ኢዜአ - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ አዲስ አምራች ኩባንያ ተመርቆ ስራ ጀመረ
Apr 20, 2024 29
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ባቲ ትሬዲንግ የተሰኘ ኩባንያ የማምረቻ ሼድ ውስጥ ማምረቻ ማሽነሪዎችን በመትከልና በመገጣጠም በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ መሀመድ አሚን እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ኩባንያውን በይፋ ስራ አስጀምረዋል። በስራ ማስጀመሪያ ስነስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ባቲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽኑ አቅም ላላቸው ሀገር በቀል ኩባንያዎች የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም አሁንም አቅም ያላቸው ሀገር በቀል ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ ያደረገውን ያጠረ የቢሮክራሲ አሰራር እና ዘርፈ ብዙ ማበረታቻዎችን በመጠቀም ወደ ኢንቨስትመንት እንዲመጡ ጋብዘዋል። በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ስራ የጀመረው ባቲ ትሬዲንግ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግ ጥጥን በግብዓትነት በመጠቀም ክር የሚያመርት መሆኑም ተመላክቷል። ኩባንያው አሁን ላይ 300 ለሚደርሱ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ምርቶቹንም ሙሉ ለሙሉ ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሪን በማዳን በኩል ሚና እንደሚኖረው መገለጹን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን ባሻገር ባለሃብቶችን በመደገፍ የኢንቨስትመንት ዘርፉን ማነቃቃት ይገባል --አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Apr 20, 2024 31
ደሴ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ከማድረግ ባሻገር የግል ባለሃብቶችን በመደገፍ ኢንቨስትመንቱን ለማነቃቃት በተሻለ ቅንጅት መስራት እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ገለጹ። ''የኢትዮጵያ ታምርት'' የንቅናቄ መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ ተካሄዷል። አፈ-ጉባኤዋ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ ክልሉ ያለው ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ሌሎች እምቅ ሃብቶች ለኢንቨስትመንት ምቹ ናቸው። ይህንኑ ሃብት በአግባቡ በማልማት የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማሳለጥ የሚያስችሉ ተግባራትን በቅንጅት ማከናወን ይገባል ብለዋል። በመሆኑም የክልሉን ዘላቂ ሰላም ከማረጋገጥ ባሻገር የግል ባለሃብቱን በመደገፍ የኢንቨስትመንት ዘርፉን የበለጠ የማነቃቃት ስራ መከናወን እንዳለበት ተናግረዋል። በተለይ የዘርፉን ተግዳሮቶች በመፍታት ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርት ከማምረት ባለፈ የውጭ ምንዛሬ እንዲያመጡ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል። የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው፤ በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በቅንጅት በመፍታት ዘርፉን የማነቃቃት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በተለይ የክልሉ መንግስት በከፍተኛ ወጪ የመሰረት ልማት ችግሮችን እያቃለለ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም ክፍተቶችን በማረም ተኪ ምርት እንዲያመርቱ የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በዚህም 241 አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ 38 ቶን ተኪ ምርት መመረቱን ጠቅሰው፤ በተመረተው ምርትም ለውጭ ምንዛሬ ይወጣ የነበረን 195 ሚሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉን ገልፀዋል። በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 276 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 1 ሺህ 885 ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ በመስጠት ዘርፉን የማገዝ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዘርፉን የማነቃቃቱ ተግባር ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሃመድ አሚን የሱፍ ናቸው። በከተማው ለሚገኙ 58 መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ በማድረግ 28 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ተኪ ምርት ለማምረት መቻላቸውን ገልፀው ምርቱን ወደ ውጪ በመላክም 36 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን አብራርተዋል። የሪሀመር ፒቢሲና ቀለም ፋብሪካ ተወካይ አቶ ጀማል ታደሰ፤ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት መሰረት በማድረግ በ114 ሚሊዮን ብር ካፒታል በኮምቦልቻ ከተማ በኢንቨስትመንት ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል። የዝገትና የብረት ቀለም፣ የተለያዩ የውሃ ማስተላለፊያ የፕላስቲክ ቱቦዎችን እና ሌሎችንም በማምረት ለገበያ ማቅረብ መጀመራቸውን ገልጸዋል። በመድረኩ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች ተገኝተዋል።
የዞኑ አርሶ አደሮች ደጋግሞ የማረስ ስነ ዘዴን በመጠቀም የእርሻ ማሳቸውን ለቀጣይ መኸር እያዘጋጁ ነው
Apr 20, 2024 51
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ የምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ለ2016/17 ዓ.ም የምርት ወቅት የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ደጋግሞ የማረስ የግብርና ስነ ዘዴን በመጠቀም ማሳቸውን ለዘር ስራ እያዘጋጁ መሆናቸውን ገለፁ። ለቀጣዩ የመኽር ሰብል ልማት ግማሽ ሚሊዮን ሄክታር መሬት በድግግሞሽ ታርሶ ለዘር ስራ መዘጋጀቱም ተገልጿል። የጎዛምን ወረዳ የሊባኖስ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር የቆየ ታምራት እንዳሉት፤ ለመጪው የመኸር ሰብል ልማት ከሁለት ሄክታር በላይ መሬት በማረስ ለዘር ስራ አዘጋጅተዋል። ቀድመው ለሚዘሩ ሰብሎችም ሁለት ኩንታል ማዳበሪያ በመግዛት የዝናቡን መጣል እየተጠባበቁ እንደሆነም ተናግረዋል። የዚሁ ወረዳ የየቦ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዳግም አራጋው እንዳሉት፤ የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚለማውን መሬት ከወዲሁ ደጋግመው እያረሱ ይገኛል። እንደ አርሶ አደሩ ገለፃ ሦስት ሄክታር መሬት እስከ ሦስት ጊዜ ደጋግመው ማረስ የቻሉ ሲሆን ከታረሰው መሬት ሩብ ሄክታር በሚሆነው ላይ ድንች መዝራታቸውን ተናግረዋል። ለመኸር ሰብል ልማቱ የሚውል ማዳበሪያ ከወዲሁ በበቂ መጠን እየቀረበ መሆኑን አመልክተው፤ ይህም ባለፈው ዓመት ከማዳበሪያ ጋር ተያይዞ ገጥሟቸው የነበረው ችግር በመፈታቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል። የዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ እምቢያለ አለኸኝ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ አርሶ አደሩ ለ2016/17 የምርት ዘመን የሚውል የመኸር እርሻ እንቅስቃሴ እያከናወነ ይገኛል። በመጪው የመኸር ወቅት ከ612 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን፤ እስካሁን በተደረገ ጥረት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር ከግማሽ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ታርሶ ለዘር ስራ ተዘጋጅቷል። ከታረሰው መሬት ውስጥም ከሦስት ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬት በትራክተር የታረሰ እንደሆነም ተናግረዋል። በዚሁ የመኸር እርሻ ዝግጅት ከ260 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ ሲሆን፤ "ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሴት አርሶ አደሮች ናቸው" ብለዋል። በመኸር ወቅት በዞኑ ከሚለማው መሬትም ከ22 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም ተመልክቷል።
የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት በሀዋሳ ይካሄዳል
Apr 20, 2024 69
ሃዋሳ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አፈጻጸም ላይ በሚያተኩረው ውይይት ላይ ለመሳተፍ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ሀዋሳ ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዋሳ ከተማ ሲገቡ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች የክልሉ አመራር አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የፌዴራልና የክልሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ሀዋሳ ገብተዋል። የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ይፋ ከተደረገበት ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የተሰሩ ስራዎችና የመጡ ለውጦችን አፈጻጸም እንደሚገመገም ታውቋል። የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንዲቻል የተቀረጸ ሲሆን፤ መርሀ ግብሩ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል። መርሀ ግብሩ በዋናነት እንቁላል፣ ዶሮ፣ ማር፣ ወተት እና አሣ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የልማት መስኮች ናቸው።
ፖለቲካ
መገናኛ ብዙሃን የአገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ላይ ግንዛቤን ለመፍጠር የተጠናከረ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል-የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን
Apr 20, 2024 56
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙሃን የአገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ፋይዳን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር በትኩረት እንዲሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሃመድ እድሪስ ለኢዜአ እንደተናገሩት የአገራዊ ምክክርና ሽግግር ፍትህ ለሰብአዊ መብት መከበርና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ትልቅ ፋይዳ አላቸው። በኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ የተፈጠሩ ስብራቶችን በመጠገንና አብሮነትን በማጠናከር ጠንካራ አገረ መንግስት ለመገንባት አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያለውን ፋይዳ አንስተዋል። በምክክሩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አጀንዳውን ይዞ በሰለጠነ መንገድ በመወያየት ለአገር የሚበጀውን ሀሳብ የጋራ ለማድረግም ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው የተናገሩት። በተመሳሳይ ቀደም ሲል የተፈጠሩ ችግሮችን፣ ለማረም፣ እውነትን ለማውጣት፣ ለተጣሱ ሰብአዊ መብቶች ፍትህ በመስጠት ወደፊት ለመሄድ የአገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትህ ትልቅ መፍትሄ እንዳለው ተናግረዋል። ስለዚህም ህብረተሰቡ ስለ የአገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ በአግባቡ ተረድቶ የታለመለትን ዓላማ ግብ እስኪመታ እንዲያገዙ መገናኛ ብዙሃን ግንዘቤ መፍጠር ላይ አበክረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪም መገናኛ ብዙሃን ህብረተሰቡ ግልጽ አረዳድ እንዲኖረው፣ አወንታዊ ምልከታ እንዲፈጠር፣ ሂደቱን ከሚያደናቅፉ ዘገባዎች በመቆጠብ ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ባለስልጣኑ መገናኛ ብዙሃን የአዘጋገብ ስነ-ምግባር ላይ ተመስርቶ እንዲዘግቡ የሚሰጠውን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የአገራዊ ምክክርና ሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ቀጣይ የአገርን እጣ ፋንታ የሚወስኑና ከፍተኛ የህዝብ ጥቅም ያላቸው በመሆናቸው መገናኛ ብዙሃን በበጎ ምልከታ ሊዘግቡ ይገባል። ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር በባለቤትነት እንዲሳተፍ፣ የሚመለከታቸው አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱና ሃሰተኛ መረጃዎችን በመመከት መስራት ይግባል ሲሉም አክለዋል። በኢትዮጵያ አላግባባ ያሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ ጠንካራ አገረ መንግስት ለመገንባትና ለተጣሱ ሰብአዊ መብቶች ፍትህ ለመስጠት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽንና የሽግግር ፍትህን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።
ዜጎች በሕገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ የጋራ አረዳድ እንዲኖራቸው ምሁራን ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
Apr 20, 2024 56
አዳማ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ ዜጎች በሕገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ የጋራ አረዳድ እንዲኖራቸው ምሁራን ሚናቸውን እንዲወጡ የሕገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ጠየቀ። በአዳማ ከተማ የሕገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመተባበር በፌዴራሊዝም ስርዓት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዷል። የሕገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኃይለእየሱስ ታዬ፣ ዜጎች በፌዴራሊዝም ዙሪያ የጋራ አረዳድ እንዲኖራቸው ምሁራን ሀሳቡን የማስረፅ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። የፌዴራሊዝም ስርዓትን በተሟላ መልኩ ለመተግበር ማህበረሰቡ በጉዳዩ ዙሪያ በቂ እውቅት መጨበጥ እንዳለበትም አንስተዋል። በዚህም የህገ መንግስትና የፌዴራሊዝም ስርዓት አረዳዱ የዳበረና ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያደርግ ማህበረሰብ ለመገንባት ምሁራን ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ በላይ ውድሻ በበኩላቸው በፌዴራሊዝም አረዳድ ላይ እየታዩ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ከዘርፉ ምሁራን ሰፊ ስራ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። እንደ አገር ወደፊት የሚያራምድ ስርዓት ለመገንባት ከምሁራን ባሻገር የተሻለ ግንዛቤ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ሀሳቡን ለማስረጽ መትጋት አለበት ብለዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ዶክተር ያዕቆብ በቀለ፣ በስርዓቱ ዙሪያ የተሟላ አረዳድ ባለመፈጠሩ የአፈፃፀም ሂደቱ ላይ ችግሮች እያጋጠሙ መሆኑን አንስተዋል። ''ዋና ትኩረት መሆን ያለበት የእውቀት ማጎልበት ስራውን በማጠናከር የህዝብ አስተዳደሩን ለህዝብ ተደራሽና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥ አቅም መፍጠር ነው'' ብለዋል። ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ አቶ የማነህ ወልዴ፣ ፌዴራሊዝምን የማስገንዘብ ስራ ውስጥ ምሁራን ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል። በቀጣይም የዘርፉን ምሁራን አቅም በመጠቀም በሁሉም ደረጃ ያለውን ማህበረሰብ ለማንቃት መትጋት እንደሚገባም ተናግረዋል።
የሜካናይዝድ ዘርፉን የውጊያ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ነው---ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምዴ
Apr 20, 2024 68
አዋሽ አርባ ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ የሜካናይዝድ ዘርፉን የውጊያ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሜካናይዝድ እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምዴ ገለፁ። በመከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የአዋሽ አርባ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት የተመሰረተበትን 46ኛ ዓመት በማስመልከት የፓናል ወይይት ተካሂዷል። በመከላከያ ሚኒስቴር የሜካናይዝድ እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ ትምህርት ቤቱ ብቁ ሰልጣኞችና አሰልጣኞችን በማፍራት የሀገርን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ በኩል ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የመከላከያን የሜካናይዝድ አቅም ለማሳደግ በትምህርት ቤቱ ብቁ ምደብተኞችና አሽከርካሪዎችን የማፍራት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል። በተለይ የመከላከያ የሜካናይዝድ ዘርፉን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በጥናትና ምርምር የተደገፈና የትምህርት ቤቱን ቀጣይ የሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ፍላጎት ያማከሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል። "እንደተቋም እየተከናወነ ባለ የሪፎርም ሥራ ኢትዮጵያን የሚመጥን የሜካናይዝድ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል" ሲሉም ሜጀር ጄነራል ከፍያለው ገልጸዋል። የስልጠናን ሥርዓተ ትምህርት በየጊዜው የማሻሻልና ከጊዜው ጋር እንዲቃኝ የማድረግ ሥራ እንደሚሰራ ጠቁመው፣ ለውስጥ የስልጠና አቅም፣ ብቃት እና ጥራት ትኩረት መሰጠቱንም አስታውቀዋል። የአዋሽ አርባ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ባለው ምንተስኖት በበኩላቸው እንዳሉት፣ ትምህርት ቤቱ ዘመኑን በሚመጥን ልክ የማሰልጠን ሥራውን እየሰራ ይገኛል። ለእዚህም በዘርፉ ብቁ የሆኑ የሜካናይዝድ ሙያተኞችን በተለይ ብቃት ያላቸውን ምድብተኞች፣ አሽከርካሪዎችና የዘርፉን አመራሮች እያፈራ መሆኑን በማሳያነት ጠቅሰዋል። በአሁኑ ወቅትም የትምህርት ቤቱን የማሰልጠን አቅም ከማጎልበት ባለፈ የስልጠና ሥርአቱን ከዘመኑ ጋር የተቃኘ በማድረግ የሜካናይዝድ ሃይሉን በተሻለ ደረጃ የመገንባት ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ኮሎኔሉ አስረድተዋል። በየዘርፉ ውጊያዎችን በብቃት መፈጸም የሚያስችል አቅም መፈጠሩን የገለጹት አዛዡ፣ መድረኩ የሜካናይዝድ ዘርፉን በቀጣይ ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡበት አመልክተዋል።
ኢትዮጵያን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት በማላቀቅ የአፍሪካ የነጻነት፣ የአንድነትና የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Apr 20, 2024 77
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት በማላቀቅ የአፍሪካ የነጻነት፣ የአንድነትና የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ጉራጌ ጎጎት በተባለው ቃል ኪዳኑ ስለ አንድነትና አብሮነት አበክሮ ያስተማረና በተግባር የኖረ ማህበረሰብ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለማጋጨት በየዕለቱ ብዙ ለሚጥሩ ጠላቶች ሁሉ መላው ኢትዮጵያዊ የአንድነትን ኃይል በመማር ይችን ድንቅ ሀገር ለልጆቹ አበልፅጎ ለማስረከብ እንዲሰራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ጉራጌ ስለ ሰላም የሚያስተምርና በሰላም የሚኖር ምሳሌ የሆነ ህዝብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ስለሰላም ሳናስብ እና ሳንኖር ሰላምን ማግኘት አይቻልም ብለዋል። መላው ኢትዮጵያን ሰላምን አብዝቶ መፈለግ፣ በአብሮነት በመኖር የበለፀገችና ለሁሉ የምትመች ኢትዮጵያን ለማየት እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያውያን ብዙ የማንነት መገለጫ እንዳለን በመቀበል፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ የአካባቢ አቀማመጥ ልዩነት ኢትዮጵያን የሚበትን መሆን እንደሌለበት ገልጸዋል። የጉራጌ ህዝብ በውስጡ የተለያዩ ማንነቶች ቢኖሩትም በጉራጌነት አንድ ሆኖ በመኖር የኢትዮጵያ አንድነት ምሳሌና ምልክት ሆኖ መኖሩን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ለነጻነቷ የተጋደለችና ያልተገዛች ሀገር ብትሆንም ከኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት በመላቀቅ ነጻነቷን ምልዑ ለማድረግ መትጋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጊዜ የወራሪዎችን ሙከራ የመከተችና ቅኝ ያልትገዛች ሀገር መሆኗን አውስተው፥ ሆኖም ኢኮኖሚያዊ ነጻነቷን ሳታረጋግጥ መቆየቷን አንስተዋል። የጉራጌ ህዝብ በንግድ ዘርፍ ያሳዩት ውጤትም ኢትዮጵያን ከኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት ለማላቀቅ አብነት መሆኑን አንስተው መላው ኢትዮጵያዊያን ለልማትና ብልፅግና መቆም እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመሆኑም ከልመና ለመውጣት፣ ቁጠባን ለማዳበር፣ ንግድን ለማስፋት በአንድነት መረባበር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያን በብርቱ ጥረት ወደ ብልፅግና ከፍታ በመውሰድ የአፍሪካ የነጻነትና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ መትጋትን መርጠናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መላው ኢትዮጵያውያንም ለዚህ ሀገራዊ ኃላፊነት እንዲነሱ ጥሪ አቅርበዋል። ታታሪው የጉራጌ ህዝብ ኢትዮጵያ አንድነቷን ጠብቃ ትበለፅጋለች የሚል ፅኑ አቋም ይዞ ከመንግስት ጎን ሊቆም እንደሚገባም አንስተዋል። ኢትዮጵያ የምትበለፅገው በብርቱ ጥረት መሆኑን ገልፀው፤ ሀገርን ለመከፋፈልና ለማጋጨት የሚሞክሩ ኃይሎችን ቅዠት ለማክሸፍ አንድነትን ማጠናከር ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል።
አንድነታችንን በማጠናከር ሀገርን ለመከፋፈልና ህዝብን ለማጋጨት የሚሞክሩ ኃይሎችን ቅዠት ማክሸፍ ይገባል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር)
Apr 20, 2024 60
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ አንድነታችንን በማጠናከር ሀገርን ለመከፋፈልና ህዝብን ለማጋጨት የሚሞክሩ ኃይሎችን ቅዠት ማክሸፍ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት የጉራጌ ህዝብ ሰላምና ልማት የሚገኘው ስለ ሰላም በመስበክና በተግባር በመኖር መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጉራጌ በአንድነትና በአብሮነት በመኖር የሚገኘውን ጸጋ በተግባር የተገነዘበ ህዝብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በረጅም ዘመን ታሪኩም ለመላው ኢትዮጵያውያን የሰላም ምሳሌ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ችግሮች ሲኖሩ በባህላዊ የምክክር፣ የሽምግልና እና የፍርድ ስርዓቶቹ በመፍታት ሰላማዊ አብሮነትን እያፀና እስከዛሬ መቀጠሉ ሊደነቅና ትምህርት ሊወሰድበት የሚገባ ነው ብለዋል። የጉራጌ ህዝብ የኢትዮጵያን አንድነት ሊንዱ ለሚፈልጉ ሃይሎች በሩን የማይከፍት እና በኢትዮጵያዊ አንድነት ፅኑ አቋም ያለው በመሆኑ ሁላችንም ለሀገራችን አንድነት መከበር በጋራ ልንቆም ይገባል ነው ያሉት። የተሟላ ሰላምን መጎናፀፍ የሚቻለው ስለ ሰላም በማሰብ፣ በመኖር እና ሰላምን በማስተማር መሆኑንም መገንዘብ እንደሚገባ አንስተዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም ለማናጋት የተነሱ አንዳንድ ወገኖች ከአፍራሽ አካሄዳቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል። አንድነታችንን በማጠናከር ሀገርን ለመከፋፈልና ህዝብን ለማጋጨት የሚሞክሩ ኃይሎችን ቅዠት ማክሸፍ ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያውያን ለሰላም፣ ለሀገራዊ አብሮነት እና አንድነት መጠናከር በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የጉራጌ ህዝብ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ን የአመራር ሂደት በተግባር በመደገፍ የለውጡን ስኬቶች ለማስቀጠል በቁርጠኝነት ይሰራል
Apr 20, 2024 69
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ የጉራጌ ህዝብ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ን የአመራር ሂደት በተግባር በመደገፍ የለውጡን ስኬቶች ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ። የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በሕዝባዊ መድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ን ጨምሮ የፌደራል፣ የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ለውጡን የሚደግፉ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በስነስርዓቱ ባስተላለፉት መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመሻገርና በመደመር ተምሳሌትነት የጉራጌን ህዝብ አክብረው ስለመጡ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል። የትጋትና የአብሮነት ምሳሌ ወደ ሆነው የጉራጌ ማህበረሰብ እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት ምክትል ርዕሰ መሰተዳድሩ የጉራጌ ህዝብ ከወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን ጋር ለሀገራዊ ለውጡ የተጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ለውጡን እውን በማድረጉ ሂደት የጉራጌ ህዝብ ሚና ከፍተኛ እንደነበር አቶ እንዳሻው ጣሰው አመልክተዋል። አክለውም የለውጡ መንግስት ያመቻቸውን የለውጥ ሂደት በመጠቀም እና በመደመር እሴት መዛነፎችን በሰከነ ሂደት በማረም በጋራ የማደግን አደረጃጀት ተግባራዊ አድርጓል ብለዋል። በዚህም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ሌሎች መስኮች ያለውን ከፍተኛ ሚና አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። የጉራጌ ህዝብ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ን የአመራር ሂደት በተግባር በመደገፍ የለውጡን ስኬቶች ለማስቀጠል በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉ አስታውቀዋል። የለውጡን ሂደት በሁሉም መስኮች ለማፋጠን የጉራጌ እና የክልሉ ህዝብ ቃሉን ያድሳል ለውጡን ይደግፋል ሲሉም ተናግረዋል። የክልሉ ህዝብም ያለውን እምቅ አቅም ወደ እሴት በመቀየር የለውጡን ሂደት በተጨባጭ ውጤቶች እያረጋገጠ ድጋፉን እንዲያጠናክር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው
Apr 20, 2024 73
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በሕዝባዊ መድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌደራል፣ የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተው ለውጡን የሚደግፉ የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
መንግስት ለሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ተግባራዊነት በቁርጠኝነት ይሰራል-- ተስፋዬ በልጅጌ
Apr 19, 2024 417
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ መንግስት ለሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ተግባራዊነትና ውጤታማነት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ ገለጹ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤን ጨምሮ የዴሞክራሲ ተቋማት አመራሮችና ሌሎች በተገኙበት በሽግግር ፍትህ ፖሊሲና የፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርአት አዋጅ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ በዚሁ ጊዜ የተለያዩ የዓለም አገራት ከተወሳሰበ ችግርና ቀውስ ለመውጣት የሽግግር ፍትህን መፍትሄ አድርገው መጠቀማቸውን አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያም በቀደሙ ስርዓቶች የተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ በታሪክ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች፣ የዴሞክራሲ ስርዓት አለመጎልበት፣ ለዘመናት የተከማቹ የፖለቲካ ቀውሶች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ ለእነዚህ ችግሮች እልባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር የሚመጋገብና ሂደቱን የሚያሳልጥ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። መንግስት ፖሊሲው እንዲዘጋጅ ከማድረግ ጀምሮ ቁርጠኛ የፖለቲካ አቋም መውሰዱን ገልጸው፤ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ችግሮችን ቀርፎ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምእራፍ የማሸጋገር ኃላፊነት እንዳለበትም ነው የተናገሩት፡፡ ፖሊሲ ለረዥም ጊዜ ስር የሰደዱ ችግሮችን በመፍታት ከችግር መውጫ አንዱ መሳሪያ መሆኑንም አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል። የትናንት ቁርሾዎችን በእርቀ ሰላምና ይቅርታ በመዝጋት ለነገ ትውልድ የተረጋጋችና ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት አገር ማስተላለፍ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለፖሊሲው ተፈጻሚነት በጋራ መስራት እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የፖሊሲው ወቅታዊነትን በሚመለከትም ከተሳታፊዎች ጥያቄ ቀርቧል፡፡ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በምላሻቸው አገራዊ የሆኑ ችግሮች በይደር የሚታለፉ አለመሆናቸውን ጠቅሰው፤ ችግሮቹን በአንድነት ለመፍታት ጊዜው አሁን መሆኑን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ገለልተኛ ተቋማትን በማደራጀት ነጻና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ለፖሊሲው ተፈጻሚነትም አስቻይ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥርም አንስተዋል። በሌላ በኩል የፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርአት አዋጅ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ አዋጁ አጠቃላይ የተጀመረው ለውጥ ስራ አካል መሆኑን በመጥቀስ ይህም የአሰራር ማነቆዎችን በመፍታት፣ አደረጃጀትን በማስተካከል፣ አገልግሎትን በማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት። አዋጁ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የተቋማት ኃላፊዎችና ሙያተኞች ተግባራዊነቱ ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ማህበራዊ
በዞኑ በግለሰቦች የእርሻ መሬታቸውን አላግባብ ተነጥቀው የቆዩ 800 ሴቶች ፍትህ አገኙ
Apr 20, 2024 60
ጎንደር ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተለያዩ ግለሰቦች የእርሻ መሬታቸውን ተነጥቀው የቆዩ 800 ሴቶች ይዞታቸው ተመልሶ የመብት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን የዞኑ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ሃላፊ ወይዘሮ ቀኑ ቢያድጎ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ መሬታቸው እንዲመለስ የተደረጉት ሴቶች በትዳር አጋሮቻቸውና በቅርብ ዘመዶቻቸው የእርሻ መሬታቸውን በጉልበት ተነጥቀው የቆዩ ናቸው፡፡ የሴቶችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተደረገ ጥረት በየደረጃው ከሚገኙ የፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት ሴቶች አፋጣኝ ፍትህ አግኝተው ዳግም የመሬት ባለቤትነት መብታቸውን ለማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል። ሴቶቹ ከአራት ዓመት በላይ ፍትህ አጥተው የቆዩ ሲሆን፤ መምሪያው ከህግ አካላት ጋር በመተባበር የህግ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረጉ አሁን ላይ የእርሻ መሬታቸው ተመልሶ መጠቀም እንደቻሉም ተናግረዋል፡፡ በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ከ18 ሺህ በላይ ሴት አርሶ አደሮች ደግሞ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰርቶ እንዲሰጣቸው መምሪያው ክትትልና ድጋፍ ማድረጉንም አስረድተዋል፡፡ በዞኑ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረትም ስምንት ሺህ ለሚጠጉ ወጣት ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ገልጸዋል፡፡ በወረዳው የእርሻ መሬታቸውን ተነጥቀው ፍትህ ላጡ 38 ሴቶች ከህግ አካላት ጋር በመተባበር "መብታቸው እንዲከበር ተደርጓል" ያሉት ደግሞ የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ሰላማዊት ጥጋቡ ናቸው፡፡ የህግ አካላት ነጻ የጥብቅና አገልግሎት በመስጠት ፍትህ ያጡ ሴቶች መብታቸው እንዲጠበቅ በማድረግ በኩል ያልተቋረጠ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ ማሪቱ ጫኔ እንደገለጹት፤ በቀድሞ የትዳር አጋራቸው ተወስዶ የቆየው የእርሻ መሬት በህግ አግባብ ተመልሶላቸዋል። በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የጭንጫዬ ቀበሌ ነዋሪ ሴት አርሶ አደር ታክላ መንግስቴ በበኩላቸው፤ መሬታቸው ተነጥቆ ላለፉት ሶስት ዓመታት ፍትህ አጥተው ሲንከራተቱ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ መምሪያው ተከራካሪ ጠበቃ በማቆም ጉዳዩ በፍርድ ቤት እልባት እንዲያገኝ በማደረጉ በመሬት ሃብታቸው የመጠቀም መብታቸው እውን እንደሆነ አመልክተዋል። በዞኑ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከ40 ሺህ በላይ ሴቶች ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝም ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
ኤጀንሲው ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ይፋ አደረገ
Apr 20, 2024 72
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016 (ኢዜአ)፦ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከወረዳ ጀምሮ ባለው መዋቅር ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ይፋ አደረገ። ኤጀንሲው በ16 ሞዴል ወረዳዎች ስራ የማስጀመሪያ መርሃግብር እያካሄደ ይገኛል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ታረቀኝ ገመቹ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በመገኘት መረሃ ግብሩን አስጀምረዋል። በዚህ ወቅት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን እንዳሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ፍጥነትና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል እየተሰራባቸው ካሉ ተቋማት መካከል የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አንዱ ነው። ኤጀንሲው እያደረገ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር እና አገልግሎቱን ለማዘመን ይረዳዋል ነው ያሉት ።
መሰረታዊና የህዝብ ተሳትፎ ያማከለውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራ በአጥጋቢ ሁኔታ አገባድጃለሁ- ኮሚሽኑ
Apr 19, 2024 267
ሀዋሳ ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መሰረታዊና የህዝብ ተሳትፎ ያማከለውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራ በአጥጋቢ ሁኔታ ማገባደዱን ገለጸ። በኦሮሚያ ክልል በዞን፣ በወረዳና በከተማ አስተዳደር ደረጃ በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ የህብረተሰብ ተወካዮች ልየታ የማጠቃለያ መድረክ ዛሬ በሻሸመኔ ከተማ ተካሄዷል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ ኮሚሽኑ መሰረታዊና የህዝብ ተሳትፎ ያማከለውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራ በአጥጋቢ ሁኔታ አገባዷል። በአገሪቱ በአሥር ክልሎች፣ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የተሳታፊዎች ልየታና መረጣ ሥራ 95 በመቶ መከናወኑን ገልፀዋል። በአንዳንድ የሶማሌ ክልልና የድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳዎች ያልተጠናቀቀውን የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ልየታና መረጣ ተግባር በቀጣዩ ሳምንት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህ አፈፃፀም ስኬታማነት የሲቪል ማህበረሰቡ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መምህራን፣ እድሮች፣ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ መስተዳድርና ፍትህ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። የተሳታፊዎች ልየታና መረጣ በተጠናቀቀባቸው ክልሎችና ከተሞች ውስጥ አጀንዳ መሰብሰብ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። ''በቀጣይ ሀገራዊ ችግሮቻችንን ሁሉ በአጀንዳ መልክ በማምጣት ተወያይተንና ተመካክረን መግባባት ላይ መድረስ ይጠበቅብናል'' ብለዋል። በአማራ ክልልም የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ልየታና መረጣ ለማካሄድ ኮሚሽኑ ከ10 ዩኒቨርሲቲዎች 26 ምሁራንን በመምረጥ ተባባሪ አካላትን እያዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይም በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለማሳለጥ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን ብለዋል። የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ሒሩት ገብረስላሴ በበኩላቸው፤ በምክክሩ ላይ ለመሳተፍ የተመረጡ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል። በተለይ ከመጡበት ማህበረሰብ ወሳኝ አጀንዳ በማምጣት በቀጣይ በሚካሄደው ምክክር ላይ በሚገባ ለማስረዳት ከወዲሁ እንዲዘጋጁም አስገንዝበዋል። ''በዓለም ላይ በጦርነት የተፈታ ችግር የለም'' ያሉት ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ፤ ይህንን በመረዳት ስለምክክሩ አስፈላጊነት በየአካባቢያቸው ላለው ማህበረሰብ በመግለጽ ማስረዳት እንደሚኖርባቸውም አብራርተዋል። በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን የነገሌ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ከዋጭሌ፣ ዳሳ፣ አሬሮ፣ መደወላቡ፣ ጉሮዶላና ሊበን ወረዳዎች የተውጣጡ 500 የሚጠጉ የኅብረተሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል
በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተወዳዳሪና የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲኖር የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር
Apr 19, 2024 159
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ በአገሪቱ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቃት ያለውና ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ሃይል ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ገለፁ። የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ''የተቋማዊ የለውጥ ስራዎችን በማፅናት የላቀ ምርታማነትን እናረጋግጣለን'' በሚል መሪ ሀሳብ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል። ስልጠናው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፣ የቴክኒክና ሙያን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ላሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች እየተሰጠ ነው። የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ስልጠናው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞችን አቅም በመገንባት ለዜጎች ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ያለመ ነው። አመራሩና ሰራተኛው አገራዊ የለውጥ እሳቤዎችን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ውጤታማ የሆነ ስራ መስራት እንዲችል ለማድረግ የሚረዳ መሆኑንም ጠቁመዋል። ስልጠናው ሰራተኛው ያለውን እውቀትና ክህሎቱ እንዲያጎለብት ከማድረጉ ባለፈ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል። በተጨማሪም በየደረጃው ያለው ሰራተኛ ተናቦና ተቀናጅቶ አገራዊ ተልኮዎችን በብቃት እንዲወጣ ለማድረግ የሚረዳ መሆኑንም አብራርተዋል። ሚኒስቴሩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሰው ኃይል አደረጃጃትን የማዘመን፣ ተደራሽነታቸውን የማስፋትና የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ስራም እያከናወነ መሆኑንም አብራርተዋል። በተጨማሪም የስራ ዕድል ፈጠራው የሃብት ምንጭ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ መሆኑንም እንዲሁ። ከዚህ ውስጥም በርካታ የሚሆኑ ዜጎች ወደስራ ለመሰማራት የሚያስችላቸውን ስልጠና በመስጠት በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ተሰማርተው የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በኩላቸው፤ ለዜጎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ተቋማት ሪፎርም እየተካሄደ ነው ብለዋል። በመዲናዋ ጥራቱን የጠበቀና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉም በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል። እየተሰጠ ያለው ስልጠና በአዲስ መልክ የተደራጀው ሰራተኛ በእውቀትና በክህሎት የተመሰረተ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያግዘው እንደሆነ ገልፀዋል። ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።
ኢኮኖሚ
በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ አዲስ አምራች ኩባንያ ተመርቆ ስራ ጀመረ
Apr 20, 2024 29
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ባቲ ትሬዲንግ የተሰኘ ኩባንያ የማምረቻ ሼድ ውስጥ ማምረቻ ማሽነሪዎችን በመትከልና በመገጣጠም በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ መሀመድ አሚን እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ኩባንያውን በይፋ ስራ አስጀምረዋል። በስራ ማስጀመሪያ ስነስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ባቲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽኑ አቅም ላላቸው ሀገር በቀል ኩባንያዎች የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም አሁንም አቅም ያላቸው ሀገር በቀል ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ ያደረገውን ያጠረ የቢሮክራሲ አሰራር እና ዘርፈ ብዙ ማበረታቻዎችን በመጠቀም ወደ ኢንቨስትመንት እንዲመጡ ጋብዘዋል። በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ስራ የጀመረው ባቲ ትሬዲንግ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግ ጥጥን በግብዓትነት በመጠቀም ክር የሚያመርት መሆኑም ተመላክቷል። ኩባንያው አሁን ላይ 300 ለሚደርሱ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ምርቶቹንም ሙሉ ለሙሉ ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሪን በማዳን በኩል ሚና እንደሚኖረው መገለጹን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን ባሻገር ባለሃብቶችን በመደገፍ የኢንቨስትመንት ዘርፉን ማነቃቃት ይገባል --አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Apr 20, 2024 31
ደሴ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ከማድረግ ባሻገር የግል ባለሃብቶችን በመደገፍ ኢንቨስትመንቱን ለማነቃቃት በተሻለ ቅንጅት መስራት እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ገለጹ። ''የኢትዮጵያ ታምርት'' የንቅናቄ መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ ተካሄዷል። አፈ-ጉባኤዋ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ ክልሉ ያለው ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ሌሎች እምቅ ሃብቶች ለኢንቨስትመንት ምቹ ናቸው። ይህንኑ ሃብት በአግባቡ በማልማት የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማሳለጥ የሚያስችሉ ተግባራትን በቅንጅት ማከናወን ይገባል ብለዋል። በመሆኑም የክልሉን ዘላቂ ሰላም ከማረጋገጥ ባሻገር የግል ባለሃብቱን በመደገፍ የኢንቨስትመንት ዘርፉን የበለጠ የማነቃቃት ስራ መከናወን እንዳለበት ተናግረዋል። በተለይ የዘርፉን ተግዳሮቶች በመፍታት ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርት ከማምረት ባለፈ የውጭ ምንዛሬ እንዲያመጡ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል። የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው፤ በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በቅንጅት በመፍታት ዘርፉን የማነቃቃት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በተለይ የክልሉ መንግስት በከፍተኛ ወጪ የመሰረት ልማት ችግሮችን እያቃለለ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም ክፍተቶችን በማረም ተኪ ምርት እንዲያመርቱ የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በዚህም 241 አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ 38 ቶን ተኪ ምርት መመረቱን ጠቅሰው፤ በተመረተው ምርትም ለውጭ ምንዛሬ ይወጣ የነበረን 195 ሚሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉን ገልፀዋል። በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 276 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 1 ሺህ 885 ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ በመስጠት ዘርፉን የማገዝ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዘርፉን የማነቃቃቱ ተግባር ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሃመድ አሚን የሱፍ ናቸው። በከተማው ለሚገኙ 58 መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ በማድረግ 28 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ተኪ ምርት ለማምረት መቻላቸውን ገልፀው ምርቱን ወደ ውጪ በመላክም 36 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን አብራርተዋል። የሪሀመር ፒቢሲና ቀለም ፋብሪካ ተወካይ አቶ ጀማል ታደሰ፤ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት መሰረት በማድረግ በ114 ሚሊዮን ብር ካፒታል በኮምቦልቻ ከተማ በኢንቨስትመንት ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል። የዝገትና የብረት ቀለም፣ የተለያዩ የውሃ ማስተላለፊያ የፕላስቲክ ቱቦዎችን እና ሌሎችንም በማምረት ለገበያ ማቅረብ መጀመራቸውን ገልጸዋል። በመድረኩ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች ተገኝተዋል።
የዞኑ አርሶ አደሮች ደጋግሞ የማረስ ስነ ዘዴን በመጠቀም የእርሻ ማሳቸውን ለቀጣይ መኸር እያዘጋጁ ነው
Apr 20, 2024 51
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ የምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ለ2016/17 ዓ.ም የምርት ወቅት የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ደጋግሞ የማረስ የግብርና ስነ ዘዴን በመጠቀም ማሳቸውን ለዘር ስራ እያዘጋጁ መሆናቸውን ገለፁ። ለቀጣዩ የመኽር ሰብል ልማት ግማሽ ሚሊዮን ሄክታር መሬት በድግግሞሽ ታርሶ ለዘር ስራ መዘጋጀቱም ተገልጿል። የጎዛምን ወረዳ የሊባኖስ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር የቆየ ታምራት እንዳሉት፤ ለመጪው የመኸር ሰብል ልማት ከሁለት ሄክታር በላይ መሬት በማረስ ለዘር ስራ አዘጋጅተዋል። ቀድመው ለሚዘሩ ሰብሎችም ሁለት ኩንታል ማዳበሪያ በመግዛት የዝናቡን መጣል እየተጠባበቁ እንደሆነም ተናግረዋል። የዚሁ ወረዳ የየቦ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዳግም አራጋው እንዳሉት፤ የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚለማውን መሬት ከወዲሁ ደጋግመው እያረሱ ይገኛል። እንደ አርሶ አደሩ ገለፃ ሦስት ሄክታር መሬት እስከ ሦስት ጊዜ ደጋግመው ማረስ የቻሉ ሲሆን ከታረሰው መሬት ሩብ ሄክታር በሚሆነው ላይ ድንች መዝራታቸውን ተናግረዋል። ለመኸር ሰብል ልማቱ የሚውል ማዳበሪያ ከወዲሁ በበቂ መጠን እየቀረበ መሆኑን አመልክተው፤ ይህም ባለፈው ዓመት ከማዳበሪያ ጋር ተያይዞ ገጥሟቸው የነበረው ችግር በመፈታቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል። የዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ እምቢያለ አለኸኝ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ አርሶ አደሩ ለ2016/17 የምርት ዘመን የሚውል የመኸር እርሻ እንቅስቃሴ እያከናወነ ይገኛል። በመጪው የመኸር ወቅት ከ612 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን፤ እስካሁን በተደረገ ጥረት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር ከግማሽ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ታርሶ ለዘር ስራ ተዘጋጅቷል። ከታረሰው መሬት ውስጥም ከሦስት ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬት በትራክተር የታረሰ እንደሆነም ተናግረዋል። በዚሁ የመኸር እርሻ ዝግጅት ከ260 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ ሲሆን፤ "ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሴት አርሶ አደሮች ናቸው" ብለዋል። በመኸር ወቅት በዞኑ ከሚለማው መሬትም ከ22 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም ተመልክቷል።
የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት በሀዋሳ ይካሄዳል
Apr 20, 2024 69
ሃዋሳ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አፈጻጸም ላይ በሚያተኩረው ውይይት ላይ ለመሳተፍ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ሀዋሳ ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዋሳ ከተማ ሲገቡ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች የክልሉ አመራር አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የፌዴራልና የክልሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ሀዋሳ ገብተዋል። የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ይፋ ከተደረገበት ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የተሰሩ ስራዎችና የመጡ ለውጦችን አፈጻጸም እንደሚገመገም ታውቋል። የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንዲቻል የተቀረጸ ሲሆን፤ መርሀ ግብሩ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል። መርሀ ግብሩ በዋናነት እንቁላል፣ ዶሮ፣ ማር፣ ወተት እና አሣ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የልማት መስኮች ናቸው።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሴቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ተሰጥኦ እንዲያወጡ ሊታገዙና ሊበረታቱ ይገባል- በስታርት አፕ አውደርዕይ የተሳተፉ ሴቶች
Apr 20, 2024 55
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ ሴቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ተሰጥኦ እንዲያወጡና አገርን የሚጠቅም ተግባራቸውን እንዲያጎለብቱ ሊታገዙና ሊበረታቱ ይገባል ሲሉ በስታርት አፕ አውደርዕይ የተሳተፉ ሴቶች ገለፁ። በ21ኛው ክፍለ ዘመንም ይሁን ወደፊት በእጅ የሚሰሩ ሥራዎች ቁጥርና በየቢሮው በስፋት የሚታዩ የወረቀት ብዛቶች በሙሉ በዘመናዊ፣ በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንደሚቀየሩ የሚያሳዩ ምልክቶች ብዙ ናቸው። በአገራችንም ይህንን ታሳቢ ያደረገ የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች እየተበረታቱና ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራባቸው መሆኑ በግልጽ ይታወቃል። በአገሪቱ ያለውን እምቅ የቴክኖሎጂ አቅም ለማስተዋወቅ ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው የኢትዮጵያ "ስታርት አፕ" አውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ ተከፍቷል። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፍ የተሰማሩ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ''ስታርት አፖች'' በአውደ-ርዕዩ በመሳተፍ ላይ ናቸው። የቢፍሮል ቲዩብ መስራች ሀይከል አህመድ በአውደርዕዩ ተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት እንዲያገኙ የሚያግዙ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን የሚያቀርብ አማራጭ ይዘው እንደቀረቡ ተናግራለች። እነዚህ ቪዲዮዎች ተማሪዎች ትምህርትን ከንድፈ ሃሳብ በዘለለ በተግባር በመማር ብቁ እንዲሆኑ የሚያግዙ መሆናቸውን ጠቅሳለች። አኪል የተሰኘ አገርበቀል በጎ አድራጎት ድርጅትና በጎ ፍቃደኞችን የሚያገናኝ ድረገፅ ያለማችው ቦንቱ ፉፋ በበኩሏ ድረገፁ በጎ ፍቃደኞችንና በጎ ስራን በማገናኘት በጉልበት፣ ገንዘብና ባላቸው አቅም እንዲደግፉ የሚያስችል ነው ብላለች። በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂው ዘርፍ የወንዶች የበላይነት ቢስተዋልም በኢትዮጵያ ፈርቀዳጅ ሆነው በዘርፉ የወጡ ሴቶች መኖራቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቅሰዋል። ማንኛዋም ሴት እንደምትችል ካመነች ያለችውን ማድረግ ስለምትችል ስራ ላይ በማተኮር በቴክኖሎጂ ዘርፍ መሰማራት እንደምትችልም ነው የገለፁት። መንግስት እንደዚህ አይነት አውደ ርዕይ አዘጋጅቶ የሚሰሩትን ስራ እንዲያስተዋውቁ፣ ሌሎች የፈጠራ ስራዎችን አይተው እንዲበረታቱና እውቀት እንዲገበዩ በማድረጉ መደሰታቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም እንደዚህ አይነት ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ ማዘጋጀትና ያላቸውን እምቅ አቅም አውጥተው ለህዝብ እንዲያሳዩ የማድረጉ ስራ ሊጠናከር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው የኢትዮጵያ "ስታርት አፕ" አውደ-ርዕይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል።
ባለመላዎቹ ታዳጊዎች
Apr 19, 2024 212
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ ችግርን ወደ እድል የቀየሩ ባለመላዎቹ ታዳጊዎች ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው የኢትዮጵያ "ስታርት አፕ" አውደ-ርዕይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፍ የተሰማሩ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ''ስታርት አፖች'' በአውደ-ርዕዩ በመሳተፍ ላይ ናቸው። አውደ-ርዕዩ የተዘጋጀው በአገሪቱ የሚገኙ ስታርት አፖች ያላቸውን ምርትና አገልግሎት እንዲሁም ፈጠራዎች ተደራሽ ለማድረግ ነው። የአቤም ዩዝ አካዳሚ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት ጎዶሊያስ ሙሉጌታና ሰላዲን መራዊ የግለሰብ መረጃን ወይንም ሲቪ የሚያደራጅ ድረ-ገፅ ሰርተው በስታርት አፕ አውደ-ርዕይ አቅርበዋል። የታዳጊ ጎዶሊያስ ወንድም ስራ ለማመልከት ሲወጣ ''ሲቪ'' ረስቶ ወደቤት በመመለስ ለተጨማሪ ወጪና እንግልት መዳረጉ የዚህ ድረ-ገፅ መልማት መነሻ የሆነ ምክንያት ነው። ሰዎች ስራን ለመቀጠር የሚያስገቡት የራስ መግለጫ ''ሲቪ'' በእጅ ስልካቸው ኖሮ በማንኛውም ሰዓት ለሚፈልጉት ቀጣሪ ማስገባት የሚያስችል ድረ-ገፅ የሰሩት ታዳጊዎች የአይ ሲ ቲ መምህራቸው ለዚህ ስራቸው እገዛ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል። ድረ-ገፁ ስለግለሰቡ የትምህርት ደረጃን ጨምሮ፣ አድራሻ፣ ክህሎቶችና የሰዎችን ምስክርነትን ማካተት የሚቻልበት መሆኑን ተናግረዋል። ድረ-ገፁ የሰዎችን ብቻ ሳይሆን የድርጅቶችን መረጃ እንዲያስቀምጥ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑንም ታዳጊዎቹ ያስረዳሉ። በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው አውደርዕይ ላይ መሳተፋቸው ከሌሎች ስታርት አፖች ልምድ እንዲቀስሙና እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑንም ገልፀዋል። ስራቸውን እንዲያሳዩ እድል ስለተፈጠረላቸውና እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ እገዛ ላደረጉላቸው አካላትም ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ችግር ፈቺ የምርመር ስራዎችን በመስራት አገራቸውን ለመጥቀም እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለስታርት አፕ የሰጠችው ትኩረት የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ርዕይና ተስፋዋን የሚያሳካ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 19, 2024 170
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለስታርት አፕ የሰጠችው ትኩረት የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ርዕይና ተስፋዋን የሚያሳካ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸውም ኢትዮጵያን በብዙ መልኩ የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦችን መመልከታቸውን ተናግረዋል። ሀገርን ሊያሳድጉ የሚችሉ የፈጠራ ሀሳቦች ያሏቸው ወጣቶችና ታዳጊዎችን የኢትዮጵያ እድገት ተስፋዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ መንግስት ይህንን በመገንዘብ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠቱን አንስተዋል። 10 ዓመቱ የልማት እቅድ የገቢና ወጪ ምርቶችን ለማመጣጠንና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ለማሳደግ የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ስታርት አፖች ሚናቸው ትልቅ ነው ብለዋል። መንግስት ስታርት አፖችን ለማጠናከር እየሰራ ስለመሆኑ አንስተው፤ ለአብነትም ምርቶቻቸውን ገዝቶ መጠቀምን የሚያበረታታ እንዲሁም የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያደርጉ የፖሊሲ አቅጣጫዎችንና የህግ ማዕቀፎችን ወደ ስራ ማስገባቱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ብዙ ተስፋ እንዳላት ገልጸው፥ ኢትዮ ቴሌኮም አካታች የዲጅታል ኢኮኖሚ ስርዓትን በማሳለጥ ትላልቅ ስራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል። በተለይ በቴሌ ብር አገልግሎት አነስተኛ ብድሮችን በማቅረብ እና አርሶና አርብቶ አደሩን ጭምር የሚያሳትፉ ማዕቀፎችን በመተግበር ትልቅ እምርታ እያስመዘገበ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ያሉ ጅምሮች ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ ራዕይ ማሳካት እንደሚቻል የሚያሳዩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን ትልቅ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ በተለይም ቴክኖሎጅን ያወቀና የአገልጋይነት መንፈስ ያለው የሰው ኃይል ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል ኢትዮጵያ በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ የዲጅታል ኢኮኖሚ ማዕከል ለመሆን እየሰራች መሆኑንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ሀገራዊ የብልፅግና ጉዞን ለማሳካት በየክልሎች ያሉ ስታርት አፖችን ሁሉም ሊያበረታታ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የግሉ ዘርፍ በዲጂታል ምህዳሩ ላይ ያለውን ተሳትፎ በማጎልበት ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
Apr 19, 2024 104
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 11/2016 (ኢዜአ)፦የግሉ ሴክተር በዲጂታል ምህዳሩ ላይ ያለውን ተሳትፎ በማጎልበት ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ይሽሩን ዓለማየሁ ገለፁ። ራይድ ትራንስፖርት እና ታዋቂው ዓለም አቀፍ የዲጂታል ክፍያ ተቋም ቪዛ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ክፍያን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ጥምረት መፍጠራቸውን አስታወቀዋል። ጥምረቱ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች እና ዳያስፖራዎች የቪዛ ካርዳቸውን ብቻ በመጠቀም የትራንስፖርት ክፍያቸውን እንዲያከናውኑ የሚያስችል ነው፡፡ ይህም ጎብኚዎች አስተማማኝና ቀልጣፋ ትራንስፖርት በማግኘት በኢትዮጵያ አስደሳች ቆይታ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ይሽሩን አለማየሁ “ዲጂታል ኢትዮጵያ”ን እውን ለማድረግ ከሚከናወኑ ስራዎች መካከል ዲጂታል ክፍያ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የዲጂታል ክፍያ ስርዓትም የተቀላጠፈና ዘመናዊ አሰራር ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ነው ያብራሩት፡፡ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ መንግስት የዲጂታል ምህዳሩን ምቹ ማድረግ ጨምሮ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ የሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ራይድ መስራች ሳምራዊት ፍቅሩ፤ ጥምረቱ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" እውን ለማድረግ እየተከናወነ ካለው ስራ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ጥምረቱ ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ጥሬ ገንዘብ ሳይጠቀሙ በቪዛ ካርዳቸው ብቻ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት፡፡ በኢትዮጵያ የቪዛ ዳይሬክተር ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው፤ ቪዛ የተቀላጠፈ እና አስተማማኝ የዲጂታል ክፍያን ለሁሉም እና በሁሉም ቦታ ለማዳረስ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በመሆኑም ከራይድ ጋር የተጀመረው ጥምረት የኢትዮጵያን የጉዞ እና ቱሪዝም ዘርፍ ለማዘመን ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም የቪዛ ክፍያ ስርዓትን በሌሎች አገልግሎቶችም ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም ነው የገለጹት፡፡
ስፖርት
በዞኑ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተደርጓል
Apr 20, 2024 62
ሚዛን አማን ፤ ሚያዝያ 12/2016 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የስፖርት ባህልን ይበልጥ ለማዳበር የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ማስፋፋት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኮይካ ለኢዜአ እንደገለጹት ስፖርተኞችን ለማፍራት የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎችን ማስፋፋት ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን የውድድር ሜዳዎችን ማመቻቸት ቀዳሚ ተግባር ነው። ለዚህም ዞኑ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው የተለያዩ ሀገር አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን ሊያስተናግድ የሚችል የሚዛን አማን ሁለገብ ስታዲየም ከ82 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል። ስታዲዮሙ የመልበሻ ክፍል፣ የአስተዳደር እና የቴክኒክ ቢሮዎች ያሉት እና አነስተኛ አዳራሽ እንዲሁም መለስተኛ ካፍቴሪያን የያዘ መሆኑን ጠቅሰዋል። አፈጻጸሙ 62 በመቶ ላይ ደርሶ በከፊል አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸው የተለያዩ ጨዋታዎችን ለመመልከት የሚያስችል ደረጃ አንድ ወይም ቪ አይ ፒ መቀመጫዎች እንደሚገጠሙለት ጠቁመዋል። በተጨማሪም ከሚዛን አማን ሁለገብ ስታዲየም ከፍ ያለ ሁለተኛ የስታዲየም ግንባታ በሲዝ ከተማ አስተዳደር ለማስጀመር ሂደቱ እየተጠናቀቀ ይገኛል ብለዋል። በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋት ለተማሪዎችና ለአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ በተደረገው ጥረት ባለፉት 9 ወራት ውስጥ 65 የስፖርት ሜዳዎችን ማመቻቸት ተችሏል ብለዋል። በወረዳ ደረጃ 18 የይዞታ ማረጋገጫ የተሰጣቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች መኖራቸውን ገልጸው በአግባቡ ተንከባክቦ የመጠበቅ እና የመጠቀም ኃላፊነትን ወጣቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች እንዲወጡም አሳስበዋል። የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪው አቶ ዐቢዩ ዳኜ፤ አዕምሯችን እረፍት እንዲያገኝና ልጆቻችን በስፖርት ተኮትኩተው እንዲያደጉ ለማስቻል የስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳ አስፈላጊ ነው ብለዋል። እየተገነባ ባለው የሚዛን አማን ሁለገብ ስታዲየም ከሥራ መልስ ገብተው እረፍት እንደሚያደርጉ እና ጠዋት ጠዋት የጤና ስፖርት እንደሚሠሩበትም ተናግረዋል። ወጣቶች አላስፈላጊ ቦታ ላይ እንዳይውሉ ከማድረግ ባሻገር ነገ ሀገር ማስጠራት የሚችሉበትን ስፖርታዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መኖር ወሳኝ በመሆኑ የሚጠበቅብንን እንደግፋለን ብለዋል። በስፖርት ማዘውተሪያ የኳስ ልምምድ ሲያደርጉ ካገኘናቸው መካከል ሚካኤል ደረጀ እንዳለው ስፖርት ጤንነትን ለመጠበቅ እና አብሮነትን ለመፍጠር ይጠቅማል። ነገ የተሻለ እግር ኳስ ተጫዋች በመሆን ትላልቅ ውድድሮች ላይ የመሳተፍ ራዕይ ይዞ ጠዋትና ማታ በሚዛን ሁለገብ ስታዲየም ከጓደኞቹ ጋር ልምምድ እንደሚያደርግ ተናግሯል። ስታዲየሙ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መገንባቱ ውድድሮች ሲደረጉበት ልምድ የመቅሰም እድልን ይዞ ይመጣል ያለው ደግሞ ታዳጊ እውነቱ ብርሃኑ ነው። ከትምህርት ውጪ ያለውን ጊዜ የምናሳልፍበት በመሆኑ የሜዳውን እና በውስጡ የሚኖሩ ንብረቶችን የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ብሏል።
ዛሬ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል
Apr 18, 2024 381
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 10/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ናይጄሪያዊው አጥቂ ጄሮም ፍሊፕ በ38 ኛው፣ወገኔ ገዛኸኝ በ80ኛው እና አቡበከር ሳኒ በ90ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ግቦች ኢትዮጵያ መድንን አሸናፊ አድርገውታል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን ወሳኝ ሶስት ነጥብ በማግኘት በ22 ነጥብ ከወራጅ ቀጠናው በመውጣት 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በአንጻሩ ተጋጣሚው ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በሌላኛው የ22ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከሀዲያ ሆሳዕና ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ዛሬ ይጀመራል
Apr 18, 2024 290
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 10/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ። በ22ኛው ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ከቀኑ 10 ሰዓት በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው ወልቂጤ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። አንድ ጊዜ ሲሸነፍ ሶስት ጊዜ አቻ ወጥቷል። ወልቂጤ በ16 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ መድን በበኩሉ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ በተመሳሳይ አንድ ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪዎቹ ሶስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። በገብረመድህን ኃይሌ የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ መድን በ19 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ምሽት 1 ሰዓት በሚደረገው የ22ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ሁለተኛ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማና ሀዲያ ሆሳዕና ይጫወታሉ። ባህር ዳር ከተማ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም። በሶስቱ ሲያሸንፍ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል። በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ በ33 ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዟል ። ሀዲያ ሆሳዕና በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሁለቱ ድል ሲቀናው በአንዱ ተሸንፎ በሁለቱ ነጥብ ተጋርቷል። በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመራው ሀዲያ ሆሳዕና በ30 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የ22ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ነገ ቀጥሎ ሲውል ሀምበሪቾ ዱራሜ ከሃዋሳ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት፤ ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች እስከ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያሉ። ፕሪሚየር ሊጉን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ43 ነጥብ እየመራ ይገኛል። የሃዋሳ ከተማው አጥቂ አሊ ሱሌይማን 12 ጎሎች በማስቆጠር የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራ ነው። ዩጋንዳዊው የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች ቻርልስ ሙሲጌ፣ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማኑኤል ኦርቦ፣ የባህር ዳር ከተማው ቸርነት ጉግሳ እና የአዳማ ከተማው ዮሴፍ ታረቀኝ በተመሳሳይ በ9ኝ ግቦች ይከተላሉ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ23ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።
አካባቢ ጥበቃ
በጋምቤላ ክልል የአካባቢ ብክለት በሰውና በተፈጥሮ ሃብቶች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ በጋራ መስራት ይገባል-- -ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ
Apr 20, 2024 62
ጋምቤላ ፤ ሚያዝያ 12/2016(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የአካባቢ ብክለት በሰውና በተፈጥሮ ሃብቶች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የክልሉ ሕዝብ በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ። "ብክለት ይብቃ! ውበት ይንቃ!" በሚል መሪ ሀሳብ ለስድስት ወራት የሚተገበር የአካባቢ ብክለትን የመከላከል የንቅናቄ መርሃ ግብር በክልል ደረጃ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የአካባቢ ብክለት ችግሮችን ለመፍታት የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቶችን ማዘመን ያስፈልጋል። በክልሉ የአካባቢ ብክለት ችግሮች በሰው ጤና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ በተፈጥሮ ሃብቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ መሆኑን ገልጸዋል። የአካባቢ ብክለት በአየር፣ በውሃ፣ በአፈርና በሌሎችም የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል ኅብረተሰቡን በማሳተፍ እንዲሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። በተለይም የፕላስቲክ ብክለት የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ምርቶቹን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል የጉዳት መጠኑን ለመቀነስ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል። ለንቅናቄው ውጤታማነት የክልሉ ህዝብ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተወካይ አቶ ሺፈራው ነጋሽ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የፕላስቲክ ቆሻሻ በሰውና በእንስሳት ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። በተጨማሪም የፕላሰቲክ ቆሻሻ በየብስና በውሃማ አካላት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ምክንያት ለአካባቢ ውበትና ለብዝሃ ህይውት መመናመን አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም የፕላስቲክ አጠቃቀምና አወጋገድ ስርዓቱን በማዘመን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቅንጅት እንዲሰራ ጠይቀዋል። የክልሉ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በንቅናቄው የክልሉ ሕዝብ በአካባቢ ብክለት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የአካባቢ ብክለት ንቅናቄ በሰዎችና በእንስሳት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስና ለማስቀረት አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
በምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች 747 ሚሊዮን የቡና ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል
Apr 20, 2024 66
ጊምቢ፤ሚያዚያ 12/2016 (ኢዜአ) በምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች ከ747 ሚሊዮን በላይ ምርታማና ፈጥነው ምርት የሚሰጡ የቡና ችግኞች ለመጪው ክረምት ተከላ መዘጋጀታቸውን የዞኖቹ ግብርና ጽህፈት ቤቶች አስታወቁ፡፡ የጽህፈት ቤቶቹ ሃላፊዎች ለኢዜአ እንዳስታወቁት ለተከላ እየተዘጋጁ ያሉት ችግኞች በምርምር ምርታማነታቸው የተረጋገጡና በአጭር ጊዜ ምርት ለመስጠት የሚችሉ ናቸው። ዘንድሮ የሚተከሉት ችግኞች አሁን በሄክታር ከአራት ኩንታል ያልበለጠ ምርት የሚሰጡትን የቡና ዝርያዎች ምርት ወደ ዘጠኝ ኩንታል እንደሚያሳድጉት አስረድተዋል። በተጨማሪም ለአራት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ምርት ስለሚሰጡ፣ይህም አሁን በአርሶ አደሩ እጅ ካሉት ዝርያዎች ምርት ለመስጠት የሚያስፈልገውን ጊዜ በሦስት ዓመታት ያሳጥሩታል ብለዋል። ችግኞቹ ከጅማ ቡና ምርምር ማዕክል የተገኙ ሲሆን፣ 'ጫላ' ፣'መና ሲቡ'፣'ሓሩ አንድ'ና 'ሲንዴ' ተብለው መሰየማቸውን ገልጸዋል፡፡ የዞኖቹ አርሶ አደሮች በግብርና ባለሙያዎች ምክርና ክትትል በመታገዝ የጉድጓድ ቁፋሮ፣ያረጁ የቡና የመንቀልና ሌሎች ለተከላ የሚያስፈልግ ዝግጅት እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የምዕራብ ወለጋ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ቡድን መሪ አቶ ኤፍሬም መሥፍን እንደተናገሩት በዞኑ ከ401 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል። ዘንድሮ ለተከላ የተዘጋጁት የቡና ችግኞች በነባር የቡና መሬትና በ66ሺህ በላይ ሄክታር አዲስ መሬት ላይ እንደሚተከሉ ተናግረዋል፡፡ ይህም በዞኑ በቡና የተሸፈነው 550 ሺህ ሄክታር ወደ 615ሺህ ሔክታር እንደሚያሳድገው አስታውቀዋል፡፡ የቡና ችግኞቹ በ3ሺህ 352 የግልና በ74 የመንግሥት ችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን የቡድን መሪው ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ በቄለም ወለጋ ዞን ከ346 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን በዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ቡድን መሪ አቶ ታደሰ ጋሩማ አስታውቀዋል፡፡ ለተከላ እየተዘጋጁ ያሉት ችግኞች በ107 የመንግሥትና በ899 የግል ችግኝ ማፍያዎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ 467 ሺህ 301 ሄክታር መሬት በቡና ተክል መሸፈኑን አመልከተው፣ በየዓመቱም ወደ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የሚጠጋ ምርት እንደሚሰበሰብ አስታውቀዋል፡፡ የጊምቢ ወረዳ አርሶ አደር አቶ ዱጉማ ያደሳ፣ በግማሽ ሔክታር መሬታቸው ላይ የቡና ችግኞች ለመትከል ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ ችግኞች ከመንግሥት ችግኝ ጣቢያ የወሰዷቸው ችግኞች በእጃቸው ካሉት የተሻለ ምርት እንደሚሰጡ ከግብርና ባለሙያዎች መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡ የላሎ አሳቢ ወረዳ አርሶ አደር አቶ ቡልቱማ ታምሩ፤ በግላቸው ከ3ሺህ በላይ የቡና ችግኞች በባለሙያ ምክር በመታገዝ እንዳዘጋጁ አመልክተዋል፡፡
የፕላስቲክ ውጤቶች አጠቃቀምና አወጋገድን በማዘመን የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቷል--ባለስልጣኑ
Apr 20, 2024 62
አርባ ምንጭ ፤ ሚያዝያ 12/2016 (ኢዜአ)፦ የፕላስቲክ ውጤቶች አጠቃቀምና አወጋገድ ስርአትን በማዘመን የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኢፌዴሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሃሳብ ክልል አቀፍ የብክለት መከላከል ንቅናቄ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል። የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት የፕላስቲክ ውጤቶች አጠቃቀምና አወጋገድ ስርአትን በማዘመን ሀገርን ከአካባቢ ብክለት የጸዳች ለማድረግ በትኩረት ይሰራል። የፕላስቲክ ቆሻሻዎች በመሬት ውስጥ ለዘመናት ሳይበሰብሱ በመቆየት ስነ-ምህዳርን በማዛባት፣ ምርትና ምርታማነት በመቀነስ እንዲሁም የውሃ አካላትን በመበከል በሰውና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተሉ ይገኛሉ ብለዋል። የፕላስቲክ ውጤቶች አካባቢን የመበከል፣ የማቆሸሽና መሠረተ ልማቶችን ከመጉዳት ባለፈ ለማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ የሚሆኑበት ሁኔታ መኖሩንም ነው ያስረዱት። የፕላስቲክ ውጤቶች አጠቃቀምና አወጋገድ ሥርአት ላይ የባህሪ ለውጥ ባለመምጣቱ በሰው ልጆች ላይም ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም የፕላስቲክ ውጤቶችን በአግባቡ የመጠቀምና የማስወገድ ሥራ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ወይዘሮ ፍሬነሽ ተናግረዋል። በአካባቢ ደህንነት መብት አዋጅ አንቀጽ 44 መሠረት ሁሉም ሰው ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት እንዳለው ጠቅሰው፣ የፕላስቲክ ውጤቶችን አወጋገድ በማዘመን የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። ዳይሬክተሯ እንዳሉት እንደ ሀገር የቆሻሻ አወጋገድ ስርአትን ለማዘመንና ቆሻሻን በመልሶ ዑደት ጥቅም ላይ ለማዋል በከተሞች የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከር ይሰራል። በእዚህ ረገድ የተጀመሩ ሥራዎችን በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች ለማስፋትና ለሥራ ዕድል መፍጠሪያነት ለማዋል ባለስልጣኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። የፕላስቲክ ምርቶች ከሚሰጡት ጥቅም ይልቅ የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ በፕላስቲክ ምትክ ባህላዊ ቁሶችን መጠቀም እንዳለበት አስገንዝበዋል። እንደሀገር ቆሻሻ አወጋገድ ሥርአቱን ለማዘንም ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አስታውቀዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቴ ግጄ በበኩላቸው እንዳሉት የፕላስቲክ ቁሶች በሰው፣ በእንስሳትና በዕጽዋት ላይ ጉዳት እያስከተሉ ነው። "የፕላስቲክ አጠቃቀማችን ኋላ ቀር በመሆኑ ፕላስቲኮችን በቸልተኝነት በየስፍራው እንጥላለን" ያሉት አቶ ግዛቴ፣ በዘፈቀደ የሚጣሉ ፕላስቲኮች በአካባቢ ስነ-ውበት ላይም አሉታዊ ጫና እየፈጠሩ ነው ብለዋል። የፕላስቲክ ውጤቶች አገልግሎት ከሰጡ በኋላ ለመልሶ ዑደት ካልዋሉ በነፋስና ጎርፍ ተወስደው ከተሞችን፣ የእርሻ ማሳዎችና የውሃ አካላትን ከመጉዳት ባለፈ የሰው ልጅ፣ የዱርና የቤት እንስሳትን የምግብ ሰንሰለት ያውካሉ ብለዋል። በአርባ ምንጭ ከተማ የሚጣሉ የፕላስቲክ ቆሻሻዎች በጎርፍ ተወስደው በአባያና ጫሞ ሐይቆች መካከል ከ70 ሄክታር በላይ የደን ሀብትን ከጥቅም ውጭ ማድረጋቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል። እንደ ክልል ፕላስቲክ ቆሻሻን በመልሶ ዑደት ጥቅም ላይ ለማዋል፣ ፕላስቲኮችን መልሶ ለሌላ አገልግሎት ለመጠቀምና በምትኩ በቀላሉ ሊበሰብሱ የሚችሉ ምርቶችን ለመጠቀም ህዝባዊ ንቅናቄ መጀመሩንም ተናግረዋል። ህብረተሰቡ አካባቢውን ከብክለት በመጠበቅ የተጀመረው ንቅናቄ ከግብ እንዲደርስ ጠንካራ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባም አቶ ግዛቴ አሳስበዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄን ባለፈው መጋቢት ወር ማስጀመራቸው የሚታወስ ነው።
የኮሪደር ልማት ሰራው የመዲናዋን አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ ሚናው የጎላ ነው - የአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ
Apr 20, 2024 50
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 12/2016 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ የመዲናዋ አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ ሚናው የጎላ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ቁጥር እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የመሰረተ ልማት ፍላጎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ ይህንንም ለዓመታት የተሻገሩ የመሰረተ ልማት ችግሮች ለመፍታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የኮሪደር ልማት ስራ ተጠቃሽ ነው፡፡ የኮሪደር ልማት ስራው ሲጠናቀቀም የህብረተሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ከመመለስ ባለፈ የመዲናዋን ውበትና ገጽታ የሚቀይር ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ይመኙሻል ታደሰ፤ ከዚህ ቀደም የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከአረንጓዴ ልማት ጋር የተሳሰሩ እንዳልነበሩ ተናግረዋል፡፡ ይህም ከተማዋን የሚመጥናት ገጽታን እንዳትላበስ አድርጓት መቆየቱን ነው ያነሱት፡፡ ካለፉት 5 ዓመታት ወዲህ የከተማዋን እድገት ከአረንጓዴ ልማት ጋር በማስተሳሰር ውብ ጽዱና ለዜጎቿ የምትመች ከተማ መፍጠር ላይ የተሻለ ስራ መከናወኑንም ጠቁመዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ደግሞ የከተማዋን ውበትና አረንጓዴ ሽፋን ለመጨመር ለሚከናወኑ ስራዎች ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ የኮሪደር ልማት ስራው በተለይ በከተማዋ መስፈርትን በጠበቀ መልኩ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሮችን ለማከናወን ማነቆ የሆኑ ችግሮችን እንዲፈቱ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ነው የገለጹት፡፡ ይህም የከተማዋን የቱሪስት ፍሰትና የቆይታ ጊዜ ለማራዘም ያግዛል ነው ያሉት፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2 ነጥብ 8 ወደ 15 በመቶ እንዲያድግ ማድረጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 982
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 1912
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1200
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።
በአባቱ የሎተሪ ስጦታ 4 ሚሊዮን ዶላር ያሸነፈው እድለኛ
Apr 4, 2024 1250
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2016(ኢዜአ)፦ በአሜሪካ ኤሊኖይ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ አባቱ ያበረከቱለት የሎተሪ ትኬት የ4 ሚሊዮን ዶላር እድለኛ አድርጎታል። ስቴቨን ሪቻርድስ ይባላል በኤሊኖይ የባሪንግተን ከተማ ነዋሪ ሲሆን ከቀናት በፊት ከአባቱ ጋር ቁርስ ለመመገብ ባቀኑበት ምግብ ቤት ከአባቱ ስጦታ ይበረከትለታል። ስጦታውም የ10 ዶላር የሎተሪ ትኬት ነበር። አዛውንቱ ያበረከቱለት የሎተሪ ትኬት ወዲያውኑ ተፍቆ ውጤቱን የሚያሳይ ሲሆን ስቴቨንም ትኬቱን በፋቀበት ቅጽበት ከፍተኛ ድንጋጤ እንደተሰማው ለማሳቹሴት የሎተሪ አስተዳደር ተናግሯል። የሎተሪ ትኬቱ የ4 ሚሊዮን ዶላር እድለኛ እንዳደረገኝ ሳውቅ በድንጋጤ ማመን አልቻልኩም በዚህም ውጤቱን ከመናገሬ በፊት በስልኬ ስካን አደረኩት ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። በመቀጠለም የአባቱ ስጦታ እድለኛ እንዳደረገው ለባለቤቱ እንዲሁም ለአባቱ መናገሩን ዩፒአይ ዘግቧል። ስቴቨን በሎተሪ ከደረሰው 4 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ በተወሰነው ገንዘብ ከባለቤቱ ጋር የተለያዩ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ማቀዱን ዘገባው አመልክቷል።
ሐተታዎች
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 220
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል። “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1333
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2239
"የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።
በከፍታ የታጀበ ስኬት
Mar 15, 2024 1853
ለህጻናትና ታዳጊዎች መልካም ስብእና የሚያግዙ ጽሁፎችን ያዘጋጀችው ኤሪን ሶዴርበርግ ዶውኒንግ 'JUST KEEP WALKING' በሚለው መጽሃፏ ባደራጀችው ገጸባህሪ አማካይነት “አንተ መልካምና ስኬታማ ሆነህ ሳለ ጥቂት ሰዎች ስለአንተ መጥፎነት አብዝተው መጨነቅና ማውራት ከጀመሩ የምትሄድበት መንገድም ሆነ አካሄድህ ትክክል ነውና መራመድህን አታቁም። ብዙሃኑ የስኬትህ ተካፋይና የስኬትህ አጋር ስለሆኑ የጥቂቶቹን ጫጫታ ከምንም ካለመቁጠር ተራመድ ብዙ አፍራሽ ወሬዎች ያንተን ስኬት የመመስከር አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን አትዘንጋ። መቆም የሽንፈት ምልክት ነውና” ትለናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 78 ዓመታት በከፍታ የዘለቀ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምና ዝናው የገነነ ተቋም ነው። አየር መንገዱ ታህሳስ 21 ቀን 1938 ዓ.ም ተመስርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ካይሮ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዘመኑ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅና አሰራሮችን በማዘመን ራሱን እያደራጀ የኢትዮጵያ ኩራት ከመሆን አልፎ የአፍሪካ ምልክት ሆኖ ዘልቋል። ዛሬ ላይ የ152 ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምስረታው ወቅት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት አውሮፕላኖች ብቻ እንደነበሩት መረጃዎች ያመለክታሉ። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ22 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞችን ፍላጎትና ምቾት ለመጠበቅ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ጨምሮ 31 አውሮፕላኖች ለመግዛት ከአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። እነዚህን ተጨማሪ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ቁጥር ጨምሮ የሚገነባቸው ዘመናዊ አየር መንገዶች ሲደመሩ በአፍሪካ ግዙፍ ተቋምነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ያደርገዋል። የበረራ አድማሱን በየጊዜው እያሰፋ የሚገኘው አየር መንገዱ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 134 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በሀገር ውስጥ ወደ 22 መዳረሻዎች ይበራል። ከዚህ ውስጥ 60 የበረራ መዳረሻዎቹ አፍሪካ ውስጥ ነው። አየር መንገዱ ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ አስገንብቶ ወደ ስራ ያስገባው ዘመናዊ የካርጎ ማእከል ከምስራቅ አፍሪካ ብሎም ከአፍሪካ ከፍተኛ ተብሎ ተመዝግቦለታል። በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው ያረፈው የካርጎ ማዕከል ለኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ ኮሜርስ) አገልግሎት የሚውል ሲሆን የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣት አየር መንገዱ የሚሰራቸው ተያያዝ በርካታ ተግባራት መስፋት፣እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ተመራጭ መሆን ለማእከሉ ግንባታ ምክንያት ተብለው ተጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ መስክ ከሚታወቅባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሴቶችን በማብቃትና የጾታ እኩልነትን በማስተግበር ረገድ አርአያነት ያለው ተግባር መፈጸሙ ነው። በየዓመቱ የሚታሰበው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ማርች 8 በሚከበርበት ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ ለሙሉ በሴቶች ብቻ የተመራ በረራን በማደረግ ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፏል። አየር መንገዱ ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ "ሴቶችን በማብቃት አፍሪካን ማስተሳሰር" በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ ወደ ለንደን በሴቶች ብቻ የተመራ የተሳካ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች በሚሰጠው ዘመኑን የዋጀና ቀልጣፋ አገልግሎት በየጊዜው የተለያዩ ሽልማቶች ባለቤት መሆን የቻለ ተቋም ነው። ለአብነት የቅርብ ጊዜያቶችን ለማንሳት ያህል ባሳለፍነው ዓመት በአየርላንዷ ደብሊን በተዘጋጀ መርሐ-ግብር ላይ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማትን አሸንፏል፡፡ በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ ጉባኤ "ኤር ካርጎ ኤሮፕ" እ.አ.አ በ2021 ባካሄደው የበይነ መረብ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና የሎጅስቲክ አገልግሎት የ2021 የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ የደንበኞች እንክብካቤ ዘርፍ ሽልማት አግኝቷል። በአውሮፓውያኑ 2024 ዓመታዊውን የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “የኮርፖሬት የዘላቂነት ስኬት ሽልማት” አሸናፊ ሆኗል። አየር መንገዱ በትላልቅ ስኬቶች የማለፉን ያህል ከባድ ፈተናዎችንም ተጋፍጦ በጽናትና በስኬት አልፏል። መላውን ዓለም ያዳረሰው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አንዱ ማሳያ ነው። በዚያን ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ምክንያት በዓለም ደረጃ በርካታ አየር መንገዶች በረራ በማቋረጥ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ አንዳንድ የመንገደኞች አውሮፕላኖቹን ወደ ዕቃ ጫኝ በመቀየር ጭምር ትኩረቱን ጭነት ማጓጓዝ ላይ አድርጓል። በዚያን ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የቀየሰውን ስትራቴጂ በመቃወም ከውስጥም ከውጭም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ትችትን አስተናግዷል። ይሁን እንጂ አየር መንገዱ ፈተናውን በመቋቋም እንደሌሎቹ ሀገራት አውሮፕላኖች በረራ የማቋረጥ እጣ ሳይገጥመው በታላቅ ብልሃት ማለፍ የቻለ ተቋም መሆኑ ተመስክሮለታል። በዚህም በካርጎ አገልግሎት ገቢ ከማገኘቱም ባሻገር ክትባትን ለዓለም በማዳረስ ወረርሽኙ ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ የራሱን አሻራ አኑሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን ከአራት አስርተ ዓመታ በላይ ልምድ አካብቷል። አየር መንገዱ በሚያስተዳድረው ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የበረራ ባለሙያዎችን በቅርቡ ያስመረቀ ሲሆን ምሩቃኑ ከታንዛንያ ከደቡብ ሱዳን ከኒጀር ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከቶጎ እና ከማዳጋስካር መሆናቸው ደግሞ የአየር መንገዱን የፓንአፍሪካኒስት መንፈስ አጉልቶ ያሳየ አድርጎታል። ስኬቶቹ በዚህ ያላበቁት አየር መንገዱ የእድገት ግስጋሴውን እንደቀጠለ ይገኛል። ከሰሞኑ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በዚህ ወቅት ከተሸለሙት ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን ሽልማቱ ለወደፊትም ለላቀ ስኬት የሚያዘጋጀው እንደሆነ ይታመናል።
ትንታኔዎች
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3586
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ) የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች
Mar 2, 2024 2374
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች። የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው። የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡ መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ። የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል። ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2256
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።
በአጭር ጊዜ ትልቅ እመርታ በሌማት ትሩፋት
Feb 6, 2024 3113
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በግብርና ልማት በተለይም በስንዴ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ በምግብ እራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል። በግብርና ልማት እየተከናወኑ ባሉ ውጤታማ ስራዎች ላይ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ሲታከሉ ከምግብ ዋስትና ባለፈ ስርአተ ምግብን በማስተካከል ረገድ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ለመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ስርአተ ምግብን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚኖረው ፋይዳ እንዴት ይታያል? በእስካሁኑ አካሄድስ ምን ውጤቶች ተገኙ? ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ‘የሌማት ትሩፋት’ መርሃ ግብርን ካስጀመሩ በኋላ በመህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሌማት አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ገልጸው ነበር። በወቅቱ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በቂ እና አመርቂ ምግብ ማግኘት መሆኑን ገልጸው በቂ የመጠን፣ አመርቂ የይዘት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም በምግብ ራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ገልጸዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር ዓላማ የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥና ክብርን ማስጠበቅ ሲሆን በተለይም ስጋ፣ እንቁላል፣ ማር እና ወተት ትርፍ ምርት ሆነው እንዲገኙ ማልማትና መጠቀምን መሰረት ያደረገ ነው። መርኃ-ግብሩ የኢትዮጵያን ደካማ የአምራችነት ታሪክ በመቀየር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የኢኮኖሚ እድገትን የማፋጠን ግብ የሰነቀ መሆኑ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሌማት ትሩፋት ዘመቻው በቤተሰብ፣ ብሎም በሀገር ደረጃ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል። የወተት፣ የዶሮ፣ የዕንቁላል፣ የማር፣ የዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን ለማሻሻል ሀገራዊ የመንግሥት ፕሮግራም ሆኖ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት በብዙ መልኩ ውጤት እያስገኘ ነው። በእርግጥም የሌማት ትሩፋት በአንድ ዓመት ጉዞው በተለይ በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና ስጋ ምርት መጠን አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑ የተረጋገጠበት ውጤት ተመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በ2015 ዓ.ም፣ የወተት፣ የዶሮ እና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት ማምጣቱንና በተያዘው ዓመትም በበለጠ ለማሳካት የሁሉም ጥረት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በማር፣ በወተትና በዶሮ ልማት ከ20 ሺህ በላይ መንደሮችን በመለየት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ለኢዜአ ገልጸዋል። ለአብነትም በወተት ልማት በተሰሩ ስራዎች 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ሊትር የነበረውን የማምረት አቅም ወደ 8 ነጥብ 6 በሊዮን ሊትር ከፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በመጪዎቹ ዓመታትም ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በእንቁላል ምርት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የጫጩቶች ስርጭት ከነበረበት 26 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ማደጉን ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ- ግብር የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን የሚናገሩት የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በእንስሳት ሃብት ልማት ብቻ በዓመት ለ259 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ለዘርፉ ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት አመርቂ ውጤት ሳያገኝ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ዘርፉ በቅንጅት ከተመራ፣ በቴክኖሎጂ ከታገዘ የምግብ አማራጭን ማብዛት ይቻላል። ወተት፣ ማር፣ ስጋ እና እንቁላል መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በገበያ ላይ ማትረፍረፍ፣ የሌማቱ በረከት ማብዛት የሚለው የብዙሃኑ እምነት ነው። የምግብ ዋስትና ጉዳይ ከተመጣጠነ ምግብ ጋር ያለው ቁርኝት የማይነጣጠል በመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ፋይዳው ብዙ ነው። በሌማት ትሩፋት ገበታን በተመጣጠነ ምግብ መሙላት ከተቻለ የእናቶችንና የህጻናትን ፍላጎት በማሟላት በአካል የዳበረና በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ መገንባት ይቻላል። በተቃራኒው ያልተመጣጠነ አመጋገብ ጤና ላይ ከሚፈጥረው ችግር ባለፈ በሰዎች መካከል ያለውን የኑሮ አለመመጣጠን በማስፋት፣ ማህበራዊ ቀውስን በመፈልፈልና ኢኮኖሚውን በመጉዳት ምርትና ምርታማነትን ወደ ኋላ የሚጎትት ይሆናል። ይህ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት በከባድ ትግል ላይ የሚገኙ ሀገራትን የልማት ግስጋሴ በመግታት ቀድሞ ወደነበሩበት የድህነት አረንቋ እንዲመለሱ ያደርጋቸዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙና እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት በዕድሜያቸው ልክ ዕድገት የማያስመዘግቡ ወይም የመቀንጨር ችግር ያለባቸው መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። ለዚህ ነው በምግብ ራስን ከመቻል ጎን ለጎን የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ የሚሆነው። በዚህ ረገድ የሌማት ትሩፋት እየተጫወተ ያለው ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። የተለያዩ ምግቦችን በገበታ ላይ ማካተት የሚያስችል ስልጠናን ከተግባራዊ የልማት ስራዎች ጋር ያካተተ ሲሆን አዲስ የአመጋገብ ባህልን የሚያለማምድ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለተሰሩ ስራዎችና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል። ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ረሀብን ዜሮ ለማድረስ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ ብልጽግናን እውን እንደምታደርግ ገልጸዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተሰሩት ስራዎች ለመጪው ትውልድ ጥሩ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ለአብነት አንስተዋል። የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ስራችን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተመጣጠነ ምግብን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል። የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ነጻ አገር እውን ማድረግን ያለመ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አመራሩ ይህንን ተገንዝቦ እንዲሰራ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ህልም የሚመስሉ በርካታ አገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ የቻለችው በዜጎቿ የተባበረ ክንድ መሆኑ እሙን ነው። ከዚህ አኳያ በምግብ ራስን ከመቻል በላይ የኢትዮጵያን የአምራችነት ታሪክ የመቀየር ግብ ለሰነቀው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ስኬታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት ይጠበቃል።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11548
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15940
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት። እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8168
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል። “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9179
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ
Mar 5, 2024 3488
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 3306
በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።