አርእስተ ዜና
የአካባቢያቸውን ሰላም  በማስጠበቅ ልማትን ለማፋጠን የድርሻቸውን እንደሚወጡ  የደብረብርሀን ከተማ ወጣቶች  አስታወቁ
Apr 23, 2024 11
ደብረ ብርሀን፤ ሚያዝያ 15/2016 (ኢዜአ)፦ የአካባቢያቸውን ሰላም በዘላቂነት በማስጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማፋጠን የድርሻቸውን እንደሚወጡ የደብረ ብርሀን ከተማ ወጣቶች አስታወቁ። በከተማዋ ወቅታዊ ሰላምና ልማት በሚጠናከርበት ዙሪያ የሚመክር የወጣቶች መድረክ ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሄዷል።   የመድረኩ ተሳታፊ ወጣት ትዕግስት ፍቅረ እንዳለችው ለአካባቢ ሰላም መጠበቅና ልማት መጠናከር የበኩሏን አስተዋጽኦ እያደረገች ነው። ''እኛ ወጣቶች ገንቢና ምክንያታዊ አስተሳሰቦችን በማጎልበት በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ዳር እንዲደርሱ ያላሰለሰ ጥረት እናደርጋለን'' ስትል ገልጻለች። በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ፈጣንና ቀልጣፋ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁማለች። አሁን ላይ የከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች የነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር የሚያግዙ መሆናቸውን ጠቅሳለች።   ከወጣቶች ጋር የሚካሄዱ ውይይቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ምክንያታዊ አስተሳሰብ በማስቀደም የአካባቢ ሰላም አስጠብቆ በዘላቂነት ለማስቀጠል የበኩሉን እንደሚወጣ የገለጸው ደግሞ ሌላው ወጣት ደምሴ ምሳወይ ነው። በከተማው እያደገ ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚደግፍ መሆኑን አስታውቋል። የእምየ ምሊኒክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰራዊት በዛ በበኩላቸው የከተማዋን ሰላምና ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል ወጣቶች በሚያከናውኗቸው ስራዎች አበረታች ለውጥ እየመጣ ነው ብለዋል። ወጣቶች ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ የልማት ስራዎች ሳይደናቀፉ እንዲቀጥሉ በማድረግ የጎላ ሚና መወጣታቸውን አመልክተዋል።   የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የወጣቶች ዘርፍ አማካሪ አቶ ኃይለማሪያም ወንድም እሸት የወጣቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት በኢንተርፕራይዞች በማደራጀት ከ9 ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶች የስራ አድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። የወጣቶችን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተው ወጣቶች ለአካባቢያቸው ሰላም በጋራ መስራትን መቀጠል እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። በምክክር መድረኩ ከደብረብርሃን የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶችና በየደረጃው ያሉ የከተማ አስተዳደሩ አመራር አባላት ተሳትፈዋል።      
የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአርሶ አደሩን ምርታማነት የሚያሳድጉ ዘጠኝ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎች በምርምር አገኘ
Apr 23, 2024 43
ባህር ዳር ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአርሶ አደሩን ምርታማነትን የሚያሳድጉ ዘጠኝ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎች በምርምር መገኘታቸውን አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አስማረ ደጀን በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት ከአምስት እስከ ስድስት ዓመታት በተካሄደ ምርምር የተገኙት የሰብል ዝርያዎቹ በሽታና ድርቅን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርት መስጠት የሚችሉ ናቸው። በምርታማነታቸውና ፈጥኖ በመድረስም ከተለምዶው የተሻሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ዝርያዎቹ በብሄራዊ ዝርያ አፅዳቂ ኮሚቴ ተገምግመው መለቀቃቸውን ገልጸው፤ ከመካከላቸውም ሁለት የማሽላ፣ ሶስት የበቆሎና ቀሪዎቹ ደግሞ የአኩሪ አተር፣ ሽምብራ፣ ድንችና ጥቁር አዝሙድ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከእነዚህም ውስጥ የማሽላ፣ የአኩሪ አተር፣ የሽምብራና የጥቁር አዝሙድ ዝርያዎች ከጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የወጡ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ የበቆሎ ሰብል ዝያዎቹ ደግሞ ከሰቆጣ ግብርና ምርምር ማዕከል በማላመድ እንደተገኙ አስረድተዋል።   እንዲሁም ከአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል አንድ የድንች ዝርያ፣ ከደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ደግሞ አንድ የማሽላ ሰብል ዝርያዎች በምርምር የተገኙ መሆናቸውን አብራርተዋል። ከጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የተገኘው የማሽላ ዝርያ በሄክታር 41 ነጥብ 5 ኩንታል፣ ከደብረ ብርሃን ምርምር ማዕከል የወጣው ደግሞ በሄክታር 52 ኩንታል ምርት መስጠት እንደሚችሉ ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል። በተጨማሪም ከዚሁ ምርምር ማዕከል የተለቀቀው አዲሱ የጥቁር አዝሙድ በሄክታር 9 ኩንታል በላይ ምርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል። ከሰቆጣ ግብርና ምርምር ማዕከል የተለቀቁት ሶስት የበቆሎ ዝርያዎች ደግሞ በሽታና ድርቅን ተቋቁመው በእርጥበት አጠር አካባቢዎች በሄክታር እስከ 48 ኩንታል ምርት እንደሚሰጡ አስረድተዋል። እንዲሁም ከአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የተለቀቀው አዲሱ የድንች ዝርያ በሄክታር 425 ኩንታል ምርት እንደሚሰጥ ጠቅሰው፤ ቀደም ብለው ከተለቀቁት የድንች ዝርያዎች በምርታማነት ደረጃ በ37 በመቶ የምርት ብልጫ እንዳለው አስታውቀዋል። ኢንስቲትዩቱ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በማፍለቅ፣ በማባዛትና የወጡትን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ ለምርታማነት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰዋል። የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከተቋቋመ ከ1992ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን 173 አዳዲስ የተለያዩ የሰብል ዝርያዎችን በማውጣት ለሰብል ምርታማነት ማደግ የድርሻውን መወጣቱም ተመልክቷል።  
የከተማውን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ተሳትፎአቸውን እንደሚያጠናክሩ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
Apr 23, 2024 43
ጎንደር ፤ ሚያዚያ 15 /2016 (ኢዜአ)፡- በጎንደር ከተማ በብሎክ አደረጃጀት ታቅፈው የአካባቢአቸውን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በከተማው የሰፈነውን ሰላም አጠናክሮ በማስቀጠል ዙሪያ የከተማው አስተዳደሩ ከህዝቡ የተወከሉ ነዋሪዎች ጋር ዛሬ ምክክር አድርጓል፡፡ ከተሳታፊዎቹ መካከል አቶ መስፍን ጌታነህ እንዳመለከቱት የብሎክ አደረጃጀቱ ነዋሪው አካባቢውን ከወንጀል ፈጻሚዎች ነቅቶ በመጠበቅ ሰላሙን እንዲያረጋግጥ አግዟል፡፡ የብሎክ አደረጃጀቱ "በመኖሪያ አካባቢያችን ይፈጸሙ የነበሩ ስርቆትና የመሰረተ ልማት ዝርፊያዎችን ማስቀረት አስችሏል" ብለዋል፡፡ ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ዘውዱ መንግስቴ በበኩላቸው የብሎክ አደረጃጀቱ በባጃጅ ይፈጸሙ የነበሩ ስርቆቶች መቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ወንጀል ፈጻሚዎችን ለህግ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ ተደራጅተው በሚያከናውኑት ጥበቃ "ከዚህ በፊት ይፈጸሙ የነበሩ የንግድ ቤቶች ዝርፊያና የሰው እገታ ወንጀሎች እየቀነሱ መጥቷል" ያሉት ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ናቸው፡፡ የብሎክ አደረጃጀቱ ህዝቡ ከመንግስት የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ለከተማው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እያገዘ በመሆኑም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።   የአዘዞ ክፍለ ከተማ አመራር አባል አቶ ሙሉጌታ አወቀ በበኩላቸው ህዝቡ በብሎክ ተደራጅቶ ባደረገው ተሳትፎ ሁለት የኤሌትሪክ ትራንስፎርመሮችን ከዝርፊያ በማዳንና ወንጀለኞችን በመያዝ ለህግ ማቅረብ መቻሉ ተናግረዋል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ የከንቲባው የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ አቶ ቻላቸው ዳኘው የከተማው ነዋሪዎች በ91 ቀጣናዎችና በ633 ብሎኮች ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላም እየጠበቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል። መንግስት ሰላሙን ለማጽናት እያደረገ ያለውን ጥረት በማገዝ በኩል የህዝቡ ተሳትፎ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው፤ "ተሳትፎው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ከተማ አስተዳደሩ እየደገፈ ይገኛል" ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ስራ አመራር አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰብስበው አጥቃው በበኩላቸው የከተማው ህዝብ የሰላሙ ባለቤት በመሆን እያደረገ ያለው ተሳትፎ ለሌሎች አካባቢዎች አርአያነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በምክክር መድረኩ በከተማው ከሚገኙ ስድስት ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና የአመራራ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።      
በኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ትምህርት የሚወሰድባቸው ናቸው 
Apr 23, 2024 35
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ትምህርት የሚወሰድባቸው ናቸው ሲሉ የደቡብ ሱዳን የሥርዓተ ጾታ፣ የሕፃናት እና የማህበራዊ ደህንነት ሚኒስትር አያ ዋሪሌይ ገለጹ። በደቡብ ሱዳን የሥርዓተ-ፆታ እና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ልኡካን ቡድን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ የሴቶች ኮከስ አባላት ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል። በልምድ ልውውጥ መድረኩም በኢትዮጵያ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ ለማሳደግ የፓርላማ ተመራጭ ሴቶች ኮከስ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን የሚመለከት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ የደቡብ ሱዳን የሥርዓተ ጾታ፣ የሕፃናት እና የማህበራዊ ደህንነት ሚኒስትር አያ ዋሪሌይ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የበኩሏን ሚና እየተወጣች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ደቡብ ሱዳናውያን ኢትዮጵያን እንደ ሁለተኛ ቤታቸው እንደሚቆጥሯት ተናግረዋል፡፡ የልዑክ ቡድኑ ጉብኝት በኢትዮጵያ ሴቶች በተለይ በፖለቲካው መስክ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች ላይ ልምድ ለመውሰድ ያለመ ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የሚበረታቱና ትምህርት የሚወሰድባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ደቡብ ሱዳንም ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ሴቶችን ለማብቃት የሚያስችል ልዩ ድጋፍ ቀርጻ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ ሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ ኪሚያ ጁንዲ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የሴቶችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እያሰራቸው ያሉ ስራዎችን በሚመለከት ለልዑክ ቡድኑ ገለጻ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡ የፓርላማ ተመራጭ ሴቶች ኮከስ ህጎች ሲወጡ እንዲሁም የአስፈጻሚ አካላት የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ሲከናወኑ የሴቶችን ተሳትፎ እንዲጎለብት በትኩረት እንደሚሰራም አውስተዋል፡፡ የሴቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እንደ ሀገር በተሰራው ስራም በምክር ቤት ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ እያደገ መምጣቱንም ጨምረው ተናግርዋል፡፡ በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ፈትሂ ማህዲ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በምክር ቤት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እያከናወነች ካለው ስራ ባሻገር በዲፕሎማሲያዊ በሰላም ጉዳዮች ያላትን ተሞክሮ ለልዑክ ቡድኑ ገለጻ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡        
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን በጋራ መደገፍ ይገባል - ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ
Apr 23, 2024 63
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን በጋራ መደገፍ ይገባል ሲሉ የመላው አፋር ህዝብ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ተናገሩ። ኢትዮጵያ የባሕር በር ለመጠቀም የጀመረችው ጥረት እንዲሳካ በሰላማዊ አማራጭ በጋራ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል። የእውቁ ሱልጣን አሊሚራህ ልጅ የሆኑት 15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ከውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። አዲስ አበባ ሲደርሱም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ዘሐራ ሁመድ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።   ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት በኢትዮጵያ የተጀመሩ የልማትና ኢንቨስስትመንት እንቅስቃሴዎችን ከዳር ለማድረስ ሰላምን ማረጋገጥ ይገባል። ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን በማጠናከር ለሰላም ዘብ እንዲቆሙና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን እንዲደግፉም ጠይቀዋል። በአፋር ክልል በሰብል ልማት ረገድ የመጣውን እምርታ ጨምሮ በለውጡ መንግስት በሁሉም መስኮች ብዙ መሻሻሎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማስፈን እያከናወኑ ያሉትን ስራ እንደሚደግፉም ነው የገለጹት፡፡ ከአፍሪካ ነጻነት በኋላም በበርካታ አፍሪካ አገራት የቅኝ ግዛት ድንበሮች እንዲቀጥሉ መደረጉን አስታውሰው፣ ይህም ኢትዮጵያን የባህር በር እንዳሳጣት ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ካላት ህዝብ ቁጥርና እያሰመዘገበች ካለው እድገት አንጻር የባህር በር የመጠቀም ጥያቄዋ ተገቢ መሆኑን አንስተው፤ ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንደሚሻም ተናግረዋል።   የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ዘሐራ ሁመድ በበኩላቸው ሱልጣን አህመድ የመላው የአፋር ህዝብ ባህላዊና ሃይማኖታዊ መሪ መሆናቸውን ገልጸው በልጅነታቸው ጀምሮ የታገሉለት የአፋርን ህዝብ ነጻነትና ልማት እውን ማድረግ የሚያስችል ስርዓት በመገንባቱም ከመንግስት ጎን ቆመው ትልቅ ቁም ነገር ማከናወናቸውን ገልጸዋል። ለዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት መስፈን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጎን በመሆን የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑንም ተናግረዋል።   በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፤ ሱልጣኑ ከበዓለ ሲመታቸው ጀምሮ የፌዴራልና የክልል መንግስታትን በሰላምና ልማት ስራዎች ሲደግፉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ የለውጡ መንግስት ሱልጣን አህመድን ከመሰሉ የህዝብ ባህላዊና ኃይማኖታዊ መሪዎች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የመላው አፋር ሱልጣን የነበሩት ወንድማቸው ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ ማረፋቸውን ተከትሎ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር መሾማቸው ይታወሳል፡፡
የሚታይ

የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጭው መስከረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ
Apr 23, 2024 68
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጪው መስከረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ "ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን - አጀንዳ 2063" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጭው መስከረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል ብለዋል። ዛሬ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሄራዊ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ የመክፈቻና የግንዛቤ መስጫ መድረክ መካሄዱንም ጨምረው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ታሪካዊት፣ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ህብረት መስራች ሀገር ይህንን ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል። በመሆኑንም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክ ለማዘጋጀት የተሰጣትን አፍሪካዊ ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ ተግባብተናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመሪነት ሚናው ፡-
Apr 23, 2024 83
 75 ዓመታትን በስኬት የተጓዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚው የአቬዬሽን ግሩፕ ነው፤  አየር መንገዱ 63 የአፍሪካ ከተሞችን ጨምሮ በየቀኑ ወደ ተለያዩ የአለም ክፍሎች በርካታ በረራዎችን ያደርጋል፣  የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የትስስር ሚናው ከየትኛውም አየር መንገድ በላይ በአህጉሩ በረራ ያደርጋል፣  አየር መንገዱ በ5 አህጉሮች በ58 መዳረሻዎች በ100 አለም አቀፍ በረራዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፤  ይህም በቱሪስቶቸ ተመራጭ የሆኑትን የአፍሪካ ስፍራዎች አዲስ አበባ፣ ዛንዚባር፣ ኪሊማንጃሮና ሲሼልስን በዋናነት ያካተተ ነው፤  በዚህም ከስካይ ትራክስ ለ5 ዓመታት ተከታታይ ስኬት ያስመዘገበ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ በመባል ባለ 4 ኮከብ ሽልማት ተበርክቶለታል፤  በቀውስ ወቅት የላቀ የአመራር ስኬት ደግሞ በ2020 ሽልማት ተብርክቶለታል፤  የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ፣ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያ ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎቸም የአለም ክፍሎች በምቹ በረራው እያገለገለ ይገኛል።  
የቤት ልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ የታዩ ልምዶች ይበልጥ መጎልበት ይገባቸዋል
Apr 23, 2024 109
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤት ልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ረገድ የታዩ ልምዶች ይበልጥ መጎልበት እንዳለባቸው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የበጀት ዓመቱን የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሲገመግሙ የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። በዚህም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የኮርፖሬሽኑን ዋና መሥሪያ ቤት፣ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል፡፡   የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል፤ ኮርፖሬሽኑ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቁበት የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ አንጋፋ የመንግሥት ተቋም ቢሆንም ለውጡ እስከመጣበት 2010 ዓ.ም ድረስ ዕድሜውን በማይመጥን ችግር ውስጥ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ከለውጡ ማግስት በተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም ለ42 ዓመታት ከቆየበት ችግር በማውጣት ትርፋማና ተወዳዳሪ ተቋም ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ በሪፎርሙ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር፣ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የኮርፖሬሽኑን የማስፈፀም አቅም ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡   ኮርፖሬሽኑ የቤቶችን የይዞታ ካርታ በማዘጋጀት፣ ለቤቶች መለያ ምልክት በመለጠፍ፣ ጂ.ፒ.ኤስ እና ወደ ጎግል ካርታ በማስገባት የኮርፖሬሽኑን የቤት አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻል መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡ ተቋሙ የንግድ ቤቶችን ኪራይ በማሻሻል የገቢ አማራጮችን እያሰፋ መሆኑን ገልጸው፤ በ2010 ዓ.ም.የተቋሙ ገቢ ከነበረበት 308 ሚሊየን ብር በ2015 ዓ.ም. ወደ 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡ ለ28 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የቤቶች ግንባታ ከማስጀመርም ባለፈ፤ የጥራት፣ ጊዜና የግንባታ ዋጋ ማሻሻል ተችሏል ነው ያሉት፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ነመራ ገበየሁ፤ የኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ አመራር ከዋና መሥሪያ ቤት እስከ ቅርንጫፍ ወጥነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የቤት አስተዳደር ሥርዓት ለማሻሻል የተጀመረው የቤቶች የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠቁመዋል። ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በመከታተል በተያዘላቸው ጊዜ፣ ጥራት እና ዋጋ እንዲጠናቀቁ እየተደረገ ያለው ተግባር ለሌሎች አርዓያ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡ ከቤቶች ልማት ጎን ለጎን በቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገነባው የብሎኬት እና የኮንክሪት ማምረቻ ፋብሪካ የዘርፉን ችግር ከመፍታት ባለፈ ለኢንዱስትሪው ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ፤ የኮርፖሬሽኑ የቤቶች ግንባታ እንደ ሀገር ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡   በግንባታ ሂደት የሚሳተፉ ባለቤቶች፣ አማካሪዎችና ተቋራጮች ጥምረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል በበኩላቸው፤ የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የመስክ ምልከታ የበለጠ ለመሥራት የሚያበረታታ ነው ብለዋል።   የተሰጠውን አስተያየት በመቀበል ተቋሙ አሁን ካለበት በተሻለ መልኩ ለመሥራት እንደሚያነሳሳም አቶ ረሻድ ተናግረዋል። የሱፐርቪዥን ቡድኑ በተመረጡና ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች የሚያደርገው የመስክ ምልከታ እስከ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል፡፡  
የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዲጂታል ስርዓትን በመተግበር ረገድ የተሻለ ስራ አከናውኗል
Apr 23, 2024 85
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዲጂታል ስርዓትን በመተግበር ረገድ የተሻለ ስራ ማከናወኑን የፌደራል መንግስት የድጋፍና የሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሰጡት አቅጣጫ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚመራና ከፌዴራል ተቋማት የተወጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ወደስራ መግባቱ ይታወቃል። ቡድኑም ከፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) የስራ ስምሪት በመቀበል በተመረጡና ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች የሚያደርገው የመስክ ምልከታ እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል። በዚህም የፌደራል መንግስት የድጋፍና የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንዲሁም በሞጆ ደረቅ ወደብ የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውሮ የመስክ ምልከታ አድርጓል።   የፌደራል መንግስት የድጋፍና የሱፐርቪዥን ቡድን አስተባባሪና የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልበር ሸምሱ፥ ኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ 98 ከመቶ በላይ ወጪና ገቢ ምርቶችን እንደሚያጓጉዝ ተናግረዋል፡፡ የድጋፍና የሱፐርቪዥን ቡድኑ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና በሞጆ ደረቅ ወደብ ተርሚናል ያደረገው ምልከታም ተስፋ ሰጪ የመሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ማረጋገጡን ገልጸዋል። የሞጆ ደረቅ ወደብ ተርሚናል ከ18 ሺህ በላይ ኮንቴነሮችን በማስተናገድ በ59 ሄክታር መሬት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። የገቢና ወጪ ዕቃዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና በሞጆ ደረቅ ወደብ ተርሚናል የተገጠሙ የደህንነት ካሜራና ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎት መልካም ጅምር መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ለማሻሻል የወሰዳቸውን የለውጥ እርምጃዎች የበለጠ ለማጠናከር በትጋት መስራት እንደሚገባም ነው የተናገሩት። ተቋሙ በድጋፍና ሱፐርቪዥን ቡድኑ በጥንካሬና በውስንነት የተሰጡ ግብዓቶች በመጠቀም ለበለጠ ስኬት መስራት እንደሚኖርበትም አንተስተዋል። የተመዘገቡ ስኬቶችን በተሞክሮነት ሌሎች ተቋማት እንዲማሩባቸውና መሻሻል ያለባቸው እንዲሻሻሉ ክትትል እንደሚያደርግም አመላክተዋል። ኢትዮጵያን የሎጀስቲክስ ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች እንዲጠናከሩ የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቅርበት እንደሚሰራ ገልጸዋል። በተቋሙ የመንግስትን ውሳኔ ሚፈልጉ ጉዳዮች ከፖሊሲና ህግጋት ማሻሻያ ጋር የሚስተዋሉ ውስንነቶችንም ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ መፍትሔ እንዲያገኙ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)፥ በአፍሪካ ቀዳሚ የሎጀስቲክ መዳረሻ ለመሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።   በ5 ዓመቱ ዕቅድ ላይ ሞጆን ጨምሮ የሎጀስቲክስ መዳረሻ ወደቦችን አቅም በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ፣ ስመጥርና ብቃት ያለው ድርጅት ለመፍጠር ራዕይ ተሰንቆ እየተሰራ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት እየተደረገ የሚገኘውን የማይተካ ሚና ለማስቀጠል በድጋፍና ሱፐርቪዥን ቡድኑ የተሰጡ ምክረ ሃሳቦችን በመውሰድ ለተሻለ ስኬት በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ምሕረተዓብ ተክሉ፥ በድጋፍና ሱፐርቪዥን ቡድኑ ተቋማዊ የሎጀስቲክስ አልግሎትን ለማሳለጥ የተወሰዱ የአሰራር ማሻሻያዎችን በጥንካሬ መውሰዱን አንስተዋል፡፡   የመንግስትን ውሳኔ ከሚጠይቁ፣ ከፖሊሲና የህግ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ በውስንነት የተነሱ ተግባራት በዕቅድ ተይዞው እየተሰራባቸው እንደሚገኝ አስረድተዋል። በዘመናዊ የቴክኖሎጂ በመታገዝ የሎጀስቲክስ ተገልጋዮች ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የጉምሩክ ቅንጅታዊ አሰራርን የበለጠ እንዲሻሻል የተሰጡ ምክረ ሃሳቦች ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በመስክ ምልከታው በተቋሙ የተመዘገቡ ስኬታማ ተግባራትን ማስቀጠል የሚያስችሉና በውስንነት የታዩ ተግባራት ላይ የማሻሻያ ርምጃ እንዲወሰድ የቀጣይ አቅጣጫ ግብረ መልስ ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ "ለጥረትዎ እሴት እንጨምራለን" በሚል መሪ ሃሳብ ተቋማዊ አቅም በማጎልበት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሺፒንግና የሎጅስቲክስ አገልግሎት የመስጠት ተልዕኮን በማንገብ ወጪና ገቢ ምርቶችን በባሕርና የብስ እያጓጓዘ የሚገኝ አንጋፋ ተቋም ነው።  
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 17959
ኢዜአ
ፖለቲካ
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን በጋራ መደገፍ ይገባል - ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ
Apr 23, 2024 63
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን በጋራ መደገፍ ይገባል ሲሉ የመላው አፋር ህዝብ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ተናገሩ። ኢትዮጵያ የባሕር በር ለመጠቀም የጀመረችው ጥረት እንዲሳካ በሰላማዊ አማራጭ በጋራ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል። የእውቁ ሱልጣን አሊሚራህ ልጅ የሆኑት 15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ከውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። አዲስ አበባ ሲደርሱም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ዘሐራ ሁመድ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።   ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት በኢትዮጵያ የተጀመሩ የልማትና ኢንቨስስትመንት እንቅስቃሴዎችን ከዳር ለማድረስ ሰላምን ማረጋገጥ ይገባል። ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን በማጠናከር ለሰላም ዘብ እንዲቆሙና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን እንዲደግፉም ጠይቀዋል። በአፋር ክልል በሰብል ልማት ረገድ የመጣውን እምርታ ጨምሮ በለውጡ መንግስት በሁሉም መስኮች ብዙ መሻሻሎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማስፈን እያከናወኑ ያሉትን ስራ እንደሚደግፉም ነው የገለጹት፡፡ ከአፍሪካ ነጻነት በኋላም በበርካታ አፍሪካ አገራት የቅኝ ግዛት ድንበሮች እንዲቀጥሉ መደረጉን አስታውሰው፣ ይህም ኢትዮጵያን የባህር በር እንዳሳጣት ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ካላት ህዝብ ቁጥርና እያሰመዘገበች ካለው እድገት አንጻር የባህር በር የመጠቀም ጥያቄዋ ተገቢ መሆኑን አንስተው፤ ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንደሚሻም ተናግረዋል።   የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ዘሐራ ሁመድ በበኩላቸው ሱልጣን አህመድ የመላው የአፋር ህዝብ ባህላዊና ሃይማኖታዊ መሪ መሆናቸውን ገልጸው በልጅነታቸው ጀምሮ የታገሉለት የአፋርን ህዝብ ነጻነትና ልማት እውን ማድረግ የሚያስችል ስርዓት በመገንባቱም ከመንግስት ጎን ቆመው ትልቅ ቁም ነገር ማከናወናቸውን ገልጸዋል። ለዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት መስፈን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጎን በመሆን የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑንም ተናግረዋል።   በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፤ ሱልጣኑ ከበዓለ ሲመታቸው ጀምሮ የፌዴራልና የክልል መንግስታትን በሰላምና ልማት ስራዎች ሲደግፉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ የለውጡ መንግስት ሱልጣን አህመድን ከመሰሉ የህዝብ ባህላዊና ኃይማኖታዊ መሪዎች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የመላው አፋር ሱልጣን የነበሩት ወንድማቸው ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ ማረፋቸውን ተከትሎ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር መሾማቸው ይታወሳል፡፡
መንግስት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከርና ለአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው--ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) 
Apr 23, 2024 86
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- መንግስት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከርና ለአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)ገለጹ። ሚኒስትሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ በኢትዮጵያ ለዘመናት ስር ሰደው የቆዩና ያለመግባባት መነሻ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት በርካታ የሪፎርም እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። ፖለቲካዊ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ መንግስት በፅኑ ይሰራል ያሉት ሚኒስትሩ፥ የተፈጸሙ በደሎችን በእርቅ በይቅርታ እና በፍትሕ ለመሻገርም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ መጽደቁን አንስተዋል። በሀገራዊ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርም ህዝብ በአጀንዳዎቹ ላይ ምክክር አድርጎ መፍትሔ የሚያቀርብበት ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑንም ጠቅሰዋል። መንግስት ኢትዩጵያዊ ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጎለብት ልዩ ትኩረት መስጠቱን በማንሳት፥ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያን አንድነት ለማፅናትና የህዝቦችን የዘመናት አብሮነት በጠንካራ መሰረት ለማዝለቅ አሰባሳቢ ትርክት ሚናው የላቀ እንደሆነ አንስተዋል። ለዚህም መንግስት በብሔራዊነት ላይ የተመሰረተ አሰባሳቢ የጋራ ትርክትን መገንባት ላይ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብለዋል። የጋራ ትርክቱ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ፣ ብሔራዊ ጥቅሟን እና ክብሯን ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም የህዝቡን አንድነት ለማጎልበት ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ ጠቅሰዋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመንግስት መረጃዎች ሳይፋለሱ ወቅታቸውን ጠብቀው ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለሀገር ብሔራዊ ጥቅም መከበር እንዲሁም ህብረተሰቡ ለልማት እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ ላይ እየሰራ ነው ብለዋል። የተዛቡ መረጃዎችን መመከት፣ ልዩነትን የሚያባብሱ አስተሳሰቦችን ማረቅ እና የህብረተሰቡን የአብሮነት እሴት የሚያጎለብቱ ስራዎችን ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ነው ያሉት። በቀጣይም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ አሰባሳቢ ትርክትና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ላይ ያተኮሩ መረጃዎችን በተቀናጀ መልኩ ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።    
በክልሉ በዘጠና ቀን ዕቅድ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና እርካታ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል--ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
Apr 23, 2024 85
ቦንጋ ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዘጠና ቀን ዕቅድ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና እርካታ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ። የክልሉ መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው።   በመድረኩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንደገለጹት፣ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በሌሎች ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ቢኖሩም ትኩረት የሚፈልጉ ቀሪ ሥራዎች አሉ። ባለፉት ወራት በተሰሩ ሥራዎች በርካታ የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸው የተሻለ መሆኑን የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች በበጀት እጥረት፣ በአስተዳደር ችግሮች እና በማስፈፀም አቅም ውስንነት ምክንያት ያልተፈፀሙ ተግባራት እንዳሉ ገልጸዋል። እነዚህን ያልተከናወኑ ተግባራት በመፈፀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና እርካታ ለማሳደግ የዘጠና ቀናት ዕቅድ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል። የዘጠና ቀናት ዕቅዱ ከክልሉ መደበኛ ዕቅድ በተጨማሪ የፌደራል ሱፐርቪዢን አባላት እና የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባልት በክልሉ ባደረጉት የድጋፍና ክትትል ሥራዎች የተሰጡ ግብረመልሶችን መሰራት ያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል። በተለይ ፈጣን ምላሽ ለሚፈልጉ የህዝብ የልማት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ለመስጠትና በተሰጠው ግብረመልስ መሰረት የማስተካከያ ስራዎችን ለመስራት የዘጠና ቀኑ እቅድ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። በክልሉ በግብርና፣ በኢንቨስትመንት እና በሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ኢንተርፕራይዞችን በተመለከተ ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን የድጋፋና ክትትል ራዎችን እየተሰሩ መሆኑንም ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ተናግረዋል። በዘጠና ቀናት ዕቅድ ውስጥ ለማከናወን የታሰቡትን ተግባራት በአግባቡ በመፈጸም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና እርካታ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስታውቀዋል መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በተለያዩ ዘርፎች የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ታውቋል።
15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ አዲስ አበባ ገቡ
Apr 23, 2024 103
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- 15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ አዲስ አበባ ገቡ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ- ጉባኤ ወይዘሮ ዘሐራ ሁመድ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሀሰን አብዱልቃድር (አምባሳደር)፣ የቀድሞ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እስማኤል አሊስሮ፣ የቀድሞው ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሀሰን አብደላ(አምባሳደር)፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የእውቁ ሱልጣን አሊሚራህ ልጅ የሆኑት 15ኛው የአፋር ሱልጣን አህመድ የመላው አፋር ሱልጣን የነበሩት ወንድማቸው ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ ማረፋቸውን ተከትሎ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ነበር የተሾሙት። በዛሬው ዕለትም ከውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። ለብዙ ዘመናት የአፋር ሱልጣን መሪዎች በመላው አፋር ህዝብ ዘንድ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን በባህላዊ ስልቶች በዘላቂነት በመፍታት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ይነገራል።
በወታደራዊ ሳይንስ የተካነ ተተኪ የሠራዊት አመራር የማፍራቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Apr 22, 2024 148
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያን የሚያስቀጥል እና በወታደራዊ ሳይንስ የተካነ ተተኪ የሠራዊት አመራር የማፍራቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የአመራር ትምህርት ቤት ተገኝተው በስልጠና ላይ ለሚገኙ የዕዙ የበታች ሹሞች የሕይወት ተሞክሯቸውን አካፍለዋል። ኢታማዦር ሹሙ በዚህ ወቅት አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ የሚገኙ የበታች ሹሞች ነገ ላይ የዛሬዎችን ከፍተኛ አመራሮች በመተካት መከላከያን የሚመሩ እንደሆኑ ገልጸዋል።   በየደረጃው በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የተካነ የነገይቷ ኢትዮጵያ ሠራዊት አመራሮችን የመገንባቱ ሥራ ለነገ የሚባል አይደለም ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ የሰራዊት አመራሮችን የማሰልጠኑ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ሠልጣኝ የበታች ሹሞች የሠራዊቱ ቁልፍ መሪዎች ለመሆን በርትተው መስራት እንዳለባቸው ገልጸው፤ በተፅዕኖዎች ሳይበገሩ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሹማ አብደታ በበኩላቸው የጠንካራ ሠራዊት መሠረቱ ለሀገሩ የማይደርቅ ፍቅር ያለው ጠንካራ አመራር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የዕዙ ማሠልጠኛ የክፍሉን የማድረግ አቅም ለማሳደግ ራሡ በቅቶ ሠራዊቱን የሚያበቃ አመራር የመገንባት ስራን በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ መግለጻቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
ሀገራዊ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በብቃት ለመምራት የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል--ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
Apr 22, 2024 132
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 14/2016(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ተልዕኮን በአግባቡ የተረዳና በእውቀት የሚመራ የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያን ለመፍጠር የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለፌደራል እና ለክልል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ሲሰጠው የቆየው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል።   የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት ስልጠናው በአምስት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። የመጀመሪያው በአስተሳሳሪ ትርክት ግንባታ ምንነት፣ የሚካሄድባቸው አቅጣጫዎች ቴክኒኮች እና ስልቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን ሁለተኛው ዓለምአቀፋዊ፣ አህጉራዊ እንዲሁም ቀጣናዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቁመዋል። የሰላም ግንባታ ስራዎች እንዲሁም የአስር ዓመቱ የመንግስት የልማት እቅድን ማእከል አድርጎ የተዘጋጀው የሶስት ዓመት የመካከለኛ ዘመን የልማት መርሀ ግብርም የስልጠናው ትኩረት ነበር ብለዋል። የህዝብ ግንኙነት መሰረታዊ ሃሳቦች እና መሳሪያዎች ትግበራ ሌላው ስልጠናው ያተኮረባቸው ርእሰ ጉዳዮች መሆናቸውን ተናግረዋል። በአጠቃላይ ስልጠናው የዘርፉ ባለሙያዎች ሀገራዊ ተልዕኮዎችን እና የመንግስት ዋና ዋና ትኩረቶች እንዲገነዘቡ እንዲሁም በእውቀት እና በክህሎት የተሟላ አቅም እንዲፈጥሩ ያስቻለ መሆኑን አመላክተዋል። በቀጣይም በየደረጃው ያለውን ሀገራዊ የመረጃ ፍሰት ለማቀናጀት የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም ማበልጸግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በዚህ ረገድ በርካታ የአቅም ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ለስራው መሳለጥ የሚረዱ አሰራሮች እና መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑን እና ሲጠናቀቁ ለዘርፉ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች በስልጠናው ብዙ ልምድ እና እውቀት ያገኙበት እና ለቀጣይ ስራዎች ስንቅ የሚሆን ትልቅ አቅም የፈጠሩበት መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ከመንግስት ተልእኮዎች እና ዓላማዎች ጋር የተጣጣሙ መልእክቶችን ለህዝብ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።  

ማህበራዊ
የአካባቢያቸውን ሰላም  በማስጠበቅ ልማትን ለማፋጠን የድርሻቸውን እንደሚወጡ  የደብረብርሀን ከተማ ወጣቶች  አስታወቁ
Apr 23, 2024 11
ደብረ ብርሀን፤ ሚያዝያ 15/2016 (ኢዜአ)፦ የአካባቢያቸውን ሰላም በዘላቂነት በማስጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማፋጠን የድርሻቸውን እንደሚወጡ የደብረ ብርሀን ከተማ ወጣቶች አስታወቁ። በከተማዋ ወቅታዊ ሰላምና ልማት በሚጠናከርበት ዙሪያ የሚመክር የወጣቶች መድረክ ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሄዷል።   የመድረኩ ተሳታፊ ወጣት ትዕግስት ፍቅረ እንዳለችው ለአካባቢ ሰላም መጠበቅና ልማት መጠናከር የበኩሏን አስተዋጽኦ እያደረገች ነው። ''እኛ ወጣቶች ገንቢና ምክንያታዊ አስተሳሰቦችን በማጎልበት በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ዳር እንዲደርሱ ያላሰለሰ ጥረት እናደርጋለን'' ስትል ገልጻለች። በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ፈጣንና ቀልጣፋ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁማለች። አሁን ላይ የከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች የነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር የሚያግዙ መሆናቸውን ጠቅሳለች።   ከወጣቶች ጋር የሚካሄዱ ውይይቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ምክንያታዊ አስተሳሰብ በማስቀደም የአካባቢ ሰላም አስጠብቆ በዘላቂነት ለማስቀጠል የበኩሉን እንደሚወጣ የገለጸው ደግሞ ሌላው ወጣት ደምሴ ምሳወይ ነው። በከተማው እያደገ ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚደግፍ መሆኑን አስታውቋል። የእምየ ምሊኒክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰራዊት በዛ በበኩላቸው የከተማዋን ሰላምና ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል ወጣቶች በሚያከናውኗቸው ስራዎች አበረታች ለውጥ እየመጣ ነው ብለዋል። ወጣቶች ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ የልማት ስራዎች ሳይደናቀፉ እንዲቀጥሉ በማድረግ የጎላ ሚና መወጣታቸውን አመልክተዋል።   የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የወጣቶች ዘርፍ አማካሪ አቶ ኃይለማሪያም ወንድም እሸት የወጣቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት በኢንተርፕራይዞች በማደራጀት ከ9 ሺህ ለሚበልጡ ወጣቶች የስራ አድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። የወጣቶችን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተው ወጣቶች ለአካባቢያቸው ሰላም በጋራ መስራትን መቀጠል እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። በምክክር መድረኩ ከደብረብርሃን የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶችና በየደረጃው ያሉ የከተማ አስተዳደሩ አመራር አባላት ተሳትፈዋል።      
የከተማውን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ተሳትፎአቸውን እንደሚያጠናክሩ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
Apr 23, 2024 43
ጎንደር ፤ ሚያዚያ 15 /2016 (ኢዜአ)፡- በጎንደር ከተማ በብሎክ አደረጃጀት ታቅፈው የአካባቢአቸውን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በከተማው የሰፈነውን ሰላም አጠናክሮ በማስቀጠል ዙሪያ የከተማው አስተዳደሩ ከህዝቡ የተወከሉ ነዋሪዎች ጋር ዛሬ ምክክር አድርጓል፡፡ ከተሳታፊዎቹ መካከል አቶ መስፍን ጌታነህ እንዳመለከቱት የብሎክ አደረጃጀቱ ነዋሪው አካባቢውን ከወንጀል ፈጻሚዎች ነቅቶ በመጠበቅ ሰላሙን እንዲያረጋግጥ አግዟል፡፡ የብሎክ አደረጃጀቱ "በመኖሪያ አካባቢያችን ይፈጸሙ የነበሩ ስርቆትና የመሰረተ ልማት ዝርፊያዎችን ማስቀረት አስችሏል" ብለዋል፡፡ ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ዘውዱ መንግስቴ በበኩላቸው የብሎክ አደረጃጀቱ በባጃጅ ይፈጸሙ የነበሩ ስርቆቶች መቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ወንጀል ፈጻሚዎችን ለህግ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ ተደራጅተው በሚያከናውኑት ጥበቃ "ከዚህ በፊት ይፈጸሙ የነበሩ የንግድ ቤቶች ዝርፊያና የሰው እገታ ወንጀሎች እየቀነሱ መጥቷል" ያሉት ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ናቸው፡፡ የብሎክ አደረጃጀቱ ህዝቡ ከመንግስት የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ለከተማው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እያገዘ በመሆኑም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።   የአዘዞ ክፍለ ከተማ አመራር አባል አቶ ሙሉጌታ አወቀ በበኩላቸው ህዝቡ በብሎክ ተደራጅቶ ባደረገው ተሳትፎ ሁለት የኤሌትሪክ ትራንስፎርመሮችን ከዝርፊያ በማዳንና ወንጀለኞችን በመያዝ ለህግ ማቅረብ መቻሉ ተናግረዋል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ የከንቲባው የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ አቶ ቻላቸው ዳኘው የከተማው ነዋሪዎች በ91 ቀጣናዎችና በ633 ብሎኮች ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላም እየጠበቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል። መንግስት ሰላሙን ለማጽናት እያደረገ ያለውን ጥረት በማገዝ በኩል የህዝቡ ተሳትፎ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው፤ "ተሳትፎው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ከተማ አስተዳደሩ እየደገፈ ይገኛል" ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ስራ አመራር አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰብስበው አጥቃው በበኩላቸው የከተማው ህዝብ የሰላሙ ባለቤት በመሆን እያደረገ ያለው ተሳትፎ ለሌሎች አካባቢዎች አርአያነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በምክክር መድረኩ በከተማው ከሚገኙ ስድስት ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና የአመራራ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።      
በኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ትምህርት የሚወሰድባቸው ናቸው 
Apr 23, 2024 35
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ትምህርት የሚወሰድባቸው ናቸው ሲሉ የደቡብ ሱዳን የሥርዓተ ጾታ፣ የሕፃናት እና የማህበራዊ ደህንነት ሚኒስትር አያ ዋሪሌይ ገለጹ። በደቡብ ሱዳን የሥርዓተ-ፆታ እና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ልኡካን ቡድን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ የሴቶች ኮከስ አባላት ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል። በልምድ ልውውጥ መድረኩም በኢትዮጵያ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ ለማሳደግ የፓርላማ ተመራጭ ሴቶች ኮከስ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን የሚመለከት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ የደቡብ ሱዳን የሥርዓተ ጾታ፣ የሕፃናት እና የማህበራዊ ደህንነት ሚኒስትር አያ ዋሪሌይ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የበኩሏን ሚና እየተወጣች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ደቡብ ሱዳናውያን ኢትዮጵያን እንደ ሁለተኛ ቤታቸው እንደሚቆጥሯት ተናግረዋል፡፡ የልዑክ ቡድኑ ጉብኝት በኢትዮጵያ ሴቶች በተለይ በፖለቲካው መስክ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች ላይ ልምድ ለመውሰድ ያለመ ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የሚበረታቱና ትምህርት የሚወሰድባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ደቡብ ሱዳንም ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ሴቶችን ለማብቃት የሚያስችል ልዩ ድጋፍ ቀርጻ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ ሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ ኪሚያ ጁንዲ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የሴቶችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እያሰራቸው ያሉ ስራዎችን በሚመለከት ለልዑክ ቡድኑ ገለጻ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡ የፓርላማ ተመራጭ ሴቶች ኮከስ ህጎች ሲወጡ እንዲሁም የአስፈጻሚ አካላት የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ሲከናወኑ የሴቶችን ተሳትፎ እንዲጎለብት በትኩረት እንደሚሰራም አውስተዋል፡፡ የሴቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እንደ ሀገር በተሰራው ስራም በምክር ቤት ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ እያደገ መምጣቱንም ጨምረው ተናግርዋል፡፡ በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ፈትሂ ማህዲ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በምክር ቤት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እያከናወነች ካለው ስራ ባሻገር በዲፕሎማሲያዊ በሰላም ጉዳዮች ያላትን ተሞክሮ ለልዑክ ቡድኑ ገለጻ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡        
ኢኮኖሚ
የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአርሶ አደሩን ምርታማነት የሚያሳድጉ ዘጠኝ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎች በምርምር አገኘ
Apr 23, 2024 43
ባህር ዳር ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአርሶ አደሩን ምርታማነትን የሚያሳድጉ ዘጠኝ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎች በምርምር መገኘታቸውን አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አስማረ ደጀን በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት ከአምስት እስከ ስድስት ዓመታት በተካሄደ ምርምር የተገኙት የሰብል ዝርያዎቹ በሽታና ድርቅን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርት መስጠት የሚችሉ ናቸው። በምርታማነታቸውና ፈጥኖ በመድረስም ከተለምዶው የተሻሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ዝርያዎቹ በብሄራዊ ዝርያ አፅዳቂ ኮሚቴ ተገምግመው መለቀቃቸውን ገልጸው፤ ከመካከላቸውም ሁለት የማሽላ፣ ሶስት የበቆሎና ቀሪዎቹ ደግሞ የአኩሪ አተር፣ ሽምብራ፣ ድንችና ጥቁር አዝሙድ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከእነዚህም ውስጥ የማሽላ፣ የአኩሪ አተር፣ የሽምብራና የጥቁር አዝሙድ ዝርያዎች ከጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የወጡ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ የበቆሎ ሰብል ዝያዎቹ ደግሞ ከሰቆጣ ግብርና ምርምር ማዕከል በማላመድ እንደተገኙ አስረድተዋል።   እንዲሁም ከአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል አንድ የድንች ዝርያ፣ ከደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ደግሞ አንድ የማሽላ ሰብል ዝርያዎች በምርምር የተገኙ መሆናቸውን አብራርተዋል። ከጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የተገኘው የማሽላ ዝርያ በሄክታር 41 ነጥብ 5 ኩንታል፣ ከደብረ ብርሃን ምርምር ማዕከል የወጣው ደግሞ በሄክታር 52 ኩንታል ምርት መስጠት እንደሚችሉ ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል። በተጨማሪም ከዚሁ ምርምር ማዕከል የተለቀቀው አዲሱ የጥቁር አዝሙድ በሄክታር 9 ኩንታል በላይ ምርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል። ከሰቆጣ ግብርና ምርምር ማዕከል የተለቀቁት ሶስት የበቆሎ ዝርያዎች ደግሞ በሽታና ድርቅን ተቋቁመው በእርጥበት አጠር አካባቢዎች በሄክታር እስከ 48 ኩንታል ምርት እንደሚሰጡ አስረድተዋል። እንዲሁም ከአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የተለቀቀው አዲሱ የድንች ዝርያ በሄክታር 425 ኩንታል ምርት እንደሚሰጥ ጠቅሰው፤ ቀደም ብለው ከተለቀቁት የድንች ዝርያዎች በምርታማነት ደረጃ በ37 በመቶ የምርት ብልጫ እንዳለው አስታውቀዋል። ኢንስቲትዩቱ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በማፍለቅ፣ በማባዛትና የወጡትን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ ለምርታማነት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰዋል። የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከተቋቋመ ከ1992ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን 173 አዳዲስ የተለያዩ የሰብል ዝርያዎችን በማውጣት ለሰብል ምርታማነት ማደግ የድርሻውን መወጣቱም ተመልክቷል።  
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተያዘው የበልግ አዝመራ ከ251 ሺህ በላይ ሄክታር ማሳ በዘር ተሸፍኗል
Apr 23, 2024 102
ቦንጋ ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዘንድሮ የበልግ አዝመራ ከ251 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የቢሮው ምክትል ሀላፊ እና የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ እንደገለጹት፣ በልግ የክልሉ ዋነኛ የአዝመራ ወቅት ነው። በዘንድሮ የበልግ አዝመራ በአዝርዕት ሰብሎች 321ሺህ 829 ሄክታር ማሳ በማልማት ከ12 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰዋል። ከዚህ ውስጥ በእስካሁኑ ሂደት ከ251 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል። አቶ አሸናፊ እንዳሉት በዘር ከተሸፈነው አጠቃላይ ማሳ ውስጥ 13ሺህ 200 ሄክታሩ በትራክተር የታረሰ ሲሆን ከ85ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬት ደግሞ በ1 ሺህ 600 ክላስተሮች የለማ ነው። በክልሉ በሰፊው እየለሙ ካሉ ሰብሎች መካከል በቆሎ፣ ቦሎቄ፣ ሩዝ፣ ማሽላ እና ሰሊጥ ተጠቃሽ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ከአምናው የተሻለ የአፈር ማዳበሪያ፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት እንዲሁም ምቹ የአየር ጸባይ እንዳለ ገልጸው፣ ይህን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።   አቶ አሸናፊ እንዳሉት ለአርሶ አደሩ የግብርና ግብዓቶችን በወቅቱና በሚፈለገው መጠን ለማቅረብ እየተሰራ ነው። እስካሁንም ቀደም ሲል የነበረን ጨምሮ 140 ሺ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እና ከ9 ሺህ 271 ኩንታል በላይ የበቆሎና የቦሎቄ ምርጥ ዘር የተሰራጨ ሲሆን አርሶ አደሮች የተሻሉ እና ነባር ዘሮችን እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራ መሠራቱንም አንስተዋል። በበልግ ወቅት በለማው የበቆሎ ማሳ ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች ተምች መከሰቱን እንደተግዳሮት ጠቅሰው፣ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባባር ተምቹ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል ለ6ቱም ዞኖች ኬሚካል መሰራጨቱን ተናግረዋል። የታቀደውን ምርት ለማግኘት አርሶ አደሩ የማሳ አሰሳና ቁጥጥር ሥራውን እንዲያጠናክር እንዲሁም ዩሪያን በአግባቡ እንዲጠቀም ትኩረት መሰጠቱንም ገልጸዋል። የልማት ጣቢያ ባለሙያዎችና በየደረጃው ያሉ ባለድርሻዎች ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል እያደረጉ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።   በክልሉ ካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ የጡላ ቀበሌ አርሶ አደር መላኩ ገብረጊዮርጊስ በበኩላቸው እንዳሉት በዘንድሮ የበልግ አዝመራ በግማሽ ሄክታር ማሳ ላይ በቆሎ እያለሙ ነው። አስፈላጊውን የግብርና ግብአት ከመጠቀም ባለፈ ለሰብላቸው አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረጋቸው በአሁኑ ወቅት ሰብሉ በጥሩ ቁመናው ላይ መሆኑን ተናግረዋል።   ሌላኛው የቀበሌው አርሶ አደር ጌታቸው ወርቁ፣ ሶስት ጥማድ መሬት ላይ በቆሎ ያለሙ ሲሆን ዘንድሮ የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱና በጠየቁት መጠን ስለቀረበላቸው ሰብላቸው ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት የተከሰተው ተምች በአዝመራው ላይ ጥቃት እንዳያደርስ የቤተሰብ ጉልበት በመጠቀም በእጃቸው እየለቀሙ የመከላከል ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። አሁን ላይ ተምቹ ብዙም ጉዳት እያደረሰ እንዳልሆነ ጠቁመው ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ኬሚካል በበቂ ሁኔታ እንዲቀርብላቸው ጠየቀዋል።  
በአዳማ ከተማ በማህበር ለተደራጁ ዜጎች የምርት መሸጫ ቦታ የሚሆን ስድስት የገበያ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል
Apr 23, 2024 54
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- በአዳማ ከተማ በማህበር ለተደራጁ ዜጎች የምርት መሸጫ ቦታ የሚሆን ስድስት የገበያ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ ገለጹ። የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ በተለያየ መስኮች የስራ ዕድል በተፈጠረላቸው ዜጎች እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ተመልክተዋል። የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ፤ በዚሁ ጊዜ በሰጡት መግለጫ በከተማዋ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። በዋናነትም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ፈጠራን ማበረታታትና ማጎልበት፣ የስራ ዕድል ፈጠራን ማጠናከር እና የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን የሚሉ አራት ግቦች ተይዘው ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል። ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ ልዩ ትኩረት የተሰጠ ሲሆን ወጣቶች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከ84 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰው፤ ከ1 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑ ሼዶች ተገንብተው ለወጣቶች መተላለፋቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡ የመስሪያ እና የመሸጫ ቦታ እጥረትን ለመቅረፍ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰው፤ በከተማዋ ለመገንባት ከታቀዱ አስር የገበያ ማዕከላት መካከል ስድስቱ መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት በማህበር የተደራጁ ዜጎች የገበያውን ሁኔታ በማረጋጋት በኩል ከፍ ያለ ሚና በመጫወት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል በካፒታል እቃ ሊዝ ፋይናንስ ሥርዓት አማካኝነት ከ5 ሺህ በላይ ማሽነሪዎች ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ሆነ
Apr 23, 2024 54
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ሥርዓት አማካኝነት ከ5 ሺህ በላይ ማሽነሪዎች ለተጠቃሚዎች ተደራሽ መሆናቸውን የክልሉ ካፒታል ዕቃ ንግድ አክሲዮን ፋይናንስ ማኅበር ገለጸ። የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ በበኩሉ በአነስተኛና መካከለኛ የተደራጁ 6 ሺህ ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን ወደ ኢንቨስትመንት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል። የኦሮሚያ ካፒታል እቃ ንግድ አክሲዮን ፋይናንስ ማኅበር ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ገለታ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ማኅበሩ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማሳለጥ ዓላማ አድርጎ የተቋቋመ የልማት ድርጅት ነው፡፡ ማኅበሩ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአገልግሎትና ቱሪዝም ልማት ለተሰማሩ ዜጎች በካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ሥርዓት የብድር አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ይህም ከዚህ በፊት የነበረውን የፋይናንስ ተደራሽነት ችግር በመቅረፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ማህበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ በክልሉ በካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ ሥርዓት አማካኝነት ከ5 ሺህ በላይ የማሽነሪ ምርቶችን በ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደተቻለ አስታውቀዋል። ድጋፍ የተደረገላቸው አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችም ከፍተኛ መነቃቃት በመፍጠር ወደ 339 ሚሊዬን ብር የሚገመት ሃብት ማስመዝገብ እንደቻሉ ገልጸዋል። በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ዜጎችም ኑሯቸውን ከማሻሻል ባለፈ በስራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ ዕድገት አዎንታዊ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኝ አስረድተዋል።   የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወሾ ከድር፤ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ የሚደረገው ድጋፍ ዘርፉ እንዲነቃቃ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አምራች ኢንዱስትሪዎች በፋይናንስ፣ በመሰረተ ልማትና የማምረቻ መሳሪያ ያለባቸውን ማነቆ ምላሽ ለመስጠት ከልማት ባንክና ሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለተኪ ምርት የተሰጠውን ትኩረት መነሻ በማድረግ እየተሰራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል። በግብርና፣ በአገልግሎት፣ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪ የተደራጁ 6 ሺህ የሚጠጉ ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን ወደ ኢንቨስትመነት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ስራዎችም ዜጎችን በስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ በማድረግ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።  
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ለስታርትአፕ የተሰጠው ትኩረት የፈጠራ ስራዎችን ወደ ተግባር ለማስገባት እድል የሚፈጥር ነው
Apr 23, 2024 70
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- ለስታርትአፕ የተሰጠው ትኩረት የፈጠራ ስራዎችን ወደ ተግባር ለማስገባት እድል እንደሚፈጥር ስታርትአፖች ገለፁ። በሳይንስ ሙዚየም በመታየት ላይ የሚገኘው የስታርትአፕ ኢትዮጵያ አውደ-ርዕይ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለሙያዎችን ለቀጣይ ስራ የሚያበረታታ መሆኑን የተለያዩ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል፡፡ ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ዕይታ ክፍት በተደረገው አውደ-ርዕይ በመጀመሪያ ደረጃ በምርት ሙከራና ምርት ወደ ገበያ ማቅረብ የጀመሩ ስታርት አፖች እየተሳፉበት ይገኛሉ። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ስታርት አፖች ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት የፈጠራ ስራዎችን ወደ ተግባር ለማስገባት እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።   ከነዚህ መካከል አንዱ የሆነው ያብቃሉ አሰፋ እናቶች የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ባሉበት ቦታ ሆነው ጤንነታቸውን የሚከታተሉበት ቴክኖሎጂ ማበልፀጉን ተናግሯል። ለስታርትአፕ የተሰጠው ትኩረት የፈጠራ ስራዎችን በቀላሉ በማስተዋወቅ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት አጋዥ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍና ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የራሱን ሚና እንዲወጣ ያስችላል ሲል ጠቁሟል።   በስታርት አፕ አውደ ርዕይ ፈጠራውን ያቀረበው ቃለአብ ግርማ በበኩሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ድጋፍ ከሚሹ ወገኖች ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ማበልፀጉን ገልጿል። ቴክኖሎጂው የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተናግሯል።   ምርቶችን ለህብረተሰቡ በቀላሉ ለማቅረብ የሚያስችል ኢ-ኮሜርስና ሎጀስቲክን ያካተተ ቴክኖሎጂ መስራቱን የተናገረው ደግሞ በረከት ታደሰ የተባለ የፈጠራ ባለሙያ ነው ። መንግስት ለስታርት አፕ ትኩረት በመስጠት ፖሊሲዎችን በማዘጋጀትና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን ተናግሯል።   በሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ድጋፍ ባለሙያ አቶ ነገደ ይስሃቅ ስታርት አፖች ፈጠራ ስራዎቻቸውን በማስተዋወቅ ወደ ስራ እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸውን መሆኑን አስታውቀዋል። ስታርት አፖች ተወዳዳሪነታቸውን በማሳደግ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረላቸው መሆኑን ገልፀዋል።    
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራፊክ አደጋን መቀነስ የሚያስችሉ ዲጂታል አሰራሮች በስፋት ተግባራዊ እንዲደረጉ አሳሰበ
Apr 22, 2024 127
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 14/2016 (ኢዜአ)፦የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የትራፊክ አደጋን መቀነስ የሚያስችሉ ዲጂታል አሰራሮችን ይበልጥ ተደራሽ እንዲያደርግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመንገድ ደህንነትና ፈንድ አገልግሎት የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም የገፅ ለገፅ ግምገማ አካሂዷል። ቋሚ ኮሚቴው አገልግሎቱ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ለተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ ማሰርን ጨምሮ ተሽከርካሪዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ ለማድረግ እየሰራ ያለውን ሰራ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። የአሽከርካሪ ሙያ ስልጠናና ተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ የሚሰጡ ተቋማት ላይ ያለው አሰራር በዲጂታል ስርዓት የታገዘ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንዳለበትም አሳስቧል። የትራፊክ አደጋ በተደጋጋሚ የሚደርስባቸው ቦታዎችን በመለየት አደጋን ለመከላከል በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ነው የተገለፀው። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሸዊት ሻንካ፤ መረጃ በተገቢው መልኩ መሰብሰቡ የትራፊክ አደጋን ለመከላከልና አስፈላጊ ህጎችን ለመተግበር የሚያስችል በመሆኑ አገልግሎቱ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን እንዲያዘምን አስገንዝበዋል፡፡ ተቋሙ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ዙሪያ ያካሄዳቸው የንቅናቄና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል። በትምህርት ቤቶች ባሉ ክበባት ተማሪዎች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እየተሰራ ያለው ስራም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል። የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ጀማል አባሶ በበኩላቸው አገልግሎቱ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ እያከናወነ ካለው ስራ በተጨማሪ የተለያዩ ማሻሻያዎችን እየተገበረ ነው ብለዋል። የተለያዩ ህግና ደንብ፣ ስታንዳርዶችንና መመሪያ ማሻሻያ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዲጂታል አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ ላይም ትኩረት ተሰጥቷል ነው ያሉት፡፡ የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማትና የፍጥነት መገደቢያ አገጣጠምና አገልግሎቱን ከማዕከል ለመከታተል የሚያስችል ሶፍትዌር እየለማ መሆኑንም ጠቁመዋል። ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ዘመቻ በማድረግ በተሽከርካሪና አሽከርካሪዎቸ ላይ ቁጥጥርና ክትትል መደረጉንም ተናግረዋል። በድግግሞሽ ከ9 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ በመደበኛ፣ ድንገተኛና የቴክኒክ ቁጥጥር መደረጉን ጠቅሰው፤ ጉድለት በተገኘባቸው 2 ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ቅጣት መተላለፉን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት በትራፊክ አደጋ የተመዘገበው ሞት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ514 መቀነሱን ተናግረዋል። የአካል ጉዳት ደግሞ በ216 መቀነሱን ጠቁመዋል፡፡ ከመንጃ ፍቃድ አሰጣጥና ተሽከርካሪ ምርመራ ጋር የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የተሽከርካሪ ምርመራን በኦንላይን መከታተል የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የአገልግሎቱ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ፈቲያ ደድገባ ናቸው። የመንጃ ፍቃድ አሰጣጡን ለማዘመን ከሰነድ ክለሳ ጀምሮ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል። የመረጃ ተዓማኒነት እንዲኖር ለማስቻልም የትራፊክ አደጋ ምዝገባን በሲስተም ለመመዝገብ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።  
ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ስርአት ወጥ የሆነ ቀልጣፋና የተቀናጀ  አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው
Apr 21, 2024 151
አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 13 /2016(ኢዜአ) ፡ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ወጥ የሆነ ሀገራዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት በመዘርጋት የተቀናጀ፣ ቀልጣፋና የተረጋገጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ። የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ማለት መሠረታዊ የሆኑ የግል ዲሞግራፊክ እና ተፈጥሯዊ የሆነውን የዓይን፣ የጣትና የፊት የባዮሜትሪክ መረጃዎችን መዝግቦ በመያዝ በማዕከላዊ ቋት የሚያስቀምጥ አሠራር ነው። የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ከተከናወነ በኋላ ልዩ ቁጥር በመስጠት ተመዝጋቢው የተደራጀና አስተማማኝ የዲጂታል መታወቂያ እንዲኖረውም ያደርጋል። የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ለሰላምና ደኅንነት፣ ለተፋጠነ ልማት፣ የምጣኔ ኃብት ሽግግርና መልካም አስተዳደር የላቀ ጠቀሜታ እንዳለው ይታወቃል። የፖሊሲ ቀረፃን፣ የምጣኔ ኃብትና ማኅበራዊ ልማት ክንውንን አካታች ለማድረግም እንዲሁ። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሐሚድ ኪኒሶ፤ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ወቅቱን የዋጀ ለሀገርና ሕዝብ የሚጠቅም ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት መሆኑን ገልፀዋል። በኢትዮጵያ አንድ ወጥ የሆነ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት በመዘርጋት የተቀናጀ፣ ቀልጣፋና የተረጋገጠ አገልግሎት ለመስጠት የላቀ ጠቀሜታ የሚኖረው መሆኑን ተናግረዋል። የውል ስምምነቶችና ሌሎችንም ሰነዶች በማጣራት በቴክኖሎጂ የታገዘ ምዝገባና ማረጋገጫ የሚደረግበት ዘመናዊ አሠራር መሆኑንም ጠቅሰዋል። የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በ15 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በየቀኑ በአማካይ ለ6 ሺህ 500 ሰዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ ቀደም ከመታወቂያ ጋር በተያያዘ ችግሮች እንደነበሩ አስታውሰው፤ የዲጂታል መታወቂያ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ግን ጥራት ያለው ቀልጣፋና የተቀናጀ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል። የዲጂታል መታወቂያ ለተቋሙ አገልግሎት መሳለጥ ወሳኝ በመሆኑ ተቋማቸው ከብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ጽህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት እየመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም እስካሁን ከ70 ሺህ 300 በላይ ተገልጋዮችን ለብሄራዊ መታወቂያ መመዝገብ ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።          
አለም አቀፉ የታዳሽ ሀይል ኤጀንሲ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በታዳሽ ሀይል ለማስተሳሰር የምታደርገውን ጥረት አደነቀ
Apr 21, 2024 153
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- አለም አቀፉ የታዳሽ ሀይል ኤጀንሲ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በታዳሽ ሀይል ለማስተሳሰር የምታደርገውን ጥረት አድንቋል። አራተኛ አለም አቀፍ የታዳሽ ሀይል ኤጀንሲ ጉባኤ በአቡ ዳቢ ከተማ ተካሄዷል። በጉባኤው ላይ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ በአረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ኡማር ሁሴን ተሳትፈዋል።   በጉባኤው አራተኛ ቀናት ታዳሽ ሀይል ማከማቸት በሚቻልበትና በአፍሪካ የሀይል አቅርቦት ሽግግርን፣ ታዳሽ ሀይልን ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮዎችና የዘርፉን የፖሊሲ ማእቀፎች ላይ ምክክር ተደርጓል። እአአ በ2030 አባል ሀገራት ታዳሽ ሀይልን ጥቅም ላይ ለማዋል በጋራ የሚሰሩበትን አቅም ማጉላት የሚቻልበትን ሁኔታን ማጠናከርም የውይይቱ አካል እንደነበር ተገልጿል። በምክክሩ ላይ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ ታዳሽ ሀይልን ለማበረታታት የመንግስትና የግል አጋርነት ፖሊሲን በመተግበር በጸሀይ ሀይል፣ በንፋስና በእንፋሎት ሀይል የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን መተግበሯን አንስተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተቀየሰው የታዳሽ የሀይል ስትራቴጂም በአፍሪካ በ2030 የሀይል አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ የተጣለውን ግብ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት መቃረቧን ጠቁመዋል። በዚህም መንግስት የቀጣናውን ሀገራት በሀይል አቅርቦት ለማስተሳሰር ለኬንያ ፣ለጅቡቲና ለሌሎች ሀገራት ሀይል ማቅረቡን ሲያስታውሱ ይህም ከሀይል አቅርቦት ባለፈ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት መስፈን ትልቅ አቅም ማበርከቱን ተናግረዋል።   የአለም አቀፉ የታዳሽ ሀይሎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አልፋሮ ፔሊኮ በበኩላቸው ለታዳሽ ሀይል የሚመደቡ በጀትን ማሳደግና እንዲሁም የመንግስትና የግል አጋርነትን በማረጋገጥ በቅንጅት መስራት እንዳለበት ሲያነሱ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን አብርክቶ አድንቀዋል። በታዳሽ ሀይል አቅርቦት አሁን ላይ ያልውን 13 ነጥብ 7 ሚሊዮን የስራ እድል ፈጠራ በ2050 ወደ 40 ሚሊዮን ማሳደግ ይገባልም ነው ያሉት። ዘርፉን ለማበረታታትም ሀገራት የፖሊሲ ማሻሻያዎች በታክስ ቅነሳ ፤በድጎማ፣ በዋስትና እና በጥናቶች መደገፍ እንደሚገባቸው መናገራቸውን ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።  
ስፖርት
በቬና በተካሄደ የማራቶን ውድድር አትሌት ጫላ ረጋሳ በአንደኝነት አጠናቀቀ
Apr 21, 2024 141
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- በቬና የተካሄደውን የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ጫላ ረጋሳ አንደኛ በመወጣት አጠናቀቀ፡፡ አትሌት ጫላ ረጋሳ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት አሸንፏል። በለንደን ማራቶን ደግሞ ትዕግስት አሰፋ እና ቀነኒሳ በቀለ ውድድራቸውን በተመሳሳይ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያ አሸናፊዎች ሆነዋል። የሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ዛሬ በተደረገው በ44 ኛው የለንደን ማራቶን በ 2ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሁለተኛ ደረጃ ውድድርዋን አጠናቃለች። በወንዶች ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ውድድርን በ2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ15 ሰኮንድ በሁተኝነት በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል። በለንደን የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት መገርቱ አለሙ በ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ34 ሰኮንድ 4ኛ፣ አትሌት ትዕግስት ከተማ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ 7ኛ፣ አትሌት ያለምዘርፍ ይሁአለው 2 ሰዓት ከ 23 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ 8ኛ እንዲሁም አትሌት ፅጌ ሀይለስላሴ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል። እንዲሁም አትሌት ክንዴ አተናው በ2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ 8ኛ ደረጃን ይዞ በመግባት ውድድሩን አጠናቋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ውድድር የገባበት ሠዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ ሲመዘገብ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለጽ የዓለም አትሌቲክስ አድናቆት መግለጹን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል
Apr 21, 2024 132
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል። በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ኢትዮጵያ ቡና ከመቻል ከቀኑ 10 ሰዓት ሲጫወቱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ደግሞ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ፣ በሶስቱ ሽንፈት ገጥሞች አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በዚሀም መሰረት በሊጉ በ33 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቻል በበኩሉ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በሁለቱ ድል ሲያደርግ ሁለት ጊዜ ተሸንፎ አንድ ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በዚህም መሰረት መቻል በ40 ነጥብ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በድሬዳዋ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ይጨወታሉ። የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከሲዳማ ቡና ዛሬ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በ43 ነጥብ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበኩሉ ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ፣ አንድ ጊዜ ተሸንፎ፣ ሁለት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በአንፃሩ ሲዳማ ቡና ባለፉት አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አላጋጠመውም። በሁለቱ ሲያሸንፍ በሶስቱ አቻ ወጥቶ በ27 ነጥብ በሊጉ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሊጉ 22ኛ ሳምንት ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ሻሸመኔ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል። የዛሬ ጨዋታዎችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የድሬዳዋ ቆይታ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከ16ኛ ሳምንት አንስቶ የሊጉ ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም ሲደረጉ እንደነበር ይታወቃል። ከ23 እስከ 27ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚደረጉ የሊጉ አክሲዮን ማህበር መግለጹ ይታወሳል።
በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ተተኪዎችን ለማፍራት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው
Apr 21, 2024 138
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2016(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ለታዳጊዎች የኳስ ብቃትና ክህሎት ጥሩ መሰረት እየጣሉና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አሰልጣኞች ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተፃፈው የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ተሽጦ ገቢው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለልማት ሥራ እንዲውል ተደርጓል። በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። በመዲናዋ የእግር ኳስ፣ የፉት ሳል፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የሜዳ ቴኒስና ሌሎች የመጫወቻ ስፍራዎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ነው። በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ ተገንብተው ወጣቶችና ታዳጊዎች እየተጫወቱባቸው ከሚገኙ የእግር ኳስ ሜዳዎች መካከል የኢዜአ ሪፖርተር በመዘዋወር አሰልጣኞችና ሰልጣኞችን አነጋግሯል።   በፈረንሳይ 41 ማዞሪያ ራስ ካሣ ሜዳ እና በልደታ ክፍለ ከተማ ቢሊሞ ሜዳ ልምምድ ሲያሰሩ ያገኘናቸው አሰልጣኝ ሰላምሰው ምዳ፤ መደመር በስፖርቱ ዘመን ተሻጋሪ አሻራ እያሳረፈ መሆኑን ገልጸዋል። በመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ የተገነቡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ለታዳጊዎች የኳስ ብቃትና ክህሎት ጥሩ መሰረት እየጣሉና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትም አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል።   በራስ ካሣ ሜዳ በስልጠና ላይ ያገኘናቸው ይስሐቅ ኃይለማርያም እና አቤሜሌክ ኤርሚያስ፤ ከመገንባቱ በፊት ሜዳው ለጨዋታ አስቸጋሪና ለጉዳት የሚዳርግ እንደነበር አስታውሰው ከተገነባ በኋላ በብዙ መልኩ ደረጃውን የጠበቀና ለስልጠና ምቹ መሆኑን ተናግረዋል።   በቢሊሞ ሜዳ ሲያሰለጥኑ ያገኘናቸው አሰልጣኝ መንግሥቱ አረጋ፤ የሜዳው በዘመናዊ መልኩ መሰራት የኢትዮጵያን እግር ኳስ የሚቀይሩ ልጆች ለማፍራት ያግዛል ብለዋል። በሜዳው ሲሰለጥኑ ያገኘናቸው ታዳጊ ልዑል ዮናስ እና ሰላዲን ሀሰን በዘመናዊ መልኩ አዲስ የተሰራው ሜዳ እኛን ጨምሮ ለበርካታ ልጆች ጥሩ የኳስ መሰረት እያስያዘ ነው ብለዋል። በመዲናዋ ከሚገኙ 24 የስፖርት ማዘውተሪያዎች መካከል ሰባቱ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ በተገኘ ገቢ የተገነቡ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በመንግሥት በጀት የተሰሩ መሆናቸው ታውቋል።
አካባቢ ጥበቃ
የምግብ ዋስትናና የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ አህጉራዊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
Apr 23, 2024 68
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፦ የምግብ ዋስትናና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልን የተመለከተ አህጉራዊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። መድረኩ“ለአየር ንብረት ለውጥ ቴክኖሎጂ ተኮር መፍትሔዎች እና በአፍሪካ ለምግብ ዋስትና የማይበገር አቅም መገንባት፤ እድሎችና ፈተናዎች” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው። 14ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ (UNFCCC) የአፍሪካ ፈራሚ አገራት ስብስባ (COP 14) በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ከስብስባው ጎን ለጎን የአፍሪካ የምግብ ስርዓቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን የተመለከተ የምክክር መድረክ ነው። በመድረኩ ላይ የአፍሪካ ሪስክ ካፓሲቲ ዳይሬክተር ጀነራል ኢብራሂማ ቼክ ዲዮንግ፣ የአፍሪካ ሕብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ “ብሉ ኢኮኖሚ” እና ዘላቂ ከባቢ አየር የስራ ክፍል አመራሮች፣ የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ለማና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሌሎች የአፍሪካ አገራት የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሮች፣ የልማት አጋሮችና የዘርፉ ተዋንያን ተገኝተዋል። የምክክር መድረኩን ያዘጋጁት የአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተቋም የሆነው የአፍሪካ ሪስክ ካፒሲቲ(ARC)፣ከግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩትና የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ነው። በውይይቱ የአፍሪካ አገራት የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም፣ የምግብ ሉዓላዊነትን በመገንባት፣ የግብርና የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍና ዓለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አኳያ የግብርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራትና በገጠሟቸው ፈተናዎች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ስብስባው ትናንት በባለሙያዎች ደረጃ መካሄዱ ይታወቃል።  
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 ተጨማሪ የካርበን ሽያጭ ማግኘት የሚያስችላትን መስፈርት አሟልታለች - የኢትዮጵያ የደን ልማት
Apr 23, 2024 79
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ 2025 ተጨማሪ የካርበን ሽያጭ ገቢ ማግኘት የሚያስችላትን መስፈርት ማሟላቷን የኢትዮጵያ የደን ልማት አስታወቀ። ባለፉት አምስት አመታት ዜጎችን በማሳተፍ በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሮች የደን ሽፋን እንዲጨምር ማድረግ ተችሏል፡፡ ከመርኃ ግብሩ ጎን ለጎን የደን ጭፍጨፋን ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት የደን ጭፍጨፋን በግማሽ መቀነስ መቻሉን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያሳያል ። በኢትዮጵያ የደን ልማት የብሔራዊ ሬድ ፕላስ አስተባባሪ ዶክተር ይተብቱ ሞገስ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የተራቆቱ አካባቢዎችን በደን በመሸፈን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም የራሷን ድርሻ እየተወጣች ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ ከሚገኘው የደን ልማት ከካርበን ሽያጭ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የካርቦን ሽያጭ ገቢ ለማግኘት የተቀመጡ ዓለም አቀፍ መስፈርቶች እንዳሉ ጠቁመው ኢትዮጵያ ከካርቦን ሽያጭ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የሚያስችሏትን መስፈርቶች እንዳሟላች ተናግረዋል። የካርበን ሽያጭ ገቢ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በአካባቢና በአየር ንብረት ሚዛናዊነት ጥበቃ ላይ የሚያበረክቱት የካርበን መጠን ተለክቶ የሚፈጸም የክፍያ ሥርዓት መሆኑን አስረድተዋል። በሰው ሰራሽ የደን ሽፋን የተራቆቱ አካባቢዎችን የማልማት ተግባሩ በባለሙያና በሳተላይት መረጃ ተንትኖ የሚቀርብ ሲሆን በዚህም ለአየር ንብረት ተጽዕኖና የካርበን ክምችት ያበረከተው አስተዋጽኦ ተለክቶ ለሽያጭ የሚቀርብ መሆኑን አንስተዋል። በኢትዮጵያ እየተሰራበት በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የደን ሽፋኑን ከ17 በመቶ በላይ ማድረስ መቻሉ ሀገሪቷ ወሳኝ የአካባቢ ጥበቃ ምዕራፍ ላይ መሆኗን እንደሚሳይ ተናግረዋል። በዚህም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ 2025 ከካርበን ሽያጭ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወኗን ገልጸዋል። የካርበን ሽያጭ ለመፈጸም የሚተከሉ ችግኞችን ደን በማድረግ፣ መረጃን በዲጂታልና በጂፒኤስ በመመዝገብ የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልቶ ማቅረብ እንደሚጠይቅ አንስተዋል። በኢትዮጵያ የተከናወኑ የደን ልማት ተግባራትን በአግባቡ አደራጅቶ በመመዝገብ ሪፖርት ቀርቦ ባለሙያዎች በአካልና በሳተላይት ምልከታ አድርገው ተጨማሪ የካርበን ሽያጭ ገቢ ማግኘት የሚያስችላትን መስፈርት ማሟላቷን የሚገልጽ ምላሸ እንደተሰጠ አስታውቀዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ የሚሰሩ አበረታች ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከዓለም ባንክ፣ከኖርዌይና የአሜሪካ ኩባንያዎች ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ እስካሁን ከካርበን ሽያጭ ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን ጠቁመው፥ በሬድ ፕላስ በተደገፈው የባሌ ደን ካርበን ሽያጭ ብቻ በሁለት ዙር 12 ሚሊዮን ዩሮ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል። ከካርበን ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ለህብረተሰብ ተሳትፎና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት በመስጠት ቀጣይነት ያለው የደን ጥበቃና እንክብካቤ ስራ እንደሚውል ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ዘመቻን በማስቀጠል ከደን ልማት የካርበን ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የአካባቢ ጥበቃ ሙያተኞች የዜጎችን ተሳትፎ በማሳደግ ለደን ችግኝ ልማት ትኩረት እንዲሰጡ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የአካባቢ ጥበቃ እና ደን ልማት ስራ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ መሰረት በመሆኑ ቀጣይነት ያለው ስራ ማከናወን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።  
በሲዳማ ክልል የፕላስቲክ ውጤቶች በአካባቢ ብክለት ላይ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቷል
Apr 23, 2024 134
ሐዋሳ፣ሚያዚያ 15/2016 (ኢዜአ)፡-በሲዳማ ክልል የፕላስቲክ ውጤቶች በአካባቢ ብክለት ላይ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ ለመከላከል ከማህበራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን አስታወቀ። የፕላሲቲክ ውጤቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የተደራጁ ማህበራት በበኩላቸው የአየር ብክለትን ለመከላከል እንደ ሀገር የተጀመረውን ንቅናቄ ውጤታማ ለማድረግ ተግተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በባለስልጣኑ የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ቲቦ ለኢዜአ እንደገለጹት"ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ በይፋ ተጀምሯል። በንቅናቄው ለስድስት ወራት የሚከናወኑ የዘመቻ ሥራዎች እንዳሉ ጠቁመው፣ስለአካባቢ ብክለት ከግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ባለፈ ባለድርሻ አካለትን ንጹህና ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል። እንደ ሀገር የብክለት መነሻ ተብለው የተለዩ የፕላስቲክ፣ የአየር፣ የውሃ፣ የአፈርና የድምጽ ብክለቶች እንዳሉ አስታውሰው፣ ብክለት በአካባቢ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ከግምት ያስገባ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መገባቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም የፕላስቲክ ብክለት በአካባቢ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመከላከል ከተደራጁ ማህበራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ማህበራቱ በተለያዩ ከተሞች የፕላስቲክ ወጤቶችን ሰብስበው መልሶ ጥቅም ላይ መዋል በሚቻልበት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን የንቅናቄው አካል እንዲሆኑም የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል። ፕላስቲክ ከ500 እስከ 1000 ዓመት አፈር ውስጥ የመቆየት አቅም እንዳለው በጥናት መረጋገጡን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በአካባቢ ብክለት ላይ ያለውን ተጽዕኖ ለመከላከል የህብተረተሰቡ ድርሻ የጎላ መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ፕላስቲክ ቆሻሻውን ለይቶ ለተደራጁ ማህበራት በመስጠት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የተጀመረውን ዘመቻ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል:: የሃዋሳ ውበት ደረቅ ቆሻሻ ማስወገድና ሪሳይክሊንግ ሥራ ማህበር መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሄኖክ ዶንጋቶ በበኩላቸው ከ2010 ጀምሮ በተደራጀ መንገድ ቆሻሻን የመሰብሰብና ጥቅም ላይ የማዋል ስራ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።   ማህበሩ 86 ቋሚ እና ከ1ሺህ 500 በላይ ጊዜያዊ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን በአምስት ተሽከርካሪዎች በመታገዝ ከየቤቱ ቆሻሻ የማሰባሰብ ሥራ ያከናውናል። ከሚሰበስቡት ቆሻሻ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፖስት ከማዘጋጀት በተጨማሪ ለአካባቢ ብክለት ተጽዕኖ ያላቸውን ፕላስቲክ ወጤቶች መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የማድረግ ስራ እያከናወነ ይገኛል "ቆሻሻ ሃብት ነው" ያሉት አቶ ሄኖክ በዘፈቀደ የሚጣሉ የፕላስቲክ ምርቶችን በመሰብሰብ የሀዋሳን ሐይቅ እና አካባቢን ከብክለት ከመከላከል ባለፈ ለመልሶ ጥቅም በማዋል ገቢ ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል። ፕላስቲክ በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመቀነስ ማህበሩ ከክልሉ አካባቢ ደንና አየር ንብረት ባለስልጣን ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በቀን ከ2ሺ 400 ኪሎ ግራም በላይ ፕላስቲክ እንደሚሰበስቡ የገለጹት ስራ አስኪያጁ ከሃዋሳ በተጨማሪ 11 በሚደርሱ የክልሉ ከተሞች፣ በሻሻመኔና ጥቁር ውሃ ኮፈሌና ሃላባ ከተሞች እንደሚሰበሰብ ተናግረዋል፡፡   በዚህም አንድ ኪሎ ፕላስቲክ ከ8እስከ 10 ብር እንደሚገዙ ገልጸው በዘርፉ የሚሰሩ ማህበራትን በማበራከት የአካባቢ ብክለትን መከላከልና ቆሻሻን ወደ ሃብት መቀየር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የኩል ፕላሲቲክ ሪሳይክልንግ ኢንተርፕራይዝ ማህበር አስተዳዳር ክፍል ሃላፊ ኢዮብ ኢያሱ ማህበሩ ለአካባቢ ብክለት ትልቅ ድርሻ ያላቸውን ፕላስቲኮች መልሶ የመጠቀም ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡   በፕላስቲክ ተረፈ ምርቶቹ በዋናነት ለችግኝ መትከያ የሚሆኑ "ፖሊ ባግ" እንደሚያመርቱ ገልጸው ፖሊ ባጎቹን በአረንጓዴ ልማት ለተሰማሩ ማህበራት እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ፕላስቲክ በአካባቢ ላይ የሚያሳድረውን ብክለት ለመቀነስ ከክልሉ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ብሏል፡፡ ከክልሉ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በወራት የተከፋፈሉ ስድስት ተግባራት የፕላስቲክ፣የአየር፣የውሃ፣የአፈርና የድምጽ ብክለትን ጨምሮ አካባቢና ማህበራዊ ተጽእኖ ግምገማ እስከ መጪው መስከረም የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡  
በክልሉ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የተቀናጀ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
Apr 22, 2024 116
ባህር ዳር ፤ ሚያዚያ 14/2016 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አባላትና ባለሙያዎች የአካባቢ ብክለት ለመከላከል የተቀናጀ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ አሳሰቡ። ‘‘ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ!’’ በሚል መሪ ሃሳብ የአካባቢ ጥበቃና ብክለትን የመከላከል ዘመቻ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ተካሂዷል።   ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት፤ በአየር ንብረት ለውጥ መባባስ በየጊዜው እየተስተዋለ ያለው ድርቅ፣ ጎርፍና ረሃብ ለዜጎች ፈተና እየሆነ መጥቷል። ለዚህም የአካባቢ ብክለትን በዘላቂነት ለመከላከል መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ ያለው ሥራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን ብክለት በዘላቂነት ለመከላከል በየተቋማቱ የሚገኙ አመራር አባላትና ባለሙያዎች ተገንዝበው የተቀናጀ ርብርብ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል። በተለይም በትላልቅ ከተሞች የብክለት ምንጭ የሆኑና በየቦታው የሚጣሉ የፕላስቲክ ውጤቶች ለገቢ ማስገኛና ለኑሮ ማሻሻያ እንዲውሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። የክልሉ የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን አለምነህ በበኩላቸው፤ በከተሞች የሚስተዋለው የአካባቢ ብክለት ለማስወገድ የሁሉንም አካላት ቅንጅታዊ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።   በተለይ በየቦታው የሚጣሉ ፕላስቲኮችን በቀላሉ መከላከል ካልተቻለ ኅብረተሰቡን ለከፋ የጤና ችግሮች ከማጋለጡም በላይ፤ የከተሞች ውበትና ደህንነት ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል። ለዚህም ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚካሄደው የአካባቢ ጥበቃ የግንዛቤ ፈጠራና የህዝብ ንቅናቄ ዘመቻ ከዚህ በፊት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ክልሉ ከአካባቢ ብክለት ነፃ፣ ምቹና ለሰው ልጆች መኖሪያ ተስማሚ እንዲሆን ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን እንዲወጡም ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል። ''በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተራቆተ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሃብት መልሶ ለመተካት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየተተገበረ ይገኛል'' ያሉት ደግሞ የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ ለማ ናቸው።   በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን የፕላስቲክ ቆሻሻን ለመከላከል የተለያዩ የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችን ማገዝና ውጤቱን ለማፅናት ትኩረት የተሰጠው ሀገራዊ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። ወጣት አይቸው ደባስ በበኩሉ፤ የወዳደቁ ፕላስቲኮችን ሰብስቦና ፈጭቶ ለተለያዩ ፋብሪካዎች እያቀረበ መሆኑን ገልጿል።   በወር ውስጥም እስከ 40 ሺህ ኪሎ ግራም የወዳደቁ ፕላስቲኮችን በመፍጨትና በመጨፍለቅ ለፋብሪካዎች ግብዓት እንዲሆኑ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል። በመድረኩ የክልል፣ የፌዴራልና የዞን የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 1076
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 1997
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ
Apr 5, 2024 1287
በዓለማችን ላይ እየተስተዋለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ የተወሳሰበ ችግር እያስከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነምህዳር ላይ እያደረሰ ያለው አደጋ ሊቀለበስ ወደ ማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን ሞደርን ዲፕሎማሲ ድረገጽ አስነበበ። ድረ ገጹ በዓለማችን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ድርቅ፣ ጎርፍ እና ተዛማጅ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደሚገደዱ አስነብቧል። የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በይነመንግስታት ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ያለው የዓለማችን የሙቀት መጠን ወደ 1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ እየተጠጋ በመምጣቱ በስነምህዳር፣ በከባቢ አየር እና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እየተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት በመሆን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የሚፈጥራቸውን ችግሮች በማባባስ ለሰዎች መፈናቀልና የህይወት መጎሳቆል እያደረሰ ይገኛል። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በማዕከላዊ አሜሪካ እና ደቡባዊ ሜክሲኮ የተከሰተው ሃሪኬን ኤታ የተባለው የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ያስከተለው የሰብል ውድመትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰው አደጋ ከባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ አደጋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በዚህም በጎርፍ፣ በመሬት መንሸራተትና በሰብል ውድመት ምክንያት ከ1 መቶ 20 ሺህ በላይ ሰዎችን ከሞቀ መኖሪያቸው ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ አድርጎ አትቷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ድረ ገጹ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አመልክቷል። በአውሮፓውያኑ 2022 ወደ 32 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ይህ አሃዝ በ2008 ከተከሰተው በ41 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል። ይህም የዓለማችን የሙቀት መጠን እየጨመረ መምጣቱን እንጂ ምንም ዓይነት የመቀነስ አዝማሚያ ያላሳየ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው በቺሊ፣ ካናዳ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሜክሲኮ፣ ኢክዋዶር፣ ሊቢያ እና በሌሎችም አገራት ሃሪኬን በተሰኘው የአየር ለውጥ፣ በሰደድ እሳት፣ በጎርፍ እና በድርቅ ምክንያት ለባለፉት በርካታ ወራት መፈናቀልን እንዳስከተለ ተገልጻል። የአለም ባንክን የትንበያ መረጃ ዋቢ ያደረገው ድረ ገጹ በአውሮፓውያኑ 2050 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ 216 ሚሊዮን ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ድረገጹ ይሄ ክስተት የሚያስከትላቸው ችግሮች እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ካስፈለገ ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮሩ ግንዛቤን የሚያሳድጉ ትምህርቶች፣ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውነተኛ ውይይቶች እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ በማሳሰብ መሪዎች የሚጠበቅባቸውን ሊተገብሩ ይገባል ሲል ምክሩን አስቀምጧል።  
ሐተታዎች
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 306
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1414
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
በህብር የተገነባ ገድል
Mar 25, 2024 2324
  "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የትውልድ አሻራ ደምቆ የተፃፈበት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ይህ ቀን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የረባ ጥቅም ሳይሰጥ ወደ ጎረቤት አገራት ሲፈስ የኖረውን የአባይ ወንዝ ወደ ብርሃን ለመቀየር በቁርጠኝነት በመነሳት የማይቻልን ነገር በይቻላል ወኔ በመቀየር ለዓለም ያሳዩበት፤ ዓለም የተደመመበት ቀን ነው። የግድቡ ግንባታ በተጀመረበት ወቅት በርካታ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ታሳካው ይሆን? የሚል ጥርጣሬ አዘል ርእስ የያዘ ተከታታይ ዘገባ አስነብበዋል። ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተሰኘው ድረ ገጽ በፈረንጆቹ 2011 ‘Can Ethiopia Afford the Grand Renaissance Dam?’ በሚል ርእስ ባወጣው ሰፋ ያለ ዘገባ ግድቡን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሊያዋጡ የሚችሉት በጣም ጥቂቱን ብቻ በመሆኑ ግንባታው ሊሳካ አይችልም በሚል ትንበያውን አስቀምጦ ነበር። የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ግሪን ፕሮፊት የተሰኘ ድረ ገጽ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ‘Defiant Ethiopia is proceeding with its plan to build the Grand Millennium Dam on the Nile River, but what kind of dam can they build without cash flow? ..... there’s one important problem: Ethiopia lacks the necessary funds to see the project to completion. In fact, they can barely get it off the ground.’ በማለት ኢትዮጵያ ግድብ መገንባት የሚያስችል ገንዘብ ስለሌላት ፕሮጀክቱ ሊተገበር አይችልም ሲል ደምድሟል፤ ተሳልቋልም። በወቅቱ የዚህ ዓይነት ግምት የብዙዎቹ ተንታኞች መንደርደሪያ ነበር። “ኢትዮጵያ ደሃ አገር ስለሆነች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር ካልተገኘ በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ፍፃሜ መድረስ አይችልም” የሚል ድምዳሜ ለመስጠት ተንታኞቹ ብዙም አይቸገሩም ነበር። ‘ግድቡ የጥራት ችግር ስላለበት ይደረመሳል’ ከሚለው ዘመቻ ጀምሮ በግድቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ተደጋጋሚ የዛቻና የማስፈራሪያ መልእክቶች ተስተጋብተዋል። በጥቅምት ወር 2013 ዓ. ም የቀድሞ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብጽ ተጎጂ እንደሆነች አቋም በመያዝ "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው፤ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" የሚል ጠንከር ያለ የዛቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያውያን ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል ሲሉ የገለጹት ትራምፕ ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም ሲሉም አክለዋል። "ግብፅ የህዳሴ ግድብ እንዲገነባ መፍቀድ አልነበረባትም፤ የስምምነት ሀሳብ ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ገንዘብ አታገኝም " ብለዋል። አትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ለመገንባትና ዳር ለማድረስ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ የተለያዩ ኃይሎች ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበር አገር ወይም ተቋም ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የነበረው አማራጭ አንድም ግድቡን አለመሥራት፣ አለበለዚያ ወጪውን በራስ አቅም መሸፈን ነበር፡፡ ከእነዚህ ከባድ ሁለት አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ወጪውን በራሱ አቅም በመሸፈን መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር አረጋገጠ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ኢትዮጵያውያን ገጠር ከተማ ሳይሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ ከጫፍ እስከ ጫፍ በእልህና በቁጭት በመነሳሳት ግድቡን በራሳቸው አቅም ገንብተው ዳር ለማድረስ ቃል ኪዳን ያደረጉት። ለግንባታው የሚውል ድጋፍ በገንዘብና በዓይነት በተለይም የቦንድ ሽያጭ፣ በ8100 አጭር መልእክት እና በእጣ አገልግሎት ህዝቡ ተረባረበ፤ የማይቻለውን እንደሚቻል ለዓለም አሳየ። በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎችን ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው 99 በመቶ መድረሱንና የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በቅርብ ያወጣቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል የህዳሴው ግድብ ቀዳሚው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ "የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው" በማለት አረጋግጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ቢኖሩባትም የግድቡን ሥራ ለአፍታም አላቋረጠችም። በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ95 በመቶ በላይ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል። ዘንድሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ይከበራል፤ መሪ ሀሳቡም "በኅብረት ችለናል!" የሚል ሲሆን ኢትዮጰያውያን ችለው ያሳዩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። እዚህ ድል ላይ የተደረሰው በመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ነው። ባለፉት 13 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ተሳትፎ ተጀምሮ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሊጠናቀቅ ወራቶች የቀሩት ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለጎረቤት አገራት ተደራሽ በማድረግ ቀጣናውን በማስተሳሰር በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው።  
በከፍታ የታጀበ ስኬት
Mar 15, 2024 1933
ለህጻናትና ታዳጊዎች መልካም ስብእና የሚያግዙ ጽሁፎችን ያዘጋጀችው ኤሪን ሶዴርበርግ ዶውኒንግ 'JUST KEEP WALKING' በሚለው መጽሃፏ ባደራጀችው ገጸባህሪ አማካይነት “አንተ መልካምና ስኬታማ ሆነህ ሳለ ጥቂት ሰዎች ስለአንተ መጥፎነት አብዝተው መጨነቅና ማውራት ከጀመሩ የምትሄድበት መንገድም ሆነ አካሄድህ ትክክል ነውና መራመድህን አታቁም። ብዙሃኑ የስኬትህ ተካፋይና የስኬትህ አጋር ስለሆኑ የጥቂቶቹን ጫጫታ ከምንም ካለመቁጠር ተራመድ ብዙ አፍራሽ ወሬዎች ያንተን ስኬት የመመስከር አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን አትዘንጋ። መቆም የሽንፈት ምልክት ነውና” ትለናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 78 ዓመታት በከፍታ የዘለቀ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምና ዝናው የገነነ ተቋም ነው። አየር መንገዱ ታህሳስ 21 ቀን 1938 ዓ.ም ተመስርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ካይሮ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዘመኑ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅና አሰራሮችን በማዘመን ራሱን እያደራጀ የኢትዮጵያ ኩራት ከመሆን አልፎ የአፍሪካ ምልክት ሆኖ ዘልቋል። ዛሬ ላይ የ152 ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በምስረታው ወቅት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት አውሮፕላኖች ብቻ እንደነበሩት መረጃዎች ያመለክታሉ። በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ22 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞችን ፍላጎትና ምቾት ለመጠበቅ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ጨምሮ 31 አውሮፕላኖች ለመግዛት ከአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። እነዚህን ተጨማሪ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ቁጥር ጨምሮ የሚገነባቸው ዘመናዊ አየር መንገዶች ሲደመሩ በአፍሪካ ግዙፍ ተቋምነቱን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ያደርገዋል። የበረራ አድማሱን በየጊዜው እያሰፋ የሚገኘው አየር መንገዱ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 134 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በሀገር ውስጥ ወደ 22 መዳረሻዎች ይበራል። ከዚህ ውስጥ 60 የበረራ መዳረሻዎቹ አፍሪካ ውስጥ ነው። አየር መንገዱ ከ55 ሚሊየን ዶላር በላይ አስገንብቶ ወደ ስራ ያስገባው ዘመናዊ የካርጎ ማእከል ከምስራቅ አፍሪካ ብሎም ከአፍሪካ ከፍተኛ ተብሎ ተመዝግቦለታል። በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው ያረፈው የካርጎ ማዕከል ለኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ ኮሜርስ) አገልግሎት የሚውል ሲሆን የካርጎ አገልግሎት እየሰፋ መምጣት አየር መንገዱ የሚሰራቸው ተያያዝ በርካታ ተግባራት መስፋት፣እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ተመራጭ መሆን ለማእከሉ ግንባታ ምክንያት ተብለው ተጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ መስክ ከሚታወቅባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሴቶችን በማብቃትና የጾታ እኩልነትን በማስተግበር ረገድ አርአያነት ያለው ተግባር መፈጸሙ ነው። በየዓመቱ የሚታሰበው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ማርች 8 በሚከበርበት ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ ለሙሉ በሴቶች ብቻ የተመራ በረራን በማደረግ ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፏል። አየር መንገዱ ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ "ሴቶችን በማብቃት አፍሪካን ማስተሳሰር" በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ ወደ ለንደን በሴቶች ብቻ የተመራ የተሳካ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች በሚሰጠው ዘመኑን የዋጀና ቀልጣፋ አገልግሎት በየጊዜው የተለያዩ ሽልማቶች ባለቤት መሆን የቻለ ተቋም ነው። ለአብነት የቅርብ ጊዜያቶችን ለማንሳት ያህል ባሳለፍነው ዓመት በአየርላንዷ ደብሊን በተዘጋጀ መርሐ-ግብር ላይ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማትን አሸንፏል፡፡ በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ ጉባኤ "ኤር ካርጎ ኤሮፕ" እ.አ.አ በ2021 ባካሄደው የበይነ መረብ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የካርጎና የሎጅስቲክ አገልግሎት የ2021 የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ የደንበኞች እንክብካቤ ዘርፍ ሽልማት አግኝቷል። በአውሮፓውያኑ 2024 ዓመታዊውን የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “የኮርፖሬት የዘላቂነት ስኬት ሽልማት” አሸናፊ ሆኗል። አየር መንገዱ በትላልቅ ስኬቶች የማለፉን ያህል ከባድ ፈተናዎችንም ተጋፍጦ በጽናትና በስኬት አልፏል። መላውን ዓለም ያዳረሰው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አንዱ ማሳያ ነው። በዚያን ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ምክንያት በዓለም ደረጃ በርካታ አየር መንገዶች በረራ በማቋረጥ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ አንዳንድ የመንገደኞች አውሮፕላኖቹን ወደ ዕቃ ጫኝ በመቀየር ጭምር ትኩረቱን ጭነት ማጓጓዝ ላይ አድርጓል። በዚያን ፈታኝ ወቅት አየር መንገዱ የቀየሰውን ስትራቴጂ በመቃወም ከውስጥም ከውጭም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ትችትን አስተናግዷል። ይሁን እንጂ አየር መንገዱ ፈተናውን በመቋቋም እንደሌሎቹ ሀገራት አውሮፕላኖች በረራ የማቋረጥ እጣ ሳይገጥመው በታላቅ ብልሃት ማለፍ የቻለ ተቋም መሆኑ ተመስክሮለታል። በዚህም በካርጎ አገልግሎት ገቢ ከማገኘቱም ባሻገር ክትባትን ለዓለም በማዳረስ ወረርሽኙ ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ የራሱን አሻራ አኑሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን ከአራት አስርተ ዓመታ በላይ ልምድ አካብቷል። አየር መንገዱ በሚያስተዳድረው ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የበረራ ባለሙያዎችን በቅርቡ ያስመረቀ ሲሆን ምሩቃኑ ከታንዛንያ ከደቡብ ሱዳን ከኒጀር ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከቶጎ እና ከማዳጋስካር መሆናቸው ደግሞ የአየር መንገዱን የፓንአፍሪካኒስት መንፈስ አጉልቶ ያሳየ አድርጎታል። ስኬቶቹ በዚህ ያላበቁት አየር መንገዱ የእድገት ግስጋሴውን እንደቀጠለ ይገኛል። ከሰሞኑ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በዚህ ወቅት ከተሸለሙት ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን ሽልማቱ ለወደፊትም ለላቀ ስኬት የሚያዘጋጀው እንደሆነ ይታመናል።  
ትንታኔዎች
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 83
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 3677
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2463
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች
Mar 1, 2024 2341
ሴቶች - የአድዋ ድል ሁለንተናዎች በአየለ ያረጋል "... መጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል..." ይህን ያሉት ታላቁ ምሁር እና የአድዋ ዘማች ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያም ናቸው። በርግጥ በአድዋ ዘመቻ ያልዘመተ የለም። የሀይማኖት መሪዎች፣ ንጉሱ፣ ንግስቲቱ፣ ገበሬው፣ አገሬው ከነማንነቱ… ገድል ፈጽሟል። በጦር ሜዳ ገድሎች የሴቶች አበርከቶ እምብዛም አይታወስም። ሴቶች የዋሉበት ግንባር አይዘከርም። ቅሉ ሴቶች በኪነ-አድዋ ያልተዘመረላቸው ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው። እቴጌ ጣይቱን መሰል የአድዋ ሴት የጦር ፊታውራሪዎች አሉ። አዝማሪ ጣዲቄና መሰል አዝማሪዎች የሰራዊቱ ስነ ልቦና ገንቢዎች ናችው። ሴቶች የሎጂስቲክስ አሳላጮች፣ የቁስለኛ ሀኪሞች፣ የጀግና አበርቺዎች፣ የስንቅ ሰናቂዎች፣….በጥቅሉ ሴቶች የአድዋ ድል ሁለንተናዎች ነበሩ። ለዚህ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳሚ ምስክር ናቸው። እቴጌ ጣይቱ ከውጫሌ እስከ መቀሌ፣ ከእንጦጦ እስከ ማርያም ሸዊቶ መላ መቺም፣ ጦር አዝማችም ነበሩ። የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዜና መዕዋል ከታቢ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ወልደአረጋይ ‘ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ’ በተሰኘው መጽሐፋቸው የሴቶችን ሚና በተመለከተ እንዲህ ይላሉ። “እንዲህም እየሆነ፣ አጤ ምኒልክ ባዳራሹ እቴጌ ጣይቱ በእልፍኝ ባለሟሎችን ወይዛዝርቱን ይዘው ግብሩ አንድ ቀን ሳይጎድል፣ ይዘምታሉ። ከዘመቻ ላይ ጠጁ ማሩ አለመጉደሉ፣ ስለምንድነው ያልህ እንደሆነ ይህን ታሪክ መመልከት ነው። በስድስት ድንኳን እንጀራው ሲጋገር ሲያድር፣ በአራት ድንኳን ወጡ ሲሠራ ሲያድር፣ ጠጁ በቀንድ በኮዳ ደግሞ ሦስት መቶ ስድስት መቶ የሚሆን ገንቦኛ ሲጓዝ ግብሩ ይጎድል ይመስልሀል” (ገጽ-241) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ይቀጥላሉ። “… ጥቂቱን ጻፍን እንጅ በአድዋ ጦርነት ዐይናቸን እንዳየው ጆሯችን እንደሰማው መጻፍ አይቻለንም። እቴጌ በዚያን ጊዜ በግምባርዎ ተደፍተው በጉልበትም ተንበርክከው ድንጋይ ተሸክመው እግዚአብሄር እያመለከቱ ሲያዝኑ ሲጨነቁ ነበር። … ሴት ወይዛዝርቱም የንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወይዘሮ ዘውዲቱም ደንገጡሮችንም ተከትለው ነበር። የኋላው ሰልፈኛ እንደመወዝወዝ ሲል ባዩ ጊዜ ቃልዎን አፈፍ አድርገው ተናገሩ። አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል! ድሉ የኛ ነው በለው! አሉት… ጣሊያ ድል ከሆነ በኋላ ወንዱ በርኮር፣ ሴቱ በገንቦ ውሃ ያዙ ብለው አዘው ለተጠማውና ለቆሰለው ውሃ ሲያጠቱት ዋሉ። እንኳን ኢትዮጵያ ሰው የኢጣሊያው ስንኳ ቁስለኛ ከዚያ ስፍራ የተገኘ ከዚህ ከእቴጌ ካዘዙት ውሃ አልቀረበትም“ይላሉ። ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው እቴጌ ጣይቱና መሰሎቻቸው አንድም በጸሎታቸው፣ አንድም ተዋጊዎችን በማደፋፈር ወኔያቸው፣ አንድም በጦር መሪነት ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዋናው ደግሞ ቁስለኞችን የማከምና ሰብዓዊነት ሙያቸው ነው። ፀሃፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ “… ሙሉ ግብር እየበላ የተጓዘ እንጂ ወታደር የስንቅ አቁማዳዉን አልፈታም“ ሲሉ የአድዋ ሴቶች ገድል ምንኛ ገናና እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ይጠቅሳሉ። እንደ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረስላሴ ስለዘመቻው አጓኳን በማስታወሻቸው እንደገለጡት ድንኳን ተካይ፤ ዕንጨት አቅራቢው፣ ወጥ ሰሪው፣ እንጀራ ጋጋሪው፣ እህል ውሃ ተሸካሚው፣ መልከኛው (አራጁ)፣ በቅሎ ጫኙ፤ ተዋጊው ሁሉም በየፊናው እንስሳቱም ሳይቀር ተደራጅቶ ዘምቷል። በርካታ የታሪክ ምንጮች የአድዋ ጦርነት ተሳታፊዎች ገሚሶቹ ሴቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ ደግሞ በአንድ ወቅት ሚዲያ ላይ ቀርበው “በአድዋ ጦርነት ዘማቾች 75 በመቶ ሴቶች ነበሩ” ብለው ነበር። በአድዋ ጦርነት ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች ተመድበው ከካምፕ እስከ ጦር ሜዳ ከመመገብ እስከ ማጀገን፣ ከማከም እስከ መዋጋት ድንቅ ሚና ተወጥተዋል። ድርብ ድርብርብ ኃላፊነት ይዘው የዘመቱ፣ ለወንዶችም ልብ፣ ሞራልና ወኔ አቀባዮች ነበሩ። ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም ‘ከአሜን ባሻገር’ በተሰኘ መጽሐፉ ‘ሴቶች በዋሉበት’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሴቶች ተጋድሎና ሚና “ከቁስ ባሻገር ከልብ ያቀርባሉ” ይላቸዋል። “ሴቶች ባዋላጅነት ከነበራቸው የማይተናነስ ሚና በጦር ሜዳ ተጫውተዋል። እናቶቻችን በጦር ወቅት፣ መሳሪያ ያቀርቡ ነበር። ምግብ ያቀርቡ ነበር። ሃሳብ ያቀርቡ ነበር። ልብ ያቀርቡ ነበር። ደስታ ያቀርቡ ነበር። ኧረ ምኑ ቅጡ። ሴቶች ባንድ በሙቀጫ ዙሪያ፣ ማኅበረሰቡን ኬሚስት፣ ገጣሚና የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው ማገልገላቸውን ልብ እንበል” ይላል። (ገጽ-138) የራስ መኮንን ባለሟል የነበሩት ፊታውራሪ ተክለሐዋሪያት ተክለማሪያም ገና በ15 ዓመት ዕድሜያቸው አድዋ ዘማች ነበሩ። "የሕይወቴ ታሪክ’ (ኦውቶባዮግራፊ) በተሰኘው ግለ ታሪካቸው ከሐረር እስከ አድዋ በዘለቀው ጉዟቸው ሴቷ (አገልጋያቸው) የነበራትን ሚና ለማብራራት ቃላት ያጥርባቸውና እንዲህ ብለው የአንባቢን ህሊና ይነካሉ። “… ከቶ እሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት እሆን ኖሯል! እያልኩ ዘወትር ሳስበው ያደንቀኛል። ዕቃ ተሸክማ ስትሄድ ትውላለች። ከሰፈርን በኋል ውሃ ቀድታ፣ እንጨት ለቅማ፣ ቂጣ ጋግራ፣ ወጥ ሰርታ፣ ታበላናለች። ወዲያውኑ እንዲዚህ ለማታ ታሰናዳለች። እንደዚህ የወለተ አማኑኤልን አገልግሎት እያሰብኩ ስደነቅ ደግሞ በየሰፈሩ እንደርሷ ስንት ሴቶች እንደሚያገለግሉ ይታሰበኛል። የሴቶቹን አገልግሎት ስገምት ደግሞ የበቅሎዎች አገልግሎት ይታወሰኛል። በመጨረሻም ድምሩን ስገምተው አድዋ ድል የተገኘው በሴቶች አገልጋዮችና በበቅሎዎች ብርታት መሆኑ ይታወቀኛል። ሁሉንም አያይዥ በደምሳሳው ስመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት ነጻነቱን ጠብቀው፤ እዚህ አሁን የደረስንበት ኑሮ ያደረሱት እነዚህ የዘመቻ ሃይሎች መሆናቸውን አልስተውም። የኢትዮጰያ መንግስት የተባለው ተቋም፣ ላገልጋዮቹ ውለታ ምላሽ ሆኗል ወይ? የዚህን ምላሽ ለመስጠት ሳስበው እልቅ የሌለው መንገድ ይገጥመኛል። ሲሄዱ መኖር ይሆንብኛል። የማልዘልቀው እየሆነብኝ፣ እየተከዝኩ እተወዋለሁ” በማለት በቁጭት ጽፈዋል። በርግጥም ሴቶች በኪነ-አድዋ በልካቸው ያልተዘመረላቸው፣ ‘’ደብዛዛዎቹ ጀግኖች” ናቸው።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11627
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16021
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8244
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9262
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25606
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21638
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16021
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12194
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 11627
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 11073
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 10831
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10388
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 25606
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 21638
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16021
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12194
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በድላችን ሐውልት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት የተቀረጸላቸው የካራማራው ዘማች አቶ በቀለ ገመቹ 
Mar 5, 2024 3569
አቶ በቀለ ገመቹ ወይም በቅፅል ስማቸው አሚኮ ይባላሉ፤ በሙያቸው ኤሌክትሪሺያን ናቸው። በ1969 ዓ.ም በዚያድባሬ የሚመራው የሶማሊያ አገዛዝ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ሀገር ስትደፈር ቁጭት ተሰምቷቸው ወደ ጦር ሜዳ መዝመታቸውን ይናገራሉ። ጦር ሜዳ ከመዝመታቸው ባሻገር የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመሆናቸው "በራ በራ የድል ጮራ" የተሰኘውን ዓርማ በመቅረጽ በ14ቱ ክፍላተ ሀገር እንዲበራ ማድረጋቸውንም ያነሳሉ። በዚህም ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ከኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ መሸለማችውን ያወሳሉ። ታንክ ማራኪው አሊ በርኬ ጓደኛቸው እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ በቀለ፤ በተለያዩ ዐውደ ግንባሮች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። አቶ በቀለ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚገኘው የድላችን ሐውልት ላይ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዘው ሐውልት ተቀርጾላቸዋል። ሐውልት እንዲቀረጽ የተደረገበት ፎቶግራፍ በያኔው ሶስተኛው አንበሳው ክፍለ ጦር በኋለኛው ምሰራቅ ዕዝ በር ላይ በቀኝ እጃቸው መሳሪያ ከፍ አድርገው ይዘው የተነሱት ፎቶ ግራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ። ከእርሳቸው ጎንም መንበረ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊ ዘማችና መትረጊስ ተኳሽ ሴት ባደረገችው አስተዋፅኦና በደረሰባት አካል ጉዳት ሐውልት እንደተቀረጸላት ያነሳሉ። የካራማራ ድል ታላቅ ድል ነው የሚሉት አቶ በቀለ ገመቹ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለውበት የተገኘና ሀገርን ያስከበረ መሆኑንም ይገልጻሉ። የካራማራ ዘማቹ አቶ በቀለ ገመቹ አሁናዊ ኑሯቸው ችግር ላይ እንደሚገኙና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። ሶማሊያን ለ21 ዓመታት ያስተዳደሩት ዚያድባሬ 'ታላቋን የሶማሊያ ሪፐብሊክ ለመመስረት' በሚል "ድንበራችን እስከ አዋሽ ይደርሳል" እያሉ በመዛት የጦርነት ነጋሪት መጎሰማቸው የሚታወስ ነው። ይሄን እውን ለማድረግ በ1969 በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ ወረራ ፈጸሙ። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የእብሪተኛውን የዚያድባሬ ጦር ካራ ማራ ላይ ድል አደረገ፤ የኢትዮጵያ አሸናፊነትም በአደባባይ ታወጀ። ድሉ በየዓመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰብ ሲሆን ዘንድሮም 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።    
የአፍሪካ ዋንጫን በመሀል ዳኝነት  የመራችው ብቸኛዋ ሴት ዳኛ
Jan 28, 2024 3397
  በይስሐቅ ቀለመወርቅ እንደ መነሻ፡- በእግር ኳስ ውድድሮች የመሃል ዳኝነቱን ቦታ በብዛት የሚይዙት ወንዶች ሲሆኑ፤ አሁን ላይ አልፎ አልፎ ሴቶች ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ሲዳኙ አስተውለናል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተከናወነው 22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት፤ ኮስታሪካ እና ጀርመን ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኛነት መርታለች። በዚህም በወንዶች ዓለም ዋንጫ ታሪክ በመሀል ዳኝነት የእግር ኳስ ጨዋታን የመራች የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች ። ዘንድሮ ደግሞ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሞሮኳዊቷ ቦችራ ካርቡቢ፤ ውድድሩን እንዲመሩ ከተመረጡት 32 የመሀል ዳኞች መካከል ብቸኛዋ ሴት ናት። በዚህም በውድድሩ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ፤ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ ታሪክ ጽፋለች። የሞሮኮ ዓለም አቀፍ ማኅበር የእግር ኳስ ዳኛ የሆነችው ቦችራ ካርቡቢ፤ በወንዶችም ሆነ በሴቶች አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ በርካታ የመጨረሻ ምዕራፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ዳኝታለች። 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ብቸኛ የሴት ዳኛ ሆና የመራችው ቦችራ ካርቡቢ ማናት? ቦችራ ካርቡቢ በሞሮኮ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው "ታዛ" ከተማ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1987 ተወለደች። የዘር ግንዷ በሰሜን ምሥራቅ ሞሮኮ ከሚገኙት ሪፊያን ከሚባሉት የበርበር ጎሳ ዝርያ ካላቸው ሕዝቦች የሚመዘዝ ሲሆን፤ ለቤተሰቦቿ አምስተኛና የመጨረሻ ልጅ ነች። ገና በልጅነቷ ለእግር ኳስ ፍቅር ያደረባት ቦችራ ካርቡቢ፤ ኳስ መጫወት የጀመረችው በአንድ ትንሽ የወጣቶች ቡድን ውስጥ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2001 በተወለደችበት ከተማ "ታዛ"፤ ለወንዶችና ለሴቶች የእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ተከፈተ ። ይኼ ትምህርት ቤት ቀልቧን የሳበው ቦችራ፤ ሥልጠናውን መውሰድ ጀመረች። "እግር ኳስን እወዳለሁ፤ ራሴንም ላስተምር ፈለኩ።ለምን አላደርገውም ብዬ ፍላጎቴን በመከተል የእግር ኳስ ጨዋታን ደንብ መማር ጀመርኩ" ስትል የእግር ኳስ ዳኝነት ትምህርት የጀመረችበትን ጊዜ ታስታውሳለች። ይኼ ድርጊቷ ካልተዋጠላቸውና፤ በበጎ ጎኑ ካልተመለከቱት ውስጥ ደግሞ፤ ወንድሞቿ ቀዳሚዎች ነበሩ። "በምኖርበት ከተማ አንድ ሴት አጭር ቁምጣ ለብሳ ከወንዶች ጋር ሥልጠና ስትወስድ መታየቷ፤ እንደ አሳፋሪ ድርጊት ስለሚታይ መነጋገሪያ ሆኜ ነበር" ትላለች። የቦችራ ካርቡቢ የዳኝነት ጉዞ እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በ2007፤ ሞሮኮ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒዮናን ጀመረች። ይህ መሆኑ ቡችራ ካርቡቢ ብሔራዊ ዳኛ እንድትሆን ዕድል የፈጠረላት ሲሆን፤ መኖሪያዋንም ከትውልድ ሥፍራዋ "ታዛ" ወደ ሞሮኮ ሌላኛዋ ከተማ "ሚከንስ" እንድትቀይር አደረጋት። "ይህን ዕድል ማግኘቴ ቤተሰቦቼ እንዲረዱኝና ሙያዊ ለሆነ ጉዳይ እንደምሄድ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል" በማለት የዳኝነት ሙያዋን በመጨረሻ እንደተቀበሉት ታስረዳለች። በሚከንስ ከተማ በእግር ኳስ ዳኝነት ሥልጠና ላይ እያለች፤ አንድ ቀን አባቷ መጥቶ እንደተመለከታትና፤ ወንድሞቿ ምርጫዋን ሊያከብሩላት እንደሚገባ እንደነገራቸውም ገልፃለች። የ19 ዓመት ወጣት እያለችም፤ በሞሮኮ የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ የሊግ ውድድር በመዳኘት፤ የዳኝነት ሥራዋን አንድ ብላ ጀመረች። ይህ ከሆነ ከ10 ዓመት በኋላ፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዳኛ በመሆን ራሷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ2018 በጋና አስተናጋጅነት በተከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፤ በዛምቢያና በኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት አጫወተች። ይህም በአህጉራዊ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት ያጫወተችው ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበላት። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020፤ "ቦቶላ" እየተባለ በሚጠራው በሞሮኮ የወንዶች ከፍተኛ የሊግ ውድድር ላይ በመሀል ዳኝነት በመዳኘት፤ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ። ከአንድ ዓመት በኋላም በካሜሮን አስተናጋጅነት በተከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ሴኔጋልና ግብፅ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የቫር ዳኛ (video assistant referee) በመሆን ሰርታለች። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊትም የሞሮኮ የንጉሱ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን በመዳኘትም ቀዳሚዋ ሴት ናት። አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወድድርም፤ በጊኒ ቢሳውና በናይጄሪያ መካከል የተከናወነውን ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በመሀል ዳኝት በመምራት፤ የመጀመሪያዋ ሰሜን አፍሪካዊት የአረብ ሴት ሆናለች። ቡችራ ካርቡቢ ከእግር ኳስ ዳኝነት ሥራዋ በተጨማሪ፤ የፖሊስ ኦፊሰር በመሆን ሀገሯን እያገለገለች ትገኛለች።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም