አርእስተ ዜና
በክልሉ አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ አቅርቦ ተጠቃሚ እንዲሆን ለመሰረተ ልማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል
Apr 16, 2024 59
ሚዛን አማን ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ለገበያ አቅርቦ ተጠቃሚ እንዲሆን ለመሠረተ ልማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ። በደቡብ ቤንች ወረዳ በ18 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የዛን ወንዝ ድልድይ የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በወቅቱ እንደገለጹት፣ አርሶ አደሩ ከሚያመርታቸው የግብርና ምርቶቹ የተሻለ ተጠቃሚ መሆን እንዲችል የመንገድና የድልድይ መሠረተ ልማቶች ትልቅ ሚና አላቸው። በመሆኑም አርሶ አደሩ ምርቱን ገበያ እውጥቶ የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ የክልሉ መንግስት ለድልድይና ለመንገድ መሰረተ ልማቶች ልዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል። በዛሬው ዕለትም በደቡብ ቤንች ወረዳ በ18 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የዛን ወንዝ ድልድይ የመሰረተ ድንጋይ መቀመጡን ገልጸው፣ በሌሎችም አካባቢዎች መሰል የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። የደቡብ ቤንች ወረዳ በልማትና የግብርና ኤክስቴንሽን ስርፀትን ተግባራዊ በማድረግ በክልሉ ካሉ ወረዳዎች ግንባር ቀደም ወረዳ መሆኑንም አመልክተዋል። ወረዳው ከ500 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ በኩታ ገጠም የለማ ሙዝ ያለው ብቸኛ ወረዳ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህን የልማት አቅም ለማሳደግ ለመሠረተ ልማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። ድልድዩ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ህዝብን ከህዝብ እንዲሁም ምርትና ገበያን እንደሚያገናኝ ተናግረዋል።   የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልዱ በጪ በበኩላቸው እንደገለጹት በአካባቢው ከፍተኛ የቡና፣ የበቆሎ፣ የሙዝ እና የቅመማ ቅመም ምርቶች ቢኖሩም የመሠረተ ልማት ችግር ያለበት ነው። የአካባቢው አርሶ አደሮች የግብርና ምርት በጀርባቸው ተሸክመው ለገበያ እንደሚያወጡ ጠቁመው፤ ወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ችግሩን ለመቅረፍ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ሦስት ድልድዮችን ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን ተናግረዋል። በቀጣይም የሕዝቡን ድጋፍ በማጠናከር የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄን ለመመለስ በትኩረት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።   የድልድዩን የግንባታ ሥራ የሚያከናውነው "ተስፋዬ አሰፋ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ" ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አሰፋ በበኩላቸው ግንባታውን በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ እንደሚሠሩ ተናግረዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል የጃንቹታ ቀበሌ አርሶ አደር አዳሙ አኩሙ "መንግስት የመንገድ ችግራቸውን ለመፍታት የጀመራቸው የልማት ሥራዎች በእርሻ ሥራችን የተሻለ ተጠቃሚ እንድንሆን የሚያስችል ነው" ብለዋል። እስከዛሬ ያመረቱትን የበቆሎ፣ የቡናና የሙዝ ምርት በሸክምና በፈረስ ጭኖ ለገበያ የሚያቀርቡበትን አድካሚ ሁኔታ እንደሚያስቀርላቸው የተናገሩት ደግሞ በአካባቢው የኮብ ቀበሌ አርሶ አደር አብዮት ካሽት ናቸው። በመንገድና ድልድይ እጦት ምክንያት ምርቶቻቸውን ሽጠው ለመጠቀም ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰው ድልድይ ሲጠናቀቅ ችግራቸውን እንደሚቃለል ተናግረዋል። በመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።        
በአገር አቀፍ ደረጃ  ገበያውን ለማረጋጋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ
Apr 16, 2024 49
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 8/2016 (ኢዜአ)፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ ገበያንና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ ገለጹ ። በሚኒስትሩ የተመራ ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወራቤና ቡታጅራ ከተሞች የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን በመስክ ተመልክቷል። በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ እንዳሉት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ስልቶችን በመከተል ገበያንና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተለይም ገበያውን ለማረጋጋት የምርት መጠን ማሳደግ ላይ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል። ለዚህም በየአካባቢው አርሶ አደሩ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና እንዲሁም ያለውን አማራጭ ተጠቅሞ እያደረገ ያለውን ጥረት ጠቅሰዋል። እንዲሁም የሸማችና ህብረት ስራ ማህበራትንና ዩኒየኖችን በማጠናከርና በመደገፍ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአምራች ኢንዱስትሪው፣ በህብረት ስራ ማህበራትና በዩኒየኖች እየተከናወነ የሚገኘው ተግባር የሚበረታታ ነው ብለዋል። በዚህም ምክንያት አልባ በሆነ የዋጋ ጭማሪና ህዝብን ለምሬት የሚዳርጉ አካላትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር መኖሩን በመስክ ምልከታው ማረጋገጥ መቻላቸውን ገልጸዋል።   የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ማሶሬ፤ በክልሉ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት አደረጃጀትና የቁጥጥር ስርዓትን የማጠናከር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል በዚህም አርሶ አደሩ፣አምራች ኢንደስትሪውና የሸማቾች ህብረት ማህበራት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል አደረጃጀት መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል። በክልሉ "ከሳምንት እስከ ሳምንት" በሚል ተነሳሽነት ሸማቹንና አምራቹን በቀጥታ የሚያገናኘው ገበያ ያለማቋረጥ እንዲቀጥልና ምርት በሚደብቁት ላይ በሚደረግ ቁጥጥር ውጤት መምጣቱን ጠቅሰዋል። በክልሉ ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ አማራጮችን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል። ቡታጅራ ከተማ የ"አገልግል ሸቀጣሸቀጦች ማከፋፈያ" ህብረት ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ገላን በበኩላቸው፤ ማህበሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ 200 አባላት ይዞ ወደስራ መግባቱን ገልጸዋል። በወቅቱ አስተዳደሩ ባደረገው ድጋፍና በአባላቱ አስተዋጽኦ በ2 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ስራ የጀመረው ማህበሩ ነዋሪውን መጥቀም ብቻ ተጠቃሚ በመሆኑ ገቢው መጨመሩን ተናግረዋል። "ከሳምንት እስከ ሳምንት ገበያ“ ሳምንቱን ሙሉ የግብይት ስርዓት ተግባራዊ መደረጉ አስፈላጊውን ግብዓት ተመቻችቶላቸው እንዲሸምቱ ማስቻሉን የተናገሩት ደግሞ በወራቤ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ሂክማ ነስረዲን ናቸው። በሚኒስትሩ የተመራው ቡድን በሁለቱም ከተሞች በዩኒየኖችና በሌሎች አደረጃጀቶች ገበያንና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።        
የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በተቀናጀ መልኩ መጠናከር አለበት - ጤና ሚኒስቴር
Apr 16, 2024 53
ሀዋሳ ፤ሚያዚያ 8/2016 (ኢዜአ)፦የኤች አይ ቪ/ኤድስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች በተቀናጀ መልኩ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ሀገር አቀፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም የጋራ ግምገማ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።   በግምገማው ላይ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ እንደገለጹት የኤች አይቪ /ኤድስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች ሊጠናከሩ ይገባል። ከዚህ ቀደም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችና አካባቢዎች ላይ በማተኮር ከግንዛቤ ማስጨበጫ ጀምሮ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መገኘቱን አስታውሰዋል። “በፈቃደኝነት ምርመራ የማድረግ ልምድ ማደግና አጋላጭ ምክንያቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ የስርጭት ምጣኔውን በሀገር ደረጃ ከአንድ በመቶ በታች ማድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተፈጠረ መዘናጋት የበሽታው የስርጭት መጠን ከፍ እያለ መምጣቱን ጠቅሰው፣ የህብረተሰቡን መዘናጋት በማስወገድ ስርጭቱን ለመግታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። አቶ ፍቃዱ እንዳሉት ቀደም ሲል በተሰሩ ሥራዎች የተገኘው ስኬት በሁሉም ባለድርሻ አካላት ላይ መዘናጋት እንዲፈጠር አድርጓል። ይህም በአሁኑ ወቅት ለሚታየው የበሽታው ስርጭት መጠን መጨመር ምክንያት መሆኑን ጠቅሰው፣ መዘናጋቱን አስወግዶ ስርጭቱን ለመቆጣጠር አቅምን በማስተባበር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ ዘርፉ እንዳሉት፣ በክልሉ ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት የበሽታውን ስርጭት የመቆጣጠር ሥራ እየተሰራ ነው።   ባለፉት ዘጠኝ ወራት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችና የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት ተደርጎ በተሰራው ሥራ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በፈቃደኝነት የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ማድረጋቸውንና 5 ሺህ የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው እንደተገኘባቸው ገልጸዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ወደሕክምና ክትትል ገብተው መድሀኒት እንዲጀምሩ ለማድረግ በተሰራው የማማከር ሥራም 95 በመቶ የሚሆኑት መድሀኒት ጀምረዋል ብለዋል። የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አስመላሽ አበራ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በክልሉ በተለይ ከፍተኛ የወርቅ ማዕድን የሚገኝባቸውና የኢንቨስትመንት አካባቢዎች ላይ በሽታውን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።   በክልሉ ከባህል ጋር ተያይዞ የወንዶች ግርዛት በማይፈጸምባቸው አካባቢዎች ያለውን የኤች አይ ቪ ተጋላጭነት ለመቀነስም የግንዛቤ ማጎልበቻ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። በክልሉ የቫይረሱ ስርጭት 3 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑን የጠቀሱት አስተባባሪው፣ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከጤና ሚኒስቴር እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለአራት ቀናት በሚካሄደው የግምገማ መድረክ የሁሉም ክልሎች የኤች.አይ.ቪ ዘርፍ ሀላፊዎችና አጋር ድርጅቶች የተገኙ ሲሆን የክልሎች አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ታውቋል።    
የክልሉን መንግስት ጥሪ በመቀበል ዘጠኝ የጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች እጃቸውን በሰላም ሰጡ - ኮማንድ ፖስቱ
Apr 16, 2024 61
ጎንደር ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ በመቀበል ዘጠኝ የጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች ከነትጥቃቸው እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ መስጠታቸውን የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ሃላፊና የኮማንድ ፖስቱ አባል አቶ አንተነህ ታደሰ አስታወቁ። ለጽንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች በሰላም እጅ ሰጥቶ መመለስ የዞኑ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተጠቁሟል። እጃቸውን ለመንግስት የሰጡት የጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች በበኩላቸው፤ በተሳሳተ መንገድ ተወናብደን የገባንበት ዓላማ ለእኛም ሆነ ለአማራ ህዝብ የሚጠቅም አይደለም ብለዋል፡፡   የመምሪያው ምክትል ሃላፊና የዞኑ ኮማንድ ፖስት አባል አቶ አንተነህ ታደሰ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ የቡድኑ ታጣቂዎች በተሳሳተ መንገድ በመንቀሳቀስ ህዝባቸውን ሲጎዱ መቆየታቸውን ጠቁመው፤ በድርጊታቸው በመጸጸት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን በመስጠት ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ በማድረግ ረገድ የዞኑ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸውም ገልጸዋል፡፡ የጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች ካለፈው ስህተታቸው በመማርና በመጸጸት ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቅለው የበደሉትን ህዝብ በሚክሱ የሰላምና የልማት ተግባራት እንዲሰማሩ ይደረጋል ብለዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ያስተላለፈውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ቀደም ሲል ወደ ዞኑ የገቡ 1ሺ 700 የሚሆኑት የተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ህብረተሰቡ በመቀላቀል ሰላማዊ ህይወት እየመሩ እንደሚገኙም አስረድተዋል፡፡ ህዝባችንን ከማጎሳቆልና ከወንድሞቻችን ጋር ደም ከመቃባት ውጪ ያተረፍነው ምንም ነገር የለም ያለው የሻለቃ መሪ እንደሆነ የገለጸው አቶ ሙሉቀን ምስጋናው ነው፡፡ በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ ብገባም ሰላምን ከማሳጣትና ልማቱን ከማደናቀፍ ውጪ መፍትሄ እንደማይገኝ በመገንዘቤ የሰላም አማራጭን ለመከተል ወስኛለሁ ብሏል፡፡ እጁን ለመንግስት የሰጠው ሌላው የጽንፈኛው ቡድን ታጣቂ አቶ አየልኝ ማሞ በበኩሉ፤ በተሳሳተ መንገድ የገባንበት ችግር የእርስ በርስ መጠፋፋት ካልሆነ በስተቀር የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ እንደማያስችል ተናግሯል፡፡ ዓላማ የለሽና የህዝብን እልቂት በሚያባብስ ተግባር የተሰማሩ ወገኖቻችን አሁንም የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲገቡ ጥሪ እናቀርባለን ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡          
የሚታይ
የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የሀገርን ሰላም እየፈተነ በመሆኑ ለዘላቂ መፍትሄ በጋራ መስራት ይገባል
Apr 16, 2024 235
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የሀገርን ሰላም እየፈተነ በመሆኑ ለዘላቂ መፍትሄ በጋራ መስራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገለጸ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ያለበትን ሁኔታ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ይፋ አድርጓል።   የሪፖርቱ የመጀመሪያ መረጃዎች ከፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዩ-ቲዩብና ኤክስ በናሙና የተሰበሰቡ ናቸው። ሁለተኛው ደግሞ በክልሎች በመጠይቆችና በነፃ የስልክ መስመር የሕዝብ አስተያየት የተሰበሰቡ መሆኑ ተገልጿል። የባለሥልጣኑ የመገናኛ ብዙኃን አቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ ኤደን አማረ በሰጡት ማብራሪያ፤ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ እየተስፋፋ መሆኑን ከተሰበሰበው መረጃ መረዳት ችለናል ብለዋል። በተለይም ብሔርን ሃይማኖትን እና ፖለቲካዊ አመለካከትን መሰረት በማድረግ ህዝብን በጠላትነት የሚፈርጁ እና አንዱ ለሌላው ስጋት የሚያስመስሉ የሃሰት መረጃዎች በስፋት መሰራጨታቸውን ጠቁመዋል። እንደ አጠቃላይ የጥላቻ ንግግር አስጊነት ካለፈው አመት አንጻር በይዘትም በአቀራረብም ተባብሶ የቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል። በጥቂት ደቂቃዎች በርካታ መረጃዎች የሚጋሩበት መድረክ እንደመሆኑ መጠን ይህንን የሚመጥን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋት እንደሚገባም ተናግረዋል። የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ሊወጣለት እንደሚገባም አመላክተዋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ፤ የሪፖርቱ ዓላማ የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ግዴታቸውን በምን ያህል መጠን እየተወጡ ነው የሚለውን ለማመላከትመሆኑን ገልጸዋል።   የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የሀገርን ሰላም እየፈተነ በመሆኑ ለዘላቂ መፈትሄ ለማሻትም የሪፖርቱን አስፈላጊነት አንስተዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም በኢትዮጵያ ለሚከሰቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የጥላቻ ንግግሮች እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ትልቁን ድርሻ የሚይዝ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚድያ የሚሰራጩ የጥላቻና ሀሰተኛ ንግግሮችን በህግ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 1185/12 የተደነገገ መሆኑ ይታወቃል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 108 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ
Apr 16, 2024 145
አዲስ አበባ ፤ሚያዝያ 8/2016 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 108 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አደም ኑሪ ለኢዜአ እንዳሉት ቢሮው በ2016 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 109 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 108 ቢሊዮን ብር የሰበሰበ ሲሆን አፈጻጸሙም 98 ነጥብ 5 በመቶ ነው። ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ45 በመቶ እድገት ወይም የ34 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱን ጠቅሰዋል። በ2015 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከተሰበሰበው 107 ቢሊዮን ብር ገቢ ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ1 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው። ቢሮው ገቢውን የሰበሰበው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክስ አገልግሎቶች ፣ ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ እና ሌሎችም መሆኑን አስረድተዋል። ሕገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል፣ የታክስ አከፋፈል አገልግሎት ለማሻሻል በዲጂታል የታገዙ አሰራሮች እየተተገበሩ መሆኑንም የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል። ቢሮው በሀሰተኛ ደረሰኝ የሚፈፀም ግብይትን ለመቆጣጠር ባደረገው ክትትል ከ5 ሺህ በላይ ግብይቶች በሀሰተኛ ደረሰኝ መፈጸማቸውን ማረጋገጡን ገልጸዋል። በሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት ሲፈፅሙ የተገኙ ግብር ከፋዮች ላይም 225 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት በማስከፈል አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ጠቁመዋል። አቶ አደም በበጀት ዓመቱ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፥ ለዚህም ስኬት ሁሉም በየደረጃው ርብርብ እንዲያደርግና ግብር ከፋዩም በታማኝነት ግብሩን እንዲከፍል አሳስበዋል። የምንከፈለው ግብር ለራሳችን ጥቅም መሆኑን መገንዘብ ይገባል ያሉት ኃላፊው፤አዲስ አበባ የምታመነጨውን ያህል ገቢ ለመሰብሰብ የግብር ከፋዩ፣ የአመራሩና የማህበረሰቡ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑንም እንዲሁ።  
የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የህክምና ባለሙያዎች ለሴቶች ጤና ድጋፍ የሚያደርግ በጎ አድራጎት ማህበር አቋቋሙ 
Apr 16, 2024 140
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 8/2016(ኢዜአ)፦የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የህክምና ባለሙያዎች "ሔዋን" የተሰኘና ለሴቶች ጤና ድጋፍ የሚያደርግ በጎ አድራጎት ማህበር ማቋቋማቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የማህጸንና ጽንሰ ስፔሻሊስት ሃኪምና የማህበሩ የቦርድ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ድልአየሁ በቀለ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት በሆስፒታሉ ወሊድን ጨምሮ የማህጸንና የጡት ካንሰር፣ የኩላሊት ህክምናና ሌሎች ውስብስብ የጤና አገልግሎቶች ይሰጣሉ። ህክምናውን ፈልገው ከሚመጡ ተገልጋዮች መካከል እናቶች፣ሴቶችና ህጻናት ትልቁን ቁጥር እንደሚይዙ ጠቁመው፤አብዛኞቹ የመረጃና የፋይናንስ እጥረት እንዳለባቸው አብራርተዋል። በተለይ ለህክምና የሚያስፈልጋቸውን ወጪ ለመሸፈን የገንዘብ እጥረት እንደሚያጋጥማቸውና የተገልጋዮች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ነው ያነሱት፡፡ ይህም ካጋጠማቸው የጤና እክል ባልተናነሰ መልኩ ኢኮኖሚያዊ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በሆስፒታሉ በጎ ፍቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች ተነሳሽነት ''ሔዋን'' የተሰኘ ለሴቶች ጤና ድጋፍ የሚያደርግ በጎ አድራጎት ማህበር ተመስርቷል ብለዋል።   በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት እና የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ወንድሙ ጉዱ በበኩላቸው ማህበሩ የህክምና እርዳታ የሚያገኙ እናቶች ያሉባቸውን የግንዛቤ ክፍተት መሙላት ላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ለሚያጋጥማቸው የፋይናንስ እጥረት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ህክምናቸው እንዳይስተጓጎል ማድደረግም ዋነኛው ተግባር መሆኑን አስረድተዋል። አንዳንድ የህክምና ሂደቶች ረዥም ጊዜን የሚወስዱ በመሆናቸው ታካሚዎቹ በተረጋጋ ሁኔታ ህክምናቸውን እንዲከታተሉ ጊዜያዊ ማረፊያ የማቋቋም እቅድ መያዙንም ጠቁመዋል። መንግስት የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በጤና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ፋጡማ ሰኢድ ናቸው።   በተለይም የእናቶችና ህጻናት ሞት ቅነሳ ላይ ትኩረት በማድረግ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት ቢመዘገብም አሁንም ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡   የሔዋን የሴቶች የጤና ድጋፍ በጎ አድራጎት ማህበር በጎ ፍቃደኛ አምባሳደር አርቲስት የትናየት ታምራት፤ ሁሉም ለድርጅቱ የአቅሙን እገዛ በማድረግ ለእናቶችንና ህጻናትን ሞት ቅነሳ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ አቅርባለች፡፡                    
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ "አስተውሎት" የተሰኘ ሳይንሳዊ ፊልም ተመረቀ
Apr 16, 2024 179
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 8/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ "አስተውሎት" የተሰኘ ሳይንሳዊ ፊልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተመረቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና፣ በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሻለ ነገ ማየት የሚያስችል ወሳኝ ቴክኖሎጂ መሆኑን ገልጸዋል።   አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የማሰብ፣ የመገንዘብና ምክንታዊ የመሆን አቅምን በማዳበር በሰውኛ ጥበብ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተጀምሮ አሁን ባለበት ደረጃ ላይ እንዲገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።   ኢንስቲትዩቱ አሁን ላይ ለሀገር የሚበጁ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከሰውኛ ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው "አስተውሎት" የተሰኘውና በዕውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው ሳይንሳዊ ፊልም ለአንድ አመት ዝግጅት የተደረገበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 17213
ኢዜአ
ፖለቲካ
የክልሉን መንግስት ጥሪ በመቀበል ዘጠኝ የጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች እጃቸውን በሰላም ሰጡ - ኮማንድ ፖስቱ
Apr 16, 2024 61
ጎንደር ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ በመቀበል ዘጠኝ የጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች ከነትጥቃቸው እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ መስጠታቸውን የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ሃላፊና የኮማንድ ፖስቱ አባል አቶ አንተነህ ታደሰ አስታወቁ። ለጽንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች በሰላም እጅ ሰጥቶ መመለስ የዞኑ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተጠቁሟል። እጃቸውን ለመንግስት የሰጡት የጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች በበኩላቸው፤ በተሳሳተ መንገድ ተወናብደን የገባንበት ዓላማ ለእኛም ሆነ ለአማራ ህዝብ የሚጠቅም አይደለም ብለዋል፡፡   የመምሪያው ምክትል ሃላፊና የዞኑ ኮማንድ ፖስት አባል አቶ አንተነህ ታደሰ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ የቡድኑ ታጣቂዎች በተሳሳተ መንገድ በመንቀሳቀስ ህዝባቸውን ሲጎዱ መቆየታቸውን ጠቁመው፤ በድርጊታቸው በመጸጸት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን በመስጠት ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ በማድረግ ረገድ የዞኑ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸውም ገልጸዋል፡፡ የጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎች ካለፈው ስህተታቸው በመማርና በመጸጸት ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቅለው የበደሉትን ህዝብ በሚክሱ የሰላምና የልማት ተግባራት እንዲሰማሩ ይደረጋል ብለዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ያስተላለፈውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ቀደም ሲል ወደ ዞኑ የገቡ 1ሺ 700 የሚሆኑት የተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ህብረተሰቡ በመቀላቀል ሰላማዊ ህይወት እየመሩ እንደሚገኙም አስረድተዋል፡፡ ህዝባችንን ከማጎሳቆልና ከወንድሞቻችን ጋር ደም ከመቃባት ውጪ ያተረፍነው ምንም ነገር የለም ያለው የሻለቃ መሪ እንደሆነ የገለጸው አቶ ሙሉቀን ምስጋናው ነው፡፡ በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ ብገባም ሰላምን ከማሳጣትና ልማቱን ከማደናቀፍ ውጪ መፍትሄ እንደማይገኝ በመገንዘቤ የሰላም አማራጭን ለመከተል ወስኛለሁ ብሏል፡፡ እጁን ለመንግስት የሰጠው ሌላው የጽንፈኛው ቡድን ታጣቂ አቶ አየልኝ ማሞ በበኩሉ፤ በተሳሳተ መንገድ የገባንበት ችግር የእርስ በርስ መጠፋፋት ካልሆነ በስተቀር የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ እንደማያስችል ተናግሯል፡፡ ዓላማ የለሽና የህዝብን እልቂት በሚያባብስ ተግባር የተሰማሩ ወገኖቻችን አሁንም የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲገቡ ጥሪ እናቀርባለን ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡          
በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የህብረተሰቡ ሚና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል
Apr 16, 2024 55
ጋምቤላ ፤ ሚያዝያ 8/2016 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መንግስት ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የህብረተሰቡ ሚና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ። በክልሉ በኑዌር ዞን ከሚገኙ አምስት ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በኝንኛንግ ከተማ መክረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ክልሉ አለመግባባቶችን በውይይት ፈትቶ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በመንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቷል። በክልሉ ህዝቦች መካከል ያለው የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴት ይበልጥ ሊናጠናክር ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ከመንግስት ጥረት ጎን ለጎን የህብረተሰቡ ሚናም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።   የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ በበኩላቸው፤ በክልሉ ለአካባቢው ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የሚተርፍ የተፈጥሮ ሃብት መኖሩን አስታውሰዋል። በመሆኑም የመሬትና የተፈጥሮ ፀጋዎች ለአካባቢው የፀጥታ ችግሮች መንስኤ ሳይሆን፤ ለብልጽግናችን ልናውል ይገባል ብለዋል። አብሮነታችንና አንድነታችንን በመጠበቅ ሰላማችንና የጋራ ተጠቃሚነታችን ለማረጋገጥ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ዶፕ ሙን በሰጡት አስተያየት፤ በክልሉ የፀጥታ ችግሮች ሲከሰቱ በጋራ ተወያይቶ የመፍታት ባህላችንን የበለጠ ልናጠናክር ይገባል ነው ያሉት። ወይዘሮ ኛሾም ቾን በበኩላቸው፤ በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት እውን እንዲሆን መንግስት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ ተናግረዋል። በክልሉ ለህግ የበላይነት መስፈን ህዝቡም አመራሩም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት የተናገሩት ሌላው የመድረኩ ተሳታፊ አቶ ራች ሬስ ናቸው። በውይይት መድረኩ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የአመራር አባላትን ጨምሮ ተዋቂ ግለሰቦች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሀይል ትስስር በመፍጠር ቀጣናዊ የመሪነት ሚና እየተጫወተች ነው- ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)
Apr 16, 2024 309
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሀይል ትስስር በመፍጠር ቀጣናዊ የመሪነት ሚና እየተጫወተች መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ 'world Future Energy Summit' የፓን አፍሪካዊ ትብብር ሚና የታዳሽ ሀይል ልማት ከማሳለጥና የኢነርጂ ዋስትና የማረጋገጥ አላማውን አድርጎ በአቡዳቢ ከአፕሪል 16 እስከ 18/2024 የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው። በመድረኩ ላይ ገለጻ ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ቀጣናዊ የሀይል ትስስር መሰረት የመጣልና የማጠናከር ጉዳዮች ኢትዮጵያ በቀጣናው ለትብብርና ቅንጅት ትኩረት መስጠቷን ገልጸዋል። በዚህም ሱዳናውያን የገጠማቸው ውስጣዊ ችግር ክፍያ እንዲፈጽሙ ባያስችላቸውም የሀይል አቅርቦት መቀጠሉን እንደማሳያ አንስተዋል፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን የምስራቅ አፍሪካ ፓወር ፑልን ለማጠናከርና ለማስቀጠል አይነተኛ ሚና እየተጫወተች መሆኗን ጠቁመዋል። በዚህም የሀይል መስመሮች፣ መንገዶችና የቴሌኮም ኔትወርኮችን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶች ወደ ጎረቤት ሀገራት ተዘርግተው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ብሔራዊ እቅድ ቀጣናዊ ቅንጅታዊ ስትራቴጂ መካተቱንና በአህጉር ደረጃ ለማሳደግ ታሳቢ መደረጉን ማንሳታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። እንደሀገር ያለን የሀይድሮፓወር እምቅ አቅምን የማልማት ልምድ መኖሩንና ተቋም መገንባት መቻሉ የምስራቅ አፍሪካ የአረንጓዴ ኢነርጂ ማዕከል ለመሆን እንድንሰራ አስችሎናል ብለዋል፡፡ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነትን በመተግበር የግሉን ዘፍፍ በሀይል ልማት ዘርፍ ለማሳተፍ ያለው ቁርጠኝነት አንዱ ማሳያ መሆኑንም ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አህጉራዊ የሀይል ሲስተም ማስተር ፕላን መሰረት በማድረግ ለሶስት ጎረቤት ሀገራት የሀይል ትስስር መፈጠሩንና ሌሎች ሀገራትን በማካተት ትስስሩን ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የሀይል መሠረተ ልማት ግንባታና ዝርጋታ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚጠይቅ በመሆኑ የልማት አጋሮች ቁርጠኝነት እጅግ አስፈፈላጊ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሀይል ልማት ኢንቨስትመንት መሰማራት በቀጣናው የስራ ዕድል ፈጣራ እና የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የሀገርን ሰላም እየፈተነ በመሆኑ ለዘላቂ መፍትሄ በጋራ መስራት ይገባል
Apr 16, 2024 235
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የሀገርን ሰላም እየፈተነ በመሆኑ ለዘላቂ መፍትሄ በጋራ መስራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገለጸ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ያለበትን ሁኔታ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ይፋ አድርጓል።   የሪፖርቱ የመጀመሪያ መረጃዎች ከፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዩ-ቲዩብና ኤክስ በናሙና የተሰበሰቡ ናቸው። ሁለተኛው ደግሞ በክልሎች በመጠይቆችና በነፃ የስልክ መስመር የሕዝብ አስተያየት የተሰበሰቡ መሆኑ ተገልጿል። የባለሥልጣኑ የመገናኛ ብዙኃን አቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ ኤደን አማረ በሰጡት ማብራሪያ፤ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ እየተስፋፋ መሆኑን ከተሰበሰበው መረጃ መረዳት ችለናል ብለዋል። በተለይም ብሔርን ሃይማኖትን እና ፖለቲካዊ አመለካከትን መሰረት በማድረግ ህዝብን በጠላትነት የሚፈርጁ እና አንዱ ለሌላው ስጋት የሚያስመስሉ የሃሰት መረጃዎች በስፋት መሰራጨታቸውን ጠቁመዋል። እንደ አጠቃላይ የጥላቻ ንግግር አስጊነት ካለፈው አመት አንጻር በይዘትም በአቀራረብም ተባብሶ የቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል። በጥቂት ደቂቃዎች በርካታ መረጃዎች የሚጋሩበት መድረክ እንደመሆኑ መጠን ይህንን የሚመጥን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋት እንደሚገባም ተናግረዋል። የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ሊወጣለት እንደሚገባም አመላክተዋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ፤ የሪፖርቱ ዓላማ የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ግዴታቸውን በምን ያህል መጠን እየተወጡ ነው የሚለውን ለማመላከትመሆኑን ገልጸዋል።   የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የሀገርን ሰላም እየፈተነ በመሆኑ ለዘላቂ መፈትሄ ለማሻትም የሪፖርቱን አስፈላጊነት አንስተዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም በኢትዮጵያ ለሚከሰቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የጥላቻ ንግግሮች እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ትልቁን ድርሻ የሚይዝ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚድያ የሚሰራጩ የጥላቻና ሀሰተኛ ንግግሮችን በህግ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 1185/12 የተደነገገ መሆኑ ይታወቃል።
ኮሚሽኑ በወረዳ ደረጃ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወክለው በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ እያካሄደ ነው
Apr 16, 2024 123
ሀዋሳ ፤ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሻሸመኔ ክላስተር በወረዳ ደረጃ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወክለው በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ እያካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ በኮሚሽኑ የኦሮሚያ ተሳታፊ ልየታ ቡድን አስተባባሪ አቶ ብዙነህ አስፋ ለኢዜአ እንደገለጹት በኮሚሽኑ ዕቅድ መሰረት በክልሉ በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ እየተካሄደ ይገኛል።   በኦሮሚያ ክልል የማህብረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ልየታ በአራት ክላስተር ተከፍሎ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው የዛሬው የሻሸመኔው ክላስተር የመጨረሻው ዙር መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ ተወካዮች ልየታ መድረክ ላይ ከምስራቅ ጉጂ ዞን 11 ወረዳዎች የተውጣጡ ከ 1 ሺህ በላይ የተለያዩ ህብረተሰብ ወኪሎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት በመድረኩ የሀገራዊ ምክክር ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም የአመራረጥ ሂደቱን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻና ማብራሪያ ለተሳታፊዎች እየተሰጠ ነው። የመድረኩ ዓላማ በሀገር አቀፍ ምክክሩ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦች “ልየታ” አካታች እና አሳታፊ እንዲሁም ሂደቱ ሁሉም የተስማማበት እና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን ለማስቻል መሆኑን አስረድተዋል። በሻሸመኔ ከተማ ዛሬ የተጀመረው በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት እስከ ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቆይ አመላክተዋል። እንደ አቶ ብዙነህ ገለፃ በሻሸመኔ ክላስተር ውስጥ የተካተቱ ዞኖች ባሌ፣ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምስራቅ ጉጂ ናቸው።  
በክልሉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለሚያሳድጉ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷል-- አቶ እንዳሻው ጣሰው
Apr 16, 2024 136
ሆሳዕና፤ ሚያዝያ 8/2016(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለሚያሳድጉ ተግባራት ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ እንዳሻው ጣሰው ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት በክልሉ ባለፉት ወራት በተለያየ መስክ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ቀጣይ የሚሰሩትን ለይቶ ወደሥራ ተገብቷል። በተለይም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለሚያሳድጉ ተግባራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ወደሥራ መገባቱን ገልጸዋል። በትምህርት፣ በጤናና ግብርና ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ለአብነት የጠቀሱት አቶ እንዳሻው፣ በትምህርት ዙሪያ ባለፈው ዓመት በብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የገጠመውን የውጤት ማሽቆልቆል ችግር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ለዚህም የትምህርት ቤቶች ደረጃን በማሻሻል ለመማር ማስተማር ሥራው ምቹ ከማድረግ ጎን ለጎን 10 ሺህ መምህራንና ርዕሰ መምህራን በኢዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ትግበራ ላይ ስልጠና አግኝተው ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን አመልክተዋል። በጤናው ዘርፍም የጤና ተቋማትን ከማስፋፋት ባለፈ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ህዝቡ የሚያነሳቸውን ችግሮች ለመፍታት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በክልሉ የማህበረሰብ ጤና መድህን አገልግሎትን በማጠናከር በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አቶ እንዳሻው ተናግረዋል። ገበያ በማረጋጋት፣ ለምሩቃን የሥራ ዕድል በመፍጠር እና በኢንቨስትመንት ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል። እንደ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ የግብርናን ውጤታማነት ለማጠናከር ለመስኖ ልማትና ለሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። ክልሉ ለም መሬትና የውሃ አማራጭ እንዳለው ያነሱት አቶ እንዳሻው፣ በዘርፉ እየተመዘገበ ያለውን አመርቂ ውጤት ለማጠናከር ትኩረት መሰጠቱንም ገልጸዋል። በመሰረተ ልማት በተለይ የመንገድ ልማት ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ካለው አበርክቶ አንጻር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ እንዳሻው፣ በዚህም የዞን፣ ወረዳና ቀበሌ ተደራሽ መንገዶች ግንባታና ዕድሳት ሥራዎች ይከናወናሉ ብለዋል። በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ለማጠናከር እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጠንካራ መሆኑን ገልጸው፣ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ የህዝብን የልማት ጥያቄዎች ለመፍታት እየተደረገ ላለው ስራ ስኬታማነት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም አቶ እንደሻው ጠይቀዋል። የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ክልሉ ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ አቅዶ በንቅናቄ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በክልሉ በቀጣይ ወራት ለማከናወን የተለዩ የልማት ሥራዎችን በተሳካ መልኩ ለማከናወን የሀብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል። ህብረተሰቡ በየአካባቢው ለልማት ሥራዎች ስኬታማነት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።    

ማህበራዊ
የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በተቀናጀ መልኩ መጠናከር አለበት - ጤና ሚኒስቴር
Apr 16, 2024 53
ሀዋሳ ፤ሚያዚያ 8/2016 (ኢዜአ)፦የኤች አይ ቪ/ኤድስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች በተቀናጀ መልኩ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ሀገር አቀፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም የጋራ ግምገማ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።   በግምገማው ላይ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ እንደገለጹት የኤች አይቪ /ኤድስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች ሊጠናከሩ ይገባል። ከዚህ ቀደም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችና አካባቢዎች ላይ በማተኮር ከግንዛቤ ማስጨበጫ ጀምሮ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መገኘቱን አስታውሰዋል። “በፈቃደኝነት ምርመራ የማድረግ ልምድ ማደግና አጋላጭ ምክንያቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ የስርጭት ምጣኔውን በሀገር ደረጃ ከአንድ በመቶ በታች ማድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተፈጠረ መዘናጋት የበሽታው የስርጭት መጠን ከፍ እያለ መምጣቱን ጠቅሰው፣ የህብረተሰቡን መዘናጋት በማስወገድ ስርጭቱን ለመግታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። አቶ ፍቃዱ እንዳሉት ቀደም ሲል በተሰሩ ሥራዎች የተገኘው ስኬት በሁሉም ባለድርሻ አካላት ላይ መዘናጋት እንዲፈጠር አድርጓል። ይህም በአሁኑ ወቅት ለሚታየው የበሽታው ስርጭት መጠን መጨመር ምክንያት መሆኑን ጠቅሰው፣ መዘናጋቱን አስወግዶ ስርጭቱን ለመቆጣጠር አቅምን በማስተባበር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ ዘርፉ እንዳሉት፣ በክልሉ ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት የበሽታውን ስርጭት የመቆጣጠር ሥራ እየተሰራ ነው።   ባለፉት ዘጠኝ ወራት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችና የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት ተደርጎ በተሰራው ሥራ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በፈቃደኝነት የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ማድረጋቸውንና 5 ሺህ የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው እንደተገኘባቸው ገልጸዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ወደሕክምና ክትትል ገብተው መድሀኒት እንዲጀምሩ ለማድረግ በተሰራው የማማከር ሥራም 95 በመቶ የሚሆኑት መድሀኒት ጀምረዋል ብለዋል። የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አስመላሽ አበራ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በክልሉ በተለይ ከፍተኛ የወርቅ ማዕድን የሚገኝባቸውና የኢንቨስትመንት አካባቢዎች ላይ በሽታውን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።   በክልሉ ከባህል ጋር ተያይዞ የወንዶች ግርዛት በማይፈጸምባቸው አካባቢዎች ያለውን የኤች አይ ቪ ተጋላጭነት ለመቀነስም የግንዛቤ ማጎልበቻ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። በክልሉ የቫይረሱ ስርጭት 3 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑን የጠቀሱት አስተባባሪው፣ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከጤና ሚኒስቴር እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለአራት ቀናት በሚካሄደው የግምገማ መድረክ የሁሉም ክልሎች የኤች.አይ.ቪ ዘርፍ ሀላፊዎችና አጋር ድርጅቶች የተገኙ ሲሆን የክልሎች አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ታውቋል።    
ለሀገር ዘላቂ ሰላምና አብሮነት ያለ ምንም ልዩነት ሁሉም በጋራ ሊቆም ይገባል - የሃይማኖት መሪዎች
Apr 16, 2024 190
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- ለሀገር ዘላቂ ሰላምና አብሮነት ያለ ምንም ልዩነት ሁሉም በጋራ ሊቆም ይገባል ሲሉ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ገለጹ። የሰላም ጉዳይ የሀገር ህልውና መሠረትና የዜጎችም ሁለንተናዊ ዋስትና በመሆኑ የጋራ ጥረትና ትብብር የሚጠይቅ መሆኑ ይታወቃል። በሰላምና ልማት እንዲሁም በመልካም ስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ በመገንባት ረገድ በተለይም ደግሞ የሃይማኖት ተቋማት ድርብ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይነሳል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ከምንም በላይ የሰላም ጉዳይ የሁላችንም የጋራ አጀንዳ መሆን አለበት ብለዋል። ከግጭት አዙሪት በመውጣት ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የዜጎች ሁሉ ትብብር ሊታከልበት ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፤ የሰላም ጉዳይ የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ ለሰላማችን በጋራ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል። የሰላም መጓደል ሲያጋጥም የበርካታ ውስብስብ ችግሮች ምክንያት መሆኑን የተለያዩ አገራትን ነባራዊ ሁኔታ ማየት በቂ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ መቆም ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል። በተለይም የሃይማኖት ተቋማት የሰላምን ጉዳይ የመደበኛ ሥራቸው አካልና የዘወትር ተግባራቸው አድርገው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡ በእስልምና እምነት የአብሮነት፣ የሰላምና የሰብዓዊነት ጉዳይ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ጠቅሰው፤ ይኸው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሊቀ-አይላፍ ቀሲስ እያሱ ናሁሰናይ፤ በሀገር ሰላም ጉዳይ በጋራ ለመሥራት የሁሉም ጥረትና ዝግጁነት ግድ መሆኑን ገልፀዋል። በተለይ አሁን ላይ እንደ ሀገር እየገጠሙን ላሉ ችገሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመሻት በሚደረገው ጥረት ቤተክርስቲያኗ የሚጠበቅባትን ሚና ለማበርከት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።   የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ፤ በምድር ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን መፀለይና ማስተማር የጋራ እሴቶቻችን ናቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚከሰቱ ችግሮችን በንግግር መፍታት ሁነኛ አማራጭ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ የሃይማኖት ተቋማት ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለሀገር ሰላም ለሚደረጉ ሁለንተናዊ ጥረቶች የድርሻዋን የምትወጣ መሆኑንም አረጋግጠዋል።   የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ-ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝዳንት ፓስተር ፃዲቁ አብዶ በበኩላቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት በሰላምና ልማት ዙሪያ አብሮነትና የጋራ ጥረታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልፀዋል። በግጭትና ጦርነት ሞትና ኪሳራ እንጂ አንዳችም የሚገኝ ውጤትና መፍትሔ አለመኖሩን ጠቅሰው፤ ሁላችንም የሰላም እጆቻችንን ልንዘረጋ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።    
የዕድሮችና የዕድር ምክር ቤቶች የምዝገባና የዕውቅና አሰጣጥ መመሪያ ወደ ሥራ ገባ 
Apr 16, 2024 102
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የዕድሮችና የዕድር ምክር ቤቶች የምዝገባና የዕውቅና አሰጣጥ መመሪያ 151/2016 ተግባራዊ መሆን መጀመሩን የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ። የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ መመሪያውን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዕድሮች ምክር ቤቶች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል። በቅርቡ ወደ ሥራ የገባው ይህ መመሪያ የተዘጋጀው ዕድሮች ሕጋዊ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ታሪካዊና የመደጋገፍ ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ የሚመዘገቡበትና ዕውቅና የሚያገኙበት ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ መሆኑን ተጠቅሷል። ዕድሮች ከቀብር ማስፈጸም ባሻገር በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ አባሎቻቸውንና የከተማውን ነዋሪ ጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከተው አካል ድጋፍ የሚያገኙበት ሥርዓት ለመዘርጋት መሆኑን በመመሪያው ተመላክቷል። በመመሪያው መሠረት በአዲስ አባበ የሚገኙ ሁሉም እድሮችና የእድር ምክር ቤቶች ምዝገባ እንደሚያካሂዱና በየዓመቱ እድሳት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል። ይህንንም ተከትሎ የዘንድሮ ምዝገባ ከመጪው ሓምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይጀምራል ተብሏል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ ገነት ቅጣው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ዕድሮች አሰራራቸውን በማዘመን ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ጠብቀው የአሰራር ሥርዓትን በማበጀት በማኅበራዊና ኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲያሳድጉ ዕድል የሚሰጥ ነው። ዕድሮች የኅብረተሰቡን አብሮ የመኖር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ እሴት በነፃነት ለማራመድ በዘመናዊ መልክ እንዲደራጁ መመሪያው ይጋብዛል ብለዋል። ይህም እድሮች ኢትዮጵያዊ እሴቱን ጠብቆ በዘመናዊ መልክ ተደራጅተው ለትውልድ እንዲተላለፉ እንደሚያስችል አስረድተዋል። ዕድሮችና የዕድር ምክር ቤቶች የአሰራር ሥርዓታቸውን በማዘመን ከአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በዳታቤዝ ለማስተሳሰር እንደሚሰራም ተናግረዋል።   የአዲስ አበባ ዕድሮች ጥምረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ታምራት ገብረ ማርያም በበኩላቸው ዕድሮች ከቀብር ማስፈጸም ባሻገር ወደ ልማት በመግባት አሰራራቸውን ከማዘመን ባለፈ አቅማቸውንም የሚያጎለብት መመሪያ መሆኑን ገልጸዋል። የዕድሮችና የዕድር ምክር ቤቶች የምዝገባና የዕውቅና አሰጣጥ መመሪያ ለሌሎች ክልሎችም አርአያ የሚሆንና ዕድሮችን ለማገዝ ድጋፍ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የአሰራር መመሪያው ቀጣይ ሥራቸውን ለማጠናከር ሕጋዊ አቅም በመሆን ከመንግሥት የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚያስችል ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ከ7 ሺህ 500 በላይ ዕድሮች እንዳሉ ፕሬዝዳንቱ አቶ ታምራት ገልጸዋል።  
የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የህክምና ባለሙያዎች ለሴቶች ጤና ድጋፍ የሚያደርግ በጎ አድራጎት ማህበር አቋቋሙ 
Apr 16, 2024 140
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 8/2016(ኢዜአ)፦የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የህክምና ባለሙያዎች "ሔዋን" የተሰኘና ለሴቶች ጤና ድጋፍ የሚያደርግ በጎ አድራጎት ማህበር ማቋቋማቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የማህጸንና ጽንሰ ስፔሻሊስት ሃኪምና የማህበሩ የቦርድ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ድልአየሁ በቀለ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት በሆስፒታሉ ወሊድን ጨምሮ የማህጸንና የጡት ካንሰር፣ የኩላሊት ህክምናና ሌሎች ውስብስብ የጤና አገልግሎቶች ይሰጣሉ። ህክምናውን ፈልገው ከሚመጡ ተገልጋዮች መካከል እናቶች፣ሴቶችና ህጻናት ትልቁን ቁጥር እንደሚይዙ ጠቁመው፤አብዛኞቹ የመረጃና የፋይናንስ እጥረት እንዳለባቸው አብራርተዋል። በተለይ ለህክምና የሚያስፈልጋቸውን ወጪ ለመሸፈን የገንዘብ እጥረት እንደሚያጋጥማቸውና የተገልጋዮች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ነው ያነሱት፡፡ ይህም ካጋጠማቸው የጤና እክል ባልተናነሰ መልኩ ኢኮኖሚያዊ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በሆስፒታሉ በጎ ፍቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች ተነሳሽነት ''ሔዋን'' የተሰኘ ለሴቶች ጤና ድጋፍ የሚያደርግ በጎ አድራጎት ማህበር ተመስርቷል ብለዋል።   በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት እና የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ወንድሙ ጉዱ በበኩላቸው ማህበሩ የህክምና እርዳታ የሚያገኙ እናቶች ያሉባቸውን የግንዛቤ ክፍተት መሙላት ላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ለሚያጋጥማቸው የፋይናንስ እጥረት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ህክምናቸው እንዳይስተጓጎል ማድደረግም ዋነኛው ተግባር መሆኑን አስረድተዋል። አንዳንድ የህክምና ሂደቶች ረዥም ጊዜን የሚወስዱ በመሆናቸው ታካሚዎቹ በተረጋጋ ሁኔታ ህክምናቸውን እንዲከታተሉ ጊዜያዊ ማረፊያ የማቋቋም እቅድ መያዙንም ጠቁመዋል። መንግስት የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በጤና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ፋጡማ ሰኢድ ናቸው።   በተለይም የእናቶችና ህጻናት ሞት ቅነሳ ላይ ትኩረት በማድረግ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት ቢመዘገብም አሁንም ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡   የሔዋን የሴቶች የጤና ድጋፍ በጎ አድራጎት ማህበር በጎ ፍቃደኛ አምባሳደር አርቲስት የትናየት ታምራት፤ ሁሉም ለድርጅቱ የአቅሙን እገዛ በማድረግ ለእናቶችንና ህጻናትን ሞት ቅነሳ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ አቅርባለች፡፡                    
ኢኮኖሚ
በክልሉ አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ አቅርቦ ተጠቃሚ እንዲሆን ለመሰረተ ልማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል
Apr 16, 2024 59
ሚዛን አማን ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ለገበያ አቅርቦ ተጠቃሚ እንዲሆን ለመሠረተ ልማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ። በደቡብ ቤንች ወረዳ በ18 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የዛን ወንዝ ድልድይ የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በወቅቱ እንደገለጹት፣ አርሶ አደሩ ከሚያመርታቸው የግብርና ምርቶቹ የተሻለ ተጠቃሚ መሆን እንዲችል የመንገድና የድልድይ መሠረተ ልማቶች ትልቅ ሚና አላቸው። በመሆኑም አርሶ አደሩ ምርቱን ገበያ እውጥቶ የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ የክልሉ መንግስት ለድልድይና ለመንገድ መሰረተ ልማቶች ልዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል። በዛሬው ዕለትም በደቡብ ቤንች ወረዳ በ18 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የዛን ወንዝ ድልድይ የመሰረተ ድንጋይ መቀመጡን ገልጸው፣ በሌሎችም አካባቢዎች መሰል የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። የደቡብ ቤንች ወረዳ በልማትና የግብርና ኤክስቴንሽን ስርፀትን ተግባራዊ በማድረግ በክልሉ ካሉ ወረዳዎች ግንባር ቀደም ወረዳ መሆኑንም አመልክተዋል። ወረዳው ከ500 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ በኩታ ገጠም የለማ ሙዝ ያለው ብቸኛ ወረዳ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህን የልማት አቅም ለማሳደግ ለመሠረተ ልማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። ድልድዩ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ህዝብን ከህዝብ እንዲሁም ምርትና ገበያን እንደሚያገናኝ ተናግረዋል።   የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልዱ በጪ በበኩላቸው እንደገለጹት በአካባቢው ከፍተኛ የቡና፣ የበቆሎ፣ የሙዝ እና የቅመማ ቅመም ምርቶች ቢኖሩም የመሠረተ ልማት ችግር ያለበት ነው። የአካባቢው አርሶ አደሮች የግብርና ምርት በጀርባቸው ተሸክመው ለገበያ እንደሚያወጡ ጠቁመው፤ ወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ችግሩን ለመቅረፍ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ሦስት ድልድዮችን ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን ተናግረዋል። በቀጣይም የሕዝቡን ድጋፍ በማጠናከር የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄን ለመመለስ በትኩረት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።   የድልድዩን የግንባታ ሥራ የሚያከናውነው "ተስፋዬ አሰፋ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ" ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አሰፋ በበኩላቸው ግንባታውን በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ እንደሚሠሩ ተናግረዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል የጃንቹታ ቀበሌ አርሶ አደር አዳሙ አኩሙ "መንግስት የመንገድ ችግራቸውን ለመፍታት የጀመራቸው የልማት ሥራዎች በእርሻ ሥራችን የተሻለ ተጠቃሚ እንድንሆን የሚያስችል ነው" ብለዋል። እስከዛሬ ያመረቱትን የበቆሎ፣ የቡናና የሙዝ ምርት በሸክምና በፈረስ ጭኖ ለገበያ የሚያቀርቡበትን አድካሚ ሁኔታ እንደሚያስቀርላቸው የተናገሩት ደግሞ በአካባቢው የኮብ ቀበሌ አርሶ አደር አብዮት ካሽት ናቸው። በመንገድና ድልድይ እጦት ምክንያት ምርቶቻቸውን ሽጠው ለመጠቀም ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰው ድልድይ ሲጠናቀቅ ችግራቸውን እንደሚቃለል ተናግረዋል። በመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።        
በአገር አቀፍ ደረጃ  ገበያውን ለማረጋጋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ
Apr 16, 2024 49
ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 8/2016 (ኢዜአ)፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ ገበያንና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ ገለጹ ። በሚኒስትሩ የተመራ ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወራቤና ቡታጅራ ከተሞች የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን በመስክ ተመልክቷል። በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ እንዳሉት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ስልቶችን በመከተል ገበያንና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተለይም ገበያውን ለማረጋጋት የምርት መጠን ማሳደግ ላይ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል። ለዚህም በየአካባቢው አርሶ አደሩ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና እንዲሁም ያለውን አማራጭ ተጠቅሞ እያደረገ ያለውን ጥረት ጠቅሰዋል። እንዲሁም የሸማችና ህብረት ስራ ማህበራትንና ዩኒየኖችን በማጠናከርና በመደገፍ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአምራች ኢንዱስትሪው፣ በህብረት ስራ ማህበራትና በዩኒየኖች እየተከናወነ የሚገኘው ተግባር የሚበረታታ ነው ብለዋል። በዚህም ምክንያት አልባ በሆነ የዋጋ ጭማሪና ህዝብን ለምሬት የሚዳርጉ አካላትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር መኖሩን በመስክ ምልከታው ማረጋገጥ መቻላቸውን ገልጸዋል።   የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ማሶሬ፤ በክልሉ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት አደረጃጀትና የቁጥጥር ስርዓትን የማጠናከር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል በዚህም አርሶ አደሩ፣አምራች ኢንደስትሪውና የሸማቾች ህብረት ማህበራት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል አደረጃጀት መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል። በክልሉ "ከሳምንት እስከ ሳምንት" በሚል ተነሳሽነት ሸማቹንና አምራቹን በቀጥታ የሚያገናኘው ገበያ ያለማቋረጥ እንዲቀጥልና ምርት በሚደብቁት ላይ በሚደረግ ቁጥጥር ውጤት መምጣቱን ጠቅሰዋል። በክልሉ ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ አማራጮችን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል። ቡታጅራ ከተማ የ"አገልግል ሸቀጣሸቀጦች ማከፋፈያ" ህብረት ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ገላን በበኩላቸው፤ ማህበሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ 200 አባላት ይዞ ወደስራ መግባቱን ገልጸዋል። በወቅቱ አስተዳደሩ ባደረገው ድጋፍና በአባላቱ አስተዋጽኦ በ2 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ስራ የጀመረው ማህበሩ ነዋሪውን መጥቀም ብቻ ተጠቃሚ በመሆኑ ገቢው መጨመሩን ተናግረዋል። "ከሳምንት እስከ ሳምንት ገበያ“ ሳምንቱን ሙሉ የግብይት ስርዓት ተግባራዊ መደረጉ አስፈላጊውን ግብዓት ተመቻችቶላቸው እንዲሸምቱ ማስቻሉን የተናገሩት ደግሞ በወራቤ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ሂክማ ነስረዲን ናቸው። በሚኒስትሩ የተመራው ቡድን በሁለቱም ከተሞች በዩኒየኖችና በሌሎች አደረጃጀቶች ገበያንና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።        
በሲዳማ ክልል ከ28 ሚሊዮን በላይ የተሻሻሉ የቡና ችግኞች ለተከላ ተዘጋጁ
Apr 16, 2024 188
ሀዋሳ፤ ሚያዚያ 8/ 2016 (ኢዜአ) ፡- በሲዳማ ክልል የቡናን ልማትን ለማስፋፋት ከ28 ሚሊዮን በላይ የተሻሻሉ የቡና ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። በተጨማሪም 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአቦካዶ ችግኞችም መሰናዳታቸውም ቢሮው ገልጿል።   የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የቡናና ፍራፍሬ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬው በሸበዲኖ ወረዳ በይፋ በተጀመረበት ውቅት የቢሮው ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በክልሉ የቡና ምርታማነትን በጥራት ለማሳደግ ለተሻሻሉ የቡና ዝርያ ትኩረት ተሰጥቷል። በክልል እስካሁን 165 ሺህ ሄክታር መሬት በቡና ተክል መሸፈኑን አውስተው፤ ልማቱን ለማስፋፋት ዘንድሮ 10 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኞች እንደሚተከሉ አስረድተዋል። ለዚህም ከ28 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኞች መዘጋጀታቸውን አሰታውቀዋል። ከተከላው ጎን ለጎንም ያረጁ ቡናዎች ነቀላና ጉንደላም በትኩረት ይከናወናል ብለዋል። በተጨማሪም እየተካሄደ ያለውን ልማት ለማስፋፋት ዘንድሮ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአቦካዶ ችግኞች መሰናዳታቸውን ገልጸዋል። በዚህም 4 ሺህ 500 ሄክታር አዲስ መሬት እንደሚለማ ጠቅሰው፤ የፍራፍሬ ችግኝ ተከላውም ከአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጋር ተቀናጅቶ የሚካሄድ መሆኑን አስረድተዋል። የሲዳማ ክልል ቡና ፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ቃሬ በበኩላቸው፤ በክልሉ በሄክታር የሚገኘውን 9 ነጥብ 5 ኩንታል የቡና ምርት ወደ 11 ነጥብ 5 ለማሳደግ መታቀዱን ገልጸዋል።   ለዚህም የቡና ምርትና ምርታማነት የሚጨምረው ፓኬጅ ሙሉ በሙሉ ለመተግባር አርሶ አደሩን ባለሙያውና አመራሩን ግንዛቤ በማሳደግ የቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የቡናን ምርታማነት ለመጨመር የተፈጥሮ ማዳበሪያ በማዘጋጀት ተፈጥሯዊ ቡና ለአለም ገበያ ለማቅረብና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰዋል። ለዚህም 3 ነጥብ 2 ቶን የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል። ክልል አቀፍ የቡናና ፍራፍሬ ችግኝ ተከላ የተጀመረበት የሸበዲኖ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ አየለ፤ በወረዳው ከ10 ሺህ 250 ሄክታር በላይ መሬት በቡና ልማት የተሸፈነ እንዳለ ተናግረዋል።   ዘንድሮ የቡና ሽፋኑን ለማሳደግ በ527 ሄክታር አዲስ የቡና ተከላ እንደሚከንና ከ1 ሚሊዮን በላይ የተሻሻለ ዝርያ የቡና ችግኞች መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል። በሸበዲኖ ወረዳ የፉራ ቀበሌው አርሶአደር ካሳ ተኮን በሰጡት አስተያየት፤ ዘንድሮ 1ሺ 500 የተሻሻሉ የየቡና ችግኞችን እንደሚተክሉ ገልጸዋል።   በማሳቸው በተካሄደ የተከላ መርሃ ግብርም በርካታ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው፤ ከዛሬ ጀምሮ እስኪ ሚያዚያ አጋማሽ ባለው የተከላው ተግባር እንደሚያጠናቅቁ ተናግረዋል። ክልል አቀፉ የቡናና ፍራፍሬ ችግኝ ተከላ በሸዲኖ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች መጀመሩንና በዚህም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።      
በክልሉ የመሬት አጠቃቀም  ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል  ትኩረት ተሰጥቷል 
Apr 16, 2024 127
አሶሳ ፤ ሚያዝያ 8/2016(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአርሶ አደሩን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ ውስጥ በመሬት አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን ገለጹ። በክልሉ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ማሻሻል ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ ፤ የብልጽግናችን ቀዳሚ ትኩረት የአርሶ አደሩን ህይወት ከመሰረቱ መለወጥ ነው ብለዋል። ይህን መሠረት በማድረግ የክልሉን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በማልማት ወደ ሃብት ለመቀየር በተደረገ ጥረት ውጤቶች ቢኖሩም አሁንም በመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ዘርፍ ያልተሻገርናቸው አፋጣኝ መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮች አሉ ሲሉ ገልጸዋል። አርሶ አደሩ መሬቱን በህገወጥ መንገድ ማከራየት፣ አንዳንዶች መሬታቸውን ባልተገባ መንገድ ለሌሎች አሳልፈው መስጠትና ህገወጥ ይዞታን ማስፋፋት ችግሮች መታየታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። የክልሉ መንግስት አዋጅ አውጥቶ ተግባራዊ ከማድረግ ባሻገር ለአርሶ አደሩ ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በመስጠት ጥረት ተደርጓል ብለዋል።   ከዚህ በተጓዳኝ በተቋማት የሚታየውን የማስፈጸም አቅም ውስንነት ፣የስነምግባር ችግርና ውጣ ውረድ የበዛበት አሰራር ፣እንዲሁም የመሬት ልኬትና ምዝገባን መሰረት ተከትሎ ያለመስራት ክፍተቶችን ለማስተካከል ትኩረት መሰጠቱ አቶ አሻድሊ ገልጸዋል። በመሬት አስተዳደር ጉዳይ የሚታዩ ችግሮችን ለዘርፉ ተቋማት ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን የአቶ አሻድሊ አስገንዝበዋል። በንቅናቄው መድረክ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት ፣በየደረጃው የሚገኙ የመሬት አስተዳደር ተቋማት ተወካዮች ፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል።    
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በዩኒቨርሲቲው እየተገነባ ያለው የባዮ ጋዝ ማብላያ ፕሮጀክት የተቋሙን የሃይል ችግር ከመፍታት ባለፈ የግብርና ሥራን ያሳልጣል 
Apr 16, 2024 149
ሶዶ ፤ሚያዝያ 8/2016 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ያለው የባዮ ጋዝ ማብላያ ፕሮጀክት የተቋሙን የሃይል ችግር ከመፍታት ባለፈ፤ ለአካባቢው ግብርና ልማት መሳለጥ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። ፕሮጀክቱ በአገሪቱ በዓይነቱ የመጀመሪያውና በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚከናወን ሲሆን፣ ከሁለት ወራት በኋላ ለአገልግሎት እንደሚበቃም ተገልጿል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ የሚመራ የፌዴራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ቡድን ዛሬ ፕሮጀክቱን ጎብኝቷል። ሚኒስትር ደኤታው ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፣ በዩኒቨርሲቲው እየተገነባ ያለው ባለ 300 ሜትር ኪዩብ የባዮ ጋዝ ማብላያ ፕሮጀክት በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው።   የፕሮጀክቱ ግንባታ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ 25 ኪሎ ዋት ሃይል ማመንጨት እንደሚችልም አስታውቀዋል። ከባዮ ጋዙ የሚመነጨው ሃይል የተቋሙን የሃይል ችግር ከማቃለል ባለፈ፤ ከባዮ ጋዝ የሚገኘው ተረፈ ምርት የግብርና ልማት ሥራዎችን ለማከናወን እንደሚያስችል አስረድተዋል። በተጨማሪም የአካባቢው አርሶ አደሮች የባዮ ጋዙን ተረፈ ምርቱን በመጠቀም ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ያስችላቸዋል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው። እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ በኢትዮጵያ እስካሁን በግለሰብ ደረጃ በተገነቡ አማራጭ የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሆኑ 46 ሺህ አባወራዎች ናቸው።   የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትልና የማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ኦላዶ ኦሎ በበኩላቸው በክልሉ በቤተሰብ ደረጃ የተገነቡ ባዮ ጋዝ ፕሮጀክቶች በርካታ አባወራዎችን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል። አሁን ላይ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ያለው ፕሮጀክት በዓይነቱ ከፍተኛ የሆነና በተቋም ደረጃ እየተካሄደ ያለ ፕሮጀክት መሆኑን አመልከተዋል። ይህም የክልሉን ሃይል የማመንጨት አቅም ከማሳደግ ባለፈ የአካባቢውን አርሶ አደሮች በግብርና ልማት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አቶ ኦላዶ ተናግረዋል።   የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በግብርናና በማዕድን ሀብት ልማት የልህቀት ማዕከል ለመሆን አቅዶ እየሠራ ነው ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አሸናፊ አበበ ናቸው። ፕሮጀክቱ ዩኒቨርሲቲው እያከናወነ ያለውን የግብርና ሥራን ከማገዝ ባለፈ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን ለማከናወን ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ፕሮጀክቱ ከሁለት ወራት በኋላ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም አቶ አሸናፊ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ከአምስት ሚሊዮን በላይ አባወራዎችን ከባዮ ጋዝ በሚመነጭ ሃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ አቅም እንዳላት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል።  
ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ይፋ ያደረገው ተናባቢ "ኪው አር ኮድ" ምንድን ነው? ምን ዓይነት ጥቅምስ ይኖረዋል? 
Apr 16, 2024 100
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያለጥሬ ገንዘብ ፈጣንና ቀልጣፋ የክፍያ ሥርዓት መፈጸም የሚያስችል ተናባቢ "ኪው አር ኮድ" አገልግሎት ይፋ አድርጓል። መንግሥት የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓቱን ለማዘመንና ዜጎች ሁሉን አቀፍ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ነው። በዚህም አሁን ላይ በኢትዮጵያ ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ምኅዳር እየሰፋ መሆኑን ነው በብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሒሳብ ማወራረጃ ሥርዓት ዳይሬክተር ሰለሞን ዳምጠው የሚናገሩት። ይህንንም ተከትሎ ዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ የክፍያ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በባንክ ሒሳባቸው አማካኝነት የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን መጠቀም የሚያስችላቸውን መሠረተ-ልማት እየተሟላ መሆኑን ገልፀዋል። ከእነዚህም መሠረተ-ልማቶች መካከል በ"ኪው አር ኮድ" አማካኝነት የሚፈጸሙ ክፍያዎች አንደኛው መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህም አንድ ግለሰብ ደንበኛ ከሆነበት ባንክ ወይም ከሚጠቀመው የሞባይል ዋሌት ባገኘው "ኪው አር ኮድ" ጋር ተዛማጅ በሆነ ሥርዓት በማናበብ ክፍያ መፈጸም ይችላል። አሁን ላይ ደግሞ ከዚህ ቀደም በተዘበራረቀ "ኪው አር ኮድ" አማካኝነት የሚፈጸሙ ክፍያዎችን ወጥና ተናባቢ በማድረግ አንዱ የሌላኛው መጠቀም የሚያስችል "ኪው አር ኮድ" ይፋ መሆኑን ነው የገለጹት። ይህም አንድ ግለሰብ የየትኛውም ባንክ ደንበኛ ወይም የሞባይል ዋሌት ተጠቃሚ ቢሆንም ክፍያውን በ"ኪው አር ኮድ" እርስ በርስ በማናበብ መክፈል እንደሚቻል ተጠቅሷል። እንደ እርሳቸው ገለፃ፤ ተናባቢ "ኪው አር ኮድ" ዜጎችም ደንበኛ በሆኑበት የፋይናንስ ተቋም ያገኙትን "ኪው አር ኮድ" በእጅ ስልክ በማስነበብ የትኛውንም ዓይነት ክፍያ መፈጸም የሚያስችላቸው የአገልግሎት ሥርዓት ነው። ደንበኞች በ"ኪው አር ኮድ" ክፍያ በሚፈጽሙበት ወቅት የደንበኛ ስም፣ የሒሳብ ቁጥር፣ የባንክ አድራሻና የግብር ከፋይ መለያ በአንድ ቦታ በቀላሉ በማስነበብ ክፍያን መፈጸም እንደሚያስችል ተናግረዋል። ዜጎችም የትኛውንም ዕቃና አገልግሎት ግዥ ሲፈጽሙ የንግድና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በሚያስቀምጡት "ኪው አር ኮድ" አማካኝነት ክፍያን በቀላሉ መፈጸም ያስችላቸዋል ብለዋል። ይህም በንግድ ሥርዓቱ ላይ የሚፈጸመውን የጥሬ ገንዘብ ክፍያ በእጅ ስልክ የዲጂታላይዝ ሥርዓት በመተካት ፈጣንና ቀልጠፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ገልፀዋል።   የኢትስዊች አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይላበስ አዲስ፤ የፋይናንስ ተቋማት በተናጠል የሚሰጡበትን የተበታተነ አገልግሎት ወጥና ተናባቢ የሆነ የ"ኪው አር ኮድ" ይፋ በማድረግ ዜጎች ቀላል ክፍያ የሚፈጽሙበት ምኅዳር መፈጠሩን ተናግረዋል። በንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በሚቀመጡ ፖስ ማሽን፣ የክፍያ ካርድ፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በሲቢኢ ብር ዋሌት፣ አሊያም በሽያጭ መሳሪያ ክፍያ የሚፈጸምባቸው አገልግሎቶች ከፍተኛ ዋጋን እንደሚጠይቁ አንስተዋል። የ"ኪው አር ኮድ" ግን በዝቅተኛ ወጪ በማንኛውም የንግድ ድርጅትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቀላሉ በማስቀመጥ ደንበኞች በቀላሉ በእጅ ስልካቸው አንብበው መፈጸም ይችላሉ ብለዋል። የ"ኪው አር ኮድ" በቀላል ወጪና በብዙ እጥፍ በማባዛት ዜጎች በታክሲ፣ በጫማ ፅዳትና ዕድሳትን ጨምሮ ከቀላል እስከ ከፍተኛ የክፍያ አገልግሎት መፈጸም እንደሚችሉ አስታውቀዋል። በኢትስዊችና በብሔራዊ ባንክ ትብብር ማንኛውም የፋይናንስና የንግድ ተቋም እንዲሁም ተገልጋይ በ"ኪው አር ኮድ" አማካኝነት ቀላል ክፍያ የሚፈጸምበት ሥርዓት መፈጠሩ ተገልጿል። ባለፈው ሳምንት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ጨምሮ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች በተገኙበት የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል።  
መንግሥት የዳታ ማዕከላት ግንባታ ላይ የሚሰማሩ ኢንቨስተሮች የሚያደርገውን እገዛ አጠናክሮ ይቀጥላል - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
Apr 16, 2024 111
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የዳታ ማዕከላት ግንባታ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራን የሚደግፍ በመሆኑ መንግሥት በዘርፉ ለሚሰማሩ ኢንቨስተሮች የሚያደርገውን እገዛ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ። ዊንጉ አፍሪካ በኢትዮጵያ የገነባው የግል ዳታ ማዕከል ታየር-3 የምስክር ወረቀት ማግኘቱን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ዊንጉ አፍሪካ በአይ ሲቲ ፓርክ የገነባው የዳታ ማዕከል ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ በመገኘቱና እያደገ የሚመጣውን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል መሠረተ-ልማት በመገንባቱ ነው ታየር-3 የምስክር ወረቀት "ከአፕታይም" ከተሰኘው ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩቱ ያገኘው ተብሏል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እያደረገች ላለችው ጉዞ መረጃ ወሳኝ ነው። መረጃ ደኅንነቱ ተጠብቆ መቀመጥና አስፈላጊ በሆነበት ሰዓት መገኘት ያለበት መሆኑን አንስተው፤ መንግሥት ተጨማሪ የዳታ ማዕከላት እንዲገነቡ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ ዊንጉ አፍሪካ፣ ኢትዮ-ቴሌኮምና ሌሎች ተቋማት የዳታ ማዕከላት መገንባታቸውን ጠቅሰው፤ ተጨማሪ የዳታ ማዕከላት እንዲገነቡ ፍላጎት መኖሩን ጠቅሰዋል። የዳታ ማዕከላት ግንባታ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራን የሚደግፍ በመሆኑ መንግሥት በዘርፉ ለሚሰማሩ ኢንቨስተሮች እገዛ እንደሚያደርግም ተናግረዋል። በዊንጉ አፍሪካ የተገነባው መሠረተ-ልማት እውቅና ማግኘቱ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን አቅም የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዳታ ማዕከሉ የእውቀት ሽግግር እንዲሁም የሥራ ዕድል በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።   የዊንጉ አፍሪካ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር ኒኮላስ ሎጂ በበኩላቸው፤ በአይ ሲቲ ፓርክ የተገነባው ዳታ ማዕከል መሠረተ-ልማት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑ ለእውቅና እንዳበቃው ገልፀዋል። እውቅናው ደንበኞች መረጃቸውን ሲያስቀምጡ ደኅንነቱ ጥበቃ ላይ መተማመን እንዲፈጠርላቸው የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል። እውቅናውን የሰጠው "አፕታይም" የተሰኘው ተቋም ከ140 በላይ ለሆኑ አገራት እውቅና መስጠቱን አንስተው፤ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ የገነባው ዳታ ማዕከል እውቅና ማግኘቱ ኢትዮጵያን ከእነዚህ አገራት መካከል እንድትካተት ያስቻላት ነው ብለዋል። ይህም አገሪቱ የያዘችውን የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን በመግለጽ። ዊንጉ አፍሪካ በኢትዮጵያ በቀጣይም ሌሎች ኢንቨስትመንቶችን እንደሚያከናውን ጠቁመው፤ ባገኘው እውቅና ኩራት እንደሚሰማውም ተናግረዋል። ዊንጉ አፍሪካ ግሩፕ በ50 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በአዲስ አበባ አይ ሲቲ ፓርክ ያስገነባውን ዘመናዊ የዳታ ማዕከል የዛሬ ዓመት ገደማ ነበር ያስመረቀው።
ኢትዮ-ቴሌኮም አካታች የዲጂታል ስርዓትን ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል- ፍሬህይወት ታምሩ 
Apr 16, 2024 219
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- ኢትዮ-ቴሌኮም ዲጂታል ፋይናንስን ጨምሮ በሁሉም መስክ አካታች የዲጂታል ስርዓት ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮቴሌኮም "ቴሌ ብር-ኢንጌጅ" የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ትናንት ምሽት ይፋ አድርጓል። በአገልግሎቱ ደንበኞች የቢዝነስ የተናጥል ወይም የቡድን ቀጥታ ውይይቶችን ለማድረግ፣ የግብይት መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣ ገንዘብ ለመላክና ለመቀበል እንደሚያስችል ገልጸዋል። እንዲሁም የቢዝነስ ወይም ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮቻቸውን በፅሁፍ፣ በፎቶ፣ በድምጽ፣ በቪዲዮና በሰነድ መልክ መለዋወጥ ይችላሉ ነው ያሉት። በመረሃ ግብሩ- ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደገለጹት፣ኩባንያው ዲጂታል ኢትዮጵያን በሁሉም ዘርፍ እውን ለማድረግ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።   በተለይ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓቱን ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ "ቴሌ ብር- ኢንጌጅ" መተግበሪያ በዲጂታል ፋይናንስ ሽግግር ውስጥ የንግድ፣ የመንግስትና የግል ተቋማትን ትኩረት በማድረግ የዲጂታል ኢኮኖሚ ምህዳሩን ለማስፋፋት የሚረዳ ነው ብለዋል። ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ የገነባቸው መሰረተ ልማቶች ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን በማገዝ ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ኩባንያው አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደግ ከ3 ዓመት በፊት ይፋ ባደረገው ቴሌ ብር አማካኝነት በየቀኑ የ5 ቢሊዮን ብር ግብይት የሚከናወን ሲሆን፤ በ3 ዓመታት ውስጥ 2 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውር ተደርጎበታል።  
ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከ23ኛ ሳምንት ጀምሮ በሃዋሳ ይካሄዳሉ
Apr 16, 2024 145
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከ23ኛ ሳምንት ጀምሮ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ። የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ደግሞ ሚያዚያ 19 እና 20 ቀን 2016 ዓ.ም ይደረጋሉ። የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ከ16ኛ ሳምንት አንስቶ በድሬዳዋ ስታዲየም እየተከናወነ ሲሆን፥ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎችም ከሚያዚያ 10 እስከ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በድሬዳዋ ይካሄዳሉ። የሊጉ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ዋንጫ ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ ወደ ውድድር ሲመለስ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከሚያዚያ 24 እስከ 27 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አመልክቷል። እስከ 27ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በሃዋሳ እንደሚደረጉም ተገልጿል። ከ28ኛ እስከ 30ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚከናወን ማህበሩ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወቃል። የሊጉ ውድድር ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዱ የሚታወስ ነው።    
26ኛው መላው የኦሮሚያ የስፖርት ውድድር በጅማ ከተማ መካሄድ ጀመረ
Apr 14, 2024 667
ጅማ፣ ሚያዚያ 6/2016(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉበት 26ኛው መላው የኦሮሚያ የስፖርት ውድድር ዛሬ በጅማ ከተማ መካሄድ ጀመረ። ውድድሩ በ21 ዘመናዊ የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉበት ታውቋል። በውድድሩ መክፈቻ መርሃግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማቴዎስ ሰቦቃ እንዳሉት ስፖርት ወዳጅነትና አንድነትን ያጎለብታል።   ስፖርት ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው ዛሬ በጅማ ከተማ የተጀመረው ውድድር ለ15 ቀናት እንደሚቆይ ገልጸዋል። ስፖርት አብሮነትን ከማጠናከር ባለፈ ለአካልና ለአዕምሮ ብቃት ወሳኝ ነው ያሉት ሃላፊው፣ በክልሉ ብቁ ታዳጊ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ኦሮሚያ የአትሌቶች መፍለቂያ መሆኗን አስታውሰው፣ ከክልሉ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን የማፍራት ስራው ይጠናከራል ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ በበኩላቸው ታዳጊ ሕጻናት እና ወጣቶችን በዚህ መሰል የስፖርት መድረክ ማሳተፍ የሚበረታታ ነው ብለዋል።   ሀገራችን በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ብቁና ተወዳዳሪ ወጣት ስፖርተኞችን ማፍራት እንድትችል በየአካባቢው ወጣቶችን ያሳተፈ ሥራ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል ። ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የስፖርት ተሳትፎ ለማሳደግ ያግዛል ያሉት አቶ ኢሳያስ፣ በየደረጃው ለታዳጊ ወጣቶች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል። የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በበኩላቸው የጅማ ከተማና የጅማ ዞን ህዝብ ለውድድሩ የመጡ እንግዶችን በእንግዳ አክባሪነት ተቀብሎ እንዲያስተናግድ አስገንዝበዋል።   ስፖርት በባህሪው አዝናኝና አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው፣ እንግዶች በጅማ ቆይታቸው የከተማዋን የተለያዩ አካባቢዎች እንዲጎበኙ ጠይቀዋል። ዛሬ በጅማ ከተማ በተጀመረው የመላው ኦሮሚያ ስፖርት ውድድር 21 ዞኖች እና 23 የከተማ አስተዳደሮች እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል።    
በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር  ኢትዮጵያ የላቀ ውጤት እንድታስመዘግብ ዝግጅት  እየተደረገ  ነው
Apr 13, 2024 634
ደሴ ፤ሚያዝያ 5 /2016(ኢዜአ)፡- በፈረንሳይ ፓሪስ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ የላቀ ውጤት እንድታስመዘግብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በደሴ ከተማ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራትና ቅብብሎሽ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ በኮሚቴው የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር የቴክኒክና ህዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ እንዳመለከቱት፤ በመጪው ሐምሌ ወር የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር በፓሪስ ይካሄዳል። በውድድሩ ኢትዮጵያ የተሻለ ውጤት እንድታስመዘገብ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በውጭና በአገር ቤት ህብረተሰቡን የማነቃቃትና ግንዛቤ የመፍጠር፣ ገቢ የማሰባሰብ፣ ስፖርተኞችን የመመልመል፣ በክልሎች የችቦ ቅብብሎሽና ሌሎችም ዝግጅቶች በመደረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በውድድሩ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ውሃ ዋና እንደምትሳተፍ ጠቁመው፤ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ወርቅ ለማምጣትና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ አድርጎ ለማውለብለብ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ስፖርት ለዘላቂ ሰላምና አብሮነትም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፤ ህብረተሰቡ በስፖርት መተሳሰርና የእርስ በእርስ ግንኙነቱን ማጠናከር እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ በበኩላቸው፤ በቀጣይ ክረምት በፓሪስ በሚካሄደው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት ክልሉ የበኩሉን እየሰራ መሆኑን ገለጸዋል፡፡   ለዚህም በክልሉ በሚገኙ 16 የአትሌቲክስ ማስልጠኛ ማዕከላት ልዩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ በማዕከላቱ በዓለም የውድድር መድረክ መሳተፍ የቻሉ ስመ ጥር አትሌቶችን ማፍራት ተችሏል ብለዋል፡፡ በክልሎች መካከል የችቦ ቅብብሎሽ እየተካሄደ መሆኑም የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከማጠናከሩ ባለፈ ስፖርቱን ለማነቃቃትና ብቁ ተወዳዳሪ ለመፍጠር እያገዘ ይገኛል ብለዋል። ከኦሮሚያ ክልል የተቀበሉትን የኦሎምፒክ ችቦ ዛሬ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አስረክበዋል፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ብላቴ እንዳሉት፤ በፓሪስ ለሚካሄደው ኦሎምፒክ የሚሳተፉ ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡   የኦሎምፒክ ችቦውን ከአማራ ክልል መረከባቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በማዘዋወር ዘርፉን ለማነቃቃትና የህብረተሰቡን አንድነት ለማጠናከር እንሰራለን ብለዋል፡፡ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ዶክተር ሙሳ አዳል በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የስፖርቱን ዘርፍ በመደገፍ የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የተንታ አትሌቲክስ ማስልጠኛ ማዕከልን ተረክቦ ስመ ጥር አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች 120 ታዳጊዎችን በቋሚነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲና የደሴ ከተማ አመራር አባላትና የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
Apr 12, 2024 590
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 4/2016(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ ባህር ዳር ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይደረጋል። በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ እስካሁን ባደረጋቸው 19 ጨዋታዎች በ9ኙ ሲያሸንፍ 5 ጊዜ ተሸንፎ 5 ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በ19 ጨዋታዎችም 23 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 17 ግቦችን አስተናግዷል። በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በአራቱ ሲያሸንፍ በአንዱ ነጥብ ጥሏል። አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ32 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የአምናው የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በውድድር ዓመቱ ባደረጋቸው 20 ጨዋታዎች 11 ጊዜ ሲያሸንፍ 4 ጊዜ ሽንፈት አስተናግዶ በ5ቱ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በ20ዎቹ ጨዋታዎች 33 ግቦችን ሲያስቆጥር 17 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ክለቡ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በሶስቱ ድል ሲቀናው በአንዱ ሽንፈት በማስተናገድ አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመሩት ፈረሰኞቹ በ38 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ይህም ዛሬ በሚካሄደው 21ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር የሁለቱ ክለቦች ፉክክር ተጠባቂ አድርጎታል። በሊጉ የዛሬ መርሐ ግብር ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ደግሞ ፋሲል ከነማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ፋሲል ከነማ ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲያሸንፍ በአንዱ ተሸንፎ በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል። በውበቱ አባተ የሚሰለጥነው ፋሲል ከነማ በ31 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በአንጻሩ ተጋጣሚው ሀምበሪቾ ዱራሜ ባለፉት አምስት ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል። በጊዜያዊ አሰልጣኝ መላኩ ከበደ የሚመራው ሀምበሪቾ በ7 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በተያያዘ ዜና ትናንት በተደረጉ የ21ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ወላይታ ድቻና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።    
አካባቢ ጥበቃ
በኦሮሚያ ክልል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጡ ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ
Apr 15, 2024 301
አዳማ ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በመጪው ክረምት የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ግብርና ቢሮ የደን ልማትና እንክብካቤ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ከተማ አብዲሳ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በክልሉ ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ወራት የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ፣ የእርከን ማሰርና የተራቆቱ መሬቶችን ከንኪኪ ነፃ የማድረግ ስራ ተከናውኗል። በዚህ ረገድ በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች የተከናወነው የተፋሰስና እርከን ማሰር ስራ ለሌሎች የክልሉ ዞኖች ጭምር ተሞክሮ እንደሚሆን ተናግረዋል። በአብዛኛው የተፋሰስ ልማት ስራ በተከናወነባቸው መሬቶች ላይ የሚተከሉ ችግኞችን በስፋት የማዘጋጀት ተግባርም ጎን ለጎን እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል። በክልሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጡ ችግኞችን የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው የእስካሁኑ አፈጻጸምም የተሻለ መሆኑን አብራርተዋል። የፍራፍሬ ችግኞች፣ ቀርከሃና ለጥምር ደን አገልግሎት የሚውሉ ችግኞች ትልቅ ትኩረት ማግኘታቸውን አመልክተዋል። ከተዘጋጁት ችግኞች ውስጥ 40 በመቶ ለደን አገልግሎት የሚውልና 10 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውን የገለፁት አቶ ከተማ ፤ ለተከላ የበቁ ችግኞችን የመለየት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። የችግኝ መትከያ ጉድጓድ የማዘጋጀት ስራም እየተከናወነ ሲሆን በክልሉ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱንም ተናግረዋል። በዚህም ከ800 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነውን መሬት የመለየት ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል። የምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አብነት ዘገየ በበኩላቸው ፤በዞኑ ዘንድሮ የሚተከል 279 ሚሊዮን የተለያየ አገልግሎት ያላቸው ችግኞች የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ 13 ወረዳዎች በተለዩ ከ300 በላይ ተፋሰሶች ላይ ለ60 ቀናት የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ መከናወኑ አስታውሰው፤ በመጪው ክረምት የፍራፍሬ ጨምሮ ሌሎችንም ችግኞች ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በተለይ ሀገር በቀል ዛፎች፣ የፍራፍሬ፣ ቀርከሃና ቴምርን ጨምሮ ለእንስሳት መኖ የሚውሉትን ለመትከል ከተፋሰስ ስራው ጎን ለጎን የጉድጓድ ዝግጁቱ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል።      
ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ በመፍጠር ሁሉን አቀፍ ልማት ለማሳካት የተቀናጀ ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ ተመላከተ
Apr 13, 2024 698
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 5/2016(ኢዜአ)፦ ለዜጎች ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ በመፍጠር የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ ልማት ለማሳካት የተቀናጀ ርብርብ እንዲደረግ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስገነዘበ። በድሬዳዋ ከተማ "የፕላስቲክ አጠቃቀም ዘይቢያችንን እናዘምን" በሚል መሪ ሃሳብ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። በመድረኩ "ብክለት ይብቃ፤ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ የሚካሄደው የአካባቢ ብክለት የመከላከል ንቅናቄ አካል ነው። የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ንቅናቄው አካባቢን እየጎዳ ያለውን የፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። የፕላስቲክ ብክለት በሰውና በእንሰሳት ጤና ላይ ከፍተኛ ችግር እያደረሰ መሆኑንም ገልጸዋል። ከአነስተኛ እስከ ዋና ዋና ከተሞቻችን በፕላስቲክ ቆሻሻ የተጥለቀለቁ፣ የኑሮና የስራ ሂደቶችን እያደናቀፉ ለብዝሃ ህይወት መመናመን ምክንያት እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል። በመሆኑም ይህንን በማህበራዊና የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚፈጥረውን ችግር በተቀናጀ ህዝባዊ ንቅናቄ በመታገዝ መፍትሄ ለማምጣት ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል። በተለይም ችግሩን ለመቀነስ የተዘጋጁ ስትራቴጂ፣ የህግ ማዕቀፎችና የማስፈፀሚያ ስልቶችን በተቀናጀ መንገድ በመተግበር ዘላቂ የአካባቢ አጠቃቀም ለመፍጠር መሥራት እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሰውን የደን መራቆትና የተፈጥሮ ሃብት መመናመን ችግር ለመታደግ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን መተግበር ይገባል ብለዋል። ባለሥልጣኑ በአስተዳደሩ ለተጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ስኬት ድጋፍ እንደሚያደርግም ወይዘሮ ፍሬነሽ አረጋግጠዋል።   የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው በንቅናቄው የአካባቢ ፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች በተቀናጀ መንገድ በመተግበር ምቹ የሥራ፣ የመኖሪያ እና የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከተማ ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግረዋል። የተጀመረው ንቅናቄ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በአስተዳደሩ በፕላስቲክ፣ በአየር፣ በውሃ፣ በአፈር፣ በድምፅ ብክለቶች ላይ ሰፋፊ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።   በንቅናቄው ላይ ለ5ሺህ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ በመፍጠርና የፕላስቲክ ውጤቶችን መልሶ መጠቀም የሚያስችሉ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እንደግፋለን ያሉት ደግሞ የድሬዳዋ የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱ መሐመድ ናቸው።
የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ ወጥ የኢነርጂ አሰራር ስርአት ለመፍጠር ወሳኝ ነው - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
Apr 12, 2024 533
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 4/2016(ኢዜአ)፦የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ ወጥ የኢነርጂ አሰራር ስርአት ለመፍጠርና የኢነርጂ ሃብትን በአግባቡ ለመጠቀም ወሳኝ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የኢነርጂ ልማት ስራ ወጥነት ባለው መልኩ እንዲተገበርና የኢነርጂ ተደራሽነትን ለማስፋት ስትራቴጂው ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል። የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት ይፋ የተደረገ ሲሆን ስትራቴጂውን የተመለከተ አውደ ጥናትም ተካሄዷል።   የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ፤ በስትራቴጂ የታገዘ ዘላቂ የኢነርጂ አጠቃቀምን መከተል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የኃይል ምንጮችን መጠቀም ለዘላቂ የኢነርጂ ልማት እውን መሆን ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ለዘርፉ ስራ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ያስፈልጋል ብለዋል። በመሆኑም በዘርፉ ያሉ እድሎችንና አማራጮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የተወጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ስትራቴጂውን ለማዘጋጀት 1 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ የወሰደ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የኢነርጂ ፖሊሲ መሬት ወርዶ በሚፈለገው ደረጃ እንዲተገበር፣ የኢነርጂ ሀብቶችን በተመለከተ የተቀናጀ መረጃ ለመስጠትና የግሉ ዘርፍ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ ስትራቴጂው የላቀ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል። በተበታተነ መልኩ ይተገበር የነበረውን የኢነርጂ የአሰራር ማዕቀፍ ወጥነት እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። ከዚህ በፊት ስትራቴጂውን የተመለከቱ ስድስት የግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች መካሄዳቸውን አስታውሰው የአሁኑ የመጨረሻ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የስትራቴጂው የማጠናቀቂያ ስራዎች ከተከናወኑ በኋላም በ2017 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ወደ ትግበራ ይገባል ብለዋል።   በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ ሬቤካ አልት፤ የሀገራቸው መንግስት በጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ድርጅት (ጂ አይ ዜድ) በኩል ለስትራቴጂው ዝግጅት ድጋፍ ማድረጉን አመልክተዋል። ለስትራቴጂው መዳበር አውደ ጥናቶች እንዲካሄዱ ማድረግና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኒክ ድጋፎችን ማድረጉን አስታውሰዋል። ጀርመን በኢነርጂው ዘርፍ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የውሃና ኢነርጂ ልማት ቢሮ የአማራጭ ኢነርጂ ጥናት ልማት ክትትል ዳይሬክተር የሱፍ ሙባረክ ስትራቴጂው የኢነርጂ ሃብትን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ማዕድን ኢነርጂና ነዳጅ ቢሮ የኢነርጂ ዘርፍ ዳይሬክተር መሐሙድ መሐመድ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገብረማርያም ሰጠኝ ስትራቴጂው ለዘርፉ ልማትና ተጠቃሚነት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ ሴቶች የኢነርጂ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ሊንዳ ላጲሶ፤ የግሉ ዘርፍ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ እንዲሁም እውቀትና ቴክኖሎጂን ስራ ለማዋል ስትራቴጂው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የብሔራዊ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት ስትራቴጂ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር ከ2024 እስከ 2030 ተግባራዊ እንደሚሆን በአውደ ጥናቱ ላይ ተመላክቷል።          
በሚቀጥሉት ቀናት በአብዛኛው የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ሥፍራዎች የተሻለ እርጥበት ይኖራቸዋል
Apr 12, 2024 441
አዲስ አበባ ፣ሚያዚያ 04/ 2016 (ኢዜአ)፡-በቀጣይ ስምንት ቀናት ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገፅታዎች በአብዛኞቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገፅታዎች፤ በአብዛኞቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የአገሪቱ አካባቢዎች እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ አመላክቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖረውም በትንበያው ተገልጿል። በሚቀጥሉት ቀናትም በአብዛኛው የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ሥፍራዎች የተሻለ እርጥበት እንደሚኖራቸውና የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን እንደሚጠቅሙ ገልጿል። ይህም የረዥም ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት፤ በቡቃያና በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች የውኃ ፍላጎት መሟላት፤ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የጠቆሙት። የሚጠበቀው እርጥበታማ ሁኔታ ለእርሻ ሥራ እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር አርሶ አደሮች ተገቢ የሆኑ ግብዓቶችን በመጠቀም የእርሻ ሥራቸውን በተሟላ መልኩ ማካሄድ እንደሚገባቸው ገልጿል። በሚቀጥሉት ቀናት በኦሞ ጊቤ፣ ስምጥ ሸለቆ፤ በላይኛውና በመካከለኛው ባሮ አኮቦ፤ አዋሽ፣ አባይ፣ ገናሌ ዳዋ፣ በመካከለኛው ተከዜ እና በላይኛው ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶች ከፍተኛ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር ጠቁሟል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚጠበቀው ከፍተኛ እርጥበት፤ ለገፀ ምድርም ሆነ ለከርሰ ምድር ውሃ ኃብት መጎልበት አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 305
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 1610
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 897
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
በአባቱ የሎተሪ ስጦታ 4 ሚሊዮን ዶላር ያሸነፈው እድለኛ 
Apr 4, 2024 950
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 26/2016(ኢዜአ)፦ በአሜሪካ ኤሊኖይ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ አባቱ ያበረከቱለት የሎተሪ ትኬት የ4 ሚሊዮን ዶላር እድለኛ አድርጎታል። ስቴቨን ሪቻርድስ ይባላል በኤሊኖይ የባሪንግተን ከተማ ነዋሪ ሲሆን ከቀናት በፊት ከአባቱ ጋር ቁርስ ለመመገብ ባቀኑበት ምግብ ቤት ከአባቱ ስጦታ ይበረከትለታል። ስጦታውም የ10 ዶላር የሎተሪ ትኬት ነበር። አዛውንቱ ያበረከቱለት የሎተሪ ትኬት ወዲያውኑ ተፍቆ ውጤቱን የሚያሳይ ሲሆን ስቴቨንም ትኬቱን በፋቀበት ቅጽበት ከፍተኛ ድንጋጤ እንደተሰማው ለማሳቹሴት የሎተሪ አስተዳደር ተናግሯል። የሎተሪ ትኬቱ የ4 ሚሊዮን ዶላር እድለኛ እንዳደረገኝ ሳውቅ በድንጋጤ ማመን አልቻልኩም በዚህም ውጤቱን ከመናገሬ በፊት በስልኬ ስካን አደረኩት ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። በመቀጠለም የአባቱ ስጦታ እድለኛ እንዳደረገው ለባለቤቱ እንዲሁም ለአባቱ መናገሩን ዩፒአይ ዘግቧል። ስቴቨን በሎተሪ ከደረሰው 4 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ በተወሰነው ገንዘብ ከባለቤቱ ጋር የተለያዩ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ማቀዱን ዘገባው አመልክቷል።
ሐተታዎች
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 744
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 1936
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
በከፍታ የታጀበ ስኬት
Mar 15, 2024 1548
ለህጻናትና ታዳጊዎች መልካም ስብእና የሚያግዙ ጽሁፎችን ያዘጋጀችው ኤሪን ሶዴርበርግ ዶውኒንግ 'JUST KEEP WALKING' በሚለው መጽሃፏ ባደራጀችው ገጸባህሪ አማካይነት “አንተ መልካምና ስኬታማ ሆነህ ሳለ ጥቂት ሰዎች ስለአንተ መጥፎነት አብዝተው መጨነቅና ማውራት ከጀመሩ የምትሄድበት መንገድም ሆነ አካሄድህ ትክክል ነውና መራመድህን አታቁም። ብዙሃኑ የስኬትህ ተካፋይና የስኬትህ አጋር ስለሆኑ የጥቂቶቹን ጫጫታ ከምንም ካለመቁጠር ተራመድ ብዙ አፍራሽ ወሬዎች ያንተን ስኬት የመመስከር አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን አትዘንጋ። መቆም የሽንፈት ምልክት ነውና” ትለናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 78 ዓመታት በከፍታ የዘለቀ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምና ዝናው የገነነ ተቋም ነው። አየር መንገዱ ታህሳስ 21 ቀን 1938 ዓ.ም ተመስርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ካይሮ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዘመኑ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅና አሰራሮችን በማዘመን ራሱን እያደራጀ የኢትዮጵያ ኩራት ከመሆን አልፎ የአፍሪካ ምልክት ሆኖ ዘልቋል። ዛሬ ላይ የ152 ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምስረታው ወቅት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት አውሮፕላኖች ብቻ እንደነበሩት መረጃዎች ያመለክታሉ። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ22 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞችን ፍላጎትና ምቾት ለመጠበቅ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ጨምሮ 31 አውሮፕላኖች ለመግዛት ከአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። እነዚህን ተጨማሪ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ቁጥር ጨምሮ የሚገነባቸው ዘመናዊ አየር መንገዶች ሲደመሩ በአፍሪካ ግዙፍ ተቋምነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ያደርገዋል። የበረራ አድማሱን በየጊዜው እያሰፋ የሚገኘው አየር መንገዱ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 134 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በሀገር ውስጥ ወደ 22 መዳረሻዎች ይበራል። ከዚህ ውስጥ 60 የበረራ መዳረሻዎቹ አፍሪካ ውስጥ ነው። አየር መንገዱ ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ አስገንብቶ ወደ ስራ ያስገባው ዘመናዊ የካርጎ ማእከል ከምስራቅ አፍሪካ ብሎም ከአፍሪካ ከፍተኛ ተብሎ ተመዝግቦለታል። በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው ያረፈው የካርጎ ማዕከል ለኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ ኮሜርስ) አገልግሎት የሚውል ሲሆን የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣት አየር መንገዱ የሚሰራቸው ተያያዝ በርካታ ተግባራት መስፋት፣እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ተመራጭ መሆን ለማእከሉ ግንባታ ምክንያት ተብለው ተጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ መስክ ከሚታወቅባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሴቶችን በማብቃትና የጾታ እኩልነትን በማስተግበር ረገድ አርአያነት ያለው ተግባር መፈጸሙ ነው። በየዓመቱ የሚታሰበው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ማርች 8 በሚከበርበት ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ ለሙሉ በሴቶች ብቻ የተመራ በረራን በማደረግ ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፏል። አየር መንገዱ ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ "ሴቶችን በማብቃት አፍሪካን ማስተሳሰር" በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ ወደ ለንደን በሴቶች ብቻ የተመራ የተሳካ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች በሚሰጠው ዘመኑን የዋጀና ቀልጣፋ አገልግሎት በየጊዜው የተለያዩ ሽልማቶች ባለቤት መሆን የቻለ ተቋም ነው። ለአብነት የቅርብ ጊዜያቶችን ለማንሳት ያህል ባሳለፍነው ዓመት በአየርላንዷ ደብሊን በተዘጋጀ መርሐ-ግብር ላይ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማትን አሸንፏል፡፡ በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ ጉባኤ "ኤር ካርጎ ኤሮፕ" እ.አ.አ በ2021 ባካሄደው የበይነ መረብ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና የሎጅስቲክ አገልግሎት የ2021 የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ የደንበኞች እንክብካቤ ዘርፍ ሽልማት አግኝቷል። በአውሮፓውያኑ 2024 ዓመታዊውን የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “የኮርፖሬት የዘላቂነት ስኬት ሽልማት” አሸናፊ ሆኗል። አየር መንገዱ በትላልቅ ስኬቶች የማለፉን ያህል ከባድ ፈተናዎችንም ተጋፍጦ በጽናትና በስኬት አልፏል። መላውን ዓለም ያዳረሰው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አንዱ ማሳያ ነው። በዚያን ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ምክንያት በዓለም ደረጃ በርካታ አየር መንገዶች በረራ በማቋረጥ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ አንዳንድ የመንገደኞች አውሮፕላኖቹን ወደ ዕቃ ጫኝ በመቀየር ጭምር ትኩረቱን ጭነት ማጓጓዝ ላይ አድርጓል። በዚያን ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የቀየሰውን ስትራቴጂ በመቃወም ከውስጥም ከውጭም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ትችትን አስተናግዷል። ይሁን እንጂ አየር መንገዱ ፈተናውን በመቋቋም እንደሌሎቹ ሀገራት አውሮፕላኖች በረራ የማቋረጥ እጣ ሳይገጥመው በታላቅ ብልሃት ማለፍ የቻለ ተቋም መሆኑ ተመስክሮለታል። በዚህም በካርጎ አገልግሎት ገቢ ከማገኘቱም ባሻገር ክትባትን ለዓለም በማዳረስ ወረርሽኙ ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ የራሱን አሻራ አኑሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን ከአራት አስርተ ዓመታ በላይ ልምድ አካብቷል። አየር መንገዱ በሚያስተዳድረው ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የበረራ ባለሙያዎችን በቅርቡ ያስመረቀ ሲሆን ምሩቃኑ ከታንዛንያ ከደቡብ ሱዳን ከኒጀር ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከቶጎ እና ከማዳጋስካር መሆናቸው ደግሞ የአየር መንገዱን የፓንአፍሪካኒስት መንፈስ አጉልቶ ያሳየ አድርጎታል። ስኬቶቹ በዚህ ያላበቁት አየር መንገዱ የእድገት ግስጋሴውን እንደቀጠለ ይገኛል። ከሰሞኑ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በዚህ ወቅት ከተሸለሙት ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን ሽልማቱ ለወደፊትም ለላቀ ስኬት የሚያዘጋጀው እንደሆነ ይታመናል።  
አድዋን የዘከሩ ስንኞች
Feb 29, 2024 1933
የታሪክ ድርሳናት የአድዋ ድልን በተለያየ መንገድ ዘክረውታል። ምሁራንም አንድምታውን በየዐውዱ ዘርዝረዋል። በዚህም ለሰው ልጆች በተለይም ለጥቁሮች አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንደሆነ ደምድመዋል። በርግጥም የአድዋ ድል ታሪክም፣ ትርክትም የለወጠ ትልቅ ሁነት ነው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ምዕራባዊያን 'አቢሲኒያ' በሚሏት ጥንታዊት አፍሪቃዊት ምድር የነበረው ክስተት ቀለምና ዘር ቀመስ በሆኑ በሰው ልጆች መካከል ድል መንሳትና መነሳት፣ ተስፋ እና ቀቢፀ ተስፋ፣ ሀሜትና ሀሞት፣ ብስራትና መርዶ... እያፈራረቀ አበሰረ። ለሀገሬው ዘመን-አይሽሬ አሻራ አነበረ። ውርስም ቅርስም ሆነ!! ይህ ክስተት በታሪኩ ልክ በኪነ ጥበብ ተዘክሯል ባይባልም ቅሉ በጥበብ ፈርጁ ተወስቷል። የኪነ-ጥበብ ሰዎች በየመክሊቶቻቸው ድሉን ለመዘከር ጥረዋል። ሙዚቀኞች በዜማዎቻቸው፣ የሲኒማ ሰዎች እና ፀሐፈ ተውኔቶች በተውኔታቸው፣ ሊቃውንት በቅኔዎቻቸው አድዋን ዘክረዋል። ዕውቅ ገጣሚያን ደግሞ ቃላት እያዋደዱ፣ በዘይቤና ዘመን እያዋሃዱ፣ ምዕናብና ገሀድ እያዛነቁ፣ ታሪክና ትዝብት እያሰባረቁ ... አድዋን በግሩም ስንኞቻቸው ከትበውታል። በአድዋ ድል ምርጥ ግጥሞች መካከል "ጥቂት ስንኞች" እየመዘዝን በወፍ በረር ቅኝት እንመልከት። ባለቅኔው ፀጋዬ ገብረመድህን በ‘እሳት ወይ አበባ’ ግጥም መድብሉ አድዋን መልክዓ ምድራዊና ሃሳባዊ ወሰኗን አድማስ ተሻጋሪ፣ ሰማይ ታካኪ፣ ታሪካዊ ስፍራዋ የአጽም ርስትና የደም ትቢያ የተሸበለለባት መቀነት አድርጎ መስሏታል። በዚህች ታሪካዊ ስፍራ በተከፈለው መስዋዕትነት ከባርነትና ነጻነት ስርየትን ሲያጎናጽፍ፣ የኩራት ቅርስ መሆኗንም ሰፊውን ታሪክ በጥቂት ስንኞች እንዲህ ቋጥሯል። ".... አድዋ ሩቅዋ፣ የዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥግዋ፣ ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ... ዓድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ- የደም ትቢያ መቀነትዋ ከሞት ከባርነት ሥርየት- በደም ለነጻነት ስለት አበው የተሰውብሽ እ’ለት የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ- የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ..." ገጣሚው አለፍ ሲልም በጦርነቱ የዋሉ መሳሪያዎችን፣ የጦር መሪዎችን እጅና ጓንትነት በፈረስ ስሞቻቸው በመቋጠር /ለአብነትም የዳግማዊ ምኒልክ፣ የራስ መኮንን፣ የደጃች ባልቻ ሳፎ፣ የፊታውራሪ ገበየሁና ሌሎችም/ ኢትዮጵያዊያንን ጀግንነትና ወኔ በአጭሩ ቋጥሮታል። ...ድው-እልም ሲል ጋሻዋ- ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣ ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ፣ ያባ መቻል ያባ ዳኘው፤ ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣ ያባ ጎራው፣ ያባ በለው በለው ሲለው..." በሚል። ደራሲና ጋዜጠኛ ነብይ መኮነን ‘ስውር ስፌት’ በተሰኘ የግጥም መድብሉ የአድዋን ድል ሲያመሰጥረው አድዋን ‘በደም ግብርነት’ ይገልጸዋል፤ ታሪኩንም ላጥፋህ ቢሉት የማይጠፋ ሕያው ቀንዲል አድርጎታል። “አድዋ የደም ግብር ነው፤ አበው የለኮሱት ቀንዲል፣ አድዋ የአፍሪካ ዱካ ነው፤ አበሽ የከተበው ፊደል፣ ላጥፋህ ቢሉት መች ይጠፋል፤ ጠላት በልቶ ያፈራ ተክል፣ ለዛሬም ታሪክ ነው፣ ‘ነገም ሌላ ቀን ነው’ ለሚል...” የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ ምሁር ሰይፉ መታፈሪያ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) “የተስፋ እግር ብረት” መጽሐፍ “የድል በዓል ማለዳ” በሚል ርዕስ የአድዋን ድባብ ከማለዳው ምናባዊ ትዕይንት ጀምሮ ይቃኛል። ገጣሚው የሰንደቁን መውለብለብ፣ የሕብረ ቀለሙን ድምቀት ከልክ በላይ ውስጥን ኮርኩሮ የሚያስፈግግ ሐሴት እንዳለው በዘይቤያዊ ቃላት ገልፆታል። ገጣሚው በቅኔው የሠራዊቱን ቆራጥነት፣ በወኔ በደም ሲቅላላ፣ የመድፍ አረር ሲያፋጭ ይስለዋል። በስሜት ስካር አድዋ ደፍርሶ በስዕለ ህሊናው የነበረውን የጦርነቱ ማለዳዊ ድባብም እንዲህ ያብራራዋል። ዐይነ-ልቦናዬ ዐጽም ያያል፤ የድል ሜዳውን ይቃኛል። ባድዋ ድል በዓሉ ማለዳ፤ የበዓል መድፍ ሲንዱዋዱዋ (ዱዋ ዱዋ ዱዋ ዱዋ!) ከሞት እንቅልፍ ተቀስቅሶ፤ ያ-ዐጽም ዙርያውን ደባብሶ ጉሮሮውን ጠረገ፣ እህህህህ! እህህህህ!... እያለ ይቀጥላል። በአድዋ ኮረብታማ ተራሮች የተኙ ጀግኖችን በሕይወት ተኝተው የሚያንኮራፉ አስመስሎም አቅርቧቸዋል። ...ድንጋይ ተንተርሶ፤ አፈር ቅጠሉን ለብሶ፣ ከዚያን ያንኮራፋል፤ እንደዚሁም በቅብልብል የወደቀበቱ ሜዳው፣ ተረተሩ፤ ቀን የማይለውጠው ምስክሩ የዚያ ጀግና፣ የዚያ ኩሩ። ገጣሚ አበረ አያሌው “ፍርድና ዕርድ” በተሰኘው የግጥም ስብስቡ ባሰፈራቸው ስንኞች ‘ነገረ አድዋ’ን ከመንደር ወደ አገር፣ ከአገር ወደ አህጉር በመጨረሻም ከአህጉር አተልቆ ‘ዓለም’ ያደርገዋል፤ አድዋን የአፍሪካ ብርሀን ፈንጣቂ፤ ለእብሪተኞች ደግሞ የትካዜና ቅስም መስበሪያ ምስጢር አድርጓታል። በተለይም ኢትዮጵያ ለገጠማት አሁናዊ የዘር ፖለቲካ አዙሪት አድዋን ለሚያሳንሱ ወገኖች በቅኔው ምላሽ ይሰጣል። "...እነ ምኒልክ ጦር ይዘው ከመድፍ የተዋደቁ ጎራዴ መዘው የሮጡ በጠብ-መንጃ አፍ ያለቁ ለጓጉለት ነጻነት -ደማቸውን ያፈሰሱ ለሰፈር ብቻ አይደለም- የአህጉር ድል አታሳንሱ። ... ዓድዋ ሰፈር አይደለም - ዓድዋ መንደር አይደለም እሱ ዓለም ናት ዓድዋ ቤቱ - ሃገር ናት የድል ትራሱ ለጠበበ የዘር ቅኔ - የደም ድል አታሳንሱ!..." በማለት ገልጾታል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ምሁሩ ተሻገር ሽፈራው (ዶ/ር) ‘የነፍስ ርችቶች’ በተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሃፉ ከቋጠራቸው ስንኞች መካከል በአድዋ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል የግጥም ውድድር ያሸነፈበትን ረጅምና ድንቅ ግጥም አካቷል። የዶክተር ተሻገር ግጥም አንጓ እና ስንኞች የአድዋን ምጡቅነት፣ ዝና፣ ነቅዓ ፍትሕ፣ ውበትና ቅኔ በውብ ቃላት ገልጠውታል። "... ዓድዋ አንቺ የዝና አጽናፍ ሕዝቦች እፍ ያሉብሽ ቁጣ - የነበልባል እቶን ጫፍ እጹብ ክስተት፤ ደቂቅ ረቂቅ፤ ምጡቅ ጠሊቅ ኬላ ድንበር፣ አድማስ ሰበር፣ የቅርብ ሩቅ ለትንግርትሽ ብቻ መጥኔ ትንግርት እውነት፣ ታምር ሁነት፣ የብርቅ ብርቅ፣ የድንቅ ድንቅ ለሰጠሽው ፍትህ መጠን - ለፍርድሽ ሚዛን ብያኔ ለንግስትሽ ሥነ ውበት - ለታሪክሽ ምስጢር ቅኔ…" ገጣሚው "... በምን ቀሰም፣ በምን ቀለም - በምን ብዕራና ሊከትበው..." ሲል የአፍሪካዊያን ሁሉን አቀፍ ድል ለመግለጽ የቀለም፣ የአንደበትና የብራና ወኔ እንዳጣባት ይናገራል። በመጨረሻም ይህችን የድል ቁንጮ የማትሞቺ ህያው ጀንበር ሁልጊዜም ተዘመሪ፤ ተወደሽ" ይላታል። "… እና ዓድዋ አንቺ በኩር የድል መኸር የቅኝ ግዛት ቀንበር ሰንሰለቱ እንዲሰበር ተጠቂዎች አጥናፍ አጥናፍ የመረጡሽ የትግል ዘር ህይወት ከፍለው እልፍ - ያርጉሽ የመረጡሽ ከአገር አገር የማታልፊ የማትከስሚ - የማትሞቺ ህያው ጀንበር ሰብዓዊ ድል ነሽና - ስምሽ ይወደስ ይዘመር…" (በአየለ ያረጋል)  
ትንታኔዎች
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 2937
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2081
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 1968
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
በአጭር ጊዜ ትልቅ እመርታ በሌማት ትሩፋት
Feb 6, 2024 2803
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በግብርና ልማት በተለይም በስንዴ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ በምግብ እራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል። በግብርና ልማት እየተከናወኑ ባሉ ውጤታማ ስራዎች ላይ የሌማት ትሩፋት ተግባራት ሲታከሉ ከምግብ ዋስትና ባለፈ ስርአተ ምግብን በማስተካከል ረገድ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ለመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ስርአተ ምግብን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚኖረው ፋይዳ እንዴት ይታያል? በእስካሁኑ አካሄድስ ምን ውጤቶች ተገኙ? ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ‘የሌማት ትሩፋት’ መርሃ ግብርን ካስጀመሩ በኋላ በመህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሌማት አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን ገልጸው ነበር። በወቅቱ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በቂ እና አመርቂ ምግብ ማግኘት መሆኑን ገልጸው በቂ የመጠን፣ አመርቂ የይዘት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም በምግብ ራስን መቻል ከሀገር ሉዓላዊነትና ክብር ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ገልጸዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር ዓላማ የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥና ክብርን ማስጠበቅ ሲሆን በተለይም ስጋ፣ እንቁላል፣ ማር እና ወተት ትርፍ ምርት ሆነው እንዲገኙ ማልማትና መጠቀምን መሰረት ያደረገ ነው። መርኃ-ግብሩ የኢትዮጵያን ደካማ የአምራችነት ታሪክ በመቀየር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የኢኮኖሚ እድገትን የማፋጠን ግብ የሰነቀ መሆኑ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሌማት ትሩፋት ዘመቻው በቤተሰብ፣ ብሎም በሀገር ደረጃ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል። የወተት፣ የዶሮ፣ የዕንቁላል፣ የማር፣ የዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን ለማሻሻል ሀገራዊ የመንግሥት ፕሮግራም ሆኖ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት በብዙ መልኩ ውጤት እያስገኘ ነው። በእርግጥም የሌማት ትሩፋት በአንድ ዓመት ጉዞው በተለይ በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና ስጋ ምርት መጠን አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና ሸማቹን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑ የተረጋገጠበት ውጤት ተመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በ2015 ዓ.ም፣ የወተት፣ የዶሮ እና የሥጋ ምርት መጠን በዕቅዱ መሠረት ጥሩ ውጤት ማምጣቱንና በተያዘው ዓመትም በበለጠ ለማሳካት የሁሉም ጥረት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በማር፣ በወተትና በዶሮ ልማት ከ20 ሺህ በላይ መንደሮችን በመለየት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ለኢዜአ ገልጸዋል። ለአብነትም በወተት ልማት በተሰሩ ስራዎች 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ሊትር የነበረውን የማምረት አቅም ወደ 8 ነጥብ 6 በሊዮን ሊትር ከፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በመጪዎቹ ዓመታትም ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በእንቁላል ምርት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የጫጩቶች ስርጭት ከነበረበት 26 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ማደጉን ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት መርኃ- ግብር የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን የሚናገሩት የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና አሣ ሃብት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጽጌረዳ ፍቃዱ በእንስሳት ሃብት ልማት ብቻ በዓመት ለ259 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ለዘርፉ ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት አመርቂ ውጤት ሳያገኝ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ዘርፉ በቅንጅት ከተመራ፣ በቴክኖሎጂ ከታገዘ የምግብ አማራጭን ማብዛት ይቻላል። ወተት፣ ማር፣ ስጋ እና እንቁላል መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በገበያ ላይ ማትረፍረፍ፣ የሌማቱ በረከት ማብዛት የሚለው የብዙሃኑ እምነት ነው። የምግብ ዋስትና ጉዳይ ከተመጣጠነ ምግብ ጋር ያለው ቁርኝት የማይነጣጠል በመሆኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ፋይዳው ብዙ ነው። በሌማት ትሩፋት ገበታን በተመጣጠነ ምግብ መሙላት ከተቻለ የእናቶችንና የህጻናትን ፍላጎት በማሟላት በአካል የዳበረና በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ መገንባት ይቻላል። በተቃራኒው ያልተመጣጠነ አመጋገብ ጤና ላይ ከሚፈጥረው ችግር ባለፈ በሰዎች መካከል ያለውን የኑሮ አለመመጣጠን በማስፋት፣ ማህበራዊ ቀውስን በመፈልፈልና ኢኮኖሚውን በመጉዳት ምርትና ምርታማነትን ወደ ኋላ የሚጎትት ይሆናል። ይህ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት በከባድ ትግል ላይ የሚገኙ ሀገራትን የልማት ግስጋሴ በመግታት ቀድሞ ወደነበሩበት የድህነት አረንቋ እንዲመለሱ ያደርጋቸዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙና እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ ህፃናት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት በዕድሜያቸው ልክ ዕድገት የማያስመዘግቡ ወይም የመቀንጨር ችግር ያለባቸው መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። ለዚህ ነው በምግብ ራስን ከመቻል ጎን ለጎን የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ የሚሆነው። በዚህ ረገድ የሌማት ትሩፋት እየተጫወተ ያለው ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። የተለያዩ ምግቦችን በገበታ ላይ ማካተት የሚያስችል ስልጠናን ከተግባራዊ የልማት ስራዎች ጋር ያካተተ ሲሆን አዲስ የአመጋገብ ባህልን የሚያለማምድ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለተሰሩ ስራዎችና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላሳዩት የአመራር ቁርጠኝነት በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል። ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ረሀብን ዜሮ ለማድረስ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ ብልጽግናን እውን እንደምታደርግ ገልጸዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተሰሩት ስራዎች ለመጪው ትውልድ ጥሩ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ለአብነት አንስተዋል። የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ስራችን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የተመጣጠነ ምግብን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል። የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ነጻ አገር እውን ማድረግን ያለመ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አመራሩ ይህንን ተገንዝቦ እንዲሰራ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ህልም የሚመስሉ በርካታ አገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ የቻለችው በዜጎቿ የተባበረ ክንድ መሆኑ እሙን ነው። ከዚህ አኳያ በምግብ ራስን ከመቻል በላይ የኢትዮጵያን የአምራችነት ታሪክ የመቀየር ግብ ለሰነቀው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ስኬታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት ይጠበቃል።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 10696
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15348
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 7882
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 8884
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 24071
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 20814
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15348
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 11630
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 10696
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 10692
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 10446
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10029
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 24071
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 20814
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 15348
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 11630
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 2861
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 3010
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም