 ሚሊዬን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማበርከቱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።  
ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዕጩ ጥቆማ መቀበል ተጀመረ
Apr 15, 2024 116
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- ኅብረተሰቡ ከዛሬ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶችና ሕፃናት ሰብዓዊ መብት ምክትል ኮሚሽነር እጩ መጠቆም እንደሚችል ተገለጸ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶችና ሕፃናት ምክትል ኮሚሽነር ሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራ ጀምሯል። ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው ስምንት አባላት ያሉት ሲሆን ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል። የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በሰብሳቢነት ሲመሩት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ምክትል ሰብሳቢ ናቸው። የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው ጸኃፊ ባንቺይርጋ መለሰ በሰጡት መግለጫ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶችና ሕፃናት ኮሚሽነር በፈቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ምትክ ለመሰየም የምልመላ መሥፈርትና የውስጥ አሠራር መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ተገብቷል። በዚህም ኅብረተሰቡ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚገኘው የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ፣ በኢሜል፣ በፖስታና በኦንላይን ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ገልጸዋል። ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶችና ሕጻናት ምክትል ኮሚሽነርነት የሚመረጡት ሴት እጩ ተወዳዳሪ ማሟላት ያለባቸው መሥፈርቶችንም አብራርተዋል። ከመሥፈርቶቹ መካከልም ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተቆርቋሪ የሆኑ፣ በሕግ ወይም አግባብነት ባለው ሙያ ሰፊ ልምድና ዕውቀት ያላቸው፣ በሥነ-ምግባርና በሥራ ታታሪነት የተመሰገኑ እንዲሁም የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆኑ የሚሉት ይገኙበታል። ኮሚቴው ከጥቆማ በኋላ ዕጩዎችን በመሥፈርቱ መሰረት የመለየትና የማጣራት ሥራ በመሥራት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለምክር ቤቱ የሚያቀርብ መሆኑንም ነው ጸኃፊዋ ያመለከቱት። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55/14/ አዋጅ መሠረት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን የማቋቋም ተቋሙን የሚመሩ አባላትን የመሰየምና ሥልጣንና ተግባራቸውን በሕግ የመወሰን ሥልጣን አለው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ ከሆኑ የዴሞክራሲ ተቋማት መካከል አንዱ ነው።
ጄኔራል አበባው ታደሰ አሁናዊ የሠላም ሁኔታን በተመለከተ ከማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ጋር ተወያዩ
Apr 15, 2024 165
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፦ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ እና የሰሜን ሸዋ ዞን አሁናዊ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም በወደፊት የሥራ አቅጣጫ ላይ ከማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ጋር ተወያይተዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አሸባሪውን ሸኔ እና ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራውን ፅንፈኛ ኃይል አከርካሪውን በመስበር በሁለቱም ዞን አንፃራዊ ሰላም መስፈን መቻሉን አረጋግጠዋል፡፡ ጄኔራል አበባው ታደሰ በከሚሴ ከተማ ከማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ከፍተኛ አመራሮችና ከሁለቱም ዞን ከተውጣጡ የአስተዳደር አካላት ጋር ባደረጉት ውይይት ፅንፈኛው ኃይል አዲስ አበባን ለማተራመስ ይመቸኛል ብሎ አለኝ ያለውን ኃይል በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ሰግስጎ እንደነበረ አስታውሰዋል።   የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት በወሰደው ፈጣን እርምጃ በሁለቱም ዞን የነበሩ ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ፅንፈኞችን በመደቆስ ሀገር የማተራመስ ቀቢፀ ተስፋቸውን በማምከን ምርጥ ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል። አሁን ለብቻው ተነጥሎ በየሸጡ ተደብቆ የሚገኘውን የፅንፈኛ ኃይል አመራሮችን የመመንጠሩ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጄኔራል መኮንኑ አሳስበዋል፡፡ የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢና የኮማንዶና አየር ወለድ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔራሰብ እና ሰሜን ሸዋ ዞን የሀገሪቷን ሰላም በማናጋት የህዝቦቿን በሰላም የመኖር ዋስትናን ለማሳጣት ቆርጠው የተነሱትን ሁለቱንም ፅንፈኛ ኃይሎች በተገቢው መንገድ በመምታት የጥፋት ተልዕኳቸውን ማኮላሸት መቻሉን ገልፀዋል።   ኮማንድ ፖስቱ ከኦፕሬሽናል ስራው ጎን ለጎን የአካባቢውን የፀጥታ ኃይል የማጠናከርና የማደራጀት ስራዎችን መስራቱን በማስታወስ አሁን በሁለቱም ዞን ለፀጥታው ኃይል ተግዳሮት የሚሆን ሃይል እንደሌለም አረጋግጠዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊውችም የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ራሱ ሞቶ ዜጎችን የሚያኖር ህዝባዊ ሀይል መሆኑን በማስታወስና በዞናቸው ለተገኘው ሰላም ሠራዊቱ ለከፈለው መስዋዕትነት እና ላስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት የላቀ ክብር እንዳላቸው አብራርተዋል። አሁን የፅንፈኞችን ሴራ ህዝባችንም በተገቢው መንገድ ስለተገነዘበ እኛም ሆነ ህዝባችን ከሠራዊታችን ጎን ስለሆን የዚህን ሀይል ርዝራዦች ለማጥፋት ብዙም አስቸጋሪ እንደማይሆን እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረስብ ዞን በዞኑ ለስመዘገቡት የተራጋጋ ሰላምና ፀጥታ እውቅና በመስጠት ለሠራዊቱ አመራሮች ልዩ ሽልማት ከምስጋና ጋር ማበርከታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ በብሪክስ የሚኖራትን ተጠቃሚነት በሚያሳድግ እና ለማዕቀፉ መጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ
Apr 14, 2024 882
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነት የሚኖራትን ተጠቃሚነት ክፍ ለማድረግና ለማዕቀፉ መጠናከር ጉልህ አስተዋጽዖ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ። በብሪክስ ማዕቀፍ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የቴክኒክ ኮሚቴ ሦስተኛ ስብሰባ ሚያዝያ 03 ቀን 2016 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተካሂዷል። ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አገራችን በዘላቂነት የምትከተለው ስትራቴጂ እና የአገራችን ተቋማት በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ እያደረጉ ያሉትን ተሳትፎ ዳስሷል፡፡   ኮሚቴው በተጨማሪም አገራችን በማዕቀፉ አባልነት የምታደርገውን ሽግግር ለማሳካት፣ ተጠቃሚነቷን ከፍ ለማድረግ፣ብሎም ለማዕቀፉ መጠናከር ጉልህ አስተዋጽዖ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክሯል። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል የሆነችው የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተጨማሪ ዕድሎችን ለመጠቀም ነው። በተጨማሪም የዓለምን የባለብዙ ወገን ሥርዓት ይበልጥ እንዲጠናከር የበኩሏን አስተዋጽዖ ለማድረግ በማሰብ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ኮሩ ባደረገው ተከታታይ ዘመቻ የአሸባሪው የሸኔ ቡድን አባላት ለመከላከያ እጅ እየሠጡ ነው
Apr 13, 2024 562
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 05/2016 (ኢዜአ)፡- በምስራቅ ሸዋ ዞን የሚንቀሳቀሰው አሸባሪው የሸኔ ቡድን ኮሩ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ እየተደመሰሰ እና እጅ እየሠጠ መሆኑ ተገልጿል። የሽብር ቡድኑን በመቀላቀል ለሽብር ቡድኑ በሎጀስቲክስ ፣ በተተኳሽ አቅርቦት፣ በሶሻል ሚዲያዎች የአሸባሪው ክንፍ በመሆን የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ የሸኔ አባላት የነበሩበት ሁኔታ የተሳሳተ እንደነበርም ገልፀዋል።   የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦኘሬሽናል ኮሎኔል ብርሃኑ አዱኛ እንዳሉት ኮሩ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ባደረገው ዘመቻ አብዛኛው የሽብር ቡድኑ ሃይል ሲደመሰሰ ቀሪው በሰላማዊ መንገድ እጁን ለመሥጠት መገደዱን ተናግረዋል። ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር 1 ብሬን፣ 1 ስናይፐር ፣ 50 ክላሽ፣ 29 ቦንብ ፣ 2892 የክላሽ ጥይት፣ 72 የክላሽ ካዝና፣ 350 የብሬን ጥይት ገቢ መደረጉን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።   የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ የሽብር በበኩላቸው ቡድኑ በዞኑ ቦሰት ወረዳ፣ ሊበን ወረዳ፣ቦራ ወረዳ እና ፈንታሌ ወረዳዎችን በመያዝ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ በማድረግ በመሰረተ ልማቶች ላይ አደጋ ሲፈጥሩ እንደቆዩም ተናግረዋል። የሸኔ ቡድን ተደጋጋሚ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ባለመቀበል በደል ሲፈፅሙ የቆየ ቢሆንም መከላከያና የክልሉ የፀጥታ ሃይል በወሰደው እርምጃ እጃቸውን መሥጠታቸውንም ተናግረዋል።
የአገራዊ ምክክሩ ሂደቱ ተሳታፊዎች ሀገራዊ መግባባት በሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው - ኮሚሽኑ
Apr 13, 2024 442
ሻሸመኔ፤ ሚያዝያ 5/2016(ኢዜአ)፦ በአገራዊ ምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ የህብረተሰብ ተወካዮች ሀገራዊ መግባባት በሚፈጥሩ ጉዳዮች በማተኮር ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስገነዘበ። ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ከባሌ ዞን 11 ወረዳዎች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ በአጀንዳ ልየታው የሚሳተፉ 176 ተወካዮችን አስመርጧል።   ኮሚሽነር ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት ኮሚሽኑ አካታች፣ አሳታፊና ግልጽነት የተሞላ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ህዝቡ በሀገሩ ጉዳይ በባለቤትነት እንዲሳተፍ እየሰራ ነው። መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚታዩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ሀገራዊ ምክክር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰው፤ በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ የህብረተሰብ ተወካዮች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል። በተለያዩ ክልሎች በአጀንዳ መረጣ የሚሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች መረጣ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልልም በአራት ክላስተሮች በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ የህብረተረሰብ ተወካዮችን የመምረጥ ሂደት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ በእስካሁኑ ሂደትም በ282 ወረዳዎች 5ሺህ 94 የህብረተሰብ ተወካዮች መመረጣቸውን ጠቅሰዋል። ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው የምክክር መድረኩ በህዝቡ ባለቤትነት የሚመራ በመሆኑ በየደረጃው በአጀንዳ ልየታው የሚሳተፉ የህብረተሰብ ተወካዮች ተሳትፎ ድርሻው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። በአገሪቱ በውይይት ችግሮችን ለመፍታት ኮሚሽኑ የያዘውን የሰላም አማራጭ ከግብ ለማድረስ ሁሉም መተባበር አለበት ብለዋል። በመድረኩ ከተሳተፉት መካከል ከባሌ ሮቤ የመጡት አባገዳ መለሰ ረታ፣ ኮሚሽኑ ለሀገር ሰላም፣ አንድነትና ልማት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ መገንዘባቸውን ተናግረዋል። ሰላምና ልማትን ማወጅ የአባገዳዎች ፍላጎት መሆኑን ገልጸው ''አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት ኮሚሽኑ ያስቀመጠው አሰራር ተገቢ ነው'' ብለዋል። ለኮሚሽኑ ስራ ውጤታማነትም ህዝቡን በማስተባበርና ጠቃሚ አጀንዳዎችን በመስጠት ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ሌላኛው ወጣት መሃመድ አማኑ በበኩሉ፤ እንደ ሀገር የሚያጋጥሙ ችግሮች በውይይትና ምክክር መፈታት አለባቸው ብሏል። ወጣቶችንን ወክሎ በተሳታፊ ልየታው መገኘቱን ጠቅሶ፤ ለምክክር ኮሚሽኑ ስኬታማነት የድርሻውን እንደሚወጣ ገልጿል።  
በአፋር ክልል የወጣቶች ምክር ቤት ተመሰረተ
Apr 13, 2024 453
ሰመራ፤ ሚያዚያ 5/2016(ኢዜአ)፦ በአፋር ክልል የወጣቶች ምክር ቤት ዛሬ በይፋ ተመሰረተ። ዛሬ በተከናወነው የምስረታ ስነ- ስርዓት የምክር ቤት አባላትና ስራ አስፈፃሚዎች ተመርጠዋል። በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ወይዘሮ የሺ ወርቅ አየነ እንዳሉት፤ በክልል ደረጃ የወጣቶች ምክር ቤት መመስረቱ የሚበረታታ ነው።   አደረጃጀቱም ከተናጠል ይልቅ በጋራ መንቀሳቀስ ለውጤት እንደሚያበቃ አመልክተው፤ አሳታፊና አካታች በሆነ መንገድ የወጣቱን ድምፅና መብት ማስከበር እንደሚገባ ጠቁመዋል። "አደረጃጀቱ ወጣቶች ያላቸውን አቅም እንዲጠቀሙና ራሳቸውን አብቅተው አገራቸውንና ራሳቸውን መጥቀም የሚችሉበት ነው" ያሉት ደግሞ የክልሉ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡመር ኑሩ ናቸው።   ለወጣቶች ሁለንተናዊ መብት መከበር ምክር ቤቱ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ ተናግረዋል። የክልሉ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጠው ኢንጂነር ኢብራሂም መሐመድ ሙሳ ፤ ለወጣቱ ሁለንተናዊ መብት መከበር ምክር ቤቱ ያለሰለሰ ጥረት ያደርጋል ብሏል።   ምክር ቤቱ 14 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ሰይሟል። የምክር ቤቱን ምስረታ መርሃ ግብር ያሰናዱት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ከአፋር ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና ከኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት በጋራ መሆኑን በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር ያሰለጠናቸውን ወታደራዊ ፖሊስ አባላትን አስመረቀ
Apr 13, 2024 487
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2016 (ኢዜአ) የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር ያሰለጠናቸውን የኮር እና የክፍለ ጦር ወታደራዊ ፖሊስ አባላትን አስመርቋል። የኮሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ወርቅነህ ጉደታ የወታደራዊ ፖሊስ ስልጠናን አጠናቃችሁ የተመረቃችሁ የደጀን ጥበቃ የሰራዊት አባላት ጠንካራ ስልጠናዎችን በብቃት ተወጥታችሁ ለምረቃ መብቃታችሁ የጥንካሬያችሁ ማሳያ ነው ብለዋል። ተመራቂዎች በቀጣይም ወታደራዊ ደንቦችንና ስርዓትን ማስከበር እንዲሁም በኮማንድ ፖስቱ የተቀመጡ ተልዕኮዎችን በድል መፈፅም ይጠበቅባችኋል ሲሉ ጄኔራል መኮንኑ አሥገንዝበዋል።   አሁን ላይ በአካላዊ ጥንካሬ ፣ በስነ-ልቦና እና በወታደራዊ ሳይንስ የበቃ ጊዜን እና ቴክኖሎጂን በአግባቡ የሚጠቀም የሰው ሃይል እያሰለጠን እንገኛለን ያሉት ብርጋዲየር ጄኔራል ወርቅነህ ጉደታ ሰራዊቱ በፅንፈኞችና በፀረ-ሰላም ሀይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ የሰላም ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች ወደ ቀደመ ሰላማቸው እንዲመለሱ በማድረግ የተሰጠውን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን አስረድተዋል።   የስልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት ሻምበል አሰፋ ቅጣው ፤ የወታደራዊ ፖሊስ ሥልጠና የወሠዱ የደጀን ጥበቃ አባላት በሰልጠና ቆይታቸው ፈታኝ በሆነ የአየር ንብረት ሁሉንም የመሬት ገፅ በማስተዋወቅ በቀጣይ የሚሰጣቸውን ግዳጅ በአጭር ጊዜ በዲሲፒሊን እና በሃላፊነት በብቃት የሚወጡበት አቅም መጨበጣቸውን ገልፀዋል። የወታደራዊ ፖሊስ ስልጠና ከወሰዱ የደጀን ጥበቃ አባላት እና አሰልጣኞች መካከል አስር አለቃ ደረጀ ደምሴና ምክትል አስር አለቃ አበራሽ መከበ ስልጠናው ውስብስብ ግዳጆችን በጥበብና በጀግንነት እንዲወጡ አይነተኛ ሚና መኖሩን ገልፀው ከስልጠናው አካላዊና አእምሯዊ ብቃት እንዳገኙ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ቀጣይም የሚሰጣቸውን ግዳጅ በአግባቡ ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ማህበራዊ
በዓለም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የመንግስታትና የሃይማኖት ተቋማት የትብብር ስራ ወሳኝ ነው - ዶክተር ከይረዲን ተዘራ
Apr 15, 2024 164
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የመንግስታትና የሃይማኖት ተቋማት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ከይረዲን ተዘራ ገለጹ። የ37 የዓለም ሀገራት የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የተሳተፉበት ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በጉባዔው የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ከይረዲን ተዘራ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት በሃይማኖት መቻቻልና መከባበር የምትታወቅ ሀገር ናት፡፡   ሁሉም ሃይማኖቶች በጎነትንና ሰላምን በመስበክ ለሀገርና ለትውልድ በአብሮነት መቀጠል ጉልህ አሻራ ማሳረፋቸውንም ገልጸዋል። መንግስት የሃይማኖት ተቋማት በሰላም ግንባታና በሀገራዊ አንድነት ላይ ቁልፍ ሚና እንዳላቸው በፅኑ በማመን በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቅርቡ ከተለያዩ የእምነት አባቶች ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያደረጉትን ውይይት በማሳያነት ጠቅሰዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የመንግስታትና የሃይማኖት ተቋማት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው ያመላከቱት፡፡ ኢትዮጵያ የጋራ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ከራሷ ባለፈ በአፍሪካና በተቀረው የዓለም ክፍል ለሰው ልጆች ሰላምና ደህንነት በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሓን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት ዋና ፍላጎትና ስራቸው በምድሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ነው ብለዋል፡፡ ይህ እውን እንዲሆንም የዓለም መንግስታትና ህዝቦች መነጋገር፣ መደማመጥ፣ ልዩነቶች እንኳ ቢኖሩ በንግግር መፍታት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ክብርንና አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ ለመከላከል አበክሮ መስራት እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ የቡድን 20 የሃይማኖት ትስስር ማህበር ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ኮል ዱርሐም ናቸው፡፡ ላምን ማህበረሰባዊ እሴትነት ለማጎልበትም የሃይማኖት ተቋማት ሃላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል። የምክክር መድረኩ የሃይማኖት ተቋማቱ በጋራ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም በመያዝ ወደ ተግባር እንዲገቡ ለማድረግ ሚናው ከፍተኛ ነውም ብለዋል፡፡ "የሃይማኖት ተቋማት ትብብር ሰላምን፣ ሰብዓዊ ክብርን፣ ልማትን፣ አካባቢ ጥበቃን፣ ማጠናከርና የጥላቻ ንግግርን ግጭትንና ጠባብ ብሔርተኝነትን መቃወም" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሔደ ያለው የምክክር መድረክ ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የኦሮሞ ባህልና ኪነ-ጥበብ የህዝቡን አንድነት የሚያስጠብቅ ሆኖ እንዲቀጥል ትኩረት ተደርጓል
Apr 15, 2024 85
አዲስ አበባ ሚያዚያ 07/2016(ኢዜአ)፦የኦሮሞ ህዝብ ባህልና የኪነ-ጥበብ ውጤቶች የህዝቡን አንድነት የሚያስጠብቁ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር አብዱልዓዚዝ ዳውድ ገለጹ። የኦሮሞ ህዝብ ባህላዊ ትውፊቶች የሚታዩበት ኤግዚቢሽን በኦሮሞ ባህል ማዕከል የተከፈተ ሲሆን በተለያዩ የኪነ-ጥብብ ዘርፎች ለሦስት ወራት የሰለጠኑ ወጣቶችም ተመርቀዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳና ሃዳ ሲንቄዎች፣ የኪነ-ጥባብ ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች ታድመዋል።   ኃላፊው በዚህ ጊዜ እንዳሉት የክልሉ ባህልና ኪነ-ጥበብ ተጽዕኖ የሚፈጥርና የህዝቡን አንድነት የሚያስጠብቅ እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። ባህልና ኪነ-ጥበብ የአንድ ህዝብ ትልቅ መገለጫ ነው ያሉት ዶክተር አብዱልአዚዝ ትውልዱ በዘርፉ በቂ እውቅት እንዲኖረው የተጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጥና የማስተዋወቅ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል። ባህልና ኪነ-ጥበብ በዘመን ሂደት የህዝብን አንድነትና ባህል ከማጠናከርና ከማስተዋወቅ አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑንም አንስተዋል። የኦሮሚያ ክልል መንግስትም የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ኪነ-ጥበብ ውጤቶች የህዝቡን አንድነት የሚያስጠብቁ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል። በተለይም የቀደመው ትውልድ የራሱን ተሰጥኦ ተከትሎ በጎ አሻራዎችን ማሳረፉን አስታውሰው የአሁኑ ትውልድ ደግሞ በባህልና ኪነ-ጥበብ ዙሪያ ዘመኑን የሚመስል እውቀት መጨበጥ አለበት ብለዋል። ''ኪነ ጥበብ ከዘመን ጋር እንዲራመድ ለማስቻል የቀደመው ትውልድ በሰራው ስራ ላይ መሻሻሎች እንዲኖሩ ወጣቱን ትውልድ እውቀት የማስጨበጡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል'' ነው ያሉት። የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲምቢሮ በበኩላቸው፣ የባህልና ኪነ ጥበብ ዘርፉ ከህዝብ መገለጫነት በላፈ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት ብለዋል። ባህልና ኪነ-ጥበብ የህዝቡን አንድነት፣ ህብረትና ትብብር ከማጠናከር በተጨማሪ ለወጣቶች እንደ ስራ እድል መፍጠሪያ ጥቅም ላይ ሊውል ይገባል ብለዋል። ወጣቶች የህዝቡን ባህልና ኪነ-ጥብብ ለማሳደግና ለማስተዋወቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተጨማሪ እወቅት እየጨበጡ ህዝባቸውን የበለጠ እንዲጠቅሙ የሚያደርግ መሆኑንም አክለዋል። የኦሮሞ ባህልና ኪነ-ጥበብ የህዝቡን አንድነት ማስጠበቅ፣ ህዝቡን ማነቃቃት፣ የአገር ፍቅር ያለው ህብረተሰብ ለመገንባትና ሰላምን ለማጽናት ትልቅ አስተዋ ማበርከቱን የገለጹት ደግሞ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ መኪያ ጀማል ናቸው። ባህልና ኪነ-ጥበብ የበለጠ ለህዝቡ የጋራ ጥቅም እንዲውል ወጣቶችን እውቀት የማስጨበጡ ስራ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንደሚከናወን ገልጸዋል። በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ለሦስት ወራት የሰለጡ ወጣቶች በበኩላቸው በአገኙት እውቀት የህዝቡን በህልና ማንነት ለማስተዋወቅ እንደሚተጉ ተናግረዋል።
ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት በመከላከል ሂደት የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ የሚያሳድግ የአሰራር ማዕቀፍ ተዘጋጀ
Apr 15, 2024 75
አዳማ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት በመከላከል ሂደት የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ የሚያሳድግ የአሰራር ማዕቀፍ መዘጋጀቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ዛሬ በአዳማ ከተማ ከፍትህና ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም የክልሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የብሔራዊ የስርዓተ ጾታ ጥቃት መከላከልና ምላሽ መስጠት የአሰራር ማዕቀፍ የማስጀመሪያ መድረክ ተካሄዷል፡፡ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዲኤታ ማእረግ የሚኒስትሯ አማካሪ አቶ ጌታቸው በዳኔ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የአሰራር ማዕቀፉ በተለይም ቀድሞ የነበረውን የአሰራር ወጥነት ችግር ለመቅረፍ ያግዛል፡፡   የአሰራር ማዕቀፉ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከልና ተጋላጭነትን ለመቀነስ እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀ የምላሽ ስራዎችን ለማከናወን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መከተል ያለባቸውን የአሰራር ስርዓት የያዘ መሆኑን ገልጸዋል። በዋናነትም ቀድሞ ይታዩ የነበሩ የአሰራር ወጥነት ችግሮችን በመቅረፍ ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙ የተቋቋመውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነቱን ለማረጋገጥም ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። ማዕቀፉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጾታዊ ጥቃት መከላከል ሂደት ተጋላጭነትን መቀነስ የሚያስችሉ አሰራሮችን ተግባራዊ እንዲያደርጉም አቅጣጫ የሚያመላክት ነው ብለዋል። ማዕቀፉ አላማውን እንዲያሳካ የጋራ ትብብራቸው አስፈላጊ የሆኑት ፍትህ፣ ጤና ሚኒስቴር፣ ፖሊስና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት መረባረብ እንደሚገባቸውም አመላክተዋል፡፡ በጉዳዩ ቀጥተኛ ኃላፊነት ከተጣለባቸው ባለድርሻ አካላት መካከልም የፍትህ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኤርሚያስ የማነብርሃን፣ ፆታዊ ጥቃትን ለመመከት የሚያግዝ ወጥ የአሰራር ማዕቀፍ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ማዕቀፉ ከሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ክፍተቶችን አስወግዶ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት የተዘጋጀ በመሆኑ በዚህ ረገድ ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።   የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ በበኩላቸው ማዕቀፉ በጾታዊ ጥቃት ምክንያት እየደረሰ ያለውን የጤናና ተያያዥ ችግሮች ለመከላከል የሚረዳ መሆኑን አክለዋል። በጤና ሚኒስቴር ዘርፍ በአሰራር ማዕቀፉ መሰረት የሚፈጸሙ ተግባራትን በማዘጋጀት እስከ ክልሎች በማውረድ የማስተባበር ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።  
የሕዝብ በዓላትና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ አብሮነት እና መተሳሰብ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተጠቆመ
Apr 15, 2024 145
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡-የሕዝብ በዓላትና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ አብሮነት እና መተሳሰብ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማሕበራዊ ልማት፣ ባሕልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል። ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያን መብት እና ጥቅም ያስከበረ፣ ትውልድ ተሻጋሪ፣ ግጭትና ንትርክን እንዲያስቀር ታስቦ እንደሚወጣ የጤና፣ ማሕበራዊ ልማት፣ ባሕልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ፣ ዘመኑን የዋጄ፣ ህጋዊ ዕውቅና ኖሮት ለሕዘብ አብሮነት እና መተሳሰብ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ሰብሳቢዋ አብራርተዋል፡፡ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ በበኩላቸው በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮቸ ካሉ እንደሚስተካከሉ ጠቅሰው፣ በውይይቱ ጠቃሚ ግብዓት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡   የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ የካቲት 12 በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተጨፈጨፉበት ዕለት ሆኖ ሳለ በረቂቅ አዋጁ ታስቦ ይውላል ከሚባል ተከብሮ እንዲውል ቢደረግ የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ እንዲሁም፣ ሃይማኖታዊ እና ብሔራዊ በዓላት በሚከበሩበት እለት በአልባሳት እና በቦታ ምክንያት ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ከፍተኛ አለመግባባት ሲፈጠር ይስተዋላልና ችግሩን ለመፍታት ምን ታስቧል? የሚል ጥያቄም ተነስቷል፡፡   የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው ምንም እንኳ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ቢደርስም፣ የየካቲት 12 በአል ቀደም ሲልም ታስቦ እንጂ ተከብሮ ስለማያውቅ እለቱ ታስቦ እንደሚውል መግለጻቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘመው መረጃ ያመላክታል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ ለስታርት አፖች ከፋይናንስ አቅርቦት ጀምሮ ምቹ ምህዳርን የሚፈጥሩ የፖሊሲ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምራለች-ዶክተር ብሩክ ታዬ
Apr 15, 2024 213
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለስታርት አፖች ከፋይናንስ አቅርቦት ጀምሮ ምቹ ምህዳርን የሚፈጥሩና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር የሚተገበሩ ጠንካራ የፖሊሲ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመሯን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ገለጹ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ስታርት አፖች ፈንድ ሊያገኙ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል። ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት መንግስት ስታርት አፖች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በተቀናጀ መልኩ ለመቅረፍ እየሰራ ነው።   ኢትዮጵያ ለስታርት አፕ ምቹ ምህዳርን ለመፍጠር ከፋይናንስ አቅርቦት፣ ከህግ፣ ከመሰረተ ልማትና ሌሎች ጉዳዮች አኳያ ጠንካራ የፖሊሲ እርምጃዎች መውሰድ መጀመሯን ለልማት አጋሮች አብራርተዋል። ይህንን ለማጠናከርም መንግስት ከልማት አጋሮች፣ ከግሉ ዘርፍና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ለስታርት አፖች ውጤታማነት ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን አንስተው፥ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ውይይቶችም እየተካሄዱ ስለመሆኑ አስረድተዋል።   በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የአካታች እድገት እና ዘላቂ ልማት የኢትዮጵያ ቡድን መሪ የሆኑት ግዛቸው ሲሳይ በበኩላቸው፥ ስታርት አፖች በፋይናንስ እጥረት ምክንያት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ከመንግስት ጋር በትብብር እየሰራን ነው ብለዋል። የመንግስታቱ የልማት ፕሮግራም ከብሔራዊ ባንክ እና ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ጋር በመሆን የፈጠራ ፋይናንስ አሰራርን መዘርጋቱን ተናግረዋል። በዚህም የቴክኒክ ድጋፍ እና ብድር ለስታርት አፖች እንዲቀርብ ይደረጋል ነው ያሉት።   የዓለም ባንክ ተወካይ ማርሎን ረውሊንስ እንዳሉት ባንኩ በኢትዮጵያ ለተለያዩ የልማት እና የድህነት ቅነሳ ፕሮግራሞች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሀገሪቱ የጀመረችው የዕድገት ጉዞ እንዲሳካ በቀጣይ ድጋፉን እንደሚቀጥል ጠቅሰው በተለይ በኢትዮጵያ በጅምር ላይ ያለው የስታርት አፕ ምቹ ምህዳርን ለማስፋት የቴክኒክ ድጋፎችን ያደርጋል ብለዋል። ባንኩ የስራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታትም ስታርት አፖችን የማማከር፣ ፕሮጀክታቸው ላይ ግብረ መልስ በመስጠት የማገዝ ስራን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ የድጋፍ ዕይታን እንደሚከተል ጠቁመዋል።              
በክልሉ በሚገኙ የባለበጀት መስሪያ ቤቶች የዘጠኝ ወራት የፋይናንስ አስተዳደር የሚፈትሽ ድጋፋዊ ግምገማ ዛሬ ተጀምሯል
Apr 15, 2024 107
ሀዋሳ ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል በሚገኙ የባለበጀት መስሪያ ቤቶች የዘጠኝ ወራት የፋይናንስ አስተዳደር የሚፈትሽ ድጋፋዊ ግምገማ ዛሬ መጀመሩን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ የፋይናንስ ቢሮው ሃላፊ ዶክተር አራርሶ ገረመው በዚሁ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። የድጋፋዊ ግምገማ ዓላማውም በክልሉ ከመንግስትና ከተለያዩ አማራጮች የሚመጣ ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ በጅት ያለምንም ብክነት የህዝብ የልማት ጥያቄ ሊመልስ በሚችል መልኩ እንዲውል ቢሮው ጠንካራ የሆነ የቁጥጥርና የምዘና ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። በክልሉ 106 ባለበጀት መስሪያ ቤቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ሃላፊው፤ እያንዳንዱ መስሪያ ቤት የሚመደብለትን ገንዘብ ለህዝብ ፍላጎት የማዋል ግብ ስለማሳካቱ ቁጥጥርና ክትትል ይደረጋል ብለዋል። የንብረትና ገንዘብ አያያዝና አስተዳደር፣ ሪፖርት ማድረግና አያያዝ፣ የግዥ ስርዓትን ጨምሮ ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ባላቸውና የአገር ዓቀፉንና ዓለም አቀፉን የፋይናንስ አሰራር በተከተሉ 26 የመገምገሚያ መስፈርቶች እንደሚፈተሹም አንስተዋል። በበጀት ዓመቱ ከተበጀተው ከ22 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር 34 በመቶ ለካፒታል ፕሮጀክቶች የተመደበ መሆኑን አስታውሰዋል። በአጠቃላይ በክልሉ የህዝብ ፍላጎት መሰረት በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ የሚገኙ የውሃ፣ የመንገድ፣ የጤናና ሌሎች መሰረተ ልማቶች በጀቱ እየዋለ ስለመሆኑ በአግባቡ እንደሚፈተሽ ተናግረዋል። የክልሉን የፋይናንስ ስርዓት ግልጽ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት ለመዘርጋት የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል። በክልሉ ባለፉት የዘጠኝ ወራት የፋይናንስ ስርዓት ለመፈተሽ የተጀመረው ድጋፋዊ ግምገማ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን፤ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩትን ማበረታታትና ጉድለት የሚታይባቸውን ማረም ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።    
በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ከአስር ቢሊዮን ብር በላይ የመንገድ ፈንድ ገቢ ተሰበሰበ
Apr 15, 2024 107
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለመንገዶች ጥገና እና የመንገድ ደህንነት ማስፈጸሚያ የሚሆን ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የመንገድ ፈንድ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ። በተሰበሰበው ገቢ የወቅታዊና መደበኛ የመንገድ ጥገና ሥራዎች መከናወናቸውም ነው አስተዳደሩ የገለጸው። ገቢው የተገኘው በነዳጅ ላይ ከተጣለ ታሪፍ፣ ከተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት፣ ከመንገድ ጠቀሜታ ክፍያ እና በክብደት ላይ የተመሰረተ ዓመታዊ የተሽከርካሪ ፈቃድ ማደሻ መሆኑም ተመልክቷል። የተሰበሰበውን ገቢ ለመንገድ ጥገና ከማዋል አንፃር በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ ባቀረቡት የክፍያ ሰርቲፊኬት መሰረት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር(ኢመአ) 4 ቢሊዮን 163 ሚሊዮን 410 ሺህ 907 ብር ከ23 ሳንቲም፣ የክልል ገጠር መንገድ ኤጀንሲዎች 1 ቢሊዮን 726 ሚሊዮን 478 ሺህ 976 ብር ከ99 ሳንቲም መከፈሉን ከአስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። በተጨማሪም የከተማ መንገድ ኤጀንሲዎች 916 ሚሊዮን 865 ሺህ 104 ብር ከ27 ሳንቲም እንዲሁም ለድጋፍ ሰጪ(የአማካሪ ክፍያ) 17 ሚሊዮን 471 ሺህ 811 ብር ከ59 ሳንቲም፣ ለመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት 26 ሚሊዮን 519ሺህ 109 ብር ከ14 ሳንቲም እና የባንክ፤ ለፖስታ ቤት ኮሚሽን ክፍያ 12ሚሊዮን 770 ሺህ 80 ብር ከ33 ሳንቲም በአጠቃላይ በመንገድ ጥገና ጥቅም ላይ እንዲያውሉ 6 ቢሊዮን 863 ሚሊዮን 515 ሺህ 989 ብር ከ55 ሳንቲም መከፈሉን ገልጿል፡፡ የተመደበው በጀት ለተገቢው አገልግሎት መዋሉን ከማረጋገጥ አኳያ በአስተዳደሩ፣ በክልል እና በከተማ የመንገድ ኤጀንሲዎች በሚያስተዳድሯቸው ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ቅኝት የማድረግና የምህንድስና(ቴክኒካል) ኦዲት ሥራ መከናወኑም በመረጃው ተገልጿል። አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ከመንገድ ፈንድ የሰበሰበው ገቢ 10 ቢሊዮን 356ሚሊዮን 19ሺህ 307 ብር ከ40 ሳንቲም መሆኑንም አስታውቋል።
በኮንሶ ዞን አንድ ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሶላር ሃይል ፕሮጀክት 70 በመቶ ተጠናቋል -- ሚኒስቴሩ
Apr 15, 2024 112
ካራት ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በኮንሶ ዞን አንድ ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው የሶላር ሃይል ፕሮጀክት 70 በመቶ መጠናቀቁን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ የሚመራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና የኮንሶ ዞን ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ፕሮጀክቱን ዛሬ ጎብኝተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው በዚህ ወቅት እንዳሉት እንደ አውሮፓውን አቆጣጠር በ2030 የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ 35 በመቶውን በሶላር ሃይል ለመሸፈን እየተሠራ ነው። መስሪያ ቤቱ የኤሌክትሪክ ሀይል የማያገኙ የገጠር ነዋሪዎችን የሶላር ሃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች 650 ኪሎ ዋት ሃይል ማመንጨት የሚችሉ አምስት የሶላር ሃይል ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተከናወኑ ካሉ የሶላር ሃይል ፕሮጀክቶች በኮንሶ ዞን ኬና ወረዳ ጌራ ቀበሌ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው ፕሮጀክት አንዱ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት የግንባታ ስራው የተጀመረው ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት 70 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ በመጪው ሰኔ ወር ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ አንድ ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን ገልጸዋል። በሀገር ደረጃ ባለፉት 10 ዓመታት ዋናው ሃይል የማይደርስባቸው አካባቢዎች ላይ ሀይል ለማዳረስ በተከናወኑ ስራዎች 320 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የሶላር ሃይል በሁሉም ክልሎች በመገንባት ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ፕሮጀክቶቹ ኅብረተሰቡን የሃይል ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለመስኖ ልማት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልጌሎ ገልሾ በዞኑ ከፍተኛ የሃይል ተደራሽነት ችግር መኖሩን ጠቅሰው፣ ፕሮጀክቱ ከመሠረተ ልማት ርቆ ለሚኖር ሕዝብ መገንባቱ ፋይዳውን የላቀ ያደርገዋል ብለዋል።   ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ኅብረተሰቡን የሃይል ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ የእህል ወፍጮ፣ የእንጨትና ብረታ ብረት ሥራዎችን መስራት ስለሚያስችል ለወጣቱ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። የሕዝቡን የዘመናት የመልካም አስተዳደር ችግር ለሚፈታው ለዚህ ፕሮጀክት ተገቢው ጥበቃ ማድረግ እንደሚገባም አስተዳዳሪው ተናግረዋል። ማህበረሰቡ ማገዶ እንጨት የሚጠቀም በመሆኑ በደን ሀብት ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በኮንሶ ዞን ኬና ወረዳ ጌራ ቀበሌ ነዋሪ አቶ በላቸው ቦራንቶ ናቸው።   ለብዙ ዓመታት በአካባቢያችን የኤሌክትሪክ ሃይል ባለመኖሩ ጨለማ ውስጥ ኖረናል ያሉት ነዋሪው፣ ፕሮጀክቱ ሥራ ሲጀምር በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከማስቀረት ባለፈ የዘመናት የሀይል ችግራችንን ይፈታል ብለዋል። በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 300 የሶላር ሃይል ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለሕዝብ የሃይል ስርጭቱን በፍትሀዊነት ለማዳረስ እየተሠራ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።  
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌ ብር-ኢንጌጅ" የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ
Apr 15, 2024 152
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌ ብር-ኢንጌጅ" የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ኩባንያው ዲጂታል ኢትዮጵያን በሁሉም ዘርፍ እውን ለማድረግ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። በተለይ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓቱን ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰዋል። ዛሬ ይፋ የሆነው "ቴሌ ብር- ኢንጌጅ" መተግበሪያ በዲጂታል ፋይናንስ ሽግግር ውስጥ የንግድ፣ የመንግስትና የግል ተቋማትን ትኩረት በማድረግ የዲጂታል ኢኮኖሚ ምህዳሩን ለማስፋት የሚረዳ ነው ብለዋል። የግለሰብም ሆነ የቢዝነስ ደንበኞች የተናጠል ወይም የቡድን ቀጥታ ውይይቶችን ለማድረግ፣ የግብይት መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣ በውይይቶች ወቅት ገንዘብ ለመላክና ለመቀበል እንደሚያስችል ገልጸዋል። እንዲሁም በዚህ አገልግሎት ደንበኞች የቢዝነስ ወይም ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮቻቸውን በፅሁፍ፣ በፎቶ፣ በድምጽ፣ በቪዲዮና በሰነድ መልክ መለዋወጥ ይችላሉ ነው ያሉት። ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደግ በጀመረው ቴሌ ብር አገልግሎት በየቀኑ 5 ቢሊዮን ብር የሚዘዋወር ሲሆን በ3 ዓመታት ውስጥ 2 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ዝውውር ተደርጎበታል።
የብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓት በቀጣይ ጊዜያት ለሚታሰቡ የልማት ውጥኖች መሠረት የሚጥል ነው
Apr 15, 2024 97
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- የብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓት በቀጣይ ጊዜያት ለሚታሰቡ የልማት ውጥኖች መሠረት የሚጥል መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዮዳሄ ዘሚካኤል ገለጹ። የፋይዳ ቁጥር የዲጂታል መታወቂያ ሲሆን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የነዋሪዎችን የተመጠነ የባዮሜትሪክና ዲሞግራፊክ መረጃ በመሰብሰብ “አንድ ሰው አንድ ነው” በሚል መርህ አንድን ሰው ልዩ በሆነ ሁኔታ መለየት የሚያስችል ሥርዓት ነው። በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት ነዋሪዎች የመታወቂያ መብታቸው እንዲረጋገጥ ከመርዳት ባሻገር በአገር አቀፍ ደረጃም የግልጽነት፣ የተጠያቂነትና የተሳለጠ አሠራር ሥርዓትን ለመዘርጋት ያስችላል። የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያው ሕብረተሰቡ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ጉልህ እገዛ እንደሚያበረክትም ይገለጻል። የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዮዳሄ ዘሚካኤል፤ የብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓት ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሠረት የሚጥል መሆኑን ይናገራሉ። ብሔራዊ መታወቂያ የማንነት መገለጫ ሆኖ ማገልገል የሚችል ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ ለዜጎች ቀልጣፋና ሕጋዊ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን የሚያስችል ነው ብለዋል። አሁን ለማኅበረሰቡ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች በሰፊው እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸው፤ ከትናንት ዛሬ የተሻለ ተቀባይነት በማግኘት ላይ መሆኑንም ገልፀዋል። ብሔራዊ መታወቂያን ቀላል በሆነ መንገድ ከፍቶ የፋይዳ ቁጥር ማግኘት እንደሚቻል የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ በኢትዮጵያ በርካታ ሰዎች የነዋሪነት ማረጋገጫ አግኝተው ወደ ኢኮኖሚው እንዲቀላቀሉ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በርካታ ሰዎችን ወደ ኢኮኖሚ ሥርዓቱ መቀላቀል መቻል የአገሪቱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት እንዲፋጠን የሚያስችል ነው ብለዋል። ዜጎች የፋይዳ ቁጥር በማግኘታቸው ወደ መደበኛ የኢኮኖሚው ሥርዓት እንዲቀላቀሉ፣ የንግድ ሥርዓቱ እንዲፋጠን እንዲሁም ከተለያዩ የፋይናንስ አማራጮች ብድርን ጨምሮ ተመሳሳይ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል። የብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓት በቀጣይ ጊዜያት ለሚታሰቡ የልማት ውጥኖች መሠረት የሚጥል መሆኑንም ጠቁመዋል። ብሔራዊ መታወቂያ ሁሉንም ዜጎች የሚጠቅም ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመው፤ የተለያዩ የማጭበርበር ሥራዎችን የሚሰሩ እንዲሁም ከአንድ ማንነት በላይ ሆነው ተግባራትን ማከናወን የሚፈልጉትን የሚከላከል መሆኑንም ተናግረዋል። በሕጋዊ መንገድ የንግድ ሥራን ለማከናወን፣ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማግኘት፣ አዳዲስ ምርቶችን ለማስተዋወቅ፣ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለማቅረብና ለማግኘት እንዲሁም ሌሎች ተግባራትን ማከናወን ለሚሹ ዜጎች ጠቃሚ መሆኑንም ተናግረዋል። መታወቂያው ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ አካታችና ፍትሃዊ የኃብት ክፍፍል እንዲኖር የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል። እንደ ባንክ፣ ጤና፣ ኢንሹራንስና የመሳሰሉት ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለኅብረተሰቡ የተፋጠነና ዘመናዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርም አቶ ዮዳሄ ተናግረዋል።    
ተማሪዎች በስፔስ ሳይንስ ላይ ያላቸውን እውቀት ለማጎልበት  እየሰራ መሆኑን  የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንሰ  ሶሳይቲ ገለጸ
Apr 13, 2024 700
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 5/2016(ኢዜአ)፦ ተማሪዎች በስፔስ ሳይንስ ላይ ያላቸውን እውቀት ለማጎልበት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንሰ ሶሳይቲ ገለጸ። የሩሲያ የሳይንስና ባህል ማዕከል ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር ዩሪ ጋጋሪ በሚያዚያ 4 ቀን 1953 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጠፈር በመንኮራኩር የመጠቀበትን ቀን መታሰቢያ በተለያዩ መርሀ ግብሮች አክብረዋል። ዩሪ ጋጋሪ በሳይንሱ ዘርፍ ለዓለም ያበረከተውን አስተዋጽኦ የሚያሳዩ ፕሮግራሞች የቀረቡ ሲሆን የጥያቄና መልስ ውድድርም ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ስራ አስኪያጅ ብሩክ ተረፈ ማህበሩ በተለያዩ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች በስፔስ ሳይንስ ላይ ያላቸውን እውቀት ለማጎልበት እየሰራ ነው ብለዋል። በተለይም ተማሪዎች ልዩ ልዩ የስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዲሁም መርሐግብሮችን በማዘጋጀት ግንዛቤ እያስጨበጠ መሆኑን ጠቅሰዋል። በክረምት ወቅት ተማሪዎች ያላቸውን የእረፍት ጊዜ በመጠቀም የስፔስ ሳይንስ እውቀታቸውን የሚያሰፉ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥም ጠቁመዋል። የሩሲያ የሳይንስና ባህል ማዕከል ዳይሬክተር አሌክሳንደር ኤቭስቲግኔቭ በበኩላቸው፥ ማዕከሉ ዩሪ ጋጋሪ ወደ ጠፈር የመጠቀበትን ቀን ስለ ስፔስ ሳይንሰ ግንዛቤ በሚፈጥር መልኩ በየዓመቱ ያከብረዋል ብለዋል። በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። በተለይም የሳይንስና ባህል ትውውቅና ሽግግርን ለማጎልበትም ኢትዮጵያውያን በሩሲያ ነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር በማእከሉ በተለያየ ጊዜያት ኪነጥበባዊ ሁነቶችን እያዘጋጀ የባህል ትስስርን ለማጠናከር በመስራት ላይ መሆኑን አመላክተዋል።   ዩሪ ጋጋሪ ሚያዚያ 4 ቀን 1953 ዓ.ም ቮስቶክ-1 በተሰኘች መንኮራኩር ወደ ጠፈር በመምጠቅ በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያው ሰው ነው። መንኮራኩሯ መሬትን በሰዓት 27 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር የዞረች ሲሆን፥ ለ108 ደቂቃዎችም መብረሯን የናሳ መረጃ ያሳያል። ዩሪ ጋጋሪ በዚህ ድንቅ ስራውም ስሙ በዓለም የናኘ ሲሆን፥ የተለያዩ ሜዳሊያዎችን፣ የክብር ስሞችንና የሶቪየት ህብረት ጀግና ሽልማትን ተቀዳጅቷል።  
ስታርት አፖች ለኢትዮጵያ እድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የሚደረጉ ድጋፎች ሊጠናከሩ ይገባል
Apr 13, 2024 279
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2016(ኢዜአ)፦ ስታርት አፖችን ለማጠናከርና ለኢትዮጵያ እድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ። ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው የኢትዮጵያ "ስታርት አፕ" አውደ-ርዕይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፍ የተሰማሩ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ''ስታርት አፖች'' በአውደ-ርዕዩ በመሳተፍ ላይ ናቸው።   አውደ-ርዕዩ የተዘጋጀው በአገሪቱ የሚገኙ ስታርት አፖች ያላቸውን ምርትና አገልግሎት እንዲሁም ፈጠራዎች ተደራሽ ማድረግ ነው። ኢዜአ ያነጋገራቸው በአውደ-ርዕዩ የተሳተፉ፤ ስታርት አፖች ለኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለዘርፉ የሚደረጉ ዘርፈ-ብዙ ድጋፎች መጠናከር እንዳለባቸው ይናገራሉ። ቴክኖሎጂ አልሚዎችን ከገበያው ጋር ለማገናኘት የሚሰራው የኢቴክ ቴክኖሎጂ የማርኬቲንግና የሪሌሽንሺፕ ቺፍ ኦፊሰር እስጢፋኖስ ብርሃኑ፤ ድርጅታቸው አጠቃላይ የቴክኖሎጂ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሷል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አምና በተዘጋጀ ውድድር ከ90 ስታርት አፖች ተመርጠው ወደ ሞሮኮ ከተጓዙት መካከል መሆናቸውን ጠቅሶ፤ ቴክኖሎጂን በአውትሶርሲንግ (በሦስተኛ ወገን) የሚያሰራ አይ ቲኦ የሚባል ቴክኖሎጂ ማቅረባቸውን ያነሳል። አሁን ላይ ለስታርት አፕ የተሰጠው ትኩረት በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶች አቅማቸውን ለማጎልበትና ለአገሪቱ እድገት አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ የሚያግዝ መሆኑን ገልፆ፤ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግሯል። የማሜ መጫወቻዎችና ፐዝሎች መሥራች ዘሩባቤል መስፍን በበኩሉ፤ በቴክኖሎጂው የቀረቡት ፊደል እያንዳንዱ ፊደል በድምፅ የሚያስተምር፣ ቁጥሮችንና አባታዊ ምክሮች ብሎም ሙዚቃዎችና ግጥሞች ያካተተ ነው። በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ያለው አውደ-ርዕይ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና ከደንበኞች ጋር ለመገናኘት እንደሚጠቅም ገልፆ፤ ከሌሎች መሰል ስታርት አፖች ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግም ያግዛል ብሏል። የሚሰራበትን ቴክኖሎጂውን ለማበልፀግ አንዳንድ ግብዓቶች ከውጭ የሚመጡ መሆኑን ገልፆ፤ ቀደም ሲል በግብዓቶች ላይ የሚጣለው ቀረጥ ከፍተኛ እንደነበርና አሁን ላይ የዋጋ ቅናሽ መደረጉ የሚበረታታ ነው ብሏል። በዚህ ረገድ ያሉት የማሻሻያ ሥራዎች ይበልጥ ሊጠናከሩ ይገባል ነው ያለው።   አሁን ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የሚሰራው ኢኔብለር ቴክ መሥራችና ሥራ አስፈጻሚ ይድነቃቸው ከድር በበኩሉ፤ መንግሥት የስታርት አፖች ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ የሚሰራቸው ሥራዎች የሚበረታታና ሊጠናከር የሚገባው ነው ብሏል። ስታርት አፖች ሥራቸውን ይዘው የሚያቀርቡባቸው ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ መድረኮች የበለጠ አዳዲስ ኃሳብ እንዲያፈልቁ የሚያግዙ እንደሆኑም ተናግረዋል። ስታርት አፖች ለተለያዩ አገራት እድገት አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያም ሚናቸውን እንዲወጡ የባለኃብቶች ድጋፍ ወሳኝ መሆኑንም ገልፀዋል።  
ስፖርት
26ኛው መላው የኦሮሚያ የስፖርት ውድድር በጅማ ከተማ መካሄድ ጀመረ
Apr 14, 2024 524
ጅማ፣ ሚያዚያ 6/2016(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉበት 26ኛው መላው የኦሮሚያ የስፖርት ውድድር ዛሬ በጅማ ከተማ መካሄድ ጀመረ። ውድድሩ በ21 ዘመናዊ የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉበት ታውቋል። በውድድሩ መክፈቻ መርሃግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማቴዎስ ሰቦቃ እንዳሉት ስፖርት ወዳጅነትና አንድነትን ያጎለብታል።   ስፖርት ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው ዛሬ በጅማ ከተማ የተጀመረው ውድድር ለ15 ቀናት እንደሚቆይ ገልጸዋል። ስፖርት አብሮነትን ከማጠናከር ባለፈ ለአካልና ለአዕምሮ ብቃት ወሳኝ ነው ያሉት ሃላፊው፣ በክልሉ ብቁ ታዳጊ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ኦሮሚያ የአትሌቶች መፍለቂያ መሆኗን አስታውሰው፣ ከክልሉ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን የማፍራት ስራው ይጠናከራል ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ በበኩላቸው ታዳጊ ሕጻናት እና ወጣቶችን በዚህ መሰል የስፖርት መድረክ ማሳተፍ የሚበረታታ ነው ብለዋል።   ሀገራችን በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ብቁና ተወዳዳሪ ወጣት ስፖርተኞችን ማፍራት እንድትችል በየአካባቢው ወጣቶችን ያሳተፈ ሥራ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል ። ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የስፖርት ተሳትፎ ለማሳደግ ያግዛል ያሉት አቶ ኢሳያስ፣ በየደረጃው ለታዳጊ ወጣቶች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል። የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በበኩላቸው የጅማ ከተማና የጅማ ዞን ህዝብ ለውድድሩ የመጡ እንግዶችን በእንግዳ አክባሪነት ተቀብሎ እንዲያስተናግድ አስገንዝበዋል።   ስፖርት በባህሪው አዝናኝና አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው፣ እንግዶች በጅማ ቆይታቸው የከተማዋን የተለያዩ አካባቢዎች እንዲጎበኙ ጠይቀዋል። ዛሬ በጅማ ከተማ በተጀመረው የመላው ኦሮሚያ ስፖርት ውድድር 21 ዞኖች እና 23 የከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል።    
በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር  ኢትዮጵያ የላቀ ውጤት እንድታስመዘግብ ዝግጅት  እየተደረገ  ነው
Apr 13, 2024 543
ደሴ ፤ሚያዝያ 5 /2016(ኢዜአ)፡- በፈረንሳይ ፓሪስ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ የላቀ ውጤት እንድታስመዘግብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በደሴ ከተማ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራትና ቅብብሎሽ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ በኮሚቴው የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር የቴክኒክና ህዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ እንዳመለከቱት፤ በመጪው ሐምሌ ወር የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር በፓሪስ ይካሄዳል። በውድድሩ ኢትዮጵያ የተሻለ ውጤት እንድታስመዘገብ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በውጭና በአገር ቤት ህብረተሰቡን የማነቃቃትና ግንዛቤ የመፍጠር፣ ገቢ የማሰባሰብ፣ ስፖርተኞችን የመመልመል፣ በክልሎች የችቦ ቅብብሎሽና ሌሎችም ዝግጅቶች በመደረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በውድድሩ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ውሃ ዋና እንደምትሳተፍ ጠቁመው፤ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ወርቅ ለማምጣትና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ አድርጎ ለማውለብለብ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ስፖርት ለዘላቂ ሰላምና አብሮነትም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፤ ህብረተሰቡ በስፖርት መተሳሰርና የእርስ በእርስ ግንኙነቱን ማጠናከር እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ በበኩላቸው፤ በቀጣይ ክረምት በፓሪስ በሚካሄደው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት ክልሉ የበኩሉን እየሰራ መሆኑን ገለጸዋል፡፡   ለዚህም በክልሉ በሚገኙ 16 የአትሌቲክስ ማስልጠኛ ማዕከላት ልዩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ በማዕከላቱ በዓለም የውድድር መድረክ መሳተፍ የቻሉ ስመ ጥር አትሌቶችን ማፍራት ተችሏል ብለዋል፡፡ በክልሎች መካከል የችቦ ቅብብሎሽ እየተካሄደ መሆኑም የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከማጠናከሩ ባለፈ ስፖርቱን ለማነቃቃትና ብቁ ተወዳዳሪ ለመፍጠር እያገዘ ይገኛል ብለዋል። ከኦሮሚያ ክልል የተቀበሉትን የኦሎምፒክ ችቦ ዛሬ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አስረክበዋል፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ብላቴ እንዳሉት፤ በፓሪስ ለሚካሄደው ኦሎምፒክ የሚሳተፉ ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡   የኦሎምፒክ ችቦውን ከአማራ ክልል መረከባቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በማዘዋወር ዘርፉን ለማነቃቃትና የህብረተሰቡን አንድነት ለማጠናከር እንሰራለን ብለዋል፡፡ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ዶክተር ሙሳ አዳል በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የስፖርቱን ዘርፍ በመደገፍ የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የተንታ አትሌቲክስ ማስልጠኛ ማዕከልን ተረክቦ ስመ ጥር አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች 120 ታዳጊዎችን በቋሚነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲና የደሴ ከተማ አመራር አባላትና የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
Apr 12, 2024 507
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 4/2016(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ ባህር ዳር ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይደረጋል። በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ እስካሁን ባደረጋቸው 19 ጨዋታዎች በ9ኙ ሲያሸንፍ 5 ጊዜ ተሸንፎ 5 ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በ19 ጨዋታዎችም 23 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 17 ግቦችን አስተናግዷል። በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በአራቱ ሲያሸንፍ በአንዱ ነጥብ ጥሏል። አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ32 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የአምናው የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በውድድር ዓመቱ ባደረጋቸው 20 ጨዋታዎች 11 ጊዜ ሲያሸንፍ 4 ጊዜ ሽንፈት አስተናግዶ በ5ቱ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በ20ዎቹ ጨዋታዎች 33 ግቦችን ሲያስቆጥር 17 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ክለቡ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በሶስቱ ድል ሲቀናው በአንዱ ሽንፈት በማስተናገድ አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመሩት ፈረሰኞቹ በ38 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ይህም ዛሬ በሚካሄደው 21ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር የሁለቱ ክለቦች ፉክክር ተጠባቂ አድርጎታል። በሊጉ የዛሬ መርሐ ግብር ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ደግሞ ፋሲል ከነማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ፋሲል ከነማ ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲያሸንፍ በአንዱ ተሸንፎ በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል። በውበቱ አባተ የሚሰለጥነው ፋሲል ከነማ በ31 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በአንጻሩ ተጋጣሚው ሀምበሪቾ ዱራሜ ባለፉት አምስት ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል። በጊዜያዊ አሰልጣኝ መላኩ ከበደ የሚመራው ሀምበሪቾ በ7 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በተያያዘ ዜና ትናንት በተደረጉ የ21ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ወላይታ ድቻና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።    
አካባቢ ጥበቃ
በኦሮሚያ ክልል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጡ ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ
Apr 15, 2024 104
አዳማ ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በመጪው ክረምት የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ግብርና ቢሮ የደን ልማትና እንክብካቤ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ከተማ አብዲሳ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በክልሉ ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ወራት የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ፣ የእርከን ማሰርና የተራቆቱ መሬቶችን ከንኪኪ ነፃ የማድረግ ስራ ተከናውኗል። በዚህ ረገድ በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች የተከናወነው የተፋሰስና እርከን ማሰር ስራ ለሌሎች የክልሉ ዞኖች ጭምር ተሞክሮ እንደሚሆን ተናግረዋል። በአብዛኛው የተፋሰስ ልማት ስራ በተከናወነባቸው መሬቶች ላይ የሚተከሉ ችግኞችን በስፋት የማዘጋጀት ተግባርም ጎን ለጎን እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል። በክልሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጡ ችግኞችን የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው የእስካሁኑ አፈጻጸምም የተሻለ መሆኑን አብራርተዋል። የፍራፍሬ ችግኞች፣ ቀርከሃና ለጥምር ደን አገልግሎት የሚውሉ ችግኞች ትልቅ ትኩረት ማግኘታቸውን አመልክተዋል። ከተዘጋጁት ችግኞች ውስጥ 40 በመቶ ለደን አገልግሎት የሚውልና 10 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውን የገለፁት አቶ ከተማ ፤ ለተከላ የበቁ ችግኞችን የመለየት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። የችግኝ መትከያ ጉድጓድ የማዘጋጀት ስራም እየተከናወነ ሲሆን በክልሉ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱንም ተናግረዋል። በዚህም ከ800 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነውን መሬት የመለየት ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል። የምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አብነት ዘገየ በበኩላቸው ፤በዞኑ ዘንድሮ የሚተከል 279 ሚሊዮን የተለያየ አገልግሎት ያላቸው ችግኞች የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ 13 ወረዳዎች በተለዩ ከ300 በላይ ተፋሰሶች ላይ ለ60 ቀናት የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ መከናወኑ አስታውሰው፤ በመጪው ክረምት የፍራፍሬ ጨምሮ ሌሎችንም ችግኞች ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በተለይ ሀገር በቀል ዛፎች፣ የፍራፍሬ፣ ቀርከሃና ቴምርን ጨምሮ ለእንስሳት መኖ የሚውሉትን ለመትከል ከተፋሰስ ስራው ጎን ለጎን የጉድጓድ ዝግጁቱ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል።      
ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ በመፍጠር ሁሉን አቀፍ ልማት ለማሳካት የተቀናጀ ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ ተመላከተ
Apr 13, 2024 608
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 5/2016(ኢዜአ)፦ ለዜጎች ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ በመፍጠር የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ ልማት ለማሳካት የተቀናጀ ርብርብ እንዲደረግ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስገነዘበ። በድሬዳዋ ከተማ "የፕላስቲክ አጠቃቀም ዘይቢያችንን እናዘምን" በሚል መሪ ሃሳብ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። በመድረኩ "ብክለት ይብቃ፤ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ የሚካሄደው የአካባቢ ብክለት የመከላከል ንቅናቄ አካል ነው። የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ንቅናቄው አካባቢን እየጎዳ ያለውን የፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። የፕላስቲክ ብክለት በሰውና በእንሰሳት ጤና ላይ ከፍተኛ ችግር እያደረሰ መሆኑንም ገልጸዋል። ከአነስተኛ እስከ ዋና ዋና ከተሞቻችን በፕላስቲክ ቆሻሻ የተጥለቀለቁ፣ የኑሮና የስራ ሂደቶችን እያደናቀፉ ለብዝሃ ህይወት መመናመን ምክንያት እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል። በመሆኑም ይህንን በማህበራዊና የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚፈጥረውን ችግር በተቀናጀ ህዝባዊ ንቅናቄ በመታገዝ መፍትሄ ለማምጣት ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል። በተለይም ችግሩን ለመቀነስ የተዘጋጁ ስትራቴጂ፣ የህግ ማዕቀፎችና የማስፈፀሚያ ስልቶችን በተቀናጀ መንገድ በመተግበር ዘላቂ የአካባቢ አጠቃቀም ለመፍጠር መሥራት እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሰውን የደን መራቆትና የተፈጥሮ ሃብት መመናመን ችግር ለመታደግ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን መተግበር ይገባል ብለዋል። ባለሥልጣኑ በአስተዳደሩ ለተጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ስኬት ድጋፍ እንደሚያደርግም ወይዘሮ ፍሬነሽ አረጋግጠዋል።   የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው በንቅናቄው የአካባቢ ፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች በተቀናጀ መንገድ በመተግበር ምቹ የሥራ፣ የመኖሪያ እና የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከተማ ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግረዋል። የተጀመረው ንቅናቄ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በአስተዳደሩ በፕላስቲክ፣ በአየር፣ በውሃ፣ በአፈር፣ በድምፅ ብክለቶች ላይ ሰፋፊ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።   በንቅናቄው ላይ ለ5ሺህ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ በመፍጠርና የፕላስቲክ ውጤቶችን መልሶ መጠቀም የሚያስችሉ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እንደግፋለን ያሉት ደግሞ የድሬዳዋ የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱ መሐመድ ናቸው።
የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ ወጥ የኢነርጂ አሰራር ስርአት ለመፍጠር ወሳኝ ነው - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
Apr 12, 2024 449
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 4/2016(ኢዜአ)፦የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ ወጥ የኢነርጂ አሰራር ስርአት ለመፍጠርና የኢነርጂ ሃብትን በአግባቡ ለመጠቀም ወሳኝ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የኢነርጂ ልማት ስራ ወጥነት ባለው መልኩ እንዲተገበርና የኢነርጂ ተደራሽነትን ለማስፋት ስትራቴጂው ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል። የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት ይፋ የተደረገ ሲሆን ስትራቴጂውን የተመለከተ አውደ ጥናትም ተካሄዷል።   የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ፤ በስትራቴጂ የታገዘ ዘላቂ የኢነርጂ አጠቃቀምን መከተል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የኃይል ምንጮችን መጠቀም ለዘላቂ የኢነርጂ ልማት እውን መሆን ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ለዘርፉ ስራ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ያስፈልጋል ብለዋል። በመሆኑም በዘርፉ ያሉ እድሎችንና አማራጮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የተወጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ስትራቴጂውን ለማዘጋጀት 1 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ የወሰደ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የኢነርጂ ፖሊሲ መሬት ወርዶ በሚፈለገው ደረጃ እንዲተገበር፣ የኢነርጂ ሀብቶችን በተመለከተ የተቀናጀ መረጃ ለመስጠትና የግሉ ዘርፍ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ ስትራቴጂው የላቀ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል። በተበታተነ መልኩ ይተገበር የነበረውን የኢነርጂ የአሰራር ማዕቀፍ ወጥነት እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። ከዚህ በፊት ስትራቴጂውን የተመለከቱ ስድስት የግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች መካሄዳቸውን አስታውሰው የአሁኑ የመጨረሻ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የስትራቴጂው የማጠናቀቂያ ስራዎች ከተከናወኑ በኋላም በ2017 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ወደ ትግበራ ይገባል ብለዋል።   በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ ሬቤካ አልት፤ የሀገራቸው መንግስት በጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ድርጅት (ጂ አይ ዜድ) በኩል ለስትራቴጂው ዝግጅት ድጋፍ ማድረጉን አመልክተዋል። ለስትራቴጂው መዳበር አውደ ጥናቶች እንዲካሄዱ ማድረግና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኒክ ድጋፎችን ማድረጉን አስታውሰዋል። ጀርመን በኢነርጂው ዘርፍ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የውሃና ኢነርጂ ልማት ቢሮ የአማራጭ ኢነርጂ ጥናት ልማት ክትትል ዳይሬክተር የሱፍ ሙባረክ ስትራቴጂው የኢነርጂ ሃብትን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ማዕድን ኢነርጂና ነዳጅ ቢሮ የኢነርጂ ዘርፍ ዳይሬክተር መሐሙድ መሐመድ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገብረማርያም ሰጠኝ ስትራቴጂው ለዘርፉ ልማትና ተጠቃሚነት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ ሴቶች የኢነርጂ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ሊንዳ ላጲሶ፤ የግሉ ዘርፍ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ እንዲሁም እውቀትና ቴክኖሎጂን ስራ ለማዋል ስትራቴጂው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር ከ2024 እስከ 2030 ተግባራዊ እንደሚሆን በአውደ ጥናቱ ላይ ተመላክቷል።          
በሚቀጥሉት ቀናት በአብዛኛው የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ሥፍራዎች የተሻለ እርጥበት ይኖራቸዋል
Apr 12, 2024 363
አዲስ አበባ ፣ሚያዚያ 04/ 2016 (ኢዜአ)፡-በቀጣይ ስምንት ቀናት ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገፅታዎች በአብዛኞቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገፅታዎች፤ በአብዛኞቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የአገሪቱ አካባቢዎች እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ አመላክቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖረውም በትንበያው ተገልጿል። በሚቀጥሉት ቀናትም በአብዛኛው የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ሥፍራዎች የተሻለ እርጥበት እንደሚኖራቸውና የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን እንደሚጠቅሙ ገልጿል። ይህም የረዥም ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት፤ በቡቃያና በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች የውኃ ፍላጎት መሟላት፤ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የጠቆሙት። የሚጠበቀው እርጥበታማ ሁኔታ ለእርሻ ሥራ እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር አርሶ አደሮች ተገቢ የሆኑ ግብዓቶችን በመጠቀም የእርሻ ሥራቸውን በተሟላ መልኩ ማካሄድ እንደሚገባቸው ገልጿል። በሚቀጥሉት ቀናት በኦሞ ጊቤ፣ ስምጥ ሸለቆ፤ በላይኛውና በመካከለኛው ባሮ አኮቦ፤ አዋሽ፣ አባይ፣ ገናሌ ዳዋ፣ በመካከለኛው ተከዜ እና በላይኛው ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶች ከፍተኛ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር ጠቁሟል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚጠበቀው ከፍተኛ እርጥበት፤ ለገፀ ምድርም ሆነ ለከርሰ ምድር ውሃ ኃብት መጎልበት አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 110
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 1529
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 821
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
በአባቱ የሎተሪ ስጦታ 4 ሚሊዮን ዶላር ያሸነፈው እድለኛ 
Apr 4, 2024 865
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2016(ኢዜአ)፦ በአሜሪካ ኤሊኖይ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ አባቱ ያበረከቱለት የሎተሪ ትኬት የ4 ሚሊዮን ዶላር እድለኛ አድርጎታል። ስቴቨን ሪቻርድስ ይባላል በኤሊኖይ የባሪንግተን ከተማ ነዋሪ ሲሆን ከቀናት በፊት ከአባቱ ጋር ቁርስ ለመመገብ ባቀኑበት ምግብ ቤት ከአባቱ ስጦታ ይበረከትለታል። ስጦታውም የ10 ዶላር የሎተሪ ትኬት ነበር። አዛውንቱ ያበረከቱለት የሎተሪ ትኬት ወዲያውኑ ተፍቆ ውጤቱን የሚያሳይ ሲሆን ስቴቨንም ትኬቱን በፋቀበት ቅጽበት ከፍተኛ ድንጋጤ እንደተሰማው ለማሳቹሴት የሎተሪ አስተዳደር ተናግሯል። የሎተሪ ትኬቱ የ4 ሚሊዮን ዶላር እድለኛ እንዳደረገኝ ሳውቅ በድንጋጤ ማመን አልቻልኩም በዚህም ውጤቱን ከመናገሬ በፊት በስልኬ ስካን አደረኩት ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። በመቀጠለም የአባቱ ስጦታ እድለኛ እንዳደረገው ለባለቤቱ እንዲሁም ለአባቱ መናገሩን ዩፒአይ ዘግቧል። ስቴቨን በሎተሪ ከደረሰው 4 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ በተወሰነው ገንዘብ ከባለቤቱ ጋር የተለያዩ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ማቀዱን ዘገባው አመልክቷል።
ሐተታዎች
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 547
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 1857
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
በከፍታ የታጀበ ስኬት
Mar 15, 2024 1467
ለህጻናትና ታዳጊዎች መልካም ስብእና የሚያግዙ ጽሁፎችን ያዘጋጀችው ኤሪን ሶዴርበርግ ዶውኒንግ 'JUST KEEP WALKING' በሚለው መጽሃፏ ባደራጀችው ገጸባህሪ አማካይነት “አንተ መልካምና ስኬታማ ሆነህ ሳለ ጥቂት ሰዎች ስለአንተ መጥፎነት አብዝተው መጨነቅና ማውራት ከጀመሩ የምትሄድበት መንገድም ሆነ አካሄድህ ትክክል ነውና መራመድህን አታቁም። ብዙሃኑ የስኬትህ ተካፋይና የስኬትህ አጋር ስለሆኑ የጥቂቶቹን ጫጫታ ከምንም ካለመቁጠር ተራመድ ብዙ አፍራሽ ወሬዎች ያንተን ስኬት የመመስከር አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን አትዘንጋ። መቆም የሽንፈት ምልክት ነውና” ትለናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 78 ዓመታት በከፍታ የዘለቀ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምና ዝናው የገነነ ተቋም ነው። አየር መንገዱ ታህሳስ 21 ቀን 1938 ዓ.ም ተመስርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ካይሮ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዘመኑ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅና አሰራሮችን በማዘመን ራሱን እያደራጀ የኢትዮጵያ ኩራት ከመሆን አልፎ የአፍሪካ ምልክት ሆኖ ዘልቋል። ዛሬ ላይ የ152 ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምስረታው ወቅት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት አውሮፕላኖች ብቻ እንደነበሩት መረጃዎች ያመለክታሉ። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ22 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞችን ፍላጎትና ምቾት ለመጠበቅ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ጨምሮ 31 አውሮፕላኖች ለመግዛት ከአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። እነዚህን ተጨማሪ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ቁጥር ጨምሮ የሚገነባቸው ዘመናዊ አየር መንገዶች ሲደመሩ በአፍሪካ ግዙፍ ተቋምነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ያደርገዋል። የበረራ አድማሱን በየጊዜው እያሰፋ የሚገኘው አየር መንገዱ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 134 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በሀገር ውስጥ ወደ 22 መዳረሻዎች ይበራል። ከዚህ ውስጥ 60 የበረራ መዳረሻዎቹ አፍሪካ ውስጥ ነው። አየር መንገዱ ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ አስገንብቶ ወደ ስራ ያስገባው ዘመናዊ የካርጎ ማእከል ከምስራቅ አፍሪካ ብሎም ከአፍሪካ ከፍተኛ ተብሎ ተመዝግቦለታል። በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው ያረፈው የካርጎ ማዕከል ለኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ ኮሜርስ) አገልግሎት የሚውል ሲሆን የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣት አየር መንገዱ የሚሰራቸው ተያያዝ በርካታ ተግባራት መስፋት፣እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ተመራጭ መሆን ለማእከሉ ግንባታ ምክንያት ተብለው ተጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ መስክ ከሚታወቅባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሴቶችን በማብቃትና የጾታ እኩልነትን በማስተግበር ረገድ አርአያነት ያለው ተግባር መፈጸሙ ነው። በየዓመቱ የሚታሰበው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ማርች 8 በሚከበርበት ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ ለሙሉ በሴቶች ብቻ የተመራ በረራን በማደረግ ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፏል። አየር መንገዱ ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ "ሴቶችን በማብቃት አፍሪካን ማስተሳሰር" በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ ወደ ለንደን በሴቶች ብቻ የተመራ የተሳካ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች በሚሰጠው ዘመኑን የዋጀና ቀልጣፋ አገልግሎት በየጊዜው የተለያዩ ሽልማቶች ባለቤት መሆን የቻለ ተቋም ነው። ለአብነት የቅርብ ጊዜያቶችን ለማንሳት ያህል ባሳለፍነው ዓመት በአየርላንዷ ደብሊን በተዘጋጀ መርሐ-ግብር ላይ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማትን አሸንፏል፡፡ በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ ጉባኤ "ኤር ካርጎ ኤሮፕ" እ.አ.አ በ2021 ባካሄደው የበይነ መረብ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና የሎጅስቲክ አገልግሎት የ2021 የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ የደንበኞች እንክብካቤ ዘርፍ ሽልማት አግኝቷል። በአውሮፓውያኑ 2024 ዓመታዊውን የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “የኮርፖሬት የዘላቂነት ስኬት ሽልማት” አሸናፊ ሆኗል። አየር መንገዱ በትላልቅ ስኬቶች የማለፉን ያህል ከባድ ፈተናዎችንም ተጋፍጦ በጽናትና በስኬት አልፏል። መላውን ዓለም ያዳረሰው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አንዱ ማሳያ ነው። በዚያን ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ምክንያት በዓለም ደረጃ በርካታ አየር መንገዶች በረራ በማቋረጥ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ አንዳንድ የመንገደኞች አውሮፕላኖቹን ወደ ዕቃ ጫኝ በመቀየር ጭምር ትኩረቱን ጭነት ማጓጓዝ ላይ አድርጓል። በዚያን ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የቀየሰውን ስትራቴጂ በመቃወም ከውስጥም ከውጭም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ትችትን አስተናግዷል። ይሁን እንጂ አየር መንገዱ ፈተናውን በመቋቋም እንደሌሎቹ ሀገራት አውሮፕላኖች በረራ የማቋረጥ እጣ ሳይገጥመው በታላቅ ብልሃት ማለፍ የቻለ ተቋም መሆኑ ተመስክሮለታል። በዚህም በካርጎ አገልግሎት ገቢ ከማገኘቱም ባሻገር ክትባትን ለዓለም በማዳረስ ወረርሽኙ ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ የራሱን አሻራ አኑሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን ከአራት አስርተ ዓመታ በላይ ልምድ አካብቷል። አየር መንገዱ በሚያስተዳድረው ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የበረራ ባለሙያዎችን በቅርቡ ያስመረቀ ሲሆን ምሩቃኑ ከታንዛንያ ከደቡብ ሱዳን ከኒጀር ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከቶጎ እና ከማዳጋስካር መሆናቸው ደግሞ የአየር መንገዱን የፓንአፍሪካኒስት መንፈስ አጉልቶ ያሳየ አድርጎታል። ስኬቶቹ በዚህ ያላበቁት አየር መንገዱ የእድገት ግስጋሴውን እንደቀጠለ ይገኛል። ከሰሞኑ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በዚህ ወቅት ከተሸለሙት ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን ሽልማቱ ለወደፊትም ለላቀ ስኬት የሚያዘጋጀው እንደሆነ ይታመናል።  
አድዋን የዘከሩ ስንኞች
Feb 29, 2024 1854
የታሪክ ድርሳናት የአድዋ ድልን በተለያየ መንገድ ዘክረውታል። ምሁራንም አንድምታውን በየዐውዱ ዘርዝረዋል። በዚህም ለሰው ልጆች በተለይም ለጥቁሮች አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንደሆነ ደምድመዋል። በርግጥም የአድዋ ድል ታሪክም፣ ትርክትም የለወጠ ትልቅ ሁነት ነው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ምዕራባዊያን 'አቢሲኒያ' በሚሏት ጥንታዊት አፍሪቃዊት ምድር የነበረው ክስተት ቀለምና ዘር ቀመስ በሆኑ በሰው ልጆች መካከል ድል መንሳትና መነሳት፣ ተስፋ እና ቀቢፀ ተስፋ፣ ሀሜትና ሀሞት፣ ብስራትና መርዶ... እያፈራረቀ አበሰረ። ለሀገሬው ዘመን-አይሽሬ አሻራ አነበረ። ውርስም ቅርስም ሆነ!! ይህ ክስተት በታሪኩ ልክ በኪነ ጥበብ ተዘክሯል ባይባልም ቅሉ በጥበብ ፈርጁ ተወስቷል። የኪነ-ጥበብ ሰዎች በየመክሊቶቻቸው ድሉን ለመዘከር ጥረዋል። ሙዚቀኞች በዜማዎቻቸው፣ የሲኒማ ሰዎች እና ፀሐፈ ተውኔቶች በተውኔታቸው፣ ሊቃውንት በቅኔዎቻቸው አድዋን ዘክረዋል። ዕውቅ ገጣሚያን ደግሞ ቃላት እያዋደዱ፣ በዘይቤና ዘመን እያዋሃዱ፣ ምዕናብና ገሀድ እያዛነቁ፣ ታሪክና ትዝብት እያሰባረቁ ... አድዋን በግሩም ስንኞቻቸው ከትበውታል። በአድዋ ድል ምርጥ ግጥሞች መካከል "ጥቂት ስንኞች" እየመዘዝን በወፍ በረር ቅኝት እንመልከት። ባለቅኔው ፀጋዬ ገብረመድህን በ‘እሳት ወይ አበባ’ ግጥም መድብሉ አድዋን መልክዓ ምድራዊና ሃሳባዊ ወሰኗን አድማስ ተሻጋሪ፣ ሰማይ ታካኪ፣ ታሪካዊ ስፍራዋ የአጽም ርስትና የደም ትቢያ የተሸበለለባት መቀነት አድርጎ መስሏታል። በዚህች ታሪካዊ ስፍራ በተከፈለው መስዋዕትነት ከባርነትና ነጻነት ስርየትን ሲያጎናጽፍ፣ የኩራት ቅርስ መሆኗንም ሰፊውን ታሪክ በጥቂት ስንኞች እንዲህ ቋጥሯል። ".... አድዋ ሩቅዋ፣ የዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥግዋ፣ ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ... ዓድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ- የደም ትቢያ መቀነትዋ ከሞት ከባርነት ሥርየት- በደም ለነጻነት ስለት አበው የተሰውብሽ እ’ለት የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ- የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ..." ገጣሚው አለፍ ሲልም በጦርነቱ የዋሉ መሳሪያዎችን፣ የጦር መሪዎችን እጅና ጓንትነት በፈረስ ስሞቻቸው በመቋጠር /ለአብነትም የዳግማዊ ምኒልክ፣ የራስ መኮንን፣ የደጃች ባልቻ ሳፎ፣ የፊታውራሪ ገበየሁና ሌሎችም/ ኢትዮጵያዊያንን ጀግንነትና ወኔ በአጭሩ ቋጥሮታል። ...ድው-እልም ሲል ጋሻዋ- ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣ ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ፣ ያባ መቻል ያባ ዳኘው፤ ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣ ያባ ጎራው፣ ያባ በለው በለው ሲለው..." በሚል። ደራሲና ጋዜጠኛ ነብይ መኮነን ‘ስውር ስፌት’ በተሰኘ የግጥም መድብሉ የአድዋን ድል ሲያመሰጥረው አድዋን ‘በደም ግብርነት’ ይገልጸዋል፤ ታሪኩንም ላጥፋህ ቢሉት የማይጠፋ ሕያው ቀንዲል አድርጎታል። “አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል፣ አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል፣ ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል፣ ለዛሬም ታሪክ ነው፣ ‘ነገም ሌላ ቀን ነው’ ለሚል...” የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ ምሁር ሰይፉ መታፈሪያ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) “የተስፋ እግር ብረት” መጽሐፍ “የድል በዓል ማለዳ” በሚል ርዕስ የአድዋን ድባብ ከማለዳው ምናባዊ ትዕይንት ጀምሮ ይቃኛል። ገጣሚው የሰንደቁን መውለብለብ፣ የሕብረ ቀለሙን ድምቀት ከልክ በላይ ውስጥን ኮርኩሮ የሚያስፈግግ ሐሴት እንዳለው በዘይቤያዊ ቃላት ገልፆታል። ገጣሚው በቅኔው የሠራዊቱን ቆራጥነት፣ በወኔ በደም ሲቅላላ፣ የመድፍ አረር ሲያፋጭ ይስለዋል። በስሜት ስካር አድዋ ደፍርሶ በስዕለ ህሊናው የነበረውን የጦርነቱ ማለዳዊ ድባብም እንዲህ ያብራራዋል። ዐይነ-ልቦናዬ ዐጽም ያያል፤ የድል ሜዳውን ይቃኛል። ባድዋ ድል በዓሉ ማለዳ፤ የበዓል መድፍ ሲንዱዋዱዋ (ዱዋ ዱዋ ዱዋ ዱዋ!) ከሞት እንቅልፍ ተቀስቅሶ፤ ያ-ዐጽም ዙርያውን ደባብሶ ጉሮሮውን ጠረገ፣ እህህህህ! እህህህህ!... እያለ ይቀጥላል። በአድዋ ኮረብታማ ተራሮች የተኙ ጀግኖችን በሕይወት ተኝተው የሚያንኮራፉ አስመስሎም አቅርቧቸዋል። ...ድንጋይ ተንተርሶ፤ አፈር ቅጠሉን ለብሶ፣ ከዚያን ያንኮራፋል፤ እንደዚሁም በቅብልብል የወደቀበቱ ሜዳው፣ ተረተሩ፤ ቀን የማይለውጠው ምስክሩ የዚያ ጀግና፣ የዚያ ኩሩ። ገጣሚ አበረ አያሌው “ፍርድና ዕርድ” በተሰኘው የግጥም ስብስቡ ባሰፈራቸው ስንኞች ‘ነገረ አድዋ’ን ከመንደር ወደ አገር፣ ከአገር ወደ አህጉር በመጨረሻም ከአህጉር አተልቆ ‘ዓለም’ ያደርገዋል፤ አድዋን የአፍሪካ ብርሀን ፈንጣቂ፤ ለእብሪተኞች ደግሞ የትካዜና ቅስም መስበሪያ ምስጢር አድርጓታል። በተለይም ኢትዮጵያ ለገጠማት አሁናዊ የዘር ፖለቲካ አዙሪት አድዋን ለሚያሳንሱ ወገኖች በቅኔው ምላሽ ይሰጣል። "...እነ ምኒልክ ጦር ይዘው ከመድፍ የተዋደቁ ጎራዴ መዘው የሮጡ በጠብ-መንጃ አፍ ያለቁ ለጓጉለት ነጻነት -ደማቸውን ያፈሰሱ ለሰፈር ብቻ አይደለም- የአህጉር ድል አታሳንሱ። ... ዓድዋ ሰፈር አይደለም - ዓድዋ መንደር አይደለም እሱ ዓለም ናት ዓድዋ ቤቱ - ሃገር ናት የድል ትራሱ ለጠበበ የዘር ቅኔ - የደም ድል አታሳንሱ!..." በማለት ገልጾታል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ምሁሩ ተሻገር ሽፈራው (ዶ/ር) ‘የነፍስ ርችቶች’ በተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሃፉ ከቋጠራቸው ስንኞች መካከል በአድዋ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል የግጥም ውድድር ያሸነፈበትን ረጅምና ድንቅ ግጥም አካቷል። የዶክተር ተሻገር ግጥም አንጓ እና ስንኞች የአድዋን ምጡቅነት፣ ዝና፣ ነቅዓ ፍትሕ፣ ውበትና ቅኔ በውብ ቃላት ገልጠውታል። "... ዓድዋ አንቺ የዝና አጽናፍ ሕዝቦች እፍ ያሉብሽ ቁጣ - የነበልባል እቶን ጫፍ እጹብ ክስተት፤ ደቂቅ ረቂቅ፤ ምጡቅ ጠሊቅ ኬላ ድንበር፣ አድማስ ሰበር፣ የቅርብ ሩቅ ለትንግርትሽ ብቻ መጥኔ ትንግርት እውነት፣ ታምር ሁነት፣ የብርቅ ብርቅ፣ የድንቅ ድንቅ ለሰጠሽው ፍትህ መጠን - ለፍርድሽ ሚዛን ብያኔ ለንግስትሽ ሥነ ውበት - ለታሪክሽ ምስጢር ቅኔ…" ገጣሚው "... በምን ቀሰም፣ በምን ቀለም - በምን ብዕራና ሊከትበው..." ሲል የአፍሪካዊያን ሁሉን አቀፍ ድል ለመግለጽ የቀለም፣ የአንደበትና የብራና ወኔ እንዳጣባት ይናገራል። በመጨረሻም ይህችን የድል ቁንጮ የማትሞቺ ህያው ጀንበር ሁልጊዜም ተዘመሪ፤ ተወደሽ" ይላታል። "… እና ዓድዋ አንቺ በኩር የድል መኸር የቅኝ ግዛት ቀንበር ሰንሰለቱ እንዲሰበር ተጠቂዎች አጥናፍ አጥናፍ የመረጡሽ የትግል ዘር ህይወት ከፍለው እልፍ - ያርጉሽ የመረጡሽ ከአገር አገር የማታልፊ የማትከስሚ - የማትሞቺ ህያው ጀንበር ሰብዓዊ ድል ነሽና - ስምሽ ይወደስ ይዘመር…" (በአየለ ያረጋል)  
ትንታኔዎች
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 2758
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2005
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 1889
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
በአጭር ጊዜ ትልቅ እመርታ በሌማት ትሩፋት
Feb 6, 2024 2718
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በግብርና ልማት በተለይም በስንዴ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ በምግብ እራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል። በግብርና ልማት እየተከናወኑ ባሉ ውጤታማ ስራዎች ላይ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ሲታከሉ ከምግብ ዋስትና ባለፈ ስርአተ ምግብን በማስተካከል ረገድ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ለመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ስርአተ ምግብን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚኖረው ፋይዳ እንዴት ይታያል? በእስካሁኑ አካሄድስ ምን ውጤቶች ተገኙ? ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ‘የሌማት ትሩፋት’ መርሃ ግብርን ካስጀመሩ በኋላ በመህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሌማት አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ገልጸው ነበር። በወቅቱ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በቂ እና አመርቂ ምግብ ማግኘት መሆኑን ገልጸው በቂ የመጠን፣ አመርቂ የይዘት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም በምግብ ራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ገልጸዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር ዓላማ የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥና ክብርን ማስጠበቅ ሲሆን በተለይም ስጋ፣ እንቁላል፣ ማር እና ወተት ትርፍ ምርት ሆነው እንዲገኙ ማልማትና መጠቀምን መሰረት ያደረገ ነው። መርኃ-ግብሩ የኢትዮጵያን ደካማ የአምራችነት ታሪክ በመቀየር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የኢኮኖሚ እድገትን የማፋጠን ግብ የሰነቀ መሆኑ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሌማት ትሩፋት ዘመቻው በቤተሰብ፣ ብሎም በሀገር ደረጃ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል። የወተት፣ የዶሮ፣ የዕንቁላል፣ የማር፣ የዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን ለማሻሻል ሀገራዊ የመንግሥት ፕሮግራም ሆኖ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት በብዙ መልኩ ውጤት እያስገኘ ነው። በእርግጥም የሌማት ትሩፋት በአንድ ዓመት ጉዞው በተለይ በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና ስጋ ምርት መጠን አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑ የተረጋገጠበት ውጤት ተመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በ2015 ዓ.ም፣ የወተት፣ የዶሮ እና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት ማምጣቱንና በተያዘው ዓመትም በበለጠ ለማሳካት የሁሉም ጥረት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በማር፣ በወተትና በዶሮ ልማት ከ20 ሺህ በላይ መንደሮችን በመለየት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ለኢዜአ ገልጸዋል። ለአብነትም በወተት ልማት በተሰሩ ስራዎች 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ሊትር የነበረውን የማምረት አቅም ወደ 8 ነጥብ 6 በሊዮን ሊትር ከፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በመጪዎቹ ዓመታትም ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በእንቁላል ምርት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የጫጩቶች ስርጭት ከነበረበት 26 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ማደጉን ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ- ግብር የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን የሚናገሩት የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በእንስሳት ሃብት ልማት ብቻ በዓመት ለ259 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ለዘርፉ ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት አመርቂ ውጤት ሳያገኝ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ዘርፉ በቅንጅት ከተመራ፣ በቴክኖሎጂ ከታገዘ የምግብ አማራጭን ማብዛት ይቻላል። ወተት፣ ማር፣ ስጋ እና እንቁላል መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በገበያ ላይ ማትረፍረፍ፣ የሌማቱ በረከት ማብዛት የሚለው የብዙሃኑ እምነት ነው። የምግብ ዋስትና ጉዳይ ከተመጣጠነ ምግብ ጋር ያለው ቁርኝት የማይነጣጠል በመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ፋይዳው ብዙ ነው። በሌማት ትሩፋት ገበታን በተመጣጠነ ምግብ መሙላት ከተቻለ የእናቶችንና የህጻናትን ፍላጎት በማሟላት በአካል የዳበረና በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ መገንባት ይቻላል። በተቃራኒው ያልተመጣጠነ አመጋገብ ጤና ላይ ከሚፈጥረው ችግር ባለፈ በሰዎች መካከል ያለውን የኑሮ አለመመጣጠን በማስፋት፣ ማህበራዊ ቀውስን በመፈልፈልና ኢኮኖሚውን በመጉዳት ምርትና ምርታማነትን ወደ ኋላ የሚጎትት ይሆናል። ይህ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት በከባድ ትግል ላይ የሚገኙ ሀገራትን የልማት ግስጋሴ በመግታት ቀድሞ ወደነበሩበት የድህነት አረንቋ እንዲመለሱ ያደርጋቸዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙና እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት በዕድሜያቸው ልክ ዕድገት የማያስመዘግቡ ወይም የመቀንጨር ችግር ያለባቸው መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። ለዚህ ነው በምግብ ራስን ከመቻል ጎን ለጎን የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ የሚሆነው። በዚህ ረገድ የሌማት ትሩፋት እየተጫወተ ያለው ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። የተለያዩ ምግቦችን በገበታ ላይ ማካተት የሚያስችል ስልጠናን ከተግባራዊ የልማት ስራዎች ጋር ያካተተ ሲሆን አዲስ የአመጋገብ ባህልን የሚያለማምድ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለተሰሩ ስራዎችና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል። ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ረሀብን ዜሮ ለማድረስ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ ብልጽግናን እውን እንደምታደርግ ገልጸዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተሰሩት ስራዎች ለመጪው ትውልድ ጥሩ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ለአብነት አንስተዋል። የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ስራችን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተመጣጠነ ምግብን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል። የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ነጻ አገር እውን ማድረግን ያለመ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አመራሩ ይህንን ተገንዝቦ እንዲሰራ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ህልም የሚመስሉ በርካታ አገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ የቻለችው በዜጎቿ የተባበረ ክንድ መሆኑ እሙን ነው። ከዚህ አኳያ በምግብ ራስን ከመቻል በላይ የኢትዮጵያን የአምራችነት ታሪክ የመቀየር ግብ ለሰነቀው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ስኬታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት ይጠበቃል።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 10460
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15190
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 7807
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 8803
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 23706
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 20683
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15190
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 11535
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 10613
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 10460
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 10362
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 9951
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 23706
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 20683
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15190
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 11535
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 2678
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 2929
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም