አርእስተ ዜና
በአፍሪካ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በይፋ ስራ ጀመረ
Apr 25, 2024 45
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- በአፍሪካ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በይፋ ስራ ጀመረ። ኢኒሼቲቩ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አነሳሽነት በአፍሪካ በተለይ ኢንቨስትመንትን፣ ስራ ፈጠራንና ስታርትአፕን ለመደገፍ የሚሰራ ነው። ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በአህጉሪቱ ግዙፍ የፓንአፍሪካ ስታርትአፕ ምህዳር መፍጠርን ያለመ ነው።   በኢንሼቲቩ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ታዬ፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ባሳለፍነው ጥር ወር በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በመሆን ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ኢኒሼቲቩ 1 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በማሰባሰብ የ100 ሚሊዮን አፍሪካውያንን ህይወት ለማሻሻልና ለ10 ሚሊዮን ሰዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ አስቀምጧል።
በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እየተሸጋገረች መሆኗን ማረጋገጫ ናቸው- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ
Apr 25, 2024 48
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እየተሸጋገረች እንደምትገኝ ማረጋገጫ መሆናቸውን የከተማዋ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ፋይዛ መሃመድ ገለጹ። የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና ጥራት እንዲከናወኑ ምክር ቤቱ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እና በልማቱ የተነሱ ነዋሪዎች በተዘጋጁላቸው ምትክ መኖሪያ መንደሮች ተገኝተው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ ቡዜና አልቃድርን ጨምሮ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ አባላት እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ፋይዛ መሃመድ እንዳሉት፤ የምክር ቤቱ አባላት የህዝብ ወኪል በመሆናቸው የመዲናዋ የልማት ስራዎችን የመከታተልና ጉድለቶችን የመገምገም ግዴታ አለባቸው። በዛሬው ዕለትም የኮሪደር ልማት ስራዎች እና በኮሪደር ልማቱ ተነስተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ በሃና ፉሪ እና ጉራራ ምትክ የጋራ መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ነዋሪዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።   ምክትል አፈ ጉባኤዋ አክለውም የተጀመረው የልማት ስራ በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ምክር ቤቱ የክትትል እና ድጋፍ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ለኑሮ ምቹ፣ ውብና ጽዱ አደርጎ የማዘመን እንዲሁም ከዓለም ከተሞች ተወዳዳሪና ተመራጭ ከተማ እንድትሆን የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እየተራመደች መሆኗን ሁነኛ ማረጋገጫ እንደሆነም ምክትል አፈ ጉባዔዋ አብራርተዋል። በኮሪደር ልማት ሳቢያ ተነስተው በአጭር ጊዜ ምትክ የጋራ መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ነዋሪዎች በልዩ ትኩረት የመሰረተ ልማት እና ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲሟሉላቸው መደረጉን አረጋግጠናል ነው ያሉት።      
ኢንስቲትዩቱ በአማራ ክልል የሰብል ጉዳት ላጋጠማቸው አርሶ አደሮች 39 ሚሊዮን ብር  የሰብል መድን ዋስትና ሰጠ
Apr 25, 2024 40
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ሰብላቸው በበሽታ ለተጎዳባቸው አርሶ አደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድን ዋስትና ሰጠ። ኢንስቲትዩቱ ለአርሶ አደሮች የሰብል መድን ዋስትና የሰጠው ከዓለም ምግብ ፕሮግራምና ፑል አድቫይዘርስ በፈጠረው ጥምረት በተቋቋመ የሰብል መድን በኩል መሆኑ ተገልጿል። የሰብል መድን ዋስትናው የስንዴ ሰብልን በሚያጠቃው ዋግ ሰብላቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን በአማራ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም ያለመ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የስራ አመራር ስራ አሰፈፃሚ ዳዊት ፊሊጶስ የሰብል መድን ዋስትና ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት የሰብል ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች የካሳ ክፍያ በመክፈል እያቋቋመ መሆኑን ተናግረዋል። በዛሬው እለት በአማራ ክልል በሁለት ወረዳዎች ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድን ዋስትና መሰጠቱን ገልጸዋል። በመድን ዋስትናው ከ50 በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የሰብል መድን መክፈሉን ገልጸው፥ በቀጣይ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በሌሎችም ክልሎች እንደሚሰፋ ጠቁመዋል። አርሶ አደሩ የሰብል መድን አባል በመሆንና ክፍያ በመክፈል ጉዳት ሲደርስበት የዋስትና ክፍያ እንዲከፈለው በማድረግ መልሶ እንዲቋቋም የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። ባለፈው ዓመት በድርቅ፣ በከባድ ዝናብ እና በተባይ በሽታ ሰብላቸው ለተጎዳባቸው ለ122 ሺህ አርሶ አደሮች የሰብል መድን ዋስትና በመስጠት ማቋቋሙን ተናግረዋል። የሰብል መድን ዋስትና በ2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት፣ በዓለም ምግብ ፕሮግራምና በፑላ አድቫይዘርስ ትብብር በግብርናው ዘርፍ በአየር ንብረት ለውጥና በሌሎች ችግሮች የሚከሰትን አደጋ መፍትሔ ለመስጠት የተመሰረተ ድርጅት ነው።  
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል  የፋይናንስ ዘርፉን ከብክነት የጸዳ ለማድረግ እየተሰራ ነው
Apr 25, 2024 46
ሚዛን አማን፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የልማት ዕቅዶች ጋር ሊጣጣም የሚችል የበጀት አመዳደብና አጠቃቀም ሥርዓት በመከተል የፋይናንስ ዘርፉን ከብክነት የጸዳ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር የሕግ ማዕቀፎችና የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ነው። የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ በመድረኩ እንዳሉት፤ በክልሉ የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር የሕግ ማዕቀፎች ላይ የአመራር ግንዛቤ ክፍተት ይስተዋላል። ለዚህም በየመዋቅሩ የሚገኙ የኦዲት ግኝት ውጤቶች ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል። ችግሩን ለማቃለል ተከታታይነት ያለው ስልጠና ነክ የምክክር መድረክ ለአመራር አባላት ተዘጋጅቶ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። እየተካሄደ ባለው መድረክም በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የሕግ ማዕቀፎች፣ በግዥ መመሪያና በመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ሥርዓት ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ውይይት ይደረጋል ነው ያሉት። የፋይናንስ ሥራዎችን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ እንዲቻል ቢሮው አስፈላጊ የኮምፒውተር እና ተያያዥ ግብዓቶችን ለታችኛው መዋቅር የማሟላት ሥራ ላይ ማተኮሩን ጠቁመዋል። የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓትን የተከተለ የበጀት አጠቃቀም ሂደት ተግባራዊ እንዲደረግ አመራሩ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት ተናግረዋል። በተለይ ከልማት ዕቅዶቻችን ጋር ሊጣጣም የሚችል የበጀት አመዳደብና አጠቃቀምን ሥርዓት በመከተል የሀብት ብክነትን ማስቀረት ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ አመላክተዋል።   የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው፤ በክልሉ እየተስተዋሉ ያሉ የፋይናንስ አጠቃቀም ግድፈቶችን ደረጃ በደረጃ ለማስተካከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ፋይናንስን በእውቀትና በክህሎት በመምራት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባ አመልክተው፤ የአቅም ውስንነቶችን ለመሙላት በተለያዩ ጊዜያት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ይሰጣሉ ብለዋል። ውስን በጀት ሚዛኑን ጠብቆ ለሕዝብ ልማት እንዲውል ለማድረግ በአግባቡ መረጃ ማደራጀት ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል። ለሁለት ቀናት በሚቆይ የውይይት መድረክ የክልል ከፍተኛ አመራር አባላትና የዞን ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።    
በአገልግሎት አሰጣጥ  ሂደት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍና  የተጠያቂነት አሰራርን መዘርጋቱን  የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ 
Apr 25, 2024 50
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍና የተጠያቂነት አሰራርን መዘርጋቱን የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ ። ኤጄንሲው የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጽም ሪፖርቱን ከተጠሪ ተቋማት ጋር ገምግሟል። የኤጀንሲው የዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹምዬ እንዳሉት፤ ኤጀንሲው በሁሉም ጽህፈት ቤቶቹ የወሳኝ ኩነትና የነዋሪነት ምዝገባ ተልዕኮውን ወቅቱን ጠብቆ በማከናወን አበረታች ውጤት አስመዝግቧል። ከጤና፣ ከሃይማኖት፣ ከትምህርት፣ ከዕድሮች እና ከሌሎች ተቋማት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ ስራዎችም ለኤጀንሲው ወቅታዊ ምዝገባ ስርዓት መሳለጥ እንዳገዙ አብራርተዋል። በወቅታዊ ምዝገባ ረገድ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የዕቅዱን 91 በመቶ በላይ በማሳካት ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ከ24 በመቶ በላይ እምርታ ማምጣቱን ጠቁመዋል። በነዋሪዎች መታወቂያ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድም ከ93 በመቶ በላይ ዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ማድረጉን ጠቅሰው፤ ጤናና መሰል ችግሮች ላሉባቸው ነዋሪዎች የቤት ለቤት አገልግሎት መስጠቱን አንስተዋል። ኤጀንሲው ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት ከአንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዬን በላይ ዜጎች አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉንም ተናግረዋል። በአገልግሎት ሂደት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የተጠያቂነት አሰራር ዘርግቶ ገቢራዊ ማድረጉን ጠቅሰዋል።   የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው ኤጀንሲው ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር አገልግሎቱን ለማሻሻል እየሰራ ነው። በሪፎርሙም የተቋሙን አገልግሎቶች ከዕጅ ንኪኪ ነጻ በሆነ ቴክኖሎጂ ስርዓት በማስገባት ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ በሁሉም ዘርፎች አበረታች ስኬቶች እንደተመዘገቡ አንስተዋል። ያም ሆኖ ኤጀንሲው ተገልጋዮችን በሚፈለገው ልክ ማርካት ባለመቻሉ የሪፎርም አሰራር ስርዓቶች ትግበራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በተለይም ለኤጀንሲው ቁልፍ የመልካም አስተዳደር ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ተጠያቂነትን መሰረት ያደረጉ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው ያነሱት።          
የሚታይ
ለመጪው የትንሣኤ በዓል መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት ተደርጓል - የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን
Apr 25, 2024 65
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- ለመጪው የትንሣኤ በዓል መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የሚገመት የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሸማች ማኅበራት በኩል እንደሚያቀርብ ነው የገለጸው። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሀብተየስ ዲሮ እንደገለጹት ለትንሣኤ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ ሥራ ጀምሯል። በዚህም ጤፍ፣ ዱቄት፣ የቁም እንስሳት፣ እንቁላል፣ ሽንኩርትና ሌሎች ምርቶች በዩኒየኖች አማካኝነት ወደ ሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት እየገቡ መሆኑን ተናግረዋል። ምርቶቹ በ800 የሸማቾች ሱቆችና በ137 የእሁድ ገበያዎች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚቀርቡም ገልጸዋል። በሸማቾች ማህበራት ስር የሚገኙ 246 ስጋ ቤቶችም በኪሎ ከ400 እስከ 460 ብር እና በቅርጫ ሥጋን ለማቅረብም ዝግጅት ማድርጋቸውን ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የተናገሩት።   በኮሚሽኑ የሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ተጫነ አዱኛ በበኩላቸው፥ ለበዓሉ የሚቀርቡ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለኅብረተሰቡ በትክክል እንዲደርሱ ጠንካራ ቁጥጥር እንደሚደረግ አመልክተዋል።  
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ታዳጊዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው -  ኢንስቲትዩቱ
Apr 25, 2024 73
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ታዳጊዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ገለጸ። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመጪው ክረምት የስልጠና መርሐ ግብር የሚሳተፉ ተማሪዎችን ምዝገባ ጀምሯል። በ3ኛ ዙር ስልጠና የሚሳተፉት የመጀመሪያና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ እና በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን እንደሚኖርባቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና፤ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ ዕድገት መለኪያ የሆነ ዘርፍ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያም ግንባር ቀደም አህጉራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተቋም በመገንባት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመስኩ የፈጠራ ዝንባሌ እና ክህሎት ላላቸው ታዳጊዎች የሚሰጠው ስልጠናም በዘርፈ ብዙ መስኮች ተወዳዳሪ ሀገር መፍጠር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በመጪው ክረምት ታዳጊ ተማሪዎችን በመቀበል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ክህሎታቸውን በማበልጸግ የተሻለ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። ስልጠናውም የኢትዮጵያን ከፍታ በማስቀጠል ፈጠራና ክህሎትን በማበረታታት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ታዳጊዎችን ማፍራት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ መሆኑን አስረድተዋል።   በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የምርምርና ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር)፥ በክረምት ወራት የሚሰጠው ስልጠና እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በቀጣይም በኢንስቲትዩቱ ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ በክልሎች ለማስፋት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።   የቴክኖሎጂ አማካሪው ሰለሞን ሙሉጌታ፥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የሚሰጥ ስልጠና ታዳጊዎች የዓለምን አዝማሚያና ዝንባሌ በቅጡ እንዲረዱ የሚያስችል ነው ብለዋል። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዕውቀትንም ለግብርና፣ ለመንግስት አገልግሎት፣ ለጤና እና ሌሎች ተግባራት እንዲያውሉት ማስተማር እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል። በመጪው ክረምት ለሁለት ተከታታይ ወራት በሚሰጠው ስልጠና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ቀናት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል። ከሀምሌ 1 እስከ ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም በሚቆየው ስልጠና ተማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት እውቀትና ክህሎት የሚያገኙበት የንድፈ ሀሳብና የተግባር ትምህርት ይሰጣቸዋል። ስልጠናው ከሚያተኩርባቸው መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ሮቦቲክስ፣ ፕሮግራሚንግ፣ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም ይገኙበታል።  
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
Apr 25, 2024 170
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። 31ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ለኢንደስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ፣ በወጪ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በማበረታታት ረገድ የታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ እና የዘርፉን ተዋንያን የሚያበረታታ ሥርዓት በመዘርጋት ተወዳዳሪነት ማላቅ ይቻል ዘንድ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም ረቂቅ ማሻሻያ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፣ የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያወጣውን ወጪ በከፊል መሸፈን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 3. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የጤና ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በስራ ላይ ያለው የጤና ፖሊሲ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ፖሊሲው በጸደቀበት ወቅት ከነበረው ጠቅላላ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ፣ እየተከሰቱ ያሉ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መበራከት፣ በሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና ዙሪያ የሚከሰቱ ለውጦች፤ ዘርፉ ጥራት እና ፍትሀዊነት ያለው አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ችግሮች የሚስተዋሉበት በመሆኑ እንዲሁም ከሀገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር የሚጣጣም የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ፖሊሲው ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 4. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው በግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በስራ ላይ የነበረው የግብርና ፖሊሲ ከአዳጊ የምርትና ምርታማነት ፍላጎት ጋር አብሮ መጓዝ የቻለ ባለመሆኑ፤ ለግብርናው ዘርፍ እድገት ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን መለወጥ አስፈላጊ በመሆኑ እንዲሁም ሀገራችን ከምትከተለው ብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ስርአት ጋር የሚጣጣም ፖሊሲ ማስፈለጉ ታምኖበታል፡፡ ስለሆነም የግብርና ዘርፍን ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር የበለጠ የሚያስተሳስር፣ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅና በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችል፤ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም በገጠር መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት የሚያግዝ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 18004
ኢዜአ
ፖለቲካ
የፀጥታ ኃይሉ አቅም እየተጠናከረ በመምጣቱ የሠላም ሁኔታው መሻሻል አሳይቷል
Apr 25, 2024 60
  አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ የባህርዳር ጎንደር ኮማንድ ፖስት የደቡብ ጎንደር ዞን የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኃይሉ አቅም እየተጠናከረ በመምጣቱ የሠላም ሁኔታው መሻሻል ማሳየቱ ገለጸ። በባህርዳር ጎንደር ኮማንድ ፖስት ደቡብ ጎንደር ዞን የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታውን አስመልክቶ ከከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ ኃይል ጋር ውይይት አድርጓል። አጠቃላይ የከተማውን የፀጥታ ሁኔታና የተልዕኮ አፈፃፀም እንዲሁም የተልዕኮ አፈፃፀሙ እያስገኘ ባለው ውጤትና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ነው ውይይት ያካሄደው።   በአካባቢው ተልዕኮ በመፈፀም ላይ የሚገኘው ክፍለጦር አዛዥና የኮማንድ ፖስቱ አስተባባሪ ኮሎኔል ሻምበል አስማማው እንደገለጹት ኮማንድ ፖስቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ የፀጥታ ኃይሎችን አቅም ማጠናከር፣ በራስ አቅም ግዳጅ መፈፀምና የቀጠናውን ሠላም ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የባህርዳር ጎንደር ኮማንድ ፖስት አስቀምጦት የነበረው የአፈፃፀም አቅጣጫ የተሻለ ነው ብለዋል። ኮሎኔል ሻምበል አስማማው የሠራዊቱን ምት መቋቋም ተስኖት የተበተነውን ፅንፈኛ የማደን ስራ በተጠናከረ መንገድ እየፈፀመ መሆኑን ጠቁመው የፀጥታ ኃይሉ ደግሞ አካባቢውን በሚገባ በራሱ አቅም መጠበቅና ሠላሙን ማጠናከር እንደሚገባው አሳስበዋል።   የደብረ ታቦር ከተማ ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን በበኩላቸው አሁናዊ የከተማ አስተዳደሩና የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል የታየበት መሆኑንና የፀጥታ ኃይሉ ራሱን ችሎ አካባቢውን በንቃት ለመጠበቅ የሚያደርገው ጥረትም አበረታች ነው ብለዋል። አቶ ደሴ መኮንን ኮማንድ ፖስቱ ያስቀመጠውን የአፈፃፀም አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ አቅማችንን የበለጠ ማጠናከር ይግባናል ብለዋል። በዚህም የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል ሁሉም የፀጥታ ኃይል ኃላፊነቱን በቁርጠኝነት ሊወጣ እንደሚገባውም መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የከተማው የኮማንድ ፖስት አባል ሻለቃ ጭፍራው አሰፋ በበኩላቸው የከተማው ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ሠላም አስከባሪና የአድማ ብተና ኃይሉ ከሠራዊቱ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልጸው፤ የሠላም ሁኔታውም ከፍተኛ መሻሻልን እያሳየ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያወጣው መግለጫ የያዛቸው አንኳር ነጥቦች፦
Apr 25, 2024 66
ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያወጣው መግለጫ የያዛቸው አንኳር ነጥቦች፦ ሀገራዊ ምክክር ሂደትን በሚመለከት የኢትዮጵያ ችግር የአሁኑን አካሄድ በማስተካከል ብቻ አይፈታም፤ በታሪክ ውስጥ የወረስናቸውን ስብራቶች መጠገንም የግድ ይለናል፤ እነዚህን ስብራቶች ነባሩን ፖለቲካዊ ችግር በሀገራዊ ምክክር መፍታት፤ የቅርብ ዘመናችንን የፖለቲካ ችግር ደግሞ በሽግግር ፍትሕ እና በተሐድሶ ማረም፤ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንድ መንግሥት በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን ቢይዝም እንኳን ብቻውን ሊወስናቸው የማይገቡ፣ ሀገራዊ እና አካታች ምክክር የሚፈልጉ ጉዳዮች አሉ፤ ይሄንን በትውልድ መካከል አንዴ የሚገኝ ዕድል ሳናባክን፤ እያቃናንና እየደገፍን፣ ለኢትዮጵያ ነባር ችግሮች መፍትሔ አዋላጅ እንዲሆን፣ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባናል፤ ዕድሎችን በሰበብ አስባቡ እያባከንን፣ ራሳችንን በችግር አዙሪት የማክረም አካሄድ ማብቃት አለበት። የሽግግር ፍትሕ ሂደትን በሚመለከት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በደል፣ ግፍ እና መሠረታዊ የመብት ጥሰቶች ተከሥተዋል የቁርሾ እና የቂም በቀል አዙሪት፣ የተበዳይነት እና የብሶት ትርክት በሀገራችን ዋነኛው የፖለቲካ ማጠንጠኛ የሆነበት አንዱ ምክንያትም ይሄው ነው፤ ይሄንን የበዳይ ተበዳይ አዙሪት ለመስበር የሽግግር ፍትሕ አንዱ ተመራጭ ስልት ነው፤ ስለዚህም የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት የፖሊሲ ማሕቀፍ ጸድቋል፤ የፖሊሲው ዓላማ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላምን፣ ዕርቅን፣ የሕግ የበላይነትን፣ ፍትሕን እና ዴሞክራሲን ማረጋገጥ ነው፤ በየክልሎች የሚታዩ ታጣቂዎችን በሚመለከት በሀገራችን ከመንግሥት ውጭ የሚኖር የታጠቀን ኃይል ሕገ መንግሥታችን አይፈቅድም፤ የመንግሥትም አንዱ መብት በብቸኝነት ኃይልን መጠቀም ነው፤ ነገር ግን በሀገራችን በወረስነው የፖለቲካ ስብራት የተነሣ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋል፤ የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውንም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በመሳተፍ መፍታት ይችላሉ፤ ለዚህ የሚሆን የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል፤ ዓላማውም መሣሪያ ማስፈታት፣ የትጥቅ ቡድኖችን ሰላማዊ ማድረግና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ናቸው፤ ይሄንን የተሐድሶ ሥራ በማሳካት ፖለቲካችን ከግንባር ወደ ጠረጴዛ፣ ከጫካ ወደ አዳራሽ እንዲመለስ ማድረግ አለብን፤ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ፦ የፕሪቶሪያው ስምምነት ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ የመቋጨት ባህል አምጥቷል፤ ስምምነቱም ለትውልድ የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክትን ከቂም ጋር ላለማውረስ የተደረገ በሳልና ቆራጥ ውሳኔ ነው፤ በአማራ፣ በአፋርና በትግራይ ክልሎች የመልሶ ግንባታ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ተጀምረዋል፤ ሰብአዊ ድጋፍም ያለመሰናከል ወደ ትግራይ መድረስ የሚችልበት ዐውድ ተፈጥሯል፤ በተለይ በስምምነቱ መሠረት የሕወሐት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው፤ የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት፤ በጦርነቱ የተፈናቀሉትን ለመመለስና ለማቋቋም የተጀመረው ሥራ እልባት ማግኘት አለበት፤ የሰላም የትርፍ ድርሻው ታላቅ በመሆኑ መንግሥት ከሚጠበቅበትም አልፎ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ፦
Apr 25, 2024 67
የወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ለኢንደስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ፤ በወጪ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በማበረታታት ረገድ የታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ እና የዘርፉን ተዋንያን የሚያበረታታ ሥርዓት በመዘርጋት ተወዳዳሪነት ማላቅ ይቻል ዘንድ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ተደርጓል። የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ ደንብን በተመለከተ፦ ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፤ የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያወጣውን ወጪ በከፊል መሸፈን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ የጤና ፖሊሲን በተመለከተ በስራ ላይ ያለው የጤና ፖሊሲ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት ቆይቷል፤ ፖሊሲው በጸደቀበት ወቅት ከነበረው ጠቅላላ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ፤ እየተከሰቱ ያሉ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መበራከት፤ በሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና ዙሪያ የሚከሰቱ ለውጦች፤ ዘርፉ ጥራት እና ፍትሀዊነት ያለው አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ችግሮች የሚስተዋሉበት በመሆኑ፤ እንዲሁም ከሀገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር የሚጣጣም የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ፖሊሲው ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ በግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲን በተመለከተ በስራ ላይ የነበረው የግብርና ፖሊሲ ከአዳጊ የምርትና ምርታማነት ፍላጎት ጋር አብሮ መጓዝ የቻለ ባለመሆኑ፤ ለግብርናው ዘርፍ እድገት ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን መለወጥ አስፈላጊ በመሆኑ እንዲሁም ሀገራችን ከምትከተለው ብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ስርአት ጋር የሚጣጣም ፖሊሲ ማስፈለጉ ታምኖበታል፤ ስለሆነም የግብርና ዘርፍን ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር የበለጠ የሚያስተሳስር፣ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅና በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችል፤ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም በገጠር መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት የሚያግዝ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር ይጀምራል 
Apr 25, 2024 67
ሀዋሳ፣ሚያዚያ 17/2016 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተሳታፊዎች መረጣ ባካሄደባቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር እንደሚጀምር የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታወቁ። ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንዳሉት ኮሚሽኑ እስካሁን ባለው ሂደት መሠረታዊና የህዝብ ተሳትፎ ባማከለ መልኩ የተሳታፊዎች ልየታና መረጣ በ10 ክልሎችና በሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች አገባዷል። በነዚህ አካባቢዎች ያገኛቸውን ልምድ በመጠቀም በአማራና በትግራይ ክልሎች የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች ልየታና መረጣ ቀሪ ስራዎች እንደሚከናወኑም አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት የተሳታፊዎች መረጣ ባካሄደባቸው ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ውሰጥ ሰሞኑን አጀንዳ የማሰባሰብ ተግባር እንደሚጀምር ጠቁመዋል። "ለዚህም በየወረዳው የተመረጡ ተወካዮች ወደ ክልላቸው ይመጡና በክልሉ ከሚገኙ 20 ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የክልላቸውን፣የአካባቢያቸውን ሀገራዊ የሚባሉ አጀንዳዎች ይሰጣሉ "ብለዋል።   ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የንግዱ ማህበረሰብና መምህራንን ጨምሮ የሁሉም ህብረተሰብ ተወካዮች ለየብቻቸው ከተወያዩ በኋላ በጋራ ያመጡትን አጀንዳ አደራጅተው ወደ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንደሚልኩ አስረድተዋል። "እነዚህ የተላኩ አጀንዳዎች በሙሉ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ታዛቢዎች ባሉበት ግልፅ በሆነ መስፈርት ከተመረጡ በኋላ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አጀንዳዎች ከተለዩ በኋላ ሀገራዊ ምክክር ይካሄዳል" ብለዋል። ይህንን ለማድረግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የቀረው ጊዜ 10 ወር መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን አስታውቀዋል። "በነዚህ ጊዜያት ውስጥ የጎላ እንቅፋት እስካላጋጠመው ድረስ ቢያንስ የሀገራዊ ምክክር ጉባዔውን አስጀምሮና የተወሰኑ አጀንዳዎችን ወደ ማግባባት በማምጣት ማጠናቀቅ እንደሚችል ሙሉ እምነት አለን" ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል። "ኮሚሽኑ የህዝብ ወገንተኛ መሆኑን በስራችን ለማሳየት እየተጋን እንገኛለን" ሲሉም ተናግረዋል። የሀገራችን ህዝቦች ለብዙ ሺህ ዘመናት ተዋደው፣ተጋብተው፣ተጋምደውና ተስማምተው የኖሩ በመሆናቸው በሀገራዊ ምክክሩ መግባባት ላይ መድረስ እንደማያዳግታቸው ያላቸውን እምነት አስታውቀዋል። በሀገራዊ ምክክሩ የኦሮሚያ ክልል የተሳታፊዎች መረጣና ልየታ ማጠቃለያ መርሀ ግብር በሻሸመኔ ከተማ መካሄዱን ይታወሳል።    
ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከመንግስት ባለፈ የሁሉም ዜጎችና ተቋማት ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት 
Apr 25, 2024 63
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከመንግስት ባለፈ የሁሉም ዜጎችና ተቋማት ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ኢትዮጵያ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የጸረ ሙስና ስምምነቶችን በመቀበል እና ሀገራዊ የህግ ማዕቀፎችን በማውጣት ለተግባራዊነቱ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። በተለይም ከለውጡ በኋላ የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1236/2013 እንደገና እንዲቋቋም ተደርጓል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደ ሀገር ስር የሰደደውን ሌብነት ለመከላከል ሰባት አባላት ያሉት ብሔራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ እንዲቋቋም ማድረጋቸው ይታወቃል። የተቋቋመው ብሔራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎችን በመቀበል እንደ ሀገር ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል የህዝብና መንግስት ሀብት ከምዝበራ ማዳን እንደተቻለ በሪፖርቱ አረጋግጧል። በፌደራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስቸኳይ የሙስና መከላከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኮሚሽኑ የሥነ ምግባር አቅም ግንባታ፣ የሙስና ቅድመ መከላከል እና ህግ ማስከበር ስራዎችን እያከናወነ ነው። ከፌዴራል፣ ከክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ጋር በመቀናጀት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። የኃይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራትና የትምህርት ተቋማትን አስተባብሮ የሥነ ምግባር ትምህርት በመስጠት የህብረተሰቡን ሙስናና ብልሹ አሰራር የማጋለጥ ባህል ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። ኮሚሽኑ ጥናት በማካሄድና የሃብት ምዝገባ በማከናወን ሙስናን ቀድሞ ከመከላከል ባለፈ፤ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በዲጂታል እና በተለያዩ አማራጮች 65 የሙስና ወንጀል ጥቆማዎችን በመቀበል ለፍትህ አካላት ቀርቦ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም እንደ ሀገር 373 የሙስና ቅድመ መከላከል ሥራዎች በማከናወን ከአንድ ነጥብ 384 ቢሊዬን ብር በላይ የህዝብና መንግስት ሃብት እንዲሁም ከ25 ሚሊዬን ካሬ ሜትር በላይ የሆነ የከተማ እና ገጠር መሬት ከምዝበራ ማዳን መቻሉን አስታወሰዋል። በ25 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ተጠሪ ተቋማት የሙስና ስጋት ያለባቸው ዘርፎችን አሰራር በማጥናት በውጤቱ መሰረት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑ በሀብት ምዝገባ፣ በእድሳትና አገልግሎት በማቋረጥ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም መሰረት እስካሁን የዘጠኝ ሺህ 992 የፌደራል የሥራ ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ሀብት ምዝገባ ማከናወኑን ተናግረዋል። መንግስት ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ጉዳዩ የሁሉንም ግለሰቦችና ተቋማት ርብርብ የሚፈልግ መሆኑን ነው የገለጹት።        
ሰላምና ልማትን የማጠናከር ስራ በትኩረት ይከናወናል  -ከንቲባ ከድር ጁሃር
Apr 25, 2024 75
ድሬዳዋ ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፡- የሰላምና የልማት ውጤታማ ተግባራትን የማጠናከር ስራ በትኩረት ይከናወናል ሲሉ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር አስታወቁ። ለድሬዳዋ አስተዳደር የፖሊስ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው። በስልጠናው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ ከድር ጁሃር እንደተናገሩት አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በአዲስ ለውጥና አደረጃጀት የተገነባው ፖሊስ በአርአያነት የሚጠቀሱ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ህዝባዊነቱን አፅንቶ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ባከናወናቸው ተግባራት በድሬዳዋ አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ መኖሩን ጠቅሰዋል። ሰላምና ፀጥታው በገጠርና በከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስችሏል ሲሉም አክለዋል። ስራዎቹን ይበልጥ ለማሳደግ የፖሊስ አመራሮችን አቅም የመገንባት ስራም በትኩረት ይተገበራል ብለዋል።   የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው ፖሊስ በዘመናዊ አሠራርና በቴክኖሎጂ ተደግፎ የነዋሪዎችን ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየተጋ መሆኑን ገልጸዋል። “ለውጡን ተከትሎ ባከናወናቸው ተግባራት የተገኙ ፍሬዎች በአገር አቀፍ ደረጃ በተሞክሮነት ተቀምረው እየተስፋፉ ናቸው” ብለዋል። እንደ ኮሚሽነር አለሙ ገለፃ ስራዎቹን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚሰጠው ስልጠና በቁርጠኝነት ይተገበራል። ለሁለት ቀናት በሚሰጠው የሙያ ስነምግባርና የመረጃ መር አገልገሎት የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ የአስተዳደሩ የፖሊስ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።  

ማህበራዊ
በአገልግሎት አሰጣጥ  ሂደት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍና  የተጠያቂነት አሰራርን መዘርጋቱን  የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ 
Apr 25, 2024 50
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍና የተጠያቂነት አሰራርን መዘርጋቱን የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ ። ኤጄንሲው የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጽም ሪፖርቱን ከተጠሪ ተቋማት ጋር ገምግሟል። የኤጀንሲው የዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹምዬ እንዳሉት፤ ኤጀንሲው በሁሉም ጽህፈት ቤቶቹ የወሳኝ ኩነትና የነዋሪነት ምዝገባ ተልዕኮውን ወቅቱን ጠብቆ በማከናወን አበረታች ውጤት አስመዝግቧል። ከጤና፣ ከሃይማኖት፣ ከትምህርት፣ ከዕድሮች እና ከሌሎች ተቋማት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ ስራዎችም ለኤጀንሲው ወቅታዊ ምዝገባ ስርዓት መሳለጥ እንዳገዙ አብራርተዋል። በወቅታዊ ምዝገባ ረገድ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የዕቅዱን 91 በመቶ በላይ በማሳካት ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ከ24 በመቶ በላይ እምርታ ማምጣቱን ጠቁመዋል። በነዋሪዎች መታወቂያ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድም ከ93 በመቶ በላይ ዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ማድረጉን ጠቅሰው፤ ጤናና መሰል ችግሮች ላሉባቸው ነዋሪዎች የቤት ለቤት አገልግሎት መስጠቱን አንስተዋል። ኤጀንሲው ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት ከአንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዬን በላይ ዜጎች አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉንም ተናግረዋል። በአገልግሎት ሂደት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የተጠያቂነት አሰራር ዘርግቶ ገቢራዊ ማድረጉን ጠቅሰዋል።   የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው ኤጀንሲው ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር አገልግሎቱን ለማሻሻል እየሰራ ነው። በሪፎርሙም የተቋሙን አገልግሎቶች ከዕጅ ንኪኪ ነጻ በሆነ ቴክኖሎጂ ስርዓት በማስገባት ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ በሁሉም ዘርፎች አበረታች ስኬቶች እንደተመዘገቡ አንስተዋል። ያም ሆኖ ኤጀንሲው ተገልጋዮችን በሚፈለገው ልክ ማርካት ባለመቻሉ የሪፎርም አሰራር ስርዓቶች ትግበራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በተለይም ለኤጀንሲው ቁልፍ የመልካም አስተዳደር ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ተጠያቂነትን መሰረት ያደረጉ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው ያነሱት።          
በስነ-ተዋልዶ የጤና ችግሮች ምክንያት በአፍላ ወጣቶች ላይ የሚከሰተውን ሞትና ጉዳት መቀነስ ትኩረት ተሰጥቷል
Apr 25, 2024 57
ጂንካ፤ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፦ በስነ-ተዋልዶ የጤና ችግሮች ምክንያት በአፍላ ወጣቶች ላይ የሚከሰተውን ሞትና ጉዳት የመቀነስ ተግባር ትኩረት መሰጠቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌና ጋምቤላ ክልሎች በቀጣይ ሶስት አመታት የሚተገበር በአፍላ ወጣቶችና በወጣቶች የጤና አገልግሎት ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት የማብሰሪያ ፕሮግራም ዛሬ በጂንካ ከተማ አካሂዷል። በአፍላ ወጣቶችና በወጣቶች የጤና አገልግሎት ላይ ያተኮረ ፕሮጀክቱ በፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ይፋ የተደረገ ሲሆን ለትግበራ ከ192 ሚሊዮን ብር በጀት በላይ መመደቡ ታውቋል። በጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የፕሮጀክት ግራንት አስተዳደር አማካሪ አቶ ውቤ ደምሴ እንደገለጹት የአፍላ ወጣቶች ጤና ጉዳይ በልዩ ትኩረት የሚሰራ ነው።   የጤና ሚኒስቴር የወጣቶችንና የአፍላ ወጣቶችን ጤና ለማስጠበቅና ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል። በአምስት አመቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ እንዲሁም በሶስት አመቱ የኢንቨስትመንት ፕላን ውስጥ በማካተት እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል። ለዚህም የጤና አገልግሎቶች ማሻሻልና ምቹ ማድረግ የሚጠበቅ ሲሆን በ2025 ደግሞ 80 በመቶ የሚሆነው የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች አቅም በማጎልበት የአፍላ ወጣቶች የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃውን የጠበቀና ምቹ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም አሁን ላይ 13 በመቶ ላይ ያለውን አላስፈላጊ የአፍላ ወጣቶች እርግዝና እኤአ በ2030 ወደ 6 ነጥብ 5 በመቶ ለማውረድ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ ወጣቶች ስለ ስነ-ተዋልዶና የጤና ችግሮች በቂ መረጃ የሚያገኙበት ''የኔ ታብ''የተሰኘ የበይነ-መረብ መተግበሪያ አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን አንስተዋል። ዛሬ የተበሰረው ፕሮጀክትም እንደ ሀገር የአፍላ ወጣቶችና የወጣቶችን ጤና ለማጎልበትና ከውስብስብ ችግሮች ለመታደግ መንግስት ለሚሰራቸው ስራዎች አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል። በስነ- ተዋልዶና በተያያዥ ችግሮች በአፍላ ወጣቶች ላይ የሚከሰተውን ሞት ለመታደግ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።   የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነብዩ ቤዛ ፤ ወጣቶች በአዕምሮ፣ በአካልና በማህበራዊ እድገት የሚያሳዩት ለውጥ ለሀገራዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። "ወጣቶችን ለውስብስብ የጤና ችግሮች እያጋለጡ ያሉ አደንፃዥ ዕፆች፣ በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የሚፈጠሩ ያልተፈለገ እርግዝና፣ አባላዘር፣ኤች አይ ቪ አዲስና ለመሰል ተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ በቅንጅት ይሰራል" ብለዋል ። ዛሬ የተጀመረው ፕሮጀክትም የክልሉ ጤና ቢሮ በወጣቶችና በአፍላ ወጣቶች ስነ-ተዋልዶና ጤና ላይ ለሚሰራቸው የጤና ልማት ስራዎች አጋዥ መሆኑን አስታውቀዋል።      
በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ጥራታቸውን ያልጠበቁ መድሀኒቶች ተወግደዋል
Apr 25, 2024 43
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ጥራታቸውን ያልጠበቁ መድሀኒቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ እንዲሁም እንዲወገዱ ማድረጉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ። የባለስልጣኑ የመድሃኒት ዘርፍ ምክትል ዳሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለስልጣኑ የመድሃኒት ጥራት፣ ደህንነትና ፈዋሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ዕቅዶች አውጥቶ እየሰራ ነው። በዚህም ከመግባቢያና መውጫ ኬላዎች ጀምሮ በመድሃኒት ዘርፍ አምራቾች፣ አስመጪና ላኪዎች ላይ ጠንካራ የቁጥጥር እና ክትትል ስራዎችን ማከናወን መቻሉን አንስተዋል። ባለስልጣኑ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ባደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ 61 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር የሚገመቱ መድሃኒቶችን ጥራትና ፈዋሽነት በማረጋገጥ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረጉን ጠቅሰዋል። ነገር ግን 132 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መድሀኒቶች ጥራት፣ ደህንነትና ፈዋሽነታቸው ባለመረጋገጡ ወደ ሀገር እንዳይገቡ እና እንዲወገዱ መደረጋቸውን ተናግረዋል። በዘጠኝ ወራት ውስጥ ለ291 የአገር ውስጥ አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት ፍቃድ መሰጠቱን ጠቁመዋል። ፈቃድ የተሰጣቸው መድሃኒት አምራቾች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊትም ሆነ በኋላ ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሻ እንደሚደረግ ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ 773 ናሙና ተወስዶ ፍተሻ ስለመደረጉ ለአብነት ጠቅሰዋል።        
በወገራ ወረዳ በእንቃሽ እና አካባቢው በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ
Apr 25, 2024 54
ባሕር ዳር፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ በእንቃሽ እና አካባቢው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 ታጣቂዎች የሰላም አማራጩን ተቀብለው ወደ ሕዝብ እና መንግሥት ተመልሰዋል። የሰላም አማራጩን ተቀብለው የተቀላቀሉ ታጣቂዎችም ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ መንግሥት ላደረገላቸው ይቅርታ አመሥግነው በቀጣይ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ተመልሰው የአካባቢያቸውን ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ እንደሚሠሩም ተናግረዋል።   በወረዳው ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሠራ እንደሚገኝም የወገራ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ይናገር ወረታው ተናግረዋል። ዋና አሥተዳዳሪው ፀረ ሰላም እና ፀረ ልማት አጀንዳ በማራገብ ኅብረተሰቡን ለእኩይ ድርጊት የሚያነሳሱ ግለሰቦችን መታገል አስፈላጊ መሆኑን መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል። ለዚህ ደግሞ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር እጅ እና ጓንት ሆኖ በመሥራት ለዘላቂ ሰላም መትጋት እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት። የሚፈጠሩ ችግሮችን በሠለጠነ መንገድ በውይይት ለመፍታት መሞከር ተገቢ መሆኑን ኀላፊው አንስተዋል፡፡ ሰላምን ማረጋገጥ የሁሉም ድርሻ በመሆኑ ሁሉም የሚጠበቅበትን ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባው ዋና አሥተዳዳሪው መናገራቸውን የዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ መረጃ ያመላክታል።
ኢኮኖሚ
በአፍሪካ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በይፋ ስራ ጀመረ
Apr 25, 2024 45
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- በአፍሪካ የስራ ፈጠራና ስታርትአፕን የሚደግፈው ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ በይፋ ስራ ጀመረ። ኢኒሼቲቩ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አነሳሽነት በአፍሪካ በተለይ ኢንቨስትመንትን፣ ስራ ፈጠራንና ስታርትአፕን ለመደገፍ የሚሰራ ነው። ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭ በአህጉሪቱ ግዙፍ የፓንአፍሪካ ስታርትአፕ ምህዳር መፍጠርን ያለመ ነው።   በኢንሼቲቩ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ታዬ፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ባሳለፍነው ጥር ወር በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በመሆን ቲምቡክቱ ኢኒሼቲቭን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ኢኒሼቲቩ 1 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በማሰባሰብ የ100 ሚሊዮን አፍሪካውያንን ህይወት ለማሻሻልና ለ10 ሚሊዮን ሰዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ አስቀምጧል።
በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እየተሸጋገረች መሆኗን ማረጋገጫ ናቸው- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ
Apr 25, 2024 48
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እየተሸጋገረች እንደምትገኝ ማረጋገጫ መሆናቸውን የከተማዋ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ፋይዛ መሃመድ ገለጹ። የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና ጥራት እንዲከናወኑ ምክር ቤቱ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እና በልማቱ የተነሱ ነዋሪዎች በተዘጋጁላቸው ምትክ መኖሪያ መንደሮች ተገኝተው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ ቡዜና አልቃድርን ጨምሮ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ አባላት እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ፋይዛ መሃመድ እንዳሉት፤ የምክር ቤቱ አባላት የህዝብ ወኪል በመሆናቸው የመዲናዋ የልማት ስራዎችን የመከታተልና ጉድለቶችን የመገምገም ግዴታ አለባቸው። በዛሬው ዕለትም የኮሪደር ልማት ስራዎች እና በኮሪደር ልማቱ ተነስተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ በሃና ፉሪ እና ጉራራ ምትክ የጋራ መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ነዋሪዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።   ምክትል አፈ ጉባኤዋ አክለውም የተጀመረው የልማት ስራ በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ምክር ቤቱ የክትትል እና ድጋፍ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ለኑሮ ምቹ፣ ውብና ጽዱ አደርጎ የማዘመን እንዲሁም ከዓለም ከተሞች ተወዳዳሪና ተመራጭ ከተማ እንድትሆን የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እየተራመደች መሆኗን ሁነኛ ማረጋገጫ እንደሆነም ምክትል አፈ ጉባዔዋ አብራርተዋል። በኮሪደር ልማት ሳቢያ ተነስተው በአጭር ጊዜ ምትክ የጋራ መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ነዋሪዎች በልዩ ትኩረት የመሰረተ ልማት እና ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲሟሉላቸው መደረጉን አረጋግጠናል ነው ያሉት።      
ኢንስቲትዩቱ በአማራ ክልል የሰብል ጉዳት ላጋጠማቸው አርሶ አደሮች 39 ሚሊዮን ብር  የሰብል መድን ዋስትና ሰጠ
Apr 25, 2024 40
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ሰብላቸው በበሽታ ለተጎዳባቸው አርሶ አደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድን ዋስትና ሰጠ። ኢንስቲትዩቱ ለአርሶ አደሮች የሰብል መድን ዋስትና የሰጠው ከዓለም ምግብ ፕሮግራምና ፑል አድቫይዘርስ በፈጠረው ጥምረት በተቋቋመ የሰብል መድን በኩል መሆኑ ተገልጿል። የሰብል መድን ዋስትናው የስንዴ ሰብልን በሚያጠቃው ዋግ ሰብላቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን በአማራ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም ያለመ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የስራ አመራር ስራ አሰፈፃሚ ዳዊት ፊሊጶስ የሰብል መድን ዋስትና ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት የሰብል ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች የካሳ ክፍያ በመክፈል እያቋቋመ መሆኑን ተናግረዋል። በዛሬው እለት በአማራ ክልል በሁለት ወረዳዎች ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድን ዋስትና መሰጠቱን ገልጸዋል። በመድን ዋስትናው ከ50 በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የሰብል መድን መክፈሉን ገልጸው፥ በቀጣይ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በሌሎችም ክልሎች እንደሚሰፋ ጠቁመዋል። አርሶ አደሩ የሰብል መድን አባል በመሆንና ክፍያ በመክፈል ጉዳት ሲደርስበት የዋስትና ክፍያ እንዲከፈለው በማድረግ መልሶ እንዲቋቋም የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። ባለፈው ዓመት በድርቅ፣ በከባድ ዝናብ እና በተባይ በሽታ ሰብላቸው ለተጎዳባቸው ለ122 ሺህ አርሶ አደሮች የሰብል መድን ዋስትና በመስጠት ማቋቋሙን ተናግረዋል። የሰብል መድን ዋስትና በ2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት፣ በዓለም ምግብ ፕሮግራምና በፑላ አድቫይዘርስ ትብብር በግብርናው ዘርፍ በአየር ንብረት ለውጥና በሌሎች ችግሮች የሚከሰትን አደጋ መፍትሔ ለመስጠት የተመሰረተ ድርጅት ነው።  
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል  የፋይናንስ ዘርፉን ከብክነት የጸዳ ለማድረግ እየተሰራ ነው
Apr 25, 2024 46
ሚዛን አማን፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የልማት ዕቅዶች ጋር ሊጣጣም የሚችል የበጀት አመዳደብና አጠቃቀም ሥርዓት በመከተል የፋይናንስ ዘርፉን ከብክነት የጸዳ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ገለጸ። ቢሮው የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር የሕግ ማዕቀፎችና የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ነው። የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ በመድረኩ እንዳሉት፤ በክልሉ የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር የሕግ ማዕቀፎች ላይ የአመራር ግንዛቤ ክፍተት ይስተዋላል። ለዚህም በየመዋቅሩ የሚገኙ የኦዲት ግኝት ውጤቶች ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል። ችግሩን ለማቃለል ተከታታይነት ያለው ስልጠና ነክ የምክክር መድረክ ለአመራር አባላት ተዘጋጅቶ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። እየተካሄደ ባለው መድረክም በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የሕግ ማዕቀፎች፣ በግዥ መመሪያና በመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ሥርዓት ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ውይይት ይደረጋል ነው ያሉት። የፋይናንስ ሥራዎችን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ እንዲቻል ቢሮው አስፈላጊ የኮምፒውተር እና ተያያዥ ግብዓቶችን ለታችኛው መዋቅር የማሟላት ሥራ ላይ ማተኮሩን ጠቁመዋል። የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓትን የተከተለ የበጀት አጠቃቀም ሂደት ተግባራዊ እንዲደረግ አመራሩ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት ተናግረዋል። በተለይ ከልማት ዕቅዶቻችን ጋር ሊጣጣም የሚችል የበጀት አመዳደብና አጠቃቀምን ሥርዓት በመከተል የሀብት ብክነትን ማስቀረት ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ አመላክተዋል።   የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው፤ በክልሉ እየተስተዋሉ ያሉ የፋይናንስ አጠቃቀም ግድፈቶችን ደረጃ በደረጃ ለማስተካከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ፋይናንስን በእውቀትና በክህሎት በመምራት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባ አመልክተው፤ የአቅም ውስንነቶችን ለመሙላት በተለያዩ ጊዜያት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ይሰጣሉ ብለዋል። ውስን በጀት ሚዛኑን ጠብቆ ለሕዝብ ልማት እንዲውል ለማድረግ በአግባቡ መረጃ ማደራጀት ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል። ለሁለት ቀናት በሚቆይ የውይይት መድረክ የክልል ከፍተኛ አመራር አባላትና የዞን ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።    
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮጵያን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ  ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል-- የፌደራል  ተቋማት የሱፐርቪዥን ቡድን 
Apr 25, 2024 50
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ወደተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የፌደራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የበጀት ዓመቱን የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሲገመግሙ የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርግ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። በዚህም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን አማካሪና የሱፐርቪዥን ቡድኑ አስተባባሪ ዶክተር ሰለሞን በላይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በሎጅስቲክስ፣ በትራንስፖርት፣ በታዳሽ ኃይል እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች ናቸው። በአንጻሩ እንደ ሀገር ትኩረት የሚፈልጉ የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያ የሚጠይቁ የመንግስትን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መኖራቸውን አመላክተዋል። ለአብነትም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እና የማበረታቻ ስርዓት ሊታዩ የሚገባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል። የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፉን ለማሳለጥ እየተከናወኑ ያሉ የቴክኖሎጂ አሰራሮች እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ በርኦ ሀሰን ዲጂታላይዜሽን ለዘርፉ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፥ እስካሁን በተተገበሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከዘርፉ የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ላይ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ለሱፐርቪዥን ቡድኑ ገልጸዋል።   ዘርፉን ለማሳደግ ሁሉም አይነት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ናቸው። በዚህም የሎጂስቲክ ዘርፉን አፈጻጸም ማሳደግ መቻሉን እና ከዚህ የበለጠ ውጤት እንዲመዘገብ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።    
በስታርትአፕ ዐውደ ርዕይ የቀረቡ የፈጠራ ሀሳቦችና ቴክኖሎጂዎች ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ተስፋ ሰጭ ናቸው
Apr 25, 2024 53
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- በስታርትአፕ ዐውደ ርዕይ የቀረቡ የፈጠራ ሀሳቦችና ቴክኖሎጂዎች ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ተስፋ ሰጭ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽመልስ እሸቱ ገለጹ። ከመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተው የስታርትአፕ ኢትዮጵያ ዐውደ ርዕይ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የተቋማት ኃላፊዎች እየተጎበኘ ነው። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የዐውደ ርዕዩ ጎብኝዎች እንዳሉት በስታርትአፖች የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች የኢትዮጵያን መፃዒ ዕድል ብሩህ የሚያደርጉ ናቸው። የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሽመልስ እሸቱ በዐውደ ርዕዩ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዕድገት እንዲመዘገብ የሚያስችሉ ፈጠራዎችን መመልከታቸውን። የስታርትአፕ የፈጠራ ስራዎች በአግባቡ ከታገዙ የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ ኮርፖሬሽኑ ቴክኖሎጂዎች ገቢራዊ እንዲሆኑ የራሱን ሚና እንደሚወጣ አረጋግጠዋል። ሀገራዊ ልማቱ ዘመኑን በዋጁ ቴክኖሎጂዎች መደገፍ እንደሚገባ ገልጸው፤ በዐውደ ርዕዩ የቀረቡ የፈጠራ ስራዎችም የተቋማትን ምርትና አገልግሎት የሚያዘምኑና የሚያቀላጥፉ እንደሆኑ ጠቁመዋል። ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጡት አቶ ተስፋ አበባና በአዲስ አበባ የልደታ ማኑፋከቸሪንግ ኮሌጅ ተማሪዋ ማህሌት ገብሬ እንዳሉት የስታርትአፕ ቴክኖሎጂዎች ሀገርን ወደ ተሻለ ልማት ያሸጋግራሉ። ስታርትአፕን መደገፍ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ መጻኢ ዕድል ካለው ቁልፍ ፋይዳ አኳያ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው፤ ለዚህም የፈጠራ ክህሎት ያላቸውን ወጣቶች ይበልጥ ማበረታታት ይገባል ነው ያሉት። ለዕይታ የቀረቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የነገዋ ኢትዮጵያን ለማዘመን ብሩህ ተሰፋ እንደሆኑ ጠቁመዋል። የስታርትአፕ ዐውደ ርዕዩ እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ይቀጥላል። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢነርጂ፣ በኢንዱስትሪ፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ 500 የሚጠጉ ስታርትአፖች እየተሳተፉ ነው።    
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ታዳጊዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው -  ኢንስቲትዩቱ
Apr 25, 2024 73
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ታዳጊዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ገለጸ። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመጪው ክረምት የስልጠና መርሐ ግብር የሚሳተፉ ተማሪዎችን ምዝገባ ጀምሯል። በ3ኛ ዙር ስልጠና የሚሳተፉት የመጀመሪያና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ እና በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን እንደሚኖርባቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና፤ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ ዕድገት መለኪያ የሆነ ዘርፍ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያም ግንባር ቀደም አህጉራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተቋም በመገንባት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመስኩ የፈጠራ ዝንባሌ እና ክህሎት ላላቸው ታዳጊዎች የሚሰጠው ስልጠናም በዘርፈ ብዙ መስኮች ተወዳዳሪ ሀገር መፍጠር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በመጪው ክረምት ታዳጊ ተማሪዎችን በመቀበል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ክህሎታቸውን በማበልጸግ የተሻለ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። ስልጠናውም የኢትዮጵያን ከፍታ በማስቀጠል ፈጠራና ክህሎትን በማበረታታት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ታዳጊዎችን ማፍራት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ መሆኑን አስረድተዋል።   በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የምርምርና ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር)፥ በክረምት ወራት የሚሰጠው ስልጠና እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በቀጣይም በኢንስቲትዩቱ ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ በክልሎች ለማስፋት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።   የቴክኖሎጂ አማካሪው ሰለሞን ሙሉጌታ፥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የሚሰጥ ስልጠና ታዳጊዎች የዓለምን አዝማሚያና ዝንባሌ በቅጡ እንዲረዱ የሚያስችል ነው ብለዋል። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዕውቀትንም ለግብርና፣ ለመንግስት አገልግሎት፣ ለጤና እና ሌሎች ተግባራት እንዲያውሉት ማስተማር እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል። በመጪው ክረምት ለሁለት ተከታታይ ወራት በሚሰጠው ስልጠና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ቀናት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል። ከሀምሌ 1 እስከ ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም በሚቆየው ስልጠና ተማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት እውቀትና ክህሎት የሚያገኙበት የንድፈ ሀሳብና የተግባር ትምህርት ይሰጣቸዋል። ስልጠናው ከሚያተኩርባቸው መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ሮቦቲክስ፣ ፕሮግራሚንግ፣ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም ይገኙበታል።  
በአዳማ እና ቢሾፍቱ የተጀመረውን የስማርት ከተማ ግንባታ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ማስፋፋት ይገባል- የፌደራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን 
Apr 25, 2024 78
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በአዳማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የተጀመረውን የስማርት ከተማ ግንባታ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ማስፋፋት እንዳለበት የፌደራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የበጀት ዓመቱን የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሲገመግሙ የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርግ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። በዚህም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የስማርት ከተማ ግንባታ ሂደት ያለበትን ደረጃ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ በአዳማ ከተማ እና በቢሾፍቱ ከተማ በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርጓል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን በዚሁ ወቅት፥ መንግስት በ10 ዓመትና በመካከለኛ ዘመን ዕቅዱ ለስማርት ከተማ ግንባታ ትኩረት መስጠቱን ገልጸዋል። የስማርት ከተማ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ለክልሎች እና ከተሞች ተደጋጋሚ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስልጠና በመስጠት በ2015 ዓ.ም አዳማ ከተማን እንደ ሞዴል በመውሰድ ወደ ተግባር መገባቱን አስረድተዋል። ከስማርት ከተማ ግንባታ ምሰሶዎች ውስጥ ለ”ስማርት አስተዳደር” ቅድሚያ በመስጠት እየተሰራ ነው ብለዋል። ክልሎችም ከተሞቻቸውን ስማርት ለማድረግ ተነሳሽነት እያሳዩ እንደሆነ ገልጸው በጅማ፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ፣ ሆሳዕና፣ ቡታጂራ፣ አርባምንጭ እና ወላይታ ሶዶ ጅምር ስራዎች እንዳሉ ተናግረዋል።   የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ በከተማዋ የተጀመረው የዲጂታላይዜሽን ስራ ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገር የመንግስትን የማስፈፀም አቅም እንዲጎለብትና ብልሹ አሰራሮች እንዲቀንሱ አድርጓል ነው ያሉት።   የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በከተማዋ የአገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታል ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል። የከተማ መሬት ይዞታን ወደ ካዳስተር በማስገባት የይዞታ ማረጋገጫ በኦንላይን መከናወኑን አንስተው፥ ይህም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን እንደሚያቀላጥፍ ጠቅሰዋል።   የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ አቶ ተገኔ ኃይሉ በአዳማና በቢሾፍቱ ከተሞች ያለው የቴክኖሎጂና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ የሚበረታታ ነው ብለዋል። በከተሞቹ የመሬት ይዞታዎችን ወደ ካዳስተር የማስገባት እና የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ምዝገባን በኦን ላይን መፈጸሙ የስማርት ከተማ ግንባታን የሚያግዝ እንደሆነ አንስተዋል። የከተማ አገልግሎቶችን በዲጂታል መስጠት መጀመራቸውም ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው እንደሆነ ገልጸዋል። በአዳማና ቢሾፍቱ ወንጀልን ለመከላከል እና የትራፊክ ፍሰትን ለመቆጣጠር የ"ስማርት ሴኪዩሪቲ" ቴክኖሎጂ ከተቋማት ጀምሮ በዋና ዋና ጎዳናዎች መተግበሩ የሚበረታታ ነው ብለዋል።   የሱፐርቪዥን ቡድኑ አባል አቶ አሸናፊ አበበ በበኩላቸው፥ ባለሙያዎችን በማብቃትና የዲጅታል መሰረተ ልማቶችን በማልማት አገልግሎቶችን ለማሳለጥ የጀመሩት ስራ መጠናከር አለበት ብለዋል። በሁለቱ ከተሞች ያለውን ውጤታማ ተሞክሮ በሌሎች ከተሞች ማስፋፋት እንደሚገባም ጠቁመዋል።        
ስፖርት
የ26ኛው የመላው ኦሮሚያ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በሸገር ሲቲ አስተዳደር አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
Apr 25, 2024 48
ጅማ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- በጅማ ከተማ ለ15 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ26ኛው የመላው ኦሮሚያ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በሸገር ሲቲ አስተዳደር አጠቃላይ አሸናፊነት ዛሬ ተጠናቀቀ። በሻምፒዮና ውድድሩ የሸገር ሲቲ አስተዳደር 47 የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት 1ኛ ሲሆን አዳማ 45 እና ማያ ከተማ 23 የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል። የእግርና የእጅ ኳስን ጨምሮ በ21 የስፖርት አይነቶች በተካሄደው ውድድሩ ከ5ሺህ በላይ ስፖርተኞች ተሳትፈዋል።   የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማቴዎስ ሰቦቃ በስነ ስርአቱ ላይ እንደገለጹት ስፖርት በማንኛውም ልዩነቶች ሳይገደብ በእኩልነት እና በእውነተኛ ፍቅርና ወንድማማችነት የሚደረግ ውድድር ነው። ዘርፉ የአገሪቱን ልማት በማፋጠንና ኢኮኖሚውን በማሳደግ ረገድ ያለውን ሚና አንስተው ልዩነቶችን በመፍታትና ዘላቂ ሰላምን በማስፈንም ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልጸዋል። “ስፖርት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ለመዝናናት ተወዳጅና ተመራጭ ዘርፍ እየሆነ መጥቷል” ያሉት ሀላፊው “ዘርፉን በበለጠ ለማጎልበት እየሰራን ነው” ብለዋል። ይህንን የአንድነታችን፣ የእድገታችንና መሰረት የሆነውን ወሳኝ ዘርፍ በማጠናከር ለሀገር ልማት ለማዋል በትኩረት እየተሰራ ነው” ሲሉም አክለዋል። 26ኛው የመላው ኦሮሚያ ጨዋታ ስፖርት ውድድር የአንድነት እና አብሮ የመኖር መሰረት በተግባር ማሳየቱን አስታውቀዋል። የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው ጅማን ለዚህ ውድድር በመመረጧ ለከተማዋ ጥቅም ሚያስገኝ መሆኑን ተናግረዋል። ስፖርት ወዳጅነትና መቀራረብን ፍቅርና ስላምን የሚያመላክት መሆኑን ገልጸው “የስፖርቱን ዘርፍ ለማጎልበት በትብብር መስራት ያስፈልጋል” ብለዋል። በ26ኛው የመላው አሮሚያ የስፖርት ሻምፒዮና የሽልማት እና የመዝጊያ መርሃግብር ላይ የስፖርቱ ዘርፍ የስራ ሀላፊዎች የስፖርቱ ቤተሰብና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።      
በቬና በተካሄደ የማራቶን ውድድር አትሌት ጫላ ረጋሳ በአንደኝነት አጠናቀቀ
Apr 21, 2024 203
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- በቬና የተካሄደውን የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ጫላ ረጋሳ አንደኛ በመወጣት አጠናቀቀ፡፡ አትሌት ጫላ ረጋሳ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት አሸንፏል። በለንደን ማራቶን ደግሞ ትዕግስት አሰፋ እና ቀነኒሳ በቀለ ውድድራቸውን በተመሳሳይ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያ አሸናፊዎች ሆነዋል። የሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ዛሬ በተደረገው በ44 ኛው የለንደን ማራቶን በ 2ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሁለተኛ ደረጃ ውድድርዋን አጠናቃለች። በወንዶች ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ውድድርን በ2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ15 ሰኮንድ በሁተኝነት በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል። በለንደን የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት መገርቱ አለሙ በ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ34 ሰኮንድ 4ኛ፣ አትሌት ትዕግስት ከተማ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ 7ኛ፣ አትሌት ያለምዘርፍ ይሁአለው 2 ሰዓት ከ 23 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ 8ኛ እንዲሁም አትሌት ፅጌ ሀይለስላሴ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል። እንዲሁም አትሌት ክንዴ አተናው በ2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ 8ኛ ደረጃን ይዞ በመግባት ውድድሩን አጠናቋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ውድድር የገባበት ሠዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ ሲመዘገብ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለጽ የዓለም አትሌቲክስ አድናቆት መግለጹን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል
Apr 21, 2024 185
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል። በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ኢትዮጵያ ቡና ከመቻል ከቀኑ 10 ሰዓት ሲጫወቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ደግሞ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ፣ በሶስቱ ሽንፈት ገጥሞች አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በዚሀም መሰረት በሊጉ በ33 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቻል በበኩሉ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በሁለቱ ድል ሲያደርግ ሁለት ጊዜ ተሸንፎ አንድ ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በዚህም መሰረት መቻል በ40 ነጥብ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በድሬዳዋ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ይጨወታሉ። የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከሲዳማ ቡና ዛሬ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በ43 ነጥብ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበኩሉ ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ፣ አንድ ጊዜ ተሸንፎ፣ ሁለት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በአንፃሩ ሲዳማ ቡና ባለፉት አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አላጋጠመውም። በሁለቱ ሲያሸንፍ በሶስቱ አቻ ወጥቶ በ27 ነጥብ በሊጉ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሊጉ 22ኛ ሳምንት ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ሻሸመኔ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል። የዛሬ ጨዋታዎችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የድሬዳዋ ቆይታ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከ16ኛ ሳምንት አንስቶ የሊጉ ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም ሲደረጉ እንደነበር ይታወቃል። ከ23 እስከ 27ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚደረጉ የሊጉ አክሲዮን ማህበር መግለጹ ይታወሳል።
በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ተተኪዎችን ለማፍራት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው
Apr 21, 2024 187
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ለታዳጊዎች የኳስ ብቃትና ክህሎት ጥሩ መሰረት እየጣሉና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አሰልጣኞች ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተፃፈው የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ተሽጦ ገቢው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለልማት ሥራ እንዲውል ተደርጓል። በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። በመዲናዋ የእግር ኳስ፣ የፉት ሳል፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የሜዳ ቴኒስና ሌሎች የመጫወቻ ስፍራዎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ነው። በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ ተገንብተው ወጣቶችና ታዳጊዎች እየተጫወቱባቸው ከሚገኙ የእግር ኳስ ሜዳዎች መካከል የኢዜአ ሪፖርተር በመዘዋወር አሰልጣኞችና ሰልጣኞችን አነጋግሯል።   በፈረንሳይ 41 ማዞሪያ ራስ ካሣ ሜዳ እና በልደታ ክፍለ ከተማ ቢሊሞ ሜዳ ልምምድ ሲያሰሩ ያገኘናቸው አሰልጣኝ ሰላምሰው ምዳ፤ መደመር በስፖርቱ ዘመን ተሻጋሪ አሻራ እያሳረፈ መሆኑን ገልጸዋል። በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ለታዳጊዎች የኳስ ብቃትና ክህሎት ጥሩ መሰረት እየጣሉና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል።   በራስ ካሣ ሜዳ በስልጠና ላይ ያገኘናቸው ይስሐቅ ኃይለማርያም እና አቤሜሌክ ኤርሚያስ፤ ከመገንባቱ በፊት ሜዳው ለጨዋታ አስቸጋሪና ለጉዳት የሚዳርግ እንደነበር አስታውሰው ከተገነባ በኋላ በብዙ መልኩ ደረጃውን የጠበቀና ለስልጠና ምቹ መሆኑን ተናግረዋል።   በቢሊሞ ሜዳ ሲያሰለጥኑ ያገኘናቸው አሰልጣኝ መንግሥቱ አረጋ፤ የሜዳው በዘመናዊ መልኩ መሰራት የኢትዮጵያን እግር ኳስ የሚቀይሩ ልጆች ለማፍራት ያግዛል ብለዋል። በሜዳው ሲሰለጥኑ ያገኘናቸው ታዳጊ ልዑል ዮናስ እና ሰላዲን ሀሰን በዘመናዊ መልኩ አዲስ የተሰራው ሜዳ እኛን ጨምሮ ለበርካታ ልጆች ጥሩ የኳስ መሰረት እያስያዘ ነው ብለዋል። በመዲናዋ ከሚገኙ 24 የስፖርት ማዘውተሪያዎች መካከል ሰባቱ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ በተገኘ ገቢ የተገነቡ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በመንግሥት በጀት የተሰሩ መሆናቸው ታውቋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የቆላማ ስርአተ ምህዳር የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት እየተገበረ ነው
Apr 25, 2024 55
መቀሌ ፤ሚያዚያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች 120 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቆላማ ስርአተ ምህዳር የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት እየተገበረ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ፕሮጀክቱን በትግራይ ክልል ለማስጀመር በተዘጋጀ የትውውቅ መድረክ ላይ እንደተመለከተው፣ ፕሮጀክቱ በቆላማ የሀገሪቱ አካባቢዎች 120 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። በባለስልጣኑ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ደሳለኝ ሙሉጌታ እንደገለጹት የቆላማ ስርአተ ምህዳር የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ፕሮጀክት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እየተተገበረ ይገኛል። በፕሮጀክቱም በዋነኛነት በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዳ ያለው የአካባቢ ስነምህዳር እንዲያገግም ለማድረግ የሚያግዙ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው። በተለይ በቆላማ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች የአፈር መከላትን ለመከላከል የደን ልማት ጥበቃ ሥራን ጨምሮ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ የሥራ እድሎች እንዲሰማሩ መደረጉን ገልጸዋል። ከእዚህ በተጨማሪ ለአየር ንብረት ለውጥ መሻሻል የበኩላቸውን እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ነው አቶ ደሳለኝ ያስረዱት። በዚህም ነዋሪዎች የአየር ንብረትን በማይጎዱ የልማት ሥራዎች እንዲሰማሩና እንደ ሶላር ያሉ የሃይል አማራጮችን የመጠቀም ባህላቸው እንዲጎለብት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። መንግስት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ካለፋት ሦስት ዓመታት ጀምሮ ፕሮጀክቱን እየተገበረ ይገኛል ያሉት አስተባባሪው፣ ፕሮጀክቱ በትግራይ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች ሳይተገበር ቢቆይም አሁን ወደስራ እየገባ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሮጀክቱን በሁለት የትግራይ ወረዳዎች በሚገኙ አራት የገጠር ቀበሌዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ለማስጀመር መታቀዱንና የዛሬው መድረክም ፕሮጀክቱን ለማስተዋወቅ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።   በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ፀጋይ ገብረማሪያም በበኩላቸው እንዳሉት፣ ፕሮጀክቱ በትግራይ ዘግይቶ ቢጀመረም በህዝቡ የተደራጀ ተሳትፎ ለማሳካት ጠንክረን እንሰራልን በለዋል። ፕሮጀክቱን ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ከሁለቱ ወረዳዎች እና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም ፕሮጀክቱን በተፋጠነ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።  
በኦሮሚያ ክልል ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር  እስካሁን 500 ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኝ ተዘጋጅቷል 
Apr 25, 2024 59
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2016 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 500 ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኝ መዘጋጀቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በኦሮሚያ ክልል አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩም ተገልጿል። የቢሮው የደን ልማትና እንክብካቤ ዳይሬክተር ከተማ አብዲሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራን ከተፋሰስ ልማትና ከሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ጋር በማቀናጀት እየተሰራ ነው። በክልሉ ባለፉት ዓመታት 18 ነጥብ 6 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉን አስታውሰው የፅድቀት መጠን በአማካኝ ከ80 በመቶ በላይ መሆኑን ተናግረዋል። ክልሉ በመጪው ክረምት 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል አቅዶ እስካሁን 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ችግኝ ዝግጁ ማድረጉን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 500 ሚሊዮኑ ለፍራፍሬ ምግብነት የሚውሉ ናቸው ብለዋል። ለደንና ሌሎችም አገልግሎቶች የሚውሉ ችግኞች መኖራቸውን ጠቅሰው፥ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶችም ዝግጁ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ገልጸዋል። በአረጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ ለዜጎች የስራ ዕድል እየተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።   በዚህም ባለፉት ሁለት ዓመታት በቋሚነት ከ80 ሺህ በላይ ሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። የአረንጓዴ አሻራን ከተፋሰስ ልማትና ከሌማት ትሩፋት ጋር በማቀናጀት ዜጎች ችግኞችን በመንከባከብ ፍራፍሬ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው ብለዋል። ወጣት ዲቢሳ ጋሹ እና ጥላሁን ደርሶ ከሌሎች ወጣቶች ጋር በማህበር በመደራጀት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የስራ እድል እንደተፈጠረላቸውና በሚያገኙት ገቢ ቤተሰባቸውን እያስተዳደሩ መሆኑን ገልጸዋል። በችግኝ ማፍላትና ሌሎችም ስራዎች በትጋት በመስራት ገቢያቸው እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት 5 ሚሊዮን ብር ካፒታል እንዳላቸው ገልጸዋል።    
ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከበቂ በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተመልከተናል - የፌደራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን
Apr 25, 2024 71
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 17/2016(ኢዜአ)፡- ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከበቂ በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን በመስክ ምልከታ ማረጋገጡን የፌደራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ። ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ መጪው ክረምት 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል የታቀደ ሲሆን በዝግጅት ደረጃ ከእቅድ በላይ 7 ቢሊዮን ችግኝ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የበጀት ዓመቱን የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሲገመግሙ የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርግ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። በዚህም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የግብርና ሚኒስቴርን የመጪው ክረምት የአረጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዝግጅትና በባለፈው ዓመት የተተከሉ ችግኞችንና የተፋሰስ ልማት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ተመልክቷል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፋኑሴ መኮንን፥ ኢትዮጵያ በአረጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዜጎችን በማሳተፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አበረታች ውጤት እያስመዘገበች ነው ብለዋል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 32 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በአማካይ ከ87 በመቶ በላይ መፅደቃቸውን ተናግረዋል። በመጪው ክረምት 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን በዝግጅት ደረጃ ከ7 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ተዘጋጅቷል ነው ያሉት። ለተከላ ከተዘጋጁት ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሲሆን 40 በመቶ ደግሞ ለደን ችግኝ የሚተከሉ እንደሆኑ ጠቁመዋል። የስፔስ ሳይንስና የጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የሱፐርቪዥን ቡድኑ መሪ አቶ አብዲሳ ይልማ፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅኖን መቋቋምና የምግብ ዋስትናን መረጋገጥ እንደሚቻል ያሳየ ነው ብለዋል።   መርሐ ግብሩን ከአፈርና ውሃ ጥበቃ ጋር በማቀናጀት መተግበሩ የተራቆቱ አካባቢዎችና የደረቁ ምንጮች እንዲያገግሙ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እያስቻለ ነው ብለዋል። የሱፐርቪዥን ቡድኑ ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በቂ ችግኝ የመትከያ ቦታ መዘጋጀቱን እንደተመለከተ ገልጸዋል። መርሐ ግብሩን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ችግኞችን በዝግጅት ወቅትና ከተተከሉ በኋላ ያሉበትን ደረጃ በቴክኖሎጂ በተደገፈ አሰራር መከታተልና መንከባከብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኦሮሚያ ክልል ድርቅን በዘላቂነት መቋቋም የሚያስችሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑን ገለጸ
Apr 25, 2024 68
ቦረና፤ ሚያዝያ 17/2016(ኢዜአ)፡- የኦሮሚያ ክልል ድርቅን በዘላቂነት መቋቋም የሚያስችሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ገለጹ። የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በቦረና ዞን ድርቅን በዘላቂነት ለመቋቋም እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። ከጉብኝቱ በኋላ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ የክልሉ መንግስት ድርቅን በዘላቂነት ለመቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም በክልሉ ቆላማ አካባቢዎች በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ከአጭር ጊዜ እቅድ መካከል ድርቅ በተደጋጋሚ በሚያጋጥማቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች በድርቅ ምክንያት ለከፋ ጉዳት እንዳይዳረጉ ተከታታይ ድጋፍ ማድረግ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ስራም በክልሉ የተወሰኑ ቦታዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት በዜጎች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ከረጅም ጊዜ ዕቅድ አንጻርም የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና የኢኮኖሚ እድገትን የሚያሳኩ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ መሆኑን አቶ ኃይሉ አስረድተዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ በክልሉ እየተተገበሩ ከሚገኙ 73 ፕሮጀክቶች መካከል 36ቱ ድርቅ በሚያጠቃቸው ቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው። ፕሮጀክቶቹ በዋናነት አርብቶ አደሩን ወደ ከፊል አርሶ አደርነት የሚለውጡ የመስኖ መሰረተ ልማቶች፣ የመጠጥ ውሃ እና የመኖ ልማት መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በቀጣይም ትላልቅ ፕሮጀክቶች እንደሚተገበሩ ገልጸዋል። የቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ በሪሶ ገኖ በበኩላቸው እንዳሉት በዞኑ ድርቅን በዘላቂነት ለመቋቋም የ18 አነስተኛ ግድቦች ግንባታ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።   የአብዛኛዎቹ ግድቦች ግንባታ መጠናቀቁን የጠቆሙት አቶ በሪሶ፣ በተሰራው የበጋ መስኖ ልማት ስራም በሄክታር እስከ 75 ኩንታል በቆሎ መገኘቱንና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትም መከናወኑን ገልጸዋል። በእንስሳት መኖ ልማትም 75 ሺህ ቶን መኖ ተዘጋጅቶ መከማቸቱን ተናግረዋል። በጉብኝቱ ከተሳተፉት የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች መካከል የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ በበኩላቸው መገናኛ ብዙሃን የልማት ስራዎችን በተከታታይ መዘገብ አለባቸው ብለዋል። ችግሮች ሲከሰቱ ብቻ ከመዘገብ የዜጎችን ህይወት ለመቀየር የሚከናወኑ ሥራዎችንም ለህዝቡ ማሳወቅ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 1143
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 2045
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1335
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
ሐተታዎች
ነገረ - አስተውሎት
Apr 24, 2024 71
ሰው በሀሳብ ከሕይወታዊያን ፍጥረት ይለያል። ከፍጥረቱ ጀምሮ ኑሮውን ቀላል ለማድረግ አስቧል። ሀሳቡም መላ ፈጥሯል። ድንጋይ አፋጭቶ እሳትን አንድዷል። እንስሳትን አላምዶ፣ ሰብልን አባዝቶ፣ መጠለያውን ቀልሶ… ኑረቱን አሳልጧል። ዕለታዊ ተግባሩን ለማቃለል በቁስ ላይ ተመራምሮ አጋዥ ቁስ ፈጥሯል። በሂደትም የኢንዱስትሪን አብዮት አፈንድቷል። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በባተው የኢንዱስትሪ አብዮት ዓለም አዲስ ክስተት አስተናግዳለች። ፋብሪካዎች፣ መኪናና አውሮፕላን፣ የእንፋሎትና የኤሌክትሪክ ኃይልና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች ተፈብርከው ምርትና ምርታማነት ጨምሯል። ከተሜነት አብቧል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ ሮቦቲክስና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በሰው ተፈጥረዋል። ሳይንስን ለመፍትሔ-እንከን አውሏል። ቴክኖሎጂን ለሁለንተናዊ ሕይወት ማቃለያ ተጠቅሟል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሀሳብን ከፈጠራ ጋር አዋዶ ኑሮና ሕይወት አቅልሏል። ኮምፒዩተር ፈበረከ፤ ኢንተርኔትን ፈጠረ፣ ዓለምን አስተሳሰረ። የተዓምር ዘመን ሆነ። ሰው እያስተዋለ... እያስተዋለ… በረቀቀ ጥበብና ግኝት ዛሬ ከዘመነ-አስተውሎት ደረሰ። ሰው ሰራሽ አስተውሎት!! የዘመኑ ቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) እንደሆነ ይጠቀሳል። ዳሩ የቴክኖሎጂው እምርታ የዘመን ክስተት ሳይሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት ጀምሮ እርሾ ሲያቦካ እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይጠቅሳሉ። ዋረን ማክኩሎች እና ዋልተር ፒትስ ለዛሬው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እርሾ የሆነ በነርቭ አውታረ መረብ የሚታገዝ ሒሳባዊ ሞዴል የፈጠሩት በ1943 ዓ.ም ነበር። በ1950 ዓ.ም ደግሞ አለን ተርኒግ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን ፈለሰፈ። በተመሳሳይ በ1960ዎቹ አጠቃላይ ችግር ፈቺ፣ ሎጂክ ቴዎሪስትና መሰል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞች በልፅገዋል። በ1950 ዓ.ም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ራሱን ችሎ እንዲጠና ተወሰነ። ለውስብስብ ችግሮች አይነተኛ መፍትሄ መሆኑ ታመነበት። በ1970 እና 80ዎቹ የዘርፉ ሊቃውንት የሰውን ልጅ የመወሰን አቅም የሚተካ የኮምፒውተር ፕሮግራም ለማበልጸግ ጥረት አድርገዋል። በ1990ዎቹ ምርምሮቹ መቀዛቀዝ ጀምረው ነበር። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም አንሰራርቷል። ስልተ ቀመርን (algorithm) የሚረዱ ማሽኖች ስራ ላይ ውለዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጥናት ዘርፍ የሰውን ስራና ሃሳብ በኮምፒዩተር መራሽ ቁሶች መተካት ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት የሆኑ ማሽኖች መገንዘብ፣ መማርና ችግሮችን እንዲቀርፉ ማስቻልም ነው። ማሽኖች በሰው ልጅ ምትክ አካባቢን ማመዛዘን፣ መማር፣ ማቀድና መፍጠር፣ መተንተንና እንከኖችን ማምከን እንዲችሉ ማድረግ ነው። የሰውን የማሰብ ኅይል በኮምፒዩተር አዳብሮ በሰውኛ ጥበብ ሕይወትን ማቅለል ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ያሉትን የስሜት ህዋሳት ክህሎቶች ለማሽኖች በማስተማር ሰዎች ነገሮችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው። በዚህም የኮምፒውተር ሊቃውንት ስልተ ቀመር ወይም አልጎሪዝምና አስበው የሚሰሩ ማሽኖች ወደ ስራ እያስገቡ ነው። ለአብነትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥበብ ቤት የሚያጸዱ ሮቦቶች፣ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ሰው አልባ ጦር መሳሪያዎች፣ የደህነንት ጥበቃ ካሜራዎች፣… በልጽገው ስራ ላይ ውለዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተስፋም ስጋትም ይዞ መምጣቱ ይነገራል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዛሬ ላይ በሁሉም መስክ ገቢራዊ እየተደረገ ነው። በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በግብርና ዘርፎች ምርትና አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለመጨመር ቁልፍ አማራጭ ተደርጓል። ቴክኖሎጂው ከዓለም ገበያ ከ350 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድርሻ አለው። አፍሪካም እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ገበያ 10 በመቶ ድርሻ መያዝ ከቻለች እኤአ 2030 አሁን ያለው አህጉራዊ ጥቅል ምርቷ (ጂዲፒ) 50 በመቶ ይጨምራል። ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በፊት ዘርፉን የሚመራ ተቋም መስርታለች፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን። ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ተጠቃሽ ሀገር ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ነው። በቅርቡ የተመረቀው “አስተውሎት” የተሰኘ ፊልም ደግሞ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሰው ልጅ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የማይገባበት ሕይወት እንደሌለ ፊልሙ ያስረዳል። በጤና፣ በማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ በመረጃ ፍለጋ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በማዕድን ፍለጋና፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የዚህ ቴክኖሎጂ ቁልፍ ሚና ተንጸባርቋል። ዘርፉ ከቅንጦት ይልቅ አስፈላጊነቱ ጨምሯል። ለበሽታ መከላከል፣ ለጤና እንክብካቤ፣ ለትምህርት መሻሻልና ድህነት ቅነሳ ይውላል። ለዚህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ መተግበሪያዎች ፈጠራና አቅም እያደገ መምጣቱ በፊልሙ ተገልጿል። ፊልሙ የኢትዮጵያ የቡና ዛፎችን የበሽታ ስርጭት ለይቶ ለማከም ያለውን ውጤታማነት ያወሳል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ገበያን ለማስፋት እና ለመሳሰሉት ሥራዎች በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እየተስፋፉ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል ማሽን ትራንስሌት ወይም የቋንቋ ትርጉም አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም አንዱን ቋንቋ ወደ ሌላ በመተርጎም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም በአንድ መተግበሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን መማር እንዲሁም ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሥርዓትን አበልጽጎ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል። መተግበሪያው አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ ለመማር የሚያስችል ሲሆን ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችለው የመተግበሪያው አካል ድምጽን በመቅዳት ወይም ከመዛግብት (አርካይቭ) የድምጽ ፋይሎችን ወደ መተግበሪያው በማስገባት የጽሁፍ ቅጂውን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ከፊልሙ መገንዘብ ተችሏል። በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የደረሰበትን ልህቀት ያማከሉና ከዘርፉ ውጤት ለማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተኬደው ርቀት ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልህቀት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የዘርፉን ውጤቶች የበለጠ ማላቅ ያስፈልጋል። በዓለም የዕለት ተለት እንቅስቃሴ ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ በመረዳት ለዘርፉ ምርምሮች የሚደረገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር ያሻል። ዓለም የሚሄድበትን ፍጥነት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችን ለመተግበር በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል። (በሰለሞን ተሰራ)      
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 371
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1466
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2384
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
ትንታኔዎች
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 137
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3737
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2520
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2395
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11694
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16079
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8291
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9303
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25795
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21703
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16079
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12253
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11694
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 11115
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 10879
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10438
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25795
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21703
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16079
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12253
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 3644
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 3447
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም